YENETUBE Telegram 54661
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስን በተመለከተ ከሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ

የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 4 ቀን፤ 2017  የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በሥር ፍርድ ቤት የተወሰነለትን የዋስትና መብት አጽንቷል። ይሁንና መርማሪ ፖሊስ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በመጠየቁ ተስፋለም ወልደየስ ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ሰዓት ድረስ ከእስር አልተፈታም። በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት ተስፋለም ወልደየስ በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ የወሰነው ትላንት ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 ነበር።

ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት የተጻፈው ትዕዛዝ በሚመለከታቸው የፖሊስ መኮንን ሳይፈረም በመቅረቱ ተስፋለም ትላንት ማክሰኞ ሳይፈታ ቀርቷል። መርማሪ ፖሊስ የተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት እንዲከበር የተላለፈው ውሳኔ ላይ ያቀረበው አቤቱታ በዛሬው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተቀባይነት አላገኘም።

የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ለቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ በጻፈው ትዕዛዝ “ይግባኝ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት ስላላገኘን” “የይግባኝ አቤቱታውን አልተቀበልንውም” ብሏል። ፍርድ ቤቱ ተስፋለም ወልደየስ “በስር ፍርድ ቤት ዋስትና መሰረት ግዴታቸውን ሲወጡ ከእስር እንዲፈቱ” ለቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ይሁንና የቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ ዋና ኢንስፔክተር ተስፋለም እንዲፈታ ትዕዛዝ የተሰጠበትን ደብዳቤ “እናንተ ጋር አቆዩትና እኛ ለሰበር ይግባኝ እንላለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የፖሊስ ይግባኝ በአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት ቢከፈትም ዛሬ ችሎት አልተሰየመም።

ስለሆነም ነገ ሐሙስ ሰኔ 5 ቀን፤ 2017 የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት መርማሪዎች ባቀረቡት ይግባኝ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። 

በሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥር የሚተዳደረው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ  ያለፉትን ሶስት ሌሊቶች በፖሊስ ጣቢያ አሳልፏል። ተስፋለም በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ባለፈው እሁድ ሰኔ 1 ቀን፤ 2017 ነበር።

የተስፋለም መታሰር በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የዘገባ ሥራዎች፣ በተቋሙ ባልደረቦች እና በወዳጆቹ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። ተቋማችን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ተፈትቶ ወደ ሥራው እንዲመለስ በድጋሚ በአጽንዖት ጥሪውን ያቀርባል። አሁንም ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ተፈትቶ ወደሚወደው እና ወደሚያከብረው የጋዜጠኝነት ሙያው እስኪመለስ ድረስ ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ከፖሊስ እና ከፍርድ ቤት የሚያገኛቸውን መረጃዎች ለሚዲያው ቤተሰቦች ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

@Yenetube @Fikerassefa

tgoop.com/yenetube/54661
Create:
Last Update:

BY YeneTube

Share with your friend now:
tgoop.com/yenetube/54661

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Telegram Channels requirements & features During a meeting with the president of the Supreme Electoral Court (TSE) on June 6, Telegram's Vice President Ilya Perekopsky announced the initiatives. According to the executive, Brazil is the first country in the world where Telegram is introducing the features, which could be expanded to other countries facing threats to democracy through the dissemination of false content. The court said the defendant had also incited people to commit public nuisance, with messages calling on them to take part in rallies and demonstrations including at Hong Kong International Airport, to block roads and to paralyse the public transportation system. Various forms of protest promoted on the messaging platform included general strikes, lunchtime protests and silent sit-ins. Your posting frequency depends on the topic of your channel. If you have a news channel, it’s OK to publish new content every day (or even every hour). For other industries, stick with 2-3 large posts a week. Done! Now you’re the proud owner of a Telegram channel. The next step is to set up and customize your channel.
from us

Telegram YeneTube
FROM American