tgoop.com/dynamicsport/174934
Create:
Last Update:
Last Update:
🚨 አሰልጣኝ ፍሬዉ ወደ ዩጋንዳ!
አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የዩጋንዳውን የሴቶች ክለብ ለማሰልጠን ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን የሴካፋ ሻምፒዮን ያደረጉት አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል በጥር ወር መጨረሻ ለአራት ዓመታት ካገለገሉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኃላፊነታቸው ከተነሱ በኋላ ያለ ስራ የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ወደ ዩጋንዳ ማምራታቸው ተረጋግጧል።
አሠልጣኝ ፍሬውን ለማስፈረም የተስማማው ካምፓላ ኩዊንስ የሴቶች ክለብ ነው። የፉፋን የሱፐር ሊግ ውድድር አንድ ጊዜ ማሸነፍ የቻለው ካምፓላ ኩዊንስ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት በቻርለስ አይኮህ እየተመራ ቢጀምርም ከ5 ጨዋታዎች ማግኘት ከሚጠበቅበት 15 ነጥቦች ዘጠኙን ብቻ በማሳካቱ እና በኩዋምፔ ሙስሊም ሌዲስ በ4 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን መሪነት በመበለጡ የክለቡ አመራሮች የአሰልጣኝ ለውጥ ለማድረግ ወስነዋል። በዚህም ኢትዮጵያዊው አሠልጣኝ ፍሬው ቡድኑን እንዲመራ መወሰናቸው ታውቋል።
➛[ሶከር ኢትዮጵያ]
"Share" @dynamicsport
@dynamicsport
BY Dÿñámîç śpőrt™🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/dynamicsport/174934