tgoop.com/yenetube/54716
Last Update:
አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ36 አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ ዕገዳ ልትጥል ነው!
የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያን ግበፅ እና ናይጄሪያን ጨምሮ የ36 አገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማገድ ሃሳብ እንዳለው ሮይተርስ እና ዋሽንግተን ፖስት የተመለከቱት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጣዊ ሰነድ አመለከተ።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ የተፈረመው ለዲፕሎማቶች የተዘጋጀው ሰነድ ላይ በቀጣይ ዜጎቻቸው ላይ ዕገዳ ሊጣልባቸው የታሰቡት 36 አገራት ዝርዝር የሰፈረ ሲሆን፣ አገራቱ ከዕገዳው ለመውጣት ማከናወን የሚጠበቁባቸው ማስተካከያዎችም ተካተውበታል።
ሰነዱ ዜጎቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ሙሉ ወይም ከፊል ዕገዳ የሚጣልባቸው አገራት በመለየት ያሉባቸውን ችግሮች በማስቀመጥ፤ ይህ ዕገዳ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት አገራቱ የሚጠበቅባቸውን መመዘኛዎች እና ማስተካከያዎችን እንዲያደርጉ የሁለት ወራት ጊዜ እንደሚሰጣቸው ተጠቅሷል።
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ለሚመለከታቸው ዲፕሎማቶች የተሠራጨው ሰነድ "[የውጭ ጉዳይ] መሥሪያ ቤቱ የተቀመጡ መመዘኛዎች እና ግዴታዎችን በ60 ቀናት የማያሟሉ ከሆነ ሙሉ ወይም ከፊል የጉዞ ዕገዳ የሚጣልባቸውን አሳሳቢ የሆኑ 36 አገራትን ለይቷል" ማለቱን ሮይተርስ አመልክቷል።
ባለፈው ግንቦት ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ አገራት ባሉባቸው 12 አገራት ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአገራቸውን እና የሕዝባቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ በሚል ትዕዛዝ ፈርመው ተግባራዊ መሆኑ ይታወሳል።
(ቢቢሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
BY YeneTube

Share with your friend now:
tgoop.com/yenetube/54716