tgoop.com/husccs/423
Last Update:
ምቹ የአጋርነትና ራስን የማስተዋወቅ አጋጣሚ ማስታወቂያ
*//*
ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓም
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 22ኛዉን "የኢትዮጵያ ጥናት ዓለም አቀፍ ጉባዔ" ከመስከረም 19-23/2018 ዓ/ም ያስተናግዳል::
በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነዉና ላለፉት ስድስት አስርት ዓመታት በተለያዩ የዓለም ሀገራት በየ2 ዓመቱ ሲካሄድ የቆየዉ "የኢትዮጵያ ጥናት ዓለም አቀፍ ጉባዔ" ለ22ኛ ጊዜ ከመስከረም 19-23/2018 ዓ/ም የሚከናወነው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው::
በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ቁጥራቸዉ ከ1000 በላይ የሚገመት ምሁራንና ተመራማሪዎች ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በጉባዔዉ ለመሳተፍ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በጉባዔዉ በኢትዮጵያ ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ዙሪያ የተካሄዱ ጥናቶች ቀርበዉ ምሁራዊ ዉይይቶች ይካሄዱበታል፡፡
ጉባዔዉንና በጉባዔዉ የሚቀርቡ ጉዳዮችን በመላዉ ዓለም ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ የራሱ ዌብሳይት ( https://ices22.hu.edu.et/ ) ሥራ የጀመረ ሲሆን ሌሎች የብዙሃን መገናኛዎች እንዲሁም የዲጅታል፣ ህትመትና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በስፋትና በተለያዩ አማራጮች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
ስለሆነም የዚህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ አጋር መሆን የምትፈልጉ በሀገር ውስጥ ያላችሁ የግልና የመንግስት ተቋማት ዝግጅቱን ስፖንሰር በማድረግ፣ ምርትና አገልግሎታችሁን ለኤግዚብሽን በማቅረብና በተለያዩ መንገዶች በመሳተፍ ራሳችሁን ለጉባዔዉ ተሳታፊዎች፣ ለዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብና ለመላዉ ዓለም እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡ 0937434532 ወይም 0925 62 95 89 ደዉሎ ማነጋገር ይቻላል!
የ22ኛዉ የኢትዮጵያ ጥናት ዓለም አቀፍ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!
BY HU Charity Sector

Share with your friend now:
tgoop.com/husccs/423