Telegram Web
. 1 እናቴ ልደታ ማርያም ናት
ባለ ፀጋ እመቤት ባለ ፀጋ እናት አፍሰናል ከደጅሽ
ብዙ በረከት ወጀቡን ቀዝፈናል ብለን ማርያም
እንዘምራለን እስከ ዘላለም!! የፍቅር እናት
ፍቅሯ በረከቷ ምልጃዋ አይለየን
ቀኑን በሰላም ታዉለን
አሜን + አሜን + አሜን🙏💓
@yadengillej
ጥር 6 በዚህች ቀን በወጣትነቷ ሰማዕትነትን የተቀበለች፣ የእርሷን አርአያነት ተከትለው ብዙ ደናግላን ከእርሷ ጋር ሰማዕትነት የተቀበሉ፣ በአማላጅነቷ ፈጥና የምትደርስ፤ ስለ ክርስቶስ ስትል በከፈለችው ሰማዕትነት፣ ድንግልናን በብጽዐት ለመጠበቅ ስትል በተቀበለችውን መከራ፣ ወጣትነቷ ሳያጓጓት ለእምነቷ በከፈለችውን ዋጋ፣ ንጽሕናዋን ቅድስናዋን ለመጠበቅ ባሳየችው ጽናት፣ በሕይወቷ ሳለች ከሠራችውም በላይ በሰማዕትነቷ ባፈራችውን ፍሬ ልናስባትና ልንማርባት ደግሞም እንደ ዓቅማችን ልንመስላት የሚገባ ታላቋ ሰማዕት #ቅድስት_አርሴማ ከእናቷ ከቅድስት አትናስያ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስ የተወለደችበት ቀን ነው።

አማላጅነቷ አይለየን!
Forwarded from áŠ á‰ĄáŠ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝
" ተጠምቀ ሰማያዊ በ እደ መርየታዊ"

በመጀመርያ እንካን ለ አምላካችንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳቹ አደረሰን።
በመቐለ ከተማ እና አካባቢዋ ለምትገኙ ምዕመናን ደብራችን ደብረ ፅጌ ቅድስት ማርያምና ቅዱስ ሚካኤል ዓዲሹምዱሑን ቤተ ክርስቲያን በዓለ ጥምቀትና በዓለ መስቀል ሲያከብር ከቀድሞው ጀምሮ በ ደብሩ ቤተክርስቲያን አፀድ እንደሚያከብር ይታወቃል። ዘንድሮም በዓለ ጥምቀትና በማግስቱ በደብሩ የሚከበረው የቃና ዘገሊላ ታላቅ በዓል ምክንያት በማድረግ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ከ 11/05/2012 ዓ/ም እስከ 13/05/2012 ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆይ ልዩ መርሐ ግብር ስላዘጋጀ ሁላችን መጥተን ቃሉን እንማር።
* ሰዓት ከምሽቱ 11፡30 ይጀምራል።
Share share share
ሰማያዊት እናት

