Telegram Web
Forwarded from ቅድስት ፌብሮኒያ (ኒፎን)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
† የክርስቶስ ፍቅር የማረከው ሳይሰስት ይዘምርለት †

ፍቅርህ ማረከኝ በህይወቴ በዘመኔ
እግዚአብሔር ለእኔ መድሃኒቴ
ፍቅርህ ማረከኝ በህይወቴ በዘመኔ
ተገዝቻለሁ በወርቅ ደምህ
ዓለምን ትቼ ላገለግልህ
ሞትህ ህይወቴ ለእኔ ሆኖኛል
በአንተ መከራ ሸክሜ ርቋል
ለክብርህ ቆሜ እዘምራለሁ
እንደ አቅሜ አገንሃለሁ

ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን ዘማሪት ሩት
መዝሙር 18
አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ!

🎙በዲ/ን ፍሬዘር

ፍጥረትን በሚያስምር📌
በእናቱ ልመና📌
ክርስቶስ ይማረን 📌
መሀሪ ነውና!📌


በጉባኤ ደቂቀ አበው ላይ የቀረበ!

@JohnDPT27 @JohnDPT27
🌐 @Learn_with_John
Watch "zemarit kalkidan mekonene (ዘማሪት ቃልኪዳን መኮንን)" on YouTube
https://youtu.be/Mm-CeOvDDAA
ሲገፉህ ፍቅር ላይ እንጂ ጥላቻ ላይ አትውደቅ ፡፡ ወደ ላይ መውጣት ያቃተውን ይገፉታል ፡፡ መገፋት ለዕድገት ነው ፡፡

የገፉህ ታች ሁነው ፣ አንተ ግን ከላይ ትሆናለህ ፡፡ የተገፋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል ፣ የተገፋ ዓለት ቤት ይወጣዋል ፣ የተገፋ አፈር ወርቅ ይወጣዋል ፡፡

የተገፋ ሰውም ክብር ይጫንለታል ፡፡ በጎልጎታ ለመነሣት በሩ ቀራንዮ ነው ፡፡ አማራጭ የለም ቀራንዮን ካላዩ ወደ ጲላጦስ አደባባይ መመለስ እንጂ የጎልጎታን ድል ማየት አይቻልም ፡፡

ላንተ የፈሰሰ ቃለ እግዚአብሔር ቤትህን ባርኮ አንተ ግን ሳትባረክ እንዳትቀር እባክህ ተጠንቀቅ ፡፡

በእግዚአብሔር ከብረህ እግዚአብሔርን እንዳትንቅ ደግመህ አስብ ፡፡ ከሙሉ ፍቅር ጎዶሎ ጥላቻ ሊታወስህ አይገባም ፡፡

በሚጠሉህ መሐል የሚወድህን ካገኘኸው የሚጠሉህን እርሳቸው ፡፡ ጤፍን የቆጠረ ፣ ሰማይን የለካ ፣ አሸዋን የደመረ ፣ ውቅያኖስን የሰበሰበ ማንም የለም ፡፡

እግዚአብሔርም ታውቆ የማይጨረስ ነው ፡፡

ንስሐህ የኅሊናን ድምፅ ፀጥ ለማሰኘት ሳይሆን አባትህን ለመታረቅ ይሁን ፡፡ ኃጢአት ስትሠራ ለሰይጣን ተላልፈህ የተሰጠህ መስሎህ ትፈራለህ ፣ ተላልፈህ የተሰጠኸው ግን ለምኞትህ ነውና ምኞትህን ፍራው ፡፡

ስትጸልይ ከራሴ አድነኝ በል ፡፡ ትዕግሥትህን ለካው ፡፡

ሰዎች ሲናገሩ ስንት ደቂቃ መስማት ትችላለህ ? መጓጓዣው እስኪመጣ በደስታ እስከ ስንት ደቂቃ ትጠብቃለህ ?

የትራፊክ መብራት እስኪለቅህ ምን ያህል ትረጋጋለህ ?

ከአፍህ ይህን ጸሎት አትለየው ፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እባክህ ትዕግሥት ስጠኝ፡፡”

ትዕግሥት ያስፈለገህ መከራን ብቻ ሳይሆን ጥጋብንም እንድትችል ነው ፡፡

@JohnDPT27 @JohnDPT27
🌐 @Learn_with_John
Forwarded from Deleted Account
+ ዕጣንና አለመታዘዝ +

ዕጣን መቅሠፍትን ያርቃል : ደዌን ይገሥጻል::
ሳይንሱ ሳይቀር ድብታን (depression) ያርቃል እስከማለት የደረሱ ጥናታዊ ምስክርነቶችን ይሠጥበታል::
ዕጣንን መቅሠፍት እንዲያርቅ የሚያደርገው ንጥረ ነገሩ ብቻ ሳይሆን በካህናት የሚደረገው ጸሎተ ዕጣን ነው::

በእስራኤላውያን ታሪክ የተፈጸመው ይህ ነው::

"አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው" ኦሪት ዘኍልቍ 16 :47

በዕጣን ምክንያት ብዙ ሺህ ሰው ካለቀበት መቅሠፍት እስራኤላውያን ዳኑ:: ይህ ታሪክ ዕጣን መቅሠፍት እንደሚያርቅ ያሳያል::

በተያያዘ ዜና :-

የብዙ ሰው ሞት ምክንያት የነበረው መቅሠፍት ግን መነሻው ምን ነበር? ስንል የሚከተሉት ነጥቦችን ማስተዋል ይገባናል::

1ኛ የመቅሠፍቱ ዋነኛ መነሻ ቆሬ ዳታንና አቤሮን የተባሉ ሰዎች ለሌዋውያኑ ካህናት ለሙሴና ለአሮን ትእዛዝ አንገዛም ማለታቸውና ክህነትን በማቃለላቸው ነበር

2ኛ ካህን ከመናቅ አልፈው እኛ ከማን እናንሳለን ብለው ያለ ሥልጣናቸው እሳት አንድደው ዕጣን ለማጠን በመሞከራቸው የተነሣ መቅሠፍት ነበር

3ኛ መቅሠፍቱ ከመነሣቱ በፊት እግዚአብሔር ለሕዝቡ መቅሠፍቱ እንዳይነካችሁ ፈቀቅ በሉ ብሎ ነበር:: ከዚያ መቅሠፍት ከዳኑት መካከል የሚበዙት ይህን ትእዛዝ ከሙሴ አፍ ሲሰሙ አክብረው መሸሽ የቻሉ ሰዎች ብቻ ነበሩ:: አልሰማ ያሉና ከኑግ ጋር የተገኙ ሰሊጦች ግን አብረው ተወቅጠዋል::

የአሮንን ክህነት የናቁት ግን ዕጣኑን ራሳቸው ይዘው ቢያጥኑም መቅሠፍቱ የጀመረው ከእነርሱና ከቤተሰባቸው ነበር:: ይህ እንግዲህ ቃል በቃል የተጻፈው ነው::

አባቶቻችንን እንስማ! በእኛ ቸልታ ምክንያትም ብዙ ሊቃውንትዋ አረጋውያን የሆኑላትን ቤተ ክርስቲያን አንጉዳት:: ታምመህ ከምትሰቃይና ለሌሎችም ሥቃይ ምክንያት ከምትሆን "ሳትታመም ዳን" "ተፈወስ እምቅድመ ትሕምም":: ተጠንቅቆ ከቤቱ የሚውለውን ሰው አንተ ወጥተህ በሽታ ሸምተህለት ማምጣትህ አያሳዝንም?

"አዬ ጉድ! ጠቢብ ከሰነፍ ጋር እንዴት ይሞታል!" መክ 2:16

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት ቂርቆስ 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
“ዳሩ ግን ይህ #መብታችሁ ለደካሞች #ዕንቅፋት እንዳይሆንባቸው #ተጠንቀቁ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 8፥9
🥀🥀 የጾሙ እኩሌታ 🥀🥀

    🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀


🍃 ብዙ ሰዎች ደስ ተሰኝተውና እርስ በእርሳቸው “ግማሹን ጾም ፈጽመናል፤ የጾሙ እኩሌታ አለፈ” ሲባባሉ ተመልክቻለሁ፡፡

🍃 እኔ ግን እነዚህ ሰዎች በዚሁ ምክንያት ደስ ሊላቸው እንደማይገባ እመክራቸዋለሁ፤ የጾሙ እኩሌታ ማለፉን ሳይሆን የኃጢአታቸው እኩሌታ መሄዱን [መወገዱን] ያስቡ፤ እንደዚያ ከኾነም ሐሴት ያድርጉ፡፡

🍃 ደስ ልንሰኝበት የተገባው ነገር ይኼ ነውና፤ ሊታይ የሚገባው ይኼ ነው፤ ጥንቱም እነዚህን ኹሉ ነገሮች የምናከናውናቸው ስሕተቶቻችንን እንድናስተካክል ጾሙ ሲጀምር እንደ ነበርንበት ሳይኾን እንድንነጻበት ክፉ ልማዶቻችንን ወደ ጎን አድርገን የተቀደሰውን በዓል [በዓለ ትንሣኤን] እንድናከብር ነውና፡፡

