tgoop.com/biranayetube/8522
Create:
Last Update:
Last Update:
"ፕራንክ" ከቀልድ ወደ ወንጀል: በሞትና አካል ማጉደል የሚያስቀጣ የሕግ ማስጠንቀቂያ!
በቅርቡ Viral በወጣው የባል እና የሚስት Prank የህግ ባለሙያዋ ወይዘሮ ሰብለ አሰፋ በኢትዮጵያ ውስጥ በስመ "ፕራንክ" እየተፈጸሙ ያሉ ተግባራት ስላስከተሉት ከባድ የሕግ ተጠያቂነት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ወይዘሮ ሰብለ እንዳሉት፣ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ በቀጥታ "ፕራንክ ወንጀል ነው" የሚል አንቀጽ ባይኖረውም፣ በፕራንክ ሰበብ የሚከሰቱ ውጤቶች ግን ወደ ከባድ የወንጀል ተጠያቂነት የሚመሩ ናቸው።
በፕራንክ ምክንያት በተቀለደበት ሰው ላይ በድንጋጤ ሞት ወይም አካል ማጉደል የሚከሰት ከሆነ፣ ድርጊቱ በቀልድነት አይታይም።
እንደነዚህ ያሉት ከባድ ጉዳቶች ከተከሰቱ፣ ፕራንኩን ያደረገው ሰው በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ ሆኖ ወደ እስራት የሚመራ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል። ድርጊቱ እንደ ግድያ ወይም ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ተቆጥሮ ይቀጣል።
"በስመ ፕራንክ የከፋ ነገር እንዳይከሰት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ቀልድ ሲያልፍ መዘዙ ከባድ የሕግና የህይወት ዋጋ ያስከፍላልና ሁሉም የፕራንክ አድራጊዎች ልብ ሊሉት ይገባል!" ብለዋል።
BY Biranaye Tube

Share with your friend now:
tgoop.com/biranayetube/8522