ሰማያዊው አባት ክርስቶስ ኢየሱስ እናቱ ያረገሽ፣ በእግዚአብሔር ተመርጠሽ ማደሪያው የሆንሽ፣ የአምላክ እናትነት ሥልጣን የተሰጠሽ፣ በልጅሽ በኢየሱስ ፊት ልዩ ክብር ያለሽ፣ የጌታ ኢየሱስ እናት፣ የሕይወት እናት፣ የብርሃን እናት፣ የወይኑ ግንድ እናት፣ የመልካሙ እረኛ እናት፣ የከበረው አምላክ የክርስቶስ ኢየሱስ እናት ሆይ በልጅሽ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ታላቅ ባለሟልነት አለሽና እባክሽ ልጅሽን ስለኔ ለምኚልኝ።
@yadengillej
ረድኤት በረከቱ ይደርብንና በዚኽች ዕለት ጥር 15 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓሉ ታስቦ የሚውለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በዐፀደ ነፍስ ተገልጦ ለንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስ ያደረገለት ታላቅ ተአምር ይኽ ነው፡- ‹‹በቅድስት ሀገር በሮሐ ከአምላኩ ዘንድ የክህነትን ሥልጣን የተቀበለ የዓለምን ተድላ ደስታ ንቆ መንግሥቱን ከተወ በኋላ በገዳም ሲኖር ለ40 ዓመት ያህል በበዓላትና በየሰንበቱ ከሰማይ ኅብስትና ወይን የወረደለት አንድ ጻድቅና ካህን ነበር፡፡ የጽድቁም ምልክት እስካሁን ክቡር ሥጋው ካረፈበት ሥፍራ አለ፡፡ በመንግሥቱ ሳለ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንፈስ ቅዱስ ባመለከተው ቦታ በባሕር ላይ ቤተ ክርስቲያን ሊያንጽ ተነሣ፡፡ ንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስን የቤተ ክርስቲያኑን መሠረት ለማሳመር ሁሉ እያንዳንዱ ደንጊያና ሸክላ እንጨትም እንዲሸከም ትእዛዙን ይነግር ዘንድ በግዛቱ ዓዋጅ ነጋሪ አዞረ፡፡ ንጉሡም ከባሕር ዳርቻ ቆሞ አገልጋዩ በባሕሩ ላይ ለቤተክርስቲያኑ መሠረት ርብራብ ሊያደርግ ከባሕሩ ገባ፡፡ ይህንንም ሲያደርግ የባሕር ጋኔን ወጥቶ መታው፣ ፈጥኖም ሞተ፡፡ ንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስ የሰይጣንን መተነኳኮል አይቶ አብዝቶ አዘነ፡፡ በዚህ ጋኔን ስለሞተ አገልጋዩ ስለ ቤተክርስቲያንም መታነጽ የሚያደርገውን ሲያስብ ስለጽድቅ የተጋደለ ማር ቂርቆስ ድንገት በታላቅ ክብር ተገልጦ ‹የተቀባህ ንጉሥ የከበርህም ካህን ሆይ! በአምላኬ ሥልጣን የሞተ አገልጋይህን እኔ አስነሣልሃለሁ፣ ጋኔኑንም እበቀለዋለሁ፣ አንተም ኃይል በተደረገልህ ሥፍራ በምትሠራት መቅደስ ውስጥ በስሜ የተሠየመ ታቦት ታኖራለህ› አለው፡፡
ንጉሡም ‹የክርስቶስ ሰማዕት ሆይ! እንዳልኸው አደርጋለሁ› ብለ መለሰ፡፡ ያን ጊዜም ማር ቂርቆስ እጁን ዘርግቶ የጋኔኑን የራስ ጠጉር ይዞ ከባሕር ውስጥ አወጣው፡፡ ቁመቱ ፈጽሞ ረጅም፣ ሁለንተናውም በእሳት እንዳቃጠሉት የእንጨት ግንድ ጥቁር ነበር፡፡ ከቅድስት ሀገር ከሮሐ ወደ ጎጃም ምዕራባዊ ክፍል እንደ ድንጊያ ወረወረው፣ በዚያም ሞተ፤ የሞተው የንጉሡ አገልጋይ ግን ከሞት ተነሣ፡፡ ንጉሡም ፈጽሞ ደስ ተሰኘ፡፡ አምስት ጊዜ ከሩቅ የዞጴ እንጨት እየተሸከመ ያችን መቅደስ ሠራት፡፡ ከአገልጋየቹም ጋር ሲሠራ ይውል ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስም የመቅደስ ሥራዋን እያመለከተው ከእርሱ ጋር ነበረ፡፡ የመቅደስ መታነጽም ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስ በከበረ ሕፃን ቂርቆስ ስም የተሠየመ ታቦት በውስጧ አኖረ፡፡ ኅብራቸው ባማረ የከበሩ ጌጦችና ልብሶችም አስጌጣት፡፡ በውስጧም በጥቅምት 19 ቀን ቀደሰ፡፡››
(ምንጭ፡- ገድለ ቅዱስ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ገጽ 98-100)
ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ሆይ! በነቢዩ ኤልያስ ሠረገላ ተሰውሮ ላለ ቅዱስ ሥጋህ ሰላም እላለኹ!
ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በዚኽች ምድር ላይ በሥጋው መከራን በሚቀበልበት ወቅት ማኅበርተኞቹ የተባሉ ዓሥራ አንድ ሺህ አራት ሰዎችን በተአምራቱና በትምህርቱ አሳምኖ ለክርስቶስ መንግሥት ያበቃ ታላቅ ሐዋርያም ጭምር ነው!!! የከበረች በረከቱ ትደርብን በጸሎቱ ይማረን!
እንኳን ለቅድስት ኪዳነምህረት አመታዊ ክብር በዓል በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ አደረስን

#ኪዳነምህርት በያላችሁበት ትጠብቃችሁ
ስላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ😢😢😢
ምስክር አልሻም ላንቺ አማላጅነት
በፀናው ፀሎት።።።።። ስላለሁ በህይወት
በተሰጠሽ ኪዳን።።።።። ከማሕፀንሽ ፍሬ
እነሆ ቆሜአለው።።።።።። ምሮኝ እስከ ዛሬ
የነገም ተስፋዬ።።።።።። እመቤቴ ክብሬ
ውለታሽ ብዙ ነው።።።።።። አልቋጨው ዘርዝሬ።

የቃል ኪዳኗ እመቤቴ እምዬ ኪዳነ ምህረት ምልጃዋ አይለየን~😢🙏🙏🙏
@yadengillej
አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት።
ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።
ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው።
"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል?
"የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት ይባላል? ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን?
በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን? በፍጹም አይሆንም! የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን? እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ?
አባ ጊዮርጊስ "ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣ ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ?" ይል የለምን? ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም።
"ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ" (መዝ 4
🌻🌻🌻#ጾመ_ነነዌ🌻🌻🌻
➕
•
✅ ጾም የነነዌ ሰዎችን በዮናስ አማካኝነት በሦስት ቀን ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት አማካኝነት የዳኑበት ሲሆን፣ የሰው ልጅም ከላይ ለመግለጽ እንደሞከረው ከጸጸት እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጥ የተረዳንበት ፆም ናት።

✅ይህቺ ፆም የሦስት ቀን ብትሆንም ብዙ በረከት እና ረድኤት የምናገኝባት ጾም ነች። በዚህም ፆም የነነዌ ሰዎች ከትልቅ እስከ ትንሹ ንጉሡኑም ጨምሮ ልባቸውን ሰብረውና ተጸጽተው አምላክ ምህረትን ይሰጣቸው ዘንድ ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው የጸለዩበት ጊዜ ነው።

✅ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርም ከልብ መጸጸታቸውን አይቶ ሀቁጣው ተመልሶ ሊመጣባቸው ከነበረው ጥፋት ድነዋል። 'ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2 ይመልከቱ።'

✅እኛም ክርስቲያኖች ይህን በማዘከር ንስሃ ብንገባ እንደ ነነዌ ሰዎች ከተቃጣው ማንኛውም መቅሰፍት እንድናለን።
በማለት በየዓመቱ ከአብይ ፆም መግቢያ ሁለት ሳምንት አስቀድሞ ካለው ከዕለተ ሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ «#ፆመ_ነነዌ» በማለት እንፆማለን። እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ የሚመጣብንን መቅሰፍት የሚያይ አምላክ ከሚመጣብን መከራና መቅሰፍት ሁሉ ይጠብቀን !

💒➕💒#ከሰንበት_ረድኤት_በረከት_ይክፈለን💒➕💒
@yadengillej
@yadengillej
አባቴ ሆይ ማረኝ😭
በእንባየ ልጠብህ በፀጉሬ ልዳብስህ ስለኔ
የተወጉ እግሮችህ ይቅር በለኝ ፣ አባ እራሴን
ማሸነፍ ከበደኝ የስጋን ምኞት አለመፈፀም
ከበደኝ በኃጢአት ተዘፍቄ መዉጣት ግን ከ
በደኝ አንተን አሳዘንኩህ አንተን ብቻ በደልኩ
ህ ይቅር በለኝ ጌታዬ እኔ ደጋማ ልጅ ነኝ ።
በፊትህ እንኳን ለመቆም አፈርኩኝ ፣ ቤትህ
መሄድ አፈርኩኝ ፣ በፊትህ ሁኜ ፊትህ መቅ
ረብ ግን ፈራሁኝ ፣ በፊትህ አድርጌ ሳደርግ
ያልፈራሁህ ምህረት ስጠይቅ ግን ፈራሁህ
እንደት ያለሁ ከንቱ ነኝ አባ ⁉

ማረኝ ጌታዬ ሆይ ማረኝ አባ
እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወራዊ መታሰቢያ በዓልና ቅዱስ አባ መርትያኖስ በዓለ ዕረፍ እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን

መልካም እለተ ሐሙስ ይሁንልን
@yadengillej
+++ #ፆመኛ_ነኝ_አትበሉ+++

አባታችን ዜና ማርቆስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ ”ስለ ነፍሳችሁ ድኅነት፣ ከመከራና ከጥፋትም ሁሉ ለማምለጥ በምትጾም ጊዜ እንዲህ እየጾማችሁ ሳላችሁ ስለምትሹት ግብር ወደ ዓለም ሰዎች ብትደርሱና በጾም ቀን ሲበሉና ሲጠጡ ብታዩአቸው መብልና መጠጥን በሚወዱ ሰዎች ፊት በውጭ በአደባባይ «ዛሬ የፆም ቀን ስለሆነ እኛ እንጾማለን» አትበሉ። ስለ እናንተ መጾምና ስለ እነርሱም አለመፆም አንዳች አትናገሩ፤ ባለመጾማቸውም አትንቀፏቸው። ስለ ሌላ ሥራ ወደማይፆሙ ሰዎች ብትደርሱ ግን በጾም ዕለት ወንድሞቻችን
«ኑ አብረን እንብላ » ቢሏችሁ እኛ እንጾማለን አትበሉ ፣ እንዲህ በሉ እንጂ፦«ወደ እናንተ ከመምጣታችን በፊት ከቤት በልተናል፣ ጠግበናል» ስትሏቸው እናንተ እንደምትጾሙ ያውቃሉ።»»»
(ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ)
.
.
.
“ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና ፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥
በሥውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።»
(ማቴዎስ 6፥16-18)።
አምላክ ቅዱሳን መድኅን ዓለም መዋዕለ ፆሙን የበረከት ያድርግልን!

#በቸር_ያውለን🙌➕🙌
@yadengillej
@yadengillej
~ አሁንም፣ ይላል፣ እግዚአብሔር፣
~ በፍፁም፣ ልባችሁ፣ በጦም፣ በልቅሶ እና
~ በዋይታ፣ ወደ እኔ፣ተመለሱ!!!

~ (መፁሐፈ እዮብ ምዕራፍ ሁለት ቁጥር 12 )
,~ ልዑል እግዚአብሔር ለሁላችንም ንፁሕ ልብ ይፍጠርልን ለንሰሀ ሞት ያብቃችሁ!!!
~በሰደት ያላችሁ.......
~ ልዑል እግዚአብሔር .......
~ ወቶ ከመቅርት ይሰውራችሁ......
~ ይሰውረን ............

~ በምድር ያበበ በሰማይ ይረግፍል.....
~ በምድር የተጎሳቀለ ያለቀሰ በሰማይ ምህርትን ያገኛል ....

~ የድንግል ማርያም ያሰራት ያደራ ልጆች በልዑል እግዚአብሔር ሥም በያላችሁበት በእግዚአብሔር የተባረከ የተቀደሰ ምሺት ይሁንላችሁ ይሁንልን አሜን!!!🙏
@yadengillej
@yadengillej
✝ ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ ✝

=> የኢትዮጵያ ገበዝ

#የካቲት 23

በዛሬዋ ቀን የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የጣሊያንን ሠራዊት በቅዱስ ጊዮርጊስ አጋዥነት ድል ያደረጉበት ዕለት ናት ::

የማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን ::

#አሜን
@yadengillej
የእምነት አባቶቻችን የጌታ ደቀመዛሙርት ህይወታቸው እንዴት አለፈ?
1.ማርቆስ:- እስኪሞት ድረስ በአሌክሳንድርያ ግብፅ ጎዳናዎች በፈረስ ታስሮ
እየተጎተተ ህይወቱ አልፋለች
2.ሉቃስ:- በግሪክ ሰቅለውት ህይወቱ አልፋለች
3.ማቲዎስ:-በቆንጨራ ተቆርጦ ሞቷል
4.ዮሐንስ:- በፈላ ዘይት ውስጥ ተቀቅሎ ህይወት አለፏል
5.ጴጥሮስ:-ተዘቅዝቆ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቷል
6.ቶማስ:- በህንድ በጦር ተወግቶ መስዋእት ሆኗል
7.ጳውሎስ:-በአሰቃቂ ሁኔታ ተገርፎ አንገቱ ተቆርጦ ህይወቱ አልፏል
8.ስምዖን:-ግማሽ ለግማሽ ተቆርጦ ነው የሞተው
9.ማቲያስ:-በድንጋይ ተወግሮና አንገቱ ተቆርጦ
10.እንድርያስ:-በስቅላት ህይወቱ አልፏል
11.ያዕቆብ:-በእየሩሳሎም አደባባይ አንገቱ ተቆርጦ የሞተ
12.በርተለሚዎስ:-በግርፋት ህይወቱ አልፏል

