tgoop.com/Dreyob/3576
Last Update:
ወደ ትክክለኛው የግንኙነት መርህ እንመለስ!
ትክክለኛ አመራር ማለት ተከታዮች አመራሩን ያለመከተል ምርጫ ሲኖቸውና ያንንም ምርጫ በመውሰዳቸው ምክንያት ምንም አይነት ጫና እና በደል እንደማይደርስባቸው ሲያውቁ ነው፡፡ ይህንን ነጻነት የሚሰጡ መሪዎች በእርግጥም የመልካም ተጽእኖ መሪዎች ናቸው፡፡ ያለመከተል ምርጫ እንዳላቸው እያወቁ የሚከተሉም ሰዎች በእርግጥም በመልካም ተጽእኖ ስር ያሉ ተከታዮች ናቸው፡፡ ይህ የምርጫ ነጻነት በሌለበት ሁኔታው ውስጥ የሚንጸባረቀው ሁኔታ አመራር ሳይሆን ኃይልና ስልጣን ነው፡፡
ትክክለኛ ፍቅር ማለት አንድ ሰው በዚያ የፍቅር ግንኑነት ያለመቀጠል ምርጫ ሲኖረውና ያንንም ምርጫ በመውሰዱ ምክንያት ምንም አይነት የበቀልና የማስፈራራት ሁኔታ እንደማይደርስበት ሲያውቅ ነው፡፡ ይህንን ነጻነት የሚሰጡ ፍቅረኞች በእርግጥም ትክክለኛ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ የፍቅር ግንኙነቱን የማቋረጥ ምርጫ እንዳላቸው እያወቁ በግንኙነቱ ለመቀጠል የሚወስኑም ሰዎች በእርግጥም በእውነተኛ ፍቅር የተማረኩ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ የምርጫ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ የሚንጻባረቅ ሁኔታ ፍቅር ሳይሆን ቁጥጥር ነው፡፡
ይህንንው መርህ በመከተል በሌሎች መስኮችም ጭምር ያሏችሁን ግንኙቶች ከጉልበተኛነት፣ ከኃይለኛነትና በግዳጅ ከመግዛትና ከመገዛት ነጻ የማውጣት ቀን ይሁንላችሁ፡፡
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
BY Dr. Eyob Mamo

Share with your friend now:
tgoop.com/Dreyob/3576