LEARN_WITH_JOHN Telegram 766
በራሳቸው በጀት የሚያሳፍሩ ታሪኮችን በቅዱሳት ሥዕላት አስጊጠው እያተሙ እያወጡ ቤተ ክርስቲያንን ለማንጓጠጥ ያመቻቹ አጽራረ ቤተክርስቲያንም እንደነበሩና ሲነቃባቸው መጽሐፎቻቸውን መደበቃቸውም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ መቼም በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ ዱላውን ያላሳረፈባት የለምና ከብዙ መቶ ክፍለ ዘመናት በፊት የተጻፉ ታሪኮችን አሁን ካለው የዘር ፖለቲካ ጋር እንዲጋጩ በሚያደርግ መንገድ እንዲቃኙና ቤተ ክርስቲያንን ለእሳት እንዲዳርጉ ሆነው የተተረጎሙ መጻሕፍትም ብዙ ናቸው፡፡ በ2009 የግንቦት ርክበ ካህናት ላይ የተነሣው ሌላ ጉዳይ ‘አራት ኪሎ ነዋሪ ስለሆኑ ሴት’ ‘ስለ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ሳይቀር የሚያወሩ ፖለቲካ ቀመስተአምራት’ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅና ተጨምረው ምእመናንን ግራ ሲያጋቡ እንደነበር ተጠቅሶ ለሊቃውንት ጉባኤ መመሪያ ተሠጥቶአል፡፡

​የሚደንቀው ይህ ሁሉ ሲሆን የአብዛኛዎቹን ተአምራትና ገድላት በዐረቢኛ ጽፋ ለኢትዮጵያ የሠጠችው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ስንክሳርዋን ፣ ተአምራትዋንና ገድላትዋን በታሪክና በነገረ መለኮት ሊቃውንትዋ በማስገምገምና አርሞ በማሳተም ትውልዱን ከቅዱሳን ገድላት ጋር ለማስተሳሰርና ገድላትን ወደ መንፈሳዊ ፊልም ሙሉ በሙሉ እስከመቀየርና በትውልዱ ልብ ውስጥ እስከመሳል ድረስ ስኬታማ መሆን ችላለች፡፡ ከእነርሱ ተቀብለን የተረጎምናቸው መጻሕፍትን እነርሱ ሲያርሟቸው በእኛ በኩል ግን ተመሳሳይ ሥራ አልተሠራም፡፡

ለምሳሌ በሚያዝያ 10 በሚነበበው ስንክሳር ላይ የተቀመጠው ‘“ወሰብአ ኢትዮጵያሰ ኢይሲሙ ሊቀ እማዕምራኒሆሙ’ /የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ/ የሚልን በ318ቱ ሊቃውንት የተነገረ አንቀጽ በመተላለፋቸውና በንጉሥ ሐርቤ ዘመን ጵጵስናን በመጠየቃቸው ምክንያት ድርቅ መቅሠፍት ሆኖ ወረደባቸው’ የሚል የሐሰት ታሪክ አንዱ ነው፡፡ ይህንን የውሸት ታሪክ ግብፃውያኑ ሆን ብለው ኢትዮጵያን ለማስፈራራት የጨመሩት አንቀጽ ቢሆንም የ318ቱ ሊቃውንትን ቃል የምታከብረዋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ያለ ጥያቄ አምና ተቀብላው ኖራለች፡፡

የሚገርመው ግብፃውያኑ ይህንን የሐሰት ትርክት ሲጨምሩ ያበላሹት ሦስት መጻሕፍትን መሆኑ ነው፡፡ አንደኛው መጽሐፈ ስንክሳር ፣ ሁለተኛው ፍትሐ ነገሥት ሦስተኛው የኒቅያ ጉባኤ ድንጋጌ ነው፡፡ ይህንን ሥራ በወቅቱ ከነበሩት ጳጳስ ጋር ተስማምቶ የሠራው የፍትሐ ነገሥት አስተጋባኢ Safey Ibn Al-Assal (13 Ad) ነበረ፡፡ ይህንን ስኅተት የግንቦት 2009 ዓ.ም. ርክበ ካህናት ላይ የብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማን ቀደምት ጥናታዊ ጽሑፍ እንደማስረጃ በመጥቀስ ከስንክሳር እንዲወጣ ወስኖአል፡፡ በመጻሕፍት ላይ ‘በሊቃውንት ጉባኤ ታርሞና ተስተካክሎ የወጣ’ የሚል አንቀጽ በመጻሕፍት ላይ የምናገኘው ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ የኖረ አሠራር ስለሆነ ነው፡፡

የሚገርመው በእኛ ቤተ ክርስቲያን ይህ ውሳኔ ከመወሰኑና ከመታረሙ አስቀድሞ ግን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ባሳተመችው የፍትሐ ነገሥት አዲስ ቅጂ ላይ ‘ይህንን የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ’ የሚል አንቀጽ ስኅተት መሆኑን በመግለጽ አብራ እንደሚከተለው ከእርማት ጋር አሳትማዋለች :-

‘The Ethiopians are not to have a Patriarch from their scientists or by their own choice alone because their patriarch should be under the hand (authority) of the one on the chair of Alexandria’ [This again is wrong, because the council of Nicea did not have any knowledge of Ethiopia which did not have a bishop at the council and did not have a bishop until St. Athanasius ordained Fremenatous for them after the council of Nicea]

‘ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው መካከል በራሳቸው ምርጫ ብቻ ፓትርያርክን ሊሾሙ አይገባቸውም፡፡ ምክንያቱም ፓትርያርካቸው በእስክንድርያ መንበር ሥልጣን ሥር መሆን ይገባዋል’ [ይህም ዳግመኛ ስኅተት ነው ፤ ምክንያቱም የኒቅያ ጉባኤ በጉባኤው ወቅት ጳጳስ ስላልነበራት ኢትዮጵያ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያም ቅዱስ አትናቴዎስ ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ ፍሬምናጦስን እስከሾመላት ድረስ ጳጳስ አልነበራትም] (Al Magmou Al-Safawy Le Ibn Al Assal – The Collection of Church and Civil Laws, 13th Century A.D. page 6)

​የግብፅ ቤተ ክርስቲያን አርአያ የምትሆነው የቀደሙ ገድሎችዋን በማረምና በማጥራት ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ አዳዲስ የቅዱሳንንና በየዘመኑ የሚሠዉ ሰማዕታትን ገድላት በመጻፍና ስንክሳር ውስጥ በማካተት ፣ አዳዲስ ተአምራትን በመመዝገብና በገለልተኛ አካል ምስክርነት በማሠጠት ፣ የሕክምና ማስረጃ ሳይቀር የተካተተበት ዘመናዊ የተአምረ ማርያም መጻሕፍት /Modern Miracles of Mary/ በማሳተም አገልግሎትዋን መቀጠልዋ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለ ጽኑዕ ሃይማኖት ፣ ባለ ብዙ ተጋድሎ ፣ ባለ ብዙ ታሪክ ብትሆንም በአስተዳደር ረገድ በሲኖዶሳዊ መንበር በሁለት እግርዋ ቆማ ራስዋን ማስተዳደር ከጀመረች ገና መቶ ዓመት እንኳን ያልሞላት በመሆንዋ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘርፍ ከሺህ ዓመታት በላይ የተላለፈ ሰንሰለት ካላቸው አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር እያነጻጸርን ልንወቅሳት አንችልም፡፡ በአዋልድ መጻሕፍት ዙሪያ ቤተ ክርስቲያኒቱ እስከዛሬ በርካታ ሥራዎችን እንዳትሠራ ጋሬጣ የሆነባት የአስተዳደራዊ ቁርጠኝነት ማጣት ብቻ አልነበረም፡፡ ከአዋልድ መጻሕፍቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በተጨማሪ ጨርሶ የድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነትዋንና ምልጃዋን የማያምኑ ነገር ግን ከሌሎች የተላኩ ሰዎች በተአምርዋና በገድል መጽሐፍዋ ላይ በስድብ መንፈስ በየዘመኑ እየተነሡ ብዙ ሥራ ሠርተዋል፡፡

ወደ አውሮጳ ጎራ ብለው ሲመጡ ወይንም ከሚስዮናውያን እግር ሥር ትንሽ ቁጭ ሲሉ የሀገራቸውን ነባር እውቀት የጠሉና ራሳቸውን በውጪ ሊቅ ሂሳብ የሚያዩ ፣ ዶ/ር እጓለ እንደሚሉት ያለ የእውቀት ተዋሕዶ በተአቅቦ ማድረግ የተሳናቸው ብዙዎችን አሳልፋለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን አስተምራቸው ፣ በብራናዎችዋ ተከብረው ሳለ እንደ ገለልተኛ አጥኚ እየተቹ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን ሰድቦ ለሰዳቢ የሠጡና ቆይተው የሚፈነዱ የውዝግብ ፈንጂዎችን ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ ቀብረው የሔዱ ምሁራንም ብዙ ናቸው፡፡

tgoop.com/learn_with_John/766
Create:
Last Update:

BY እልመስጦአግያ+++

Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/766

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Earlier, crypto enthusiasts had created a self-described “meme app” dubbed “gm” app wherein users would greet each other with “gm” or “good morning” messages. However, in September 2021, the gm app was down after a hacker reportedly gained access to the user data. Today, we will address Telegram channels and how to use them for maximum benefit. As five out of seven counts were serious, Hui sentenced Ng to six years and six months in jail. You can invite up to 200 people from your contacts to join your channel as the next step. Select the users you want to add and click “Invite.” You can skip this step altogether. Polls
from us

Telegram እልመስጦአግያ+++
FROM American