ሁሉም መልካሙን ገድል ተጋደሉ ክርስቶስን ካዱ ሲባል አይሆንም ብለው
አንገታቸውን ለካራ ሰውነታቸውን በዘይት ለመቀቀል ለግርፋት ለስቅላት
አሷልፈው ሰጡ።እርስዎስ በአሁኑ ሰዓት ስለምን እያማረሩ ይሆን?በላይ ያለው
ክብር ይበልጣል።ይኸኛው አላፊ ጠፊ ነው።
በረክታቸው ይደርብን

መልካም ቀን አሜን🙏🙏🙏
@yadengillej
እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ ድኅነታችንም ተግሳፅ በርሱ ላይ ነበር በሱ ቁስል እኛ ተፈወስን። [[ ኢሳይያስ 53፥5 ]]

💟ማልደራደርበት ማልቀብረው እውነት
አንገቴን የማያስደፋኝ የማላፍርበት
#ኢየሱስ የሚለው ስም እስትንፋሴ ነው
እውነቱ ይኸው ነው።

#ክብርና_ምሥጋና_ሁሉ_ለድንግል_ማርያም_ልጅ_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ይሁን~~~አሜን💟➕💟
@yadengillej
#የትርፍ_ጊዜ(part time)እና #የሙሉ_ጊዜ(full time) ክርስቲያን★--------------🔘----------🔘----------🔘-------------🔘 ክርስትና በክርስትና ሕይወትነት ለዓለምና ለጠላት ዲያብሎስ ሃሳብ ሙት ሆነን የምንኖረው አስደሳች ሕይወት ነው። (ዮሐንስ 14፥6፣ ገላትያ 2፥20)። የክርስትና ኑሮ የዕድሜ ገደብ የለውም። ይህ ማለት ክርስትና በምድርም በሰማይም ዘለዓለም የምንኖረው ሕይወት ነው ማለት ነው።

በምድር በክርስትና ኑሮ የተለማመድነውን ምስጋና በሠማይ ስለምንደግመው ክርስትና ዘለዓለማዊ ነው። ክርስትና አስደሳች ህይወት እንደሆነ ሁሉ በእሾህ የተከበበም ማንነት ነው። በክርስትና ሕይወት እየኖሩ እሾህ (ፈተና) አይድረስብኝ ማለት በውሃ ውስጥ ሆኖ ውሃ አይንካኝ እንደማለት ይቆጠራል። ክርስቲያን በመሆናችን የሚያደርስብንን ፈተና እንድንከላከል እግዚአብሔር ጸሎትን አስታጥቆናል። (ማቴዎስ 26፥41)።
ፈተናን በጸሎት የመከላከል አቅም ሲያንሰንና በፈተና ውስጥ ስንጣል ዝም የማይል እግዚአብሔር የሚያጸና መንፈሱ ለፈተናው እጅ እንዳንሰጥ ያጽናናል (ያዕቆብ 1፥12)። በፈተና በጸናን መጠን ከፈተና መውጫውንም ያዘጋጅልናል (1ኛ. ቆሮንቶስ 10፥13)።

ብዙውን ጊዜ በክርስትና እንኖራለን የምንልና በገዛ ምኞታችን እየተጎተትን የምንፈተን እግዚአብሔር ክርስቲያን በመሆኔ ፈተነኝ የምንል ካለን መልሱ እግዚአብሔር ያመኑትን በከንቱ አይፈትንም የሚል ነው ( ያዕቆብ 1፥13-15)።
ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ተደሰትንም አዘንንም፣ ወደቅንም ተነሳንም፣
አገኘንም አጣንም ፣ ተሳካልንም አልተሳካልንም በእግዚአብሔር ፊት ክርስቲያን ሆነን ወይም በክርስቶስ ሕይወትነት ለዓለምና ለጠላት ሃሳብ ሙት ሆነን መኖርን ገንዘብ ማድረግ አለብን። በዚህ መንገድ ስንኖር የሙሉ ጊዜ ክርስቲያኖች ነን።
የትርፍ ጊዜ ክርስቲያኖች ክርስትናቸው በተመቻቸው ወይም ባልተመቻቸው ጊዜ ብቻ ትዝ የሚላቸው ሲሆኑ በክርስትና ጉዳይ ከሙሉ ጊዜ ክርስትያኖች በላይ ተቆርቋሪ መስለው ይታዩና ወዲያው ታጥቦ ጭቃ ይሆናሉ።
መስረቅ ፣መስክር፣ መዘሞት፣ ጭፈራ፣ ጫት መቃም፣ ሺሻ ማጨስ፣ በአቋራጭ መክበር ወ. ዘ.ተ ሲያምራቸው ክርስትናቸውን አውልቀው የሚጥሉ የትርፍ ጊዜ ክርስትያኖች ናቸው። የሙሉ ጊዜ ክርስትያኖች ግን ማንነታቸው የሚፈትን የኃጢአት ድግስ ቢቀርብላቸውና ሰው ባያያቸው እንደ ዮሴፍ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን እንዴት እሰራለሁ በማለት ክርስቲያናዊ ቁርጠኝነታቸውን ያሳያሉ (ዘፍጥረት 39)

አሁን ያለንበት ዘመን የትርፍ ጊዜ ክርስቲያኖች የበዙበት ይመስላል። ክርስትናቸውን አውልቀው ጥለው በኃጢአት ቦታ ፊት አውራሪ (መሪ) የሆኑና በአምልኮ ስፍራም ካለ እኛም ሰው የለም የሚሉ የጥምቀ፣ የመስቀል፣ የታቦት ክርስቲያኖች የሆኑ ግለሰቦች ማስተዋል የተለመደ ሆኗል። አንዳንዴም በኃጢአት ሥፍራ የደረሰባቸውንና ያደረሱትን ኪሳራ ለማካከስ ስደቡ ሲባሉ የሚሰድቡና ግደሉ ሲባሉ የሚገድሉ ምስኪኖች አሉ።።
እንድ ነገር እንወቅ ኃጢአት በእምነት በሆነ ንስሓ ይታጠባል እንጂ በሌላ ኃጢአት አይካሰስም። ስለዚህ እግዚአብሔር የጠራን ለሙሉ ጊዜ ክርስትና መሆኑን በመገንዘብ በትርፍ ጊዜ ክርስትናን እየኖርን ያለን እራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል።

በልጅነቴ አንድ ሰባኪ፦ “ክርስትና በረደን ብለን የምንደርበው፤ ሞቀን ብለን የማናወልቀው ይዘውትር ልብስ ነው" በማለት ያስተላለፈው መልእክት ከዚህ ጽሁፍ ጋር ይገናኛል። ክርስትና ጨው ነው። ለፖለቲካው ዘርፍ፣ ለኢኮኖሚውን ዘርፍ ይሁን ለማኅበራዊው ኑሮ ዘርፍ ክርስትና ማጣፈጫ ጨው ነው። ፖለቲካው ፣ ኢኮኖሚውና ማኅበራዊው ኑሮ በክርስትና ቢቃኙ ምድር እፎይ ትል ነበር። ሌላው ይቅርና ክርስቲያን ሆኖ ኃጢአት መስራትና ክርስቲያን ሳይሆኑ ኃጢአት መስራት ይለያያል ። ክርስቲያን ኃጢአት ቢያደርግ በንስሓ የመታደስ ተስፋ አለው። ክርስቲያን ያልሆነ ግን ይህ ተስፋ ስለሌለው በቶሎ ይሰበራል። የትርፍ ጊዜ ክርስቲያኖች በገዛ ምኞታቸው እየተጎተቱ ክርስቲያን የማይሆኑበት ጊዜ አለ። የሙሉ ጊዜ ክርስቲያኖች ግን ክርስቲያን የማይሆኑበት ጊዜ የለም ።
የሙሉ ጊዜ ክርስቲያኖች እንድንሆን መንፈስ ቅዱስ ያግዘን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@yadengillej
🛑 ለጥንቃቄ🛑


🅾አንብባችሁ ለሌሎችም አስተላልፉ
ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ
ያቆመዋል!

◾️በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው
ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ
የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ
ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ
የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

➖ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው
አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል
የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

➖ ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም
የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ
...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን
ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

➖ በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ!

➖ የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ
ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ
በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት
ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡

➖ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና
ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው::

➖አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ
ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ
ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12
ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ
እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም
መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን
በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት
ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር
በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡
በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው
ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡
በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ
ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት
ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::
2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ
ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን
በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት
የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!!
በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?
1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን
ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ
መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ
በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን
ያስገነዝበናል፡፡
< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ
ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን
ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ
ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ
ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡
< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ
በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡
2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም
መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን
መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ
አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም
ሊቀንሰው ይችላል፡፡
3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

© ምንጭ : ዶ/ር ቤዛ አያሌዉ
2025/08/24 05:24:55
Back to Top
HTML Embed Code: