tgoop.com/https_Asselfya/11331
Last Update:
◼️ከትዳር በፊት ጥንቃቄ ለሴቶች‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✅ ብዙ ጊዜ ከትዳር በፊት ከHIVና ሌላም በሽታ ፍራቻ የደም ምርመራ ይደረጋል። ነገር ግን ከደም ምርመራ በላይ የመንሀጅ፣ የአቂዳ፣ የሱናና የአኽላቅ ምርመራ ሊደረግ ይገባል።
↪️ የመንሀጅ ምርመራ፦ ለትዳር አጋር ይሆነኛል ብለሽ የምትመርጭው አካል መንሀጁ ምን እንደሆነ ማጤን ወሳኝ ይሆናል። በሶሀቦች መንገድ በሰለፎች ጎዳና ቀጥ ያላለ ከሆነ አልፎም፦
🔻አህባሽ
🔻ኢህዋንይ
🔻ሱፍይ
🔻ሀዳድይ
🔻አሽአርይ
🔻ተክፊርይና ሌላም ከሆነ
♻️ከጠማሞችና ከጠፊዎች ስለሆነ ለትዳር አይበጅምና ጠንቀቅ በይ።
↪️ የአቂዳ ምርመራ፦ የትዳር አጋርሽ አቂዳው የተስተካከለ፣ አላህን በብቸኝነት የሚያመልክና አቂዳን ከሚያበላሹ ነገሮች የራቀ መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅብሻል። ምክንያቱም የአላህን ሀቅ ያልተወጣ የኔን ሀቅ ይወጣል ብለሽ አታስቢ።
♻️ቀብር አምላኪ
♻️ሰይድና ኸድር አብዱልቃድር ጅላሌ የሚል
♻️ለቀብር ባለቤት የሚያርድና የሚሳል
♻️ከአላህ ውጪ ያሉትን ድረሱልኝ የሚል
♻️ወልይ ሷሊህና ነብያት የሚለምን
♻️ሁዝ ቢየዲ ያረሱሉላህ የሚል
♻️አብሬት ቃጥባሬ ንጉሶቹ ሸኸና ሁሴን አባድር አኒ ዳኒ ሌላም የሚል ከሆነ
♨️ሙሽሪክ ነውና ለትዳር ስለማይሆን ጠንቀቅ በይ።
↪️ የሱና ምርመራ፦ ለትዳር ያሰብሽው አካል አቅሙ በቻለ መጠን ሱናን የሚከተል፣ ከቢድአና ከቢድአ ባለቤቶች የሚርቅ መሆን አለበት።
🔸መውሊድ የሚያከብር
🔸ሀሙስ፣ እስነይን እያለ ቀን ሚከፋፍል
🔸ኢስራ ወል ሚእራጅ እያለ ሚያከብር
🔸የሸእባን ግማሽን ከሌላው ቀን የሚለይ ከሆነ
♨️ሙብተዲእ ነውና ለትዳር ስለማይሆን ጠንቀቅ በይ።
↪️ የዲን ምርመራ፦ ለትዳር ያሰብሽው አካል፦
🔹ሶላት በቋሚነት ቀጥ ብሎ የማይሰግድ
🔹ሙዚቃ የሚሰማና ነሺዳ የሚያዳምጥ
🔹በፊልም በድራማና በኳስ ጊዜው ሚገል
🔹ቁርአን የማይቀራ ዲኑን የማይማር
🔹ሲጋራ የሚነፋ ጫት የሚቅም
🔹ፂሙን የሚላጭ ፀጉሩን የሚያበላልጥ
🔹ሱሪውን ሚጎትት ፋሽን የሚከተል
🔹ሴትን የሚጨብጥ ኢኽቲላጥ ሚያበዛ ከሆነ
♨️ለትዳር አይሆንሽምና ጠንቀቅ በይ።
✍️አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://www.tgoop.com/https_Asselfya
BY 💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Share with your friend now:
tgoop.com/https_Asselfya/11331