Telegram Web
ከስሜታችን በላይ መሆን
Success = Stress Tolerance

የሰዎ ልጅ ስሜት እጅግ ተለዋዋጭ ነው። በተለዋዋጭነቱ ከምናውቀው ከአየር ጸባይ በፈጠነ ሁኔታ የሚለዋወጥ ነገር ቢኖር ስሜታችን ነው፡፡

በሀሳባችን በኩል የሚወለዱ ማንኛውም ጥሩ/መጥፎ ስሜት እኛ ላይ ሀይል አለው። በከፊል/ሙሉ ለሙሉ እኛነታችንንና ባህሪያችንን ይቆጣጠራል።

በጣም የሚገርመው እውነት ግን ስሜታችን ምንም እንኳ ሀይል ቢኖረው የሰው ልጅ ሊቅነቱን ካወቀና የአዕምሮውን ሀይል ከተረዳ ስሜቱን መቆጣጠር ይችላል።

በነገራችን ላይ ከስሜታችን በላይ ካልሆንን መለወጥ ከባድ ነው። ብዙ ጊዜ እኛን የሚለውጡ ሀሳቦችና ስሜቶች የኛን ከስምታችን በላይ አንድ እርምጃ መጓዝ ይሻሉ። ካልሆነ ባለህበት ርገጥ ነው ወዳጄ...Anyway Win your Negative feelings

ምን እናርግ ሊቅነት
1. እስስት አትሁን። አቋም ይኑርህ! ስሜትህ ከፍ ዝቅ ባለ ቁጥር ሃሳብን ተግባርን ተግባርህን አለመለዋወጥ፡፡
2. ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ዓላማን አለመለዋወጥ፡፡ ስሜታችን ጥሩ ሆነም መጥፎ ከዓላማችን ለይተን ማየትና ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡ ማንኛውም ስሜት እያለ ዓላማችንን መከታተላችንን መቀጠል ስኬታማ ሰዎች ያደርገናል፡፡

3. ስሜት በተለዋወጠ ቁጥር ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት አለመዋወጥ፡፡ ስሜቴ ጥሩ በሆነና መጥፎ በሆነ ቁጥር ከሰዎች ጋር ያለኝን ግንኙነት የሚነካው ከሆነ የተበላሸ ማሕበራ ሕይወትና የሕይወት አቅጣጫ ውስጥ መግባህ አይቀርም፡፡

ዋናኛው መፍትሔ ደግሞ ዲሲፕሊን ነው። ራስህን ስሜቱን አሸንፎ የሚሰራ የሚጥር የሚተጋ አድርገህ ማንነትህን መስራት።

ይህን ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ይምጡ ይማሩ ይደጉ።
ሊቅነት-ራስን የማሳደግ ስልጠና!
ለ2 ወራት የሚሰጥ!
0929192323
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ነገራችን ወሬ ብቻ እንዳይሆን!

“ስለ አንድ ነገር የምታወሩ ከሆነ ነገሩ ህልም ይባላል፣ ስለነገሩ በሚገባ ማሰብ ስትጀምሩ ነገሩ ወደመቻል ይሸጋገራል ማለት ነው፣ ለነገሩ የጊዜ ሰሌዳ ካዘጋጃችሁለት ግን ነገሩ እውን ወደመሆን ይመጣል” - ANTHONY ROBBINS

• ቁጭ ብላችሁ ወደማሰብና ስለነገሩ ወደማሰላሰል ያልደረሰ እስካሁን በወሬ ብቻ የቀረውን ነገር እስቲ ለማስታወስ ሞክሩ!

• ካሰባችሁና ካሰላሰላችሁት በኋላ ወደ እርምጃ እና ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት የጊዜ ገደብና ሰሌዳ ያላስቀመጣችሁለትንም ነገር እስቲ አስቡት!

ነገሮቻችሁ ከወሬ አልፈው ሃሳባችሁን እንዲገዙት፣ ከሃሳብ አልፈው ደግሞ ወደ እውነታ እንዲመጡ ከፈለጋችሁ ይህንን መርህ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

ንግግራችን ረገብ፣ ሃሳባችሁን ሰፋ፣ እቅዳችሁ ደግሞ ተግባራዊ በማድረግ ልቃችሁ ተገኙ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የኢቲኬር 7ኛ ቅርንጫፍ በጎንደር የመክፈቻ ስነስርዓት
ማክሰኞ መጋቢት 12  ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ
የድርጅቱ መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል
Etcare  I care! You care! We care
@etcareofficial
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ጭንቀትን ስንገነዘበው
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ጭንቀትን ስንገነዘበው

ጭንቀት አለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ ብዙ ሰዎች ስለ ብዙ ነገርና በሆነ ባልሆነው ነገር ይጨነቃሉ፡፡ የዘመኑ ጭንቀት ለብዙዎች አሳሳቢ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ጭንቀቱን ለማቆም ቢፈልጉም ያለመቻላቸው ጉዳይ ነው፡፡

በአጭሩ ሲገለጥ ጭንቀት አንድ ነገር ከቁጥጥር ውጪ እንደሆነ ወይም ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ከእኔ ንግዴ ቢከስርስ፣ ብታመምስ፣ የምወደው ሰው ትቶኝ ቢሄድስ . . . የሚል ስጋትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች፡፡

ለጭንቀት መፍትሄን ለማግኘት የምንወስደው የመጀመሪያ እርምጃ ጭንቀቶቻችንን ለሁለት በመክፈል ማየት ነው፡፡

1. አንድ የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድ ለውጥ ልናመጣባቸው የምንችልባቸው የጭንቀት አይነቶች

ይህንን አይነቱን የጭንቀት ስሜት በእግሊዝኛው worry በመባል የምናውቀው ሲሆን ትክክለኛ እና ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚችል፣ እንዲሁም ደግሞ ከስሜቱ የተነሳ ባስጨነቀን ነገር ላይ አንድ ብልህ የሆነን እርምጃ በመውሰድ የምናረግበው ስሜት ነው፡፡

2. ምንም ነገር ብናደርግ ለውጥ የማናመጣባቸው የጭንቅ አይነቶች

ይህንን አይነቱን የጭንቀት ስሜት በእግሊዝኛው anxiety በመባል የምናውቀው ሲሆን ትክክለኛ ያልሆነ እና ከቁጥጥራቸው ውጪ በሆኑ ሁኔታዎች ዙሪያ ስሜታቸው እስኪዛባ ድረስ የሚያስቡ ሰዎች የሚጋሩት ነው፡፡

ከአንዳንድ በግል mentor እና coach ከማደርጋቸው ሰዎች ጋር አብረን የምንሰራውን ቀላል ስራ እንድትሰሩ ላደፋፍራችሁ፡፡ ምንም እንኳን ከእነሱ ጋር በግል ሰፋ ያለ ሃሳብ ውስጥ ብንገባም፣ በዚህች አጭር ጽሁፌ ግን አንድ ቀላል ስራን መስራት እንችላለን፡፡

ያስጨንቀኛል የምትሏቸውን ነገሮች በሙሉ በዝርዝር ጻፏቸው፡፡ ለምሳሌ፣ የስራ ጉዳይ፣ የጤንነት ጉዳይ፣ የሃገር ሰላም ጉዳይ፣ መኖሪያ የማጣት ጉዳይ . . . ፡፡

ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ እነዚህን ነገሮች ለሁለት ክፈሏቸው፡፡ በአንድ ጎን worry ብለን የሰየምነውን አይነት ስሜት የሚሰጧችሁን ነገሮች አስፍሩ፡፡ በሌላው ጎን ደግሞ anxiety ብለን የሰየምነውን አይነት ስሜት የሚሰጧችሁን አስፍሩ፡፡

አንዳንድ ነገር በማድረግ ለውጥን እንደምታመጡ የምታስቧቸው ነገሮች (worry) ላይ ቁጭ ብሎ ከመጨነቅ ይልቅ እቅድ በማውጣት የመፍትሄ ስራ መስራት፣ ሰውን ማማከርና የመሳሰሉትን ነገሮች ማድረግ ዋናው የመፍትሄ መንገድ ነው፡፡

ምንም ብታደርጉ ለውጥን ማምጣት እንደማትችሉ የምታስቧቸው ነገሮች (anxiety) ላይም ቢሆን ቀንም ሌሊትም ከመጨነቅ መለወጥና መቆጣጠር እንደማንችለው በመገንዘብ ፈጣን ማመንና የትኩረት ለውጥ ማድረግ ዋናው የመፍትሄ መንገድ ነው፡፡

ነገሩን worryም አልነው anxiety እድትረጋጉና ውስጣችሁ ያለው እምቅ ብቃት ላይ እንድታተኩሩ ፈጣሪ ይርዳችሁ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ወደ ትክክለኛው የግንኙነት መርህ እንመለስ!

ትክክለኛ አመራር ማለት ተከታዮች አመራሩን ያለመከተል ምርጫ ሲኖቸውና ያንንም ምርጫ በመውሰዳቸው ምክንያት ምንም አይነት ጫና እና በደል እንደማይደርስባቸው ሲያውቁ ነው፡፡ ይህንን ነጻነት የሚሰጡ መሪዎች በእርግጥም የመልካም ተጽእኖ መሪዎች ናቸው፡፡ ያለመከተል ምርጫ እንዳላቸው እያወቁ የሚከተሉም ሰዎች በእርግጥም በመልካም ተጽእኖ ስር ያሉ ተከታዮች ናቸው፡፡ ይህ የምርጫ ነጻነት በሌለበት ሁኔታው ውስጥ የሚንጸባረቀው ሁኔታ አመራር ሳይሆን ኃይልና ስልጣን ነው፡፡

ትክክለኛ ፍቅር ማለት አንድ ሰው በዚያ የፍቅር ግንኑነት ያለመቀጠል ምርጫ ሲኖረውና ያንንም ምርጫ በመውሰዱ ምክንያት ምንም አይነት የበቀልና የማስፈራራት ሁኔታ እንደማይደርስበት ሲያውቅ ነው፡፡ ይህንን ነጻነት የሚሰጡ ፍቅረኞች በእርግጥም ትክክለኛ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ የፍቅር ግንኙነቱን የማቋረጥ ምርጫ እንዳላቸው እያወቁ በግንኙነቱ ለመቀጠል የሚወስኑም ሰዎች በእርግጥም በእውነተኛ ፍቅር የተማረኩ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ የምርጫ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ የሚንጻባረቅ ሁኔታ ፍቅር ሳይሆን ቁጥጥር ነው፡፡

ይህንንው መርህ በመከተል በሌሎች መስኮችም ጭምር ያሏችሁን ግንኙቶች ከጉልበተኛነት፣ ከኃይለኛነትና በግዳጅ ከመግዛትና ከመገዛት ነጻ የማውጣት ቀን ይሁንላችሁ፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Etcare Official®️ (Kloud ፲፩)
የኢቲኬር ጎንደር ቅርንጫፍ  ተመርቆ ተከፈተ።
የኢቲኬር 7ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የጎንደር ቅርንጫፍ በዛሬው እለት የድርጅቱ ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ የድርጅቱ የማኔጅመንት አባላት አሰልጣኞች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም በርካታ የኢቲኬር የምርት አስተዋዋቂዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተመርቆ ተከፍቷል። ኢቲኬር በአጭር ጊዜ  ውስጥ እየሄደ ያለበት የስኬት ጉዞ  አንዱ ማሳያ  ይህ የጎንደር ቅርንጫፍ ሲሆን በቀጣይም ድርጅቱ ቅርንጫፎችን ለማስፋት በሂደት ላይ መሆንን የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አሳውቀዋል።
ኢቲኬር በጎንደር ቅርንጫፍ የምርቃት ስነስርአት በርካታ የምርት አስተዋዋቂዎች እንግዶች እንዲሁም የድርጅቱ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በይፋ በዛሬው እለት ተመርቋል።
Etcare I care! You care! We care!
@etcareofficial
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ራዕይ የሌለው ልፋት!

በሕይወታቸን ስኬታማ ለመሆን በጥምረት ልንይዛቸው የሚያስልጉን ሁለት ልምምዶች አለ፡- 1) ራእይን ማወቅና መያዝ፣ 2) ጠንካራ ሰራተኛ መሆን፡፡

1) ራእይ ኖሮን ጠንካራ ስራ ከጎደለን የምኞትና የቀን-ሕልመኞች (Day dreamers) ከመሆን አናመልጥም፡፡

2) በተቃራኒው፣ ጠንካራ ሰራተኞች ሆነን ምንም ብንለፋም ራእይ ከሌለን የተበታተነ ውጤትና ማንነት ስለሚኖረን ምንም የምንገነባው ነገር አይኖረንም፡፡

ጠንካራ ስራ መልካም ውጤት የሚያመጣው ግልጽ ከሆነ ራእይ ጋር ሲያዝ ብቻ ነው፡፡

ራእያችሁ ምድን ነው?
የጠንካራ ሰራተኛነት ልምምዳችሁስ ምን ደረጃ ላይ ነው?

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ልቆ የመገኛው ምስጢር!

በዚህ ውድድርና ፉክክር በሞላበት አለም ውስጥ ስንኖር ልቆ ከመገኘት ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ የለንም፡፡ በተሰማራንበት መስክም ሆነ በስብእናችን ልቀን ካልተገኘን ፈጠነም ዘገየም መጨረሻ ላይ መገኘታችን የማይቀር ነው፡፡ ልቆ የመገኛው መንገድ ደግሞ ለፍጽምና መስራት ነው፡፡

በባህሪይም ሆነ በማንኛውም የስራ ዘርፍ ውስጥ ፍጹም ሆኖ መገኘት በፍጹም የማይቻል ነገር ነው፡፡ ሆኖም፣ ለፍጽምና መስራት እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ምንም እንኳን ፍጽምና ላይ ባንደርስም ልህቀት ደረጃ ላይ መድረሳችን አይቀርምና፡፡
መጠንቀቅ የሚገቡን ነገሮች፡-

• ፍጹም መሆን አይቻልም በሚል ሰበብ መለወጥና ማሳደግ የምንችላቸውን ነገሮች ችላ ማለት፡፡

• እኛ ፍጹም ሳንሆን ከሌላው ሰው ምንም ስህተት እንዳይገኝበት መጠበቅ፡፡

• ፍጹም ለመሆን የሚሰሩ ሰዎችን ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮችን መናገር፡፡

ዝም ብላችሁ ፍጽምናን ተከታተሉት፡፡ አንድ ቀን ልህቀት ላይ መድረሳችሁ አይቀርም፡፡

መልካም ቀን!
"በህይወት ውስጥ ምርጥ እና እጅግ ውብ የሆኑ ነገሮች በአዓይን አይታዩም ፣ በእጅም አይዳሰሱም ነገር ግን ለልቦናችን ብቻ የሚሰሙ ናቸው!"

"በአለም ላይ ደስታ ብቻ ቢኖር ኖሮ ጀግንነትን አንማርም ነበር!"

"ህይወት በድፍረት የሚኖር ተጋድሎ ነው አለበለዚያ ህይወት አይሆንም!"

"በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ችግርን መሸሽ ችግርን ከመጋፈጥ የተሻለ አደለም!"

"አንተነትህን መቼም ቢሆን አትሰባብረው ቀና ብለህ ኑር!"

እነዚህ ምርጥ ንግግሮች የተሰሙት ማየትም ሆነ መስማት ከማትችለውና አስር መፅሐፍቶችን ከፃፈችው ሄለን ኬለር አንደበት ነው።

መልካም ቀን!
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የማስገባትና የማቆየት ሕግ
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የማስገባትና የማቆየት ሕግ

የማይለወጠው እውነታ፡- አንድን ነገር በእጅህ ባስገባህበት መንገድ ብቻ በእጅህ ታቆየዋለህ!

ቀድሞ የአንተ ያልነበረና አሁን ግን በእጅህ ላይ ያለ ማንኛውንም ነገር ንገረኝ፡፡ ከዚያም በእንዴት አይነት ሁኔታ በእጅህ እንዳስገባኸውና የአንተ እንዳደረከው ግለጽልኝ፡፡ እኔ ደግሞ ጊዜ ሳላባክን ወደፊት ያንን ነገር በእጅህ ለማቆየት ያለህን ብቸኛ መንገድ እነግርሃለሁ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ነገሮችን በእጃችን ለማስገባት እንጣጣራን፡፡ ያፈቀርነውን ሰው የእኛ ለማድረግ፣ ስራን ለማግኘት፣ ንግድን ለመጀመር፣ የተለያዩ ንብረቶችና ቁሳቁሶች ባለቤት ለመሆን፣ ስልጣንን ለመጨበጥ . . . ፍላጎታችን ዘርፈ-ብዙ ነው፡፡ ይህ ፍላጎት ሲጋጋል ደግሞ ምንም አይነት መንገድ ተጠቅመንም ቢሆን ያንን ነገር በእጃችን የማስገባታችንን ሩጫ ጥጉ ድረስ ይወስደዋል፡፡

አንድን ነገር የእኛ ለማድረግ የመፈለጋችንን ያህን፣ ያንን ለማድረግ የምንጠቀምበትን መንገድ ጉዳይ አብረን ማሰቡ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውንም ነገር በእጃችን ለማስገባት በተጠቀምንበት መንገድ ብቻ ነው ነገሩ እጃችን ከገባ በኋላ ማቆየት የምንችለው፡፡ ከጊዜያዊው ያላለፈ አይነት ሕይወት የመኖር ፍላጎት ካላደረብን በስተቀር፡፡

ሲተነተን፡- በኃይል እጃችን የገባን ነገር በእጃችን ለማቆየት ካለማቋረጥ ኃይልን መጠቀም አለብን፡፡ በማታለል እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ ማታለል አለብን፡፡ በውሸት እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ መዋሸት አለብን . . . እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ከተርታው ሰው እስከ አገር አመራሩ ድረስ እውነታው ፈጽሞ አይለወጥም፡፡

አንዲትን ሴት ለማግባት ካለው ፍላጎት የተነሳ የሌለውን ነገር እንዳለው የዋሸን አንድ ሰው ብናስብ፣ ተሳክቶለት ያችን ሴት ቢያገባት፣ ነኝና አለኝ ብሎ ያስተዋወቀው እንደሌለ እንዳይታወቅበት ምን አይነት ጡዘት ውስጥ እንደሚገባ ማስላት አያዳግትም፡፡ ቀድሞ ለማስታወቂያነት የተጠቀመበትን ድራማ እውን ማድረግ ሲያቅተው ግንኙነት መዛባት ይጀምራል፡፡

በስራውም መስክ ቢሆን እውነታው ይኸው ነው፡፡ የሌለንን እንዳለን፣ ያልሆንነውን ደግሞ እንደሆንን አሳይተን በውሸት በገባንበት የስራ መስክ ውስጥ ለመቆየት ምን ማድረግ እንዳለብን መገመት አያስቸግርም፡፡ ካለማቋረጥ ስንሸፋፍንና ስንዋሽ ልንኖር ነው፡፡

መፍትሄው፣ አታላይነትን፣ ዛቻን፣ ኃይልንና ጉልበትን ተጠቅመን በወጣንበት የውሸት ከፍታ ላይ ለመቆየት እድሜ ልካችንን ስንታገልና ስንፍጨረጨር ከመኖር ይልቅ፣ ያለንንና የሆንነውን ትክክለኛውን ነገር አቅርበን በተረጋጋ ሁኔታ ውሎ ማደርና በልክ መኖር እጅግ የተመረጠ ነው፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
2025/10/08 12:42:03
Back to Top
HTML Embed Code: