HUSCCS Telegram 329
Forwarded from Hawassa University
የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የበዓል ምሣ ከተማሪዎች ጋር ተጋሩ::
*//****
ታህሳስ 30/2017 ዓም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎች እና የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንት ተማሪ እሰይ ጴጥሮስ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ለሚያከብሩ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የተሰናዳውን ምግብ በየምግብ አዳራሾቹ ተዘዋውረው ከተማሪዎች ተጋርተዋል።

ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ስለ ጉብኝቱ ሲያብራሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለረጅም አመታት ሲተገበር የነበረው የተማሪዎች የምግብ ሜኑ በበጀት ጫና ምክንያት አቅርቦት ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍና ለማሻሻል ሌት ተቀን እየሰራን ነው ብለዋል:: የዛሬውን ዓመት በዓል ምክንያት  በማድረግ ዩኒቨርሲቲው በልዩ ሁኔታ ግብዓት ጨምሮ ተማሪዎቻችን የተሻለ እንዲመገቡ አድርገናል ያሉት ዶ/ር ችሮታው ተማሪዎች አብዛኛውን በዓላት ከወላጅ ቤተሰቦቻቸው ርቀው ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር የሚያሳልፉ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ቤተሰባዊ ስሜትን ለመፍጠር ዕለቱን አስመልክቶ ለየት ያለ የምግብ አይነት በማዘጋጀት ማቅረቡን እና እነሱም ከልጆቹ ጋር ምሣ መጋራታቸው ጥሩ የቤተሰብነት ስሜት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ በበኩላቸው የጉብኝቱ ዋነኛ አላማ በዓሉን ከተማሪዎች ጋር በጋራ የማሳለፍና ቅርርብ የመፍጠር መሆኑን አንስተው ዩኒቨርሲቲው ሁሉም ሀገራዊ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት ተመሳሳይ ዝግጅቶችን በማካሄድ በዓሉን የሚያከብሩ ተማሪዎች ባይተዋር እንዳይሆኑ ማድረግ ችሏል ብለዋል።
👍1

tgoop.com/husccs/329
Create:
Last Update:

BY HU Charity Sector

Share with your friend now:
tgoop.com/husccs/329

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Those being doxxed include outgoing Chief Executive Carrie Lam Cheng Yuet-ngor, Chung and police assistant commissioner Joe Chan Tung, who heads police's cyber security and technology crime bureau. Healing through screaming therapy Content is editable within two days of publishing In the next window, choose the type of your channel. If you want your channel to be public, you need to develop a link for it. In the screenshot below, it’s ”/catmarketing.” If your selected link is unavailable, you’ll need to suggest another option. When choosing the right name for your Telegram channel, use the language of your target audience. The name must sum up the essence of your channel in 1-3 words. If you’re planning to expand your Telegram audience, it makes sense to incorporate keywords into your name.
from us

Telegram HU Charity Sector
FROM American