tgoop.com/biranayetube/8489
Last Update:
1 ግለሰብ የእሬቻ በዓል በሚከበርበት በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ውስጥ "ዶሮ ሊጥል ሲል" በልጅ ያሬድና ጓደኞቹ ተይዞ አካላዊ እርምጃ እንደተወሰደበትና ሲሰደብም እንደነበር ታይቷል።
ሰዓሊ ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ)፣ ከቡድኑ ጋር በመሆን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ አካባቢውን በሥዕል የማስዋብ ስራ እየሰራ እንደነበር ይገልጻል። በዚህ ወቅት፣ 1 ግለሰብ ዶሮ ይዞ ወደ ሐይቁ ሲያመራ እንዳየና በሁኔታው መጠርጠሩን ተናግሯል።
"ዶሮውን ምን ልታደርገው ነው?" ብሎ ሲጠይቀው "ሐይቁ ውስጥ ልጥለው ነው" የሚል ምላሽ አግኝቷል። ይህንን ተከትሎ ያሬድና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
ሰዓሊው ድርጊቱን "የኢሬቻን በዓልና የኦሮሞን ባህል ለማጠልሸት የሚደረግ የተደራጀ ተንኮል" በማለት የገለጸው ሲሆን፣ በዓሉ "የሰይጣን ነው" የሚል የተሳሳተ ትርጓሜ እንዲሰጠው ያደርጋሉ ሲል በምሬት ተናግሯል።
1 ግለሰብ የፈለገውን የማመን መብት አለው። ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ቢጠረጠር ጉዳዩን በህግ አግባብ ለፖሊስ ከማቅረብ ይልቅ እነ ልጅ ያሬድ በራሳቸው እጅ እርምጃ እንዲወስድ መገፋፋት፣ መስደብና፣ መደብደብ