tgoop.com/https_Asselfya/11262
Last Update:
ስኬታማ ትዳር ለመመስረት የሚረዱ ምክሮች
1. አላህን መፍራት (تقوى الله):
• ለአላህ ታማኝ መሆን: በትዳር ውስጥም ሆነ በሌላው የሕይወት ዘርፍ አላህን መፍራት እና ትእዛዛቱን መፈጸም ግደታ ነው ፤ ይህም ለትዳር አጋር ታማኝ መሆንን ይጨምራል።
• የትዳር ትክክለኛውን አላማ ማወቅ: ትዳር ለመመሥረት ዋናው አላማው አላህን መታዘዝ እና መልካም ዘርን ማፍራት መሆን አለበት።
• በዱዓ ላይ መበርታት: በመጀመሪያ አላህ መልካም ባል ወይም ሚስት እንዲሰጥ መማጸንና በተጨማሪ አላህ ትዳራችንን እንዲባርክልን መለመን ይኖርብናል።
2. በመልካም ስነ-ምግባር ላይ የተመሰረተ ትዳር መገንባት (حسن الخلق):
• ለትዳር ስንመርጥ ዲንን መመልከት: ዲን ያለው/ያላት (ሃይማኖተኛ) የትዳር አጋር መፈለግ፤ ምክንያቱም ዲን ትክክለኛውን መንገድ ለመከተል ይረዳል።
• መልካም ስነምግባር: ጥሩ ስብዕና፣ ገርነት፣ ትህትና እና ለሰዎች ደግ መሆን በትዳር ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
• በመንሐጅና በአቂዳ ተመሳሳይ መሆን: በአመለካከት፣ በእሴቶች እና በአኗኗር ዘይቤ ተስማሚ የሆነን ሰው መምረጥ።
3. በትዳር ውስጥ መተዛዘንና መዋደድ (المودة والرحمة):
• ለጋስ መሆን: ለትዳር አጋር በገንዘብም ሆነ በስሜት ለጋስ መሆን እና የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማሟላት።
• ርህራሄና መተሳሰብ: የትዳር አጋርን ስሜት መረዳት፣ ማዘን እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ መደገፍይኖርብናል።
• ይቅር መባባል: በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩትን ጥቃቅን ስህተቶች ይቅር ማለት እና ቂም አለመያዝ፤ ምክንያቱም ፍጹም የሆነ ሰው የለምና ጥፋት ሲኖር ፈጥኖ ይቅርታ መጠያየቅ ይቅር መባባል ይኖርብናል።
4. ምክክር (الشوری):
• በጋራ መመካከር: በትዳር ሕይወት ውስጥ ትልልቅ ውሳኔዎችን በሚወስኑበት ጊዜ በጋራ መመካከርና መወያየት፤ ይህም የሁለቱንንም አስተያየት ግምት ውስጥ ማስገባት ያካትታል።
• አክብሮት: የትዳር አጋርን አስተያየት ማክበር እና በጥሞና ማዳመጥ።
• መተማመን: በጋራ በመመካከር ውሳኔዎችን መወሰን በመካከላችሁ መተማመንን ይጨምራል።
5. የትዳር ግዴታዎችን መወጣት (حقوق الزوجية):
• ባል ለሚስቱ: ሚስቱን መንከባከብ፣ መጠበቅ፣ መመገብ፣ ልብስ ማልበስ እና ጥሩ መኖሪያ ማዘጋጀት። በተጨማሪም በትህትና መያዝ፣ ማስተማር እና በሃይማኖቷ ላይ መርዳት።
• ሚስት ለባሏ: ባሏን ማክበር፣ መታዘዝ (በመልካም ነገር)፣ ቤቱን መጠበቅ፣ ልጆችን መንከባከብ እና የባሏን ስም እና ንብረት መጠበቅ ይኖርባታል።
6. ትዕግስት እና ይቅርታ (الصبر والصفح):
• በትዕግስት መጽናት: በትዳር ውስጥ ችግሮች እና ፈተናዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፤ ስለዚህ በትዕግስት መጽናትና መፍትሄ መፈለግ ያስፈልጋል።
• ይቅር ማለት: የትዳር አጋርን ስህተት ይቅር ማለት እና ቂም አለመያዝ ትዳርን ያጠናክራል።
• ከስህተት መማር: ከስህተት ተምሮ ወደፊት ላለመድገም መሞከር።
7. የቤተሰብን ትስስር መጠበቅ (صلة الرحم):
• ዘመዶችን መጎብኘት: የሁለቱም የትዳር አጋሮች ዘመዶችን መጎብኘትና መልካም ግንኙነት መፍጠር።
• ዘመዶችን መርዳት: ችግር ላይ የወደቁ ዘመዶችን መርዳትና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት።
• በዘመዶች መካከል ሰላምን ማስፈን: በዘመዶች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ለማስታረቅ መሞከር።
እነዚህና ሌሎችም ብዙ ያልተጠቀሱ ትዳራችንን ስኬታማ የሚያደርጉ ምክሮች አሉ... እነዚህ በመማርና በመተግበር ትዳራችንን ስኬታማ ማድረግ ይኖርብናል።
አላህ ላከቡት ትዳራቸውን ያሳምርላቸው ላላገቡት ሷሊህ የሆነ ትዳርን ይወፍቃቸው
ወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን ኢስማኢል
https://www.tgoop.com/Abu_hibetillah_Asselfiy
BY 💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Share with your friend now:
tgoop.com/https_Asselfya/11262