🍃 እንደዚህ ካልሆነ ግን ጾሙን መጨረሳችን በራሱ ለእኛ ታላቅ ጉዳትን ይዞ ከመምጣት ውጪ ሌላ ምንም ረብ ጥቅም አይሰጠንም፡፡

🍃 ስለዚህ ብዙ ጊዜ መጾማችንን ብቻ አንመልከት፤ ይህ ምንም ትልቅ ነገር አይደለምና፤ ይልቁንስ በዚህ ጾም ራሳችንን አሻሽለን እንደ ሆነ፤ ጾሙ ከተፈታ በኋላም የዚሁ ፍሬ ጎምርቶ ይታይብን እንደ ኾነ ሐሴት እናድርግ፡፡

🍃 የክረምት ጥቅሙ ይበልጥ የሚታወቀው ወራቱ ካለፈ በኋላ ነውና፤ የዚያን ጊዜ የአበባው ማበብ የአዝመራው ማፍራት ሌሎች ዕፅዋትም በቅጠላቸውና በፍሬያቸው በወርሐ ክረምት ያገኙትን ጥቅም ግልጽ አድርገው ይናገራሉና! በእኛም ዘንድ ልክ እንደዚህ ይኹን፡፡


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚በእንተ ሐውልታት 18፥1

@Learn_with_John
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ #እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም #አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም #እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ #ሽሬአለሁ

#ዛሬስ_በመስተዋት_በድንግዝግዝ_እንደምናይ_ነን በዚያን ጊዜ ግን #ፊት_ለፊት_እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።

እንዲህም ከሆነ፥ #እምነት_ተስፋ_ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው #ይኖራሉ፤ ከእነዚህም #የሚበልጠው #ፍቅር ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 13:11-13
#ንቁ፥ በሃይማኖት #ቁሙ፥ ጎልምሱ #ጠንክሩ። በእናንተ ዘንድ ሁሉ #በፍቅር_ይሁን

1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13-14
አንዳንድ ሰዎች እጅግ የጠለቀ ኀዘንና መቆርቆር ውስጥ ሲገቡ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ረስቶኛል” ብለው ሲያማርሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ነቢዩ እንዲህ ከሚሉ ሰዎች ጋር ክርክር አለው፡፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀኗ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃኗን ትረሳ ትችላለችን?” በማለትም ይጠይቃቸዋል (ኢሳ.49፡14)፡፡ ይህም ማለት ሴቷ ከማኅፀኗ የተወለደው ልጇን ልትረሳ ዘንድ እንደማይቻላት እግዚአብሔርም ሰውን ይረሳ ዘንድ ባሕርይ አይደለም እያላቸው ነው፡፡

ነቢዩ ይህን ምሳሌና ማነጻጸርያ አንሥቶ ክርክር መግጠም የፈለገው እያንዳንዷ እናት ለልጇ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ስለሚያውቅ ነው፡፡ ኾኖም ይህን ያህል የምናንቆለጳጵሰው የእናት ፍቅር ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው “አዎን እርሷ ትረሳ ይኾናል፤ እኔ ግን አልረሳሽም… ይላል እግዚአብሔር” በማለት የሚቀጥለው፡፡ እንግዲህ የአምላካችን ፍቅር እንደምን የበዛ እንደ ኾነ ታስተውላላችሁን?

እንግዲያውስ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “አባት ለልጆቹ እንዲያዝን እንዲራራ እንደዚህም ኹሉ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይራራላቸዋል” ብሎ እንደተናገረ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፤ የእሥራኤል አምላክ ትቶኛል” የሚል ማንም አይገኝ (መዝ.102፡13)፡፡ ጆሮን የፈጠረ እርሱ ይሰማል፤ ዐይንን የፈጠረ እርሱ ያያል፡፡ እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ የቀረጻቸው ልጆቹን አይረሳም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹
@Learn_with_John
"ረድኤትኽ ከነፋስ እና ከአውሎ ነፋስ የፈጠነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ ለሚማፀኑኽ ኹሉ ለምሕረት ቅርብ የሆንክ የእኔንም ጸሎቴን የመማፀኔን ቃላት ኹሉ ተቀበል የአምላክ ልብ በአንተ ለለመነው ሩህሩህ ነውና"


አቃቤ ኢትዮጵያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኾይ የኾነብንን እና እየኾነብን ያለውን ተመልክተኽ ፈጥነኽ ድረስልን ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድነን።
🕊🌿አሜን በእውነት
በደቡብ ኦሞ ሀገረስብከት የሚገኙት የጋንጩራ ቀበሌ ማህበረሰቦች ሙሉ በሙሉ ኦርቶዶሳዊት ተዋህዶ ክርስትናንን ተቀበለዋል።
~~~

እግዚአብሔር ይመስገን ደስ የሚል ቀን

ከዚህ በላይ ምን ደስታ አለ!!!


ስለሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን!!!



ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አደሩጉ
@Learn_with_John
2025/07/07 03:36:21
Back to Top
HTML Embed Code: