Telegram Web
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† ስንክሳር ዘወርኀ ጥር ፳፪ †

† አባ እንጦንስ †

=>አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ሃያ ሁለት በዚች ቀን በግብጽ አገር ከአቅማን ከተማ የከበረና የገነነ የመነኰሳት ሁሉ አባት በገዳም ለሚኖሩ እንደ ኮከብ የሚያበራላቸው አባት እንጦንዮስ አረፈ።

የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ንጹሐን ክርስቲያን ናቸው እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ተንኮል ሽንገላ በልቡ ውስጥ የለውም ከወላጆቹም ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ሒዶ በቆረበ ጊዜ ከሕፃናት ጋር በመጫወት ከቶ አይሳሳቅም ነበር።

ጥቂት በአደገም ጊዜ ራሱን ዝቅ አድርጎ ለወላጆቹ ይታዘዝ ነበር ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ተማረ ያን ጊዜም የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ቲዎናስ የተሾመበት ዘመን ነበር የእንጦንዮስንም ወሬውን ሰምቶ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ባረከውና ስለርሱ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ ይህ ሕፃን በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናል ዜናውም በዓለሙ ሁሉ ይወጣል እጁንም በላዩ ጭኖ ዲቁና ሾመው።

ከዚህም በኋላ ወላጆቹ በሞቱ ጊዜ ታናሽ ብላቴና እኅት ትተውለት ነበር። ከሰባት ወርም በኋላ እንደ ልማዱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በሔደ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ፍቅር በልቡ አደረበትና በኀሳቡ በዓለም የሚሠራውን ሁሉ አባቶቻችን ሐዋርያት ሁሉን የዓለምን ሥራ ትተው ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ተከተሉት በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም እንደተጻፈ ጥሪታቸውን እየሸጡ የሽያጩንም ዋጋ በሐዋርያት እግር ሥር ያኖሩትን አሰበ እግዚአብሔር በሰማያት ያዘጋጀላቸው ዋጋቸው ምን ያህል ይሆን አለ ይህም ኀሳብ በልቡ ውስጥ የሚመጣ የሚወርድ ሆነ።

ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደ የክብር ባለቤት ጌታችን በከበረ ወንጌል ለባለጸጋው የተናገረውን ሰማ እንዲህ ሲል ፍጹም ትሆን ዘንድ ከወደድክ ሒድ ጥሪትህን ሁሉ ሸጠህ ለድኆች ስጥ በሰማይም ላንተ ድልብ አድርገው መጥተህም ተከተለኝ።

ከእግዚአብሔርም ዘንድ ይህን ልዩ ኀሳብ አግኝቶ ይህ ቃል ስለርሱ እንደተነገረ አሰበ በዚያንም ጊዜ ከቤተ ክርስቲያን ወጣ ለአባቱም ያማረ ሰፊ ምድር ነበረው ለአገሩም ሰዎች ሰጣቸው ለርሱ የተዉለትንም ጥሪታቸውን ሁሉ ሽጦ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጣቸው እኅቱንም ወስዶ ከደናግል ገዳም አስገባት።

በዚያንም ወራት የምንኩስና ሥርዓት አልተገለጸም ነበር እግዚአብሔርንም ለማገልገል የሚሻ ከመንደር ጥቂት ወጣ ብሎ ብቻውን በመቀመጥ በጾም በጸሎት ተወስኖ ይጋደላል የከበረ እንጦንዮስም እንዲሁ አደረገ ሰይጣናትም በስንፍናና በዝሙት ጦር የሚዋጉት ሆኑ በሕልሙም የሴት ገጽ በማሳየት አብራውም እንደምትተኛ ያደርጓታል።

ከዚህም በኋላ በባህር ዳርቻ ወዳለች የመቃብር ቤት ሒዶ በዚያ የሚኖር ሆነ በላዩ በአደረ በእግዚአበሔርም ረድኤት በተጋድሎ በረታ ምግቡንም ከዘመዶቹ ወገን ያመጡላት ነበር ሰይጣናትም ሲጋደል አይተው ቀኑበት ታላቅ ድብደባንም ደብድበው ጥለውት ሔዱ ዘመዶቹም ሲመጡ እንደ ሞተ ሆኖ ወድቆ አገኙት ተሸክመውም ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዱት ጌታችንም አዳነው በነቃም ጊዜ ወደ ቦታው ተመልሶ ይጋደል ዘንድ ተጋድሎውን ጀመረ።

በዚያንም ጊዜ ሰይጣናትን ወደርሱ ሲመጡ አያቸው በአራዊት አምሳል በአንበሶችና በተኩላዎች የተመሰሉ አሉ በእባቦችና በጊንጦችም የተመሰሉ አሉ ያስፈሩትም ዘንድ አንዱም አንዱ በላዩ ተነሣሡ እንጦንዮስም በእኔ ላይ ለእናንተ ሥልጣን ካላችሁ ከእናንተ አንዱ ያቸንፈኝ ነበር ብሎ ዘበተባቸው ወዲያውኑ እንደ ጢስ ተበተኑ በሰይጣናት ላይ ድልን እግዚአብሔር ሰጥቶታልና ሰይጣናትም ከሚያመጡበት መከራና ሥቃይ አረፈ።

ምግቡንም በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ያበስላል በፀሐይም ያደርቀዋል ወደበዓቱም ማንም እንዲገባ አያሰናብትም የሚሻውም ሁሉ በውጭ ይቆምና ድምፁን ይሰማል እንጂ ሃያ ዓመትም እንዲህ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በገድል ተጠምዶ ኖረ።

ከዚህም በኋላ ፍጹም የሆነ እግዚአብሔርን መፍራትንና አምልኮቱን ለሰዎች ወጥቶ ያስተምር ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘው ስለዚህም ወደ ፍዩም አገር ወጥቶ ብዙዎች ደቀ መዛሙርትን ሰብሰቦ አስተማራቸው በእግዚአብሔርም ሕግ አጸናቸው ደቀ መዛሙርቶቹ በውስጣቸው የሚኖሩባቸው ብዙዎች ገዳማት ተሠሩለት።

ስለ ሃይማኖትም ስደት በሆነበት ወራት በሰማዕትነት መሞትን ወዶ ወደ እስክንድርያ ሀገር ሔዶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ከቶ አልያዙትም በክርስቶስም ስም የታሠሩ እሥረኞችን በመጎብኘት ቢአረጋጋቸውና ቢአጽናናቸውም አልያዙትም መኮንኑም እንደማይፈራ በአየው ጊዜ ከፍርድ አደባባይ ውስጥ እንዳይታይ አዘዘው እርሱ ግን ሁል ጊዜ መታየቱን አልተወም እንዲአሠቃየውና በሰማዕትነትም እንዲሞት የሚያስቆጣውን ነገር ይናገረው ነበር መኮንኑም በእርሱ ላይ ምንም ክፉ ነገር አላደረገም አምላካዊት ኃይል ከልክላዋለችና።

ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስ ለሰማዕታት ፍጻሜ ሁኖ የመከራው ወራት ከአለፈ በኋላ እንጦኒ ወደ ገዳሙ ተመለሰ ይህም በአምላክ ፈቃድ ሆነ የሚለብሰውም ማቅ ነበር በዘመኑ ሁሉ ገላውን በውኃ አልታጠበም ብዙዎች በሽተኞችም ወደርሱ ይመጣሉ በላያቸውም ሲጸልይ ይድናሉ።

ብዙዎች ሕዝቦችም ትምህርቱን ሊሰሙ ወደርሱ ሲመጡ በአያቸው ጊዜ ብቻውንም ይኖር ዘንድ እንዳልተውት አይቶ ከእርሱ ስለሚደረገው ነገር ልቡ እንዳይታበይ ፈራ እነርሱ ወደማያውቁት ቦታ ወደላይኛው ግብጽ ይሔድ ዘንድ ወዶ ወደ ባሕሩም ወደብ ደርሶ መርከብ እየጠበቀ ተቀመጠ ከሰማይም ወደርሱ ቃል መጣ እንዲህም አለው እንጦንዮስ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ ከዚህስ ምን ትሻለህ አለው እርሱም ብዙዎች ወደእኔ ስለሚመጡ እንደምፈልገው ለብቻ መኖር አልተቻለኝም ስለዚህም ወደ ላይኛው ግብጽ እሔድ ዘንድ ወደድኩ አለ ያም ቃል መልሶ እንዲህ አለው ወደ ላይኛው ግብጽ ብትሔድ ድካምህ ደግሞ እጥፍ ይሆናል ብቻህን መኖር ከወደድክ ግን የሦስት ቀን ጎዳና ያህል ወደ ውስጠኛው በረሀ ተጓዝ።

በዚያንም ጊዜ በዚያች ጎዳና ሊጓዙ የሚሹ የዓረብ ሰዎችን አያቸው ወደ እርሳቸውም ሒዶ አብሮአቸው ይሔድ ዘንድ ለመናቸው እነርሱም በደስታ ተቀበሉት ወደ አንድ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ እስከሚደርስ የሦስት ቀን ጎዳና ተጓዘ በዚያም የጠራና የቀዘቀዘ ውኃ አለ ደግሞም የሰሌን የተምር ዕንጨቶች መቃዎችም በብዛት አሉበት እንጦንዮስም ያንን ቦታ ወደደው ዓረቦችም ምግቡን የሚያመጡለት ሆኑ ብዙዎች የከፉ አራዊትም ነበሩ በጸሎቱም እግዚአብሔር አስወገዳቸው ወደዚያም ቦታ ከቶ አልተመለሱም።

አንዳንድ ጊዜም ወደ ባሕሩ ዳርቻ በመውጣት ደቀ መዛሙርቶቹን ጎብኝቶና አረጋግቶ በበረሀ ወስጥ ወደአለው ቦታው ይመለሳል።

ከዚህም በኋላ በጻድቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ዜናው በተሰማ ጊዜ በጸሎቱ ያስበው ዘንድ ንጉሡ እየለመነዉ ደብዳበ ጻፈለት የከበረ እንጦንዮስ ግን ወደ ንጉሥ ደብዳቤ ዘወር አላለም ለወገኖቹ እንዲህ አላቸው እንጂ የንጉሠ ነገሥት ደብዳቤ እነሆ በላያችን ይነበባል ወንድሞችም እንዲህ ብለው ለመኑት ይህ ንጉሥ የክርስቲያንን ወገኖች የሚወድ ጻድቅ ሰው ነው ደብዳቤ ጽፈህ ልታጽናናው ይገባል ከዚህም በኋላ እያጽናናውና እየባረከው ቤተ መንግሥቱንና ሠራዊቱንም እየባረከ ጻፈለት።

ዳግመኛም በአፍርንጊያ ንጉሥ ዘንድ ዜናው በተሰማ ጊዜ ወደ ከበረ እንጦንዮስ እንዲህ ብሎ ጻፈ ወደ እኛ መጥተህ በእኛ ላይ በአገራችንና በሠራዊታችን ላይ በረከትን ታሳድር ዘንድ ስለ ጌታችን ክርስቶስ መከራዎች እኔ ወዳንተ ፈጽሜ እማልዳለሁ።
የከበረ እንጦንዮስም ይህን በሰማ ጊዜእጅግ አዘነ ቁሞም እንዲህ ብሎ ጸለየ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እለምንሃለሁ በአፍርንጊያ ውስጥ ወዳለ ወደ በርኪኖን አገር እንድሔድ ፈቃድህ ከሆነ ምልክትን ግለጥልኝ ነገር ግን ያንተ ፈቃድ ይሁን ይህንንም ባለ ጊዜ ብርህት ደመና መጣች በዚያችም ሰዓት ተሸክማ ወደ አፍርንጊያ አገር አደረሰችው ንጉሡም ደስ አለው ሕዝቡና ሠራዊቱም ሁሉ በሽተኞችንም አቀረቡለትና ሁሉንም ፈወሳቸው የጽድቅና የሕይወትንም መንገድ እያስተማራቸው ከእነርሳቸው ዘንድ ስድስት ወር ኖረ።

በእሑድም ዕለት ያቺ ብርህት ደመና ተሸክማ ወደ ገዳሙ ታደርሰውና ከልጆቹ ጋር ተገናኝቶ ያረጋጋቸዋል በማግሥቱም ዳግመኛ ተሸክማ ወደ አፍርንጊያ አገር ትመልሰዋለች። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ በደመና ተጭኖ ወደ ገዳሙ አንደኛውን ተመለሰ።

በአንዲት ዕለትም ስንፍና መጣበት እንዲህ የሚለውም ቃል መጣ ታይ ዘንድ ወደ ውጭ ውጣ በወጣ ጊዜም መልአኩን አየው በላዩም የምንኩስና ልብስ አለ መታጠቂያ፣ ቅናት፣ የመስቀል ምልክት ያለው ቀሚስ በወገቡም አስኬማ በራስ ቁር አምሳልም በራሱ ላይ ቆብ አለ እርሱም ተቀምጦ ሰሌን ይታታል ከዚያም ተነሥቶ ይጸልያል ዳግመኛም ተቀምጦ ሰሌኑን ይታታል በየሰዓቱም እንዲህ በማድረግ ይጸልያል።

ሁለተኛም እንዲህ የሚል ቃል ወደርሱ መጣ እንጦንዮስ ሆይ እንደዚህ ሥራ አንተም ከሰንፍና ከሰይጣናት ጦርነት ታርፋለህ ያንን ያየውንም ተቀብሎ እንዲሁ አስመስሎ የሚሠራ ሆነ ከዚያችም ዕለት ወዲህ ስንፍናና የሰይጣናት ውጊያ አልመጣበትም።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ጊዜ ተገልጾ አረጋግቶታል አጽንቶታልም። አሁንም እንዲህ አለው የመረጥሁህ እንጦንዮስ ሆይ በእውነት እነግርሃለሁ እኔን ስለመውደድህ በዚች በረሀ ውስጥ ብቻህን በመጋደልህና በማገልገልህ ስለ ድካምህ ስምህን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ሥልጣንህንም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ከፍ አደርገዋለሁ።

ገዳማትንና አድባራትንም መነኩሳትን የተመሉ ሁነው ቅኖች የዋሃን ጻድቃን እንደሚኖሩባቸው አደርጋቸዋለሁ ይልቁንም ያንተ ገዳማት እነርሱ እስከ ፍጻሜ ይኖራሉ።

መታሰቢያህንም የሚያደርገውን ሁሉ ለድኆች ምጽዋትን ለቤተክርስቲያን መባ በስምህ የሚሰጠውን ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ ከቶ ሥቃይን አያያትም በውስጡ ሥጋህ የሚቀበርበትንም ገዳም እጅግ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ በውስጡም እንደ መላእክት የሆኑ ደጋጎች መነኮሳት እንዲኖሩበት አደርጋለሁ ከእርሳቸውም እስከ ዓለም ፍጻሜ አለቃ የሚሆን አይታጣም የምድር ነገሥታት መሳፍንትና ሹማምንት ለገዳምህና ፍለጋህን ለሚከተሉ ልጆችህም እጅ መንሻ ተሸክመው እንዲመጡ አደርጋለሁ ጌታችንም ይህን ከተናገረው በኋላ ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በታላቅ ክብር ዐረገ አባ እንጦኒም ፈጽሞ ደስ አለው።

ከዚህም በኋላ ስለ ቤተክርስቲያን መፍረስ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ መናፍቃን በላይዋ ይሠለጥናሉ ከዚህም በኋላ ወደቀድሞ ሥርዓቷ ትመለሳለች ዳግመኛም ስለ መነኮሳት እነርሱ እጅግ እንደሚበዙ ገዳሞቻቸውንና አድባራቶችን በመተው ወርደው ከዓለማውያን መካከል በከተማዎችና በቦታዎች ውስጥ እንደሚኖሩ ስለ ዓለም ፍጻሜም ትንቢት ተናገረ።

ይህም አባ እንጦንዮስ አባ መቃርስን አስኬማንና የምንኩስና ልብስን ያለበሰው ያረጋጋውና ያጽናናው ከእርሱ የሚሆነውንም ያስረዳው ነው ደቀ መዝሙሩና ልጁ ስለሆነ።

ከዚህም በኋላ የገዳማውያን አለቃ ወደሆነ ወደ አባ ቡላ ሔደ እርሱም ለሥጋው ያሰበና በሐዋርያዊ አትናቴዎስ ልብስ የገነዘው ነው። ዕረፍቱም እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ በትሩን ለልጁ ለአባ መቃርስ ምንጣፉን ለአባ አትናቴዎስ የፍየል ሌጦ ዐጽፉን ለልጁ ለኤጲስቆጶሱ ለአባ ስራብዮን እንዲሰጡ ልጆቹን አዘዛቸው።

ከዚህም በኋላ ከምድር ላይ ጋደም አለ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ወደርሱም ሁሉም የመላእክት ማኅበር መጥተው በክብር በምስጋና ፍጹም ተድላ ደስታ ወዳለበት ዘላለማዊ ዕረፍት ተቀብለው አሳረጉት።

ሥጋውን ግን ልጆቹ እንዳዘዛቸው ሰወሩት እርሱ የቅዱሳን ሰማዕታትን ሥጋቸውን የሚገልጡትን ይገሥጻቸው ነበርና ስለ እነርሱ ሥጋ ብዙ ገንዘብ እስከ መቀበል ደርሰው ዓለማዊ ጥሪት ያደርጉታልና።

ይህም የከበረና የተመሰገነ አባት እንጢንዮስ እስከ መልካም ሽምግልና ደረሰ እጅግም አረጀ ግን ወደ ወደደውም ክርስቶስ እስከ ሔደ ድረስ መልኩ አልተለወጠም ብርታቱ ጽናቱም መላው ዕድሜውም መቶ ሃያ ዓመት ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

፨፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለብሕታዌሁ እንበለ ሕጸጽ ወንትጋ። ውስተ ናሕስ ከመ ዖፍ ወበቤት አምሳለ ጉጋ። ብእሴ ሰማይ እንጦኒ ወመልአከ ምድር በጸጋ። ለቤተ ብለኔ እንዘ ይሜንን ሕጋ። መዋዕለ ሕይወቱ ኢተኀዕበ ሥጋ።
፨፨፨፨

=>በዚችም ዕለት የማፍን ኤጲስቆጶስ ሚናስ መታሰቢያው ነው በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

=>ጥር 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ እንጦንስ (የመነኮሳት አባት - የበርሐው ኮከብ / ልደቱና ዕረፍቱ)
2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላዕክት (ለተጠሙ ጽዋዓ ልቡናን የሚያጠጣ: ምሥጢር ገላጭ መልዐክ)
3.ቅዱስ ሚናስ ኤዺስ ቆዾስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ ደቅስዮስ ኤዺስ ቆዾስ
3.አባ ዻውሊ የዋህ

=>+"+ በዚያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል ፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: +"+ (ማቴ. 16፥24-26)

፨፨፨፨
ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውክፈ እምእለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሂቅ እምንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
፨፨፨፨

( ጌታ ሆይ ከብልፅግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
+++ አሁንም አርብ ላይ +++

እግር ጥሏት ድንገት
በዚያ መንገድ ስታልፍ ሰዎች በበዙበት
ወታደር ባለበት
የምትወደው ልጇ
አሁንም መስቀል ላይ ያለ እየመሰላት
" ውዷ እናቴ ሆዬ " " ነይ" ብሎ ሳይጠራት
" ወይ " ብላ ሳትመልስ
የጀመረችውን ያ ጉዞዋን ትታ
ሄደች ቀራንዮ
የመድኃኔ ዓለም ቤት ቤተ ጎልጎታ
.
.
.
እኔም ያኔ
በቅደመ ታቦቱ
ጦሩን የታጠቀ ወታደር ቆሞ ሳይ
መሆኔ ትዝ አለኝ ቀራንዮ ሰፈር
አሁንም አርብ ላይ
ስለዚህ
መንገዷን አቋርጣ
ሳይጠራት " ወይ ብላ " መሄዷ ልጇ ቤት
አልተሳሳተችም ድንግል ትክክል ናት

ዘአማን
2014/ጥር /27
አዲስ አበባ
@Learn_with_John
❖ ኃጢአት ሠርተሃልን?

❖ እንግዲያውስ ወደ ቤተክርስቲያን ግባ ኃጢአትህንም አርቃት፤ በአደባባይ የምትወድቀው ቊጥሩ ከምትነሣው ጋር እኩል ይሁን፤ ልክ እንደዚሁ በደል ኃጢአት የምትሠራውን ያህልም ፍጹም ተስፋ ሳትቈርጥ ንስሐ ግባ ኹለተኛ ብትበድል ኹለተኛ ንስሐ ግባ፤ በስንፍና ተይዘህ በፍጹም ምግባር ትሩፋት መሥራት አይቻለኝም አትበል፤ በእርጅና ዘመን ብትኾንና ብትበድልም እንኳን ወደ ቤተክርስቲያን መጥተህ ንስሐ ግባ።

✍️ ቤተክርስቲያን ሆስፒታል እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፤ እዚህ ስትመጣ ካህናት ከኃጢአት እስራት ፈትተው ይቅርታ ይሰጡሃል እንጂ 'ለምን በደልህ?' ብለው አይፈርዱብህምና፤ ስለዚህ 'አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ' ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ ኃጢአትህም
ይቀርልሃል "

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊

@Learn_With_john
ወጣት መነኩሴ ወደ አባ እንጦንዮስ መጣ። እየተማረረ እንዲህ አለ "አባቴ ሆይ ከመነኮስሁ ዓሥር ዓመታት አለፉኝ። ነገር ግን የዲያቢሎስን ፈተናውን መታገስ አቃተኝ ፣ እጅግ እየታገለኝ ነው" አባ እንጦንስም ለዚህ መነኩሴ የሚገባውን ምክርና ተግሣፅ ሠጥቶ አሰናበተው። መነኩሴው ከወጣ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ አባ እንጦንስ ቀርቦ እንዲህ አለ። "በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ ፣ ይኼ ሰው መመንኮሱንም አላውቅም"

እኛ በዲያቢሎስ ተፈተንሁ ለማለት ራሱ ገና ነን ፣ ምክንያቱም የራሳችንን ድካምና ምኞት ገና ድል አልነሣንም።

"ምንም እንደ መቅደሱ መንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው" (2 ዜና 30: 19)

@Learn_with_John
የጋለ ብረትን ለመቀጥቀጥ የሚነሣ ሰው አስቀድሞ በብረቱ ምን ለመሥራት እንዳሰበ መወሰን አለበት፤ መጥረቢያ፥ ሰይፍ፥ ወይስ ማጭድ? እኛም በምን ዓይነት የሕይወት መስመር ፍሬ ለማፍራት እንዳሰብን አስቀድመን ልቡናችንን ማዘጋጀት አለብን፡፡

📚 አባ እንጦንስ


🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊
🕊 🕊🕊
🕊
Forwarded from እልመስጦአግያ+++ (Tazena /ታዜና/)
ማውጫ
ጉባኤ ተዘክሮ ዘብሉይ ኪዳን(መዝሙረ ዳዊት ማብራሪያ) ማውጫ
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 1
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/250
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 2
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/252
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 3
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/254
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 4
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/256
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 5
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/258
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 6
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/260
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 7
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/262
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 8
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/264
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 9
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/287
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 10
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/313
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 11
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/330
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 12
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/353
መዝሙረ ዳዊት ክፍል13
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/602
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 14
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/891
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 15
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/977
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 16
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1095
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 17
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1120
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 18
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1147
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 19
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1205
መዝሙረ ዳዊት ክፍል 20
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1302

ጉባኤ ተዘክሮ ዘሐዲስ ኪዳን(ዕብራውያን ማብራሪያ)
ማውጫ
ዕብራውያን ክፍል 1
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/232
ዕብራውያን ክፍል 2
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/247
ዕብራውያን ክፍል 3
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/298
ዕብራውያን ክፍል 4 ቁጥር 1
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/316
ዕብራውያን ክፍል 4 ቁጥር 2
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/338
ዕብራውያን ክፍል 5
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/380
ዕብራውያን ክፍል 6
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/402
ዕብራውያን ክፍል 7
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/606
ዕብራውያን ክፍል 8
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/914
ዕብራውያን ክፍል 9
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1046
ዕብራውያን ክፍል 10
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1091
ዕብራውያን ክፍል 11
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1138
ዕብራውያን ክፍል 12
👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/abagebrekidan/1177

በፍለጋ ከምትደክሙ የምትፈልጉትን ክፍል ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ተጠቀሙ Pinned ስለሚደረግ ማውጫውን በቀላሉ ታገኙታላችሁ
#ነነዌን ሊያቃጥል

ነነዌን ሊያቃጥል የወረደው እሳት(፪)
ተመልሶ ዐረገ(፪) በሀዘን በጸሎት(፪)
ስለሆነ ከልብ የሀዘናቸው ምንጩ(፪)
ነበር እንደ ራሔል(፪)እንባን እየረጩ(፪)
ለነነዌ ሰዎች ደስታን ያበሰረ(፪)
ጋሻ እና ጦራቸው(፪)ጾም ጸሎት ነበረ(፪)
እንኳን የሰው ልጆች እንስሳት ሳይቀሩ(፪)
በዮናስ ስብከት(፪)ፆም ጸሎት ተማሩ(፪)
የካቲት ፰ በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከከበረ ልደቱ ከአርባ ቀኖች በኋላ ወደቤተ መቅደስ የገባበት ሆነ፡፡ ለዚህ ምሥጢር አገልጋይ የሆነ ጻድቁ ዮሴፍና የወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የክብር ባለቤት እርሱ በእስራኤል ሕዝብ ላይ የሠራውን ሕግ ይፈጽሙ ዘንድ መሥዋዕትም ሊአቀርቡ መጡ። ጻድቅ ሰው ስሞዖን ካህንም ሕፃኑን ተቀብሎ አቀፈው።
Forwarded from ቅድስት ፌብሮኒያ (ኒፎን)
አቤቱ፥ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ፤ እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ፤ ልቤን ወደ ምስክርህ አዘንብል፥ ወደ ስስትም አይሁን፤ ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዓይኖቼን መልስ፤ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ፤ እንዲፈራህ ባሪያህን በቃልህ አጽና፤ ፍርድህ መልካም ናትና የተጠራጠርሁትን ስድብ ከእኔ አርቅ፤ እነሆ፥ ትእዛዝህን ናፈቅሁ፤ በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ።

// መዝሙረኛው ክቡር ዳዊት ||
+ ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ +

ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ ጌታ ትንሣኤ ማስረጃ እያቀረበ ነው:: በዚያን ዘመን ለጌታ ትንሣኤ ማስረጃ ስትጠቅስ በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ይላል ብለህ እንዳትጠቅስ ገና ወንጌላት አልተጻፉም:: ቢጻፉም ማቴዎስ በሕይወት እያለ በቃሉ መመስከር ሲችል ጽሑፉን ማስረጃ ማድረግ አያስፈልግህም:: ስለዚህ ለመነሣቱ ማስረጃዎች ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች ነበሩ:: በሕይወት ያሉትን የዓይን ምስክሮችን መጥቀስ ይቻላል:: የዓይን እማኞች ምስክርነት ከጽሑፍ በላይ የታሪክ ማስረጃ ነው:: ስለዚህ ጳውሎስ ስለ ጌታ ትንሣኤ "እነ እገሌ አይተውታል" እያለ መዘርዘርን መረጠ::

ጌታ ከተነሣ በኋላ እንደ ቀድሞው ለሁሉ አልታየም:: እርሱን ለማየት የተገባቸው ጥቂት ወደ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ:: በማኅበር ያዩት አሉ:: በግል ያዩት አሉ::
ያዩት ነገር ወንጌል የሆነላቸው ብፁዓን ዓይኖች ያሏቸው እንዴት የታደሉ ናቸው? የተሰቀለውን ተነሥቶ ያዩት! ዳግም በሚመጣበት አካል የተገለጠላቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? ከመድኃኔ ዓለም አፍ ተቀብለው ኪዳን ያደረሱ! የጌታን ቅዳሴ ተቀብለው ያስቀደሱ! የትንሣኤው ማግስት ምስክሮች እንዴት ዕድለኞች ናቸው? ቢሞቱም እንኳን መነሣታቸውን በጌታ ትንሣኤ አይተው ደስ ብሎአቸው ያንቀላፉ እነርሱ ምንኛ የታደሉ ናቸው?

ቅዱስ ጳውሎስ በወንጌል ከተጠቀሱት ከነ ኬፋ በተጨማሪ ለይቶ ጌታ ለማን ለማን እንደታየ ገለጸ:: ለያዕቆብ ታየ ብሎ የእልፍዮስን ልጅ ለይቶ ጠቀሰው:: የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፍት እንደሚሉት ይህ ሐዋርያ ከሌሎች በተለየ የጌታን ትንሣኤ ሳላይ እህል አልቀምስም ብሎ የተሳለና አክፍሎትን የጀመረ ነበርና ጌታ ለይቶ ክብሩን አሳይቶታል:: ከዚያም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ ብሎ የጌታን ድኅረ ትንሣኤ አስተርእዮ ዘረዘረ:: እኔ ማለትን የማይወደው ትሑት ቅዱስ ጳውሎስ "ከሁሉ በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ አለ::

ጭንጋፍ ምንድር ነው? ጭንጋፍ (ጸዕጻዕ/ ተውራድ) ለፅንስ የሚነገር ቃል ነው:: መወለድ ያለበትን ጊዜ ያልጠበቀ ያለ ጊዜው የተወለደ ፅንስ ነው:: በመጠኑ ከሌላው ጊዜውን ከጠበቀ ፅንስ የሚያንስ ሲሆን ዕድገቱን በተገቢው ጊዜ ከሚወለድ ልጅ ጋር ለማስተካከል ሲባል በሙቀት ማቆያ ክፍል እንዲቆይ ይደረጋል:: ይህ ፅንስ ሲወለድ በሕመም ውስጥ ሆኖ ተሰቃይቶ ተጨንቆ ነው::

ቅዱስ ጳውሎስ ራሱን ለመግለጽ የተጠቀመበት ይህ አንድ ቃል የሕይወት ታሪኩን ጠቅልሎ የያዘ ድንቅ ቃል ነበር::
ቅዱስ ጳውሎስ ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያን ብርሃን የሆነ ሐዋርያ ቢሆንም እንደ ዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት በጊዜው የተጠራ አልነበረም:: እርሱ ከሐዋርያት ጋር አብሮ በዳግም ልደት የተወለደ ሳይሆን ያለ ጊዜው ክርስቶስ ባረገ በስምንተኛው ዓመት የተጠራ ነበረና ራሱን ካለ ጊዜው ከተወለደው ፅንስ ጋር አመሳስሎ እንደ ጭንጋፍ የምሆን ብሎ ጠራ::

ጭንጋፍ ሲወለድ በመጠኑ ከሌላው ፅንስ ያነሰ ይሆናል::
ቅዱስ ጳውሎስም ራሱን ጭንጋፍ ካለ በኋላ "እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ብሎ አብራርቶታል:: (1ቆሮ 15:9)

ልጅ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ በሥቃይ ነው:: ጤና ያጣል ይታመማል:: እናቲቱም ትታወካለች በድብታ በጭንቀት ትቸገራለች:: ባለሙያዎቹ እንደሚሉት እናት ያለ ጊዜው ከተወለደ ልጅዋ ጋር እናታዊ ትስስር ለመፍጠርና የእናትነት ፍቅርዋን ለመሥጠት ባልጠበቀችው ጊዜ የመጣ በመሆኑ ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ትቸገራለች:: በአጭሩ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ እሱም ይሰቃያል እናቱንም ያስጨንቃል:: ወዲያው እንደሌላ ሕፃን በሰው እጅ አይታቀፍም:: ከተፈጥሮአዊ እስከ ሰው ሠራሽ እንደየጊዜው እየዘመነ በሔደው የልጅ ሙቀት መስጫ መንገድ እየታገዘ የሰውነት አካሎቹ በአግባቡ መሥራት እስከሚችሉና በሽታ መቋቋም እስከሚችል ይቆያል::

ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጭንጋፍ ነበርኩ ያለው ለዚህ ነው:: በዳግም ልደት የተወለደው በደማስቆ መንገድ ወድቆ ሊቋቋመው ባልቻለው ብርሃን ተመትቶ ነበር:: "ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ?" የሚል ድምፅ ሲሰማ ፅንስ ነውና ዓይኑን እንኳን መግለጥ አልቻለም ነበር::
ከተወለደ በኋላም ወዲያው ወደ ቤተ ክርስቲያን እቅፍ ወደ ሐዋርያት ማኅበር አልገባም:: እንደ ጭንጋፍ የምሆን እንዳለ ሙቀት ያስፈልገው ነበርና የሰው እጅ ሳያቅፈው ሦስት ዓመት በሱባኤ ቆይቶ በመንፈስ ቅዱስ ተማወቀ::

"ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። ከሦስት ዓመት በኁዋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ" ብሎ ስለ መንፈሳዊ ኃይል መልበሱ ይናገራል:: (ገላ 1:15-18)

ጭንጋፍ ሆኖ የተወለደ ልጅ የሚገጥመው ችግር ከወላጆቹ ጋር በሥነ ልቡና ለመተሳሰር መቸገሩ ነው::
ቅዱስ ጳውሎስን ለማመንና እንደ ልጅ ለመቀበል የቤተ ክርስቲያን ማኅበርም ተቸግራ ነበር::
"ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት" ሐዋ 9:26 ስለዚህ ሐዋርያው እንደ ጭንጋፍ ነኝ አለ::

ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ጌታ መነሣት ምስክሮች ብሎ ሌሎችን ከዘረዘረ በኋላ "ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ" ብሎ ተናገረ:: ክርስቶስ ተነሥቶአል ወይ ብለው ሲጠይቁህ አዎ ተነሥቶአል እነ እገሌ አይተውታል ብለህ ዘርዝረህ
"ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለህ መናገር መቻል እንዴት መታደል ነው!?

ወዳጄ ክርስቶስ መነሣቱን ታምናለህ:: ልክ ነህ ለብዙዎች ታይቶአል:: አንተስ ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ ማለት ትችል ይሆን? ጌታ ከተነሣ በኁዋላ ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ለብዙዎች ታይቶአል:: ብዙዎቹ ቅዱሳን አይተውታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ አይቶታል : ቅድስት አርሴማ አይታዋለች : አቡነ ተክለ ሃይማኖት አይተውታል : አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተመልክተውታል:: አባ ጳኩሚስ በዕንባ ተመልክቶታል : ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አይታዋለች::

ሁሉም ቅዱሳን ብዕር ቢሠጣቸው ከዕንባ ጋር
"ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለው የትንሣኤውን ማስረጃ ዝርዝር ይቀጥላሉ:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በበረሃ ሲጸልይ አይቶት ነበርና ሰው ባገኘ ቁጥር
ወቅቱ የፋሲካ ሰሞን ባይሆንም እንኳን በፈገግታ ተሞልቶ
"ክርስቶስ ተነሥቶአል!" ብሎ ያበሥርና ሰላምታ ይሠጥ ነበር::

ጌታ ሆይ ለእኔ ለኃጢአተኛው የምትታየኝ መቼ ይሆን? ቸርነትህን አይቻለሁ! ፍቅርህን አይቻለሁ! ብሩሕ ገጽህን የማየው መቼ ይሆን? መች እደርሳለሁ የአምላኬንስ ፊት መቼ አየዋለሁ? እኔም እንደ ቅዱሳንህ "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔ ታየኝ" ብዬ የተቀመጠውን ብዕር አንሥቼ የምጽፈው መቼ ይሆን? አቤቱ ፊትህን እሻለሁ! አቤቱ ፊትህን ከእኔ አትመልስ! አቤቱ ፊትህን እሻለሁ!

"ኢየሱስ ክርስቶስ በግዕ ዘቀራንዮ
ለላሕይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ"
"የቀራንዮው በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ውበትህን ልናየው እንመኛለን"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ማዕዶት 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ
Forwarded from 🦋 NIGHT BUTTERFLY (ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ😭)
እውነትን ወደ ማወቅ የደረሰው የፕሮቴስታንት መምህር(Patric M.peace) እንዲህ ይላል"የጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን ምን እንደሚመስሉ(ሥርዓተ አምልኮ) ለማወቅ በጥልቀት መመራመር እና ማንበብ ጀመርኩኝ ።በተጨማሪም የጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶችን ህይወት መመርመር ጀመርኩኝ። እናም አንድ ነገር ተረዳሁኝ 'ፕሮቴስታንት(Protestant) ቤተክርስቲያን ብሎ የሚጠራው በታሪክ ውስጥ ካየኋቸው አብያተክርስቲያናት ፈፅሞ የተለየ ነው። ልዩነቱም የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን በመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ የተመሰረቱ አይደሉም በተጨማሪም ልቅ የሆነ የሙዚቃ አምልኮን "አምልኮ" ብላ የምታቀርብ ናት። በተጨማሪም የተወሰኑ ቡድኖች የሚመሠርቱትና የሚመሩት ነው።ጥንታዊቷ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግን ፍፁም መፅሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ሥርዓተ አምልኮ ያላት እና የተወሰኑ ቡድኖች የማይመሯት(በመንፈስ ቅዱስ የምትመራ):የአምልኮ ሥርዓቷ(ቅዳሴ:ዝማሬ:ማህሌት) ወንጌል(መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ይህም ነፍስ እግዚአብሔርን እንድታገኝ የሚያስችል ነው ።ይህንንም የቤተክርስቲያኒቷን ቅዱሳን አባቶች ህይወት በምመረምር ወቅት አረጋግጫለሁ።"
ይህንን ፅሁፉን ሲቋጭ ለፕሮቴስታንት ወንድሞች እና እህቶች "እናም ወንድሞቼ "ቤተክርስቲያን ተመልከቱ"።" ይላል።

| ቤተክርስቲያንን አየኋት + አወኳት + ወደድኳት| ቅዱስ ያሬድ |
ትርጉም | ዲያቆን አቤሴሎም ድንቅአለም
ዘመኔ ሁሉ ላንተ ያርጅ


ለኔ የፈጠርካቸው ሁሉ ሳያረጁ እንዳበቡ አሉ እኔ ግን በኃጢአት ወይቤ አረጀሁ፣ የእጆችህ ስራ የሆነው ሰማይ ሳያረጅ ሳይቀደድ ዛሬም ከነውበቱ አለ እኔ ግን በበደል አርጅቼ ገረጀፍኩ እባክህ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ ይብቃህ በለኝ!

ለዓለም ሳንቲሜን ሳወጣ አልሰስትም ላንተ ለመስጠት ግን አይሆንልኝ፤ ለዓለም ቀኑ አንሶኝ ለሊቱን ሙሉ ስጨፍርላት ባድር አልጠግብም ላንተ ግን ቢዚ ነኝ ብዬ ጊዜ ነሳውህ እንኳን ለሊቴን ቀኔን እንኳ ላካፍልህ አልቻልኩም፤ እግሮቼ ወደዓለም ተግተው ይሮጣሉ ወዳንተ ለመገስገስ ግን ሰነፍ ናቸው ይለግማሉ። እባክህ በአለም ፍቅር ያረጀችውን ነፍሴን በፍቅርህ ቀስቅሳት፣ ወዳንተ ሳባት። አንተው ተገልግለህባት ታርጅ!

በእውነት እጆቼ ወዳንተ እንደተዘረጉ፤ ልቤ ወዳንተ እንደሮጠች፤ ሃሳቤ ወዳንተ እንደተሰቀለ፤ አንደበቴ አንተን ብቻ እንዳወደሰ፤ ዓይኖቼ አንተን ብቻ እንዳዩ፤ ጣቶቼ ስላንተ ብቻ እንደከተቡ ዘመናቸው ይለቅ አንተን አንተን አንተን ብለው ያርጁ።

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለኔ ተወልደህ፣ ለኔ ተሰቃይተህ፣ ለኔ ሞተኻል ሕይወቴ ሁሉ ላንተ ኖራ ላንተው አገልግላ ላንተው ትሙትልህ! ይህንን ጭካኔ አድላት። በስምህ ፀለይኩ አሜን።

@Learn_with_john
ምን ያህሎቻችን ፈረምን? ለስንት ወገኖቻችንስ #የኦንላይን መፈረሚያውን ሊንክ አጋራን? የዛሬ ስራችንን ወደ መወያያው ገጽ ይህን 👇👇በዚህ ገብተን ሪፖርት እናድርግ። 👉https://www.tgoop.com/Defend_Orthodoxy_EOTC_Discussion
2025/07/14 04:22:01
Back to Top
HTML Embed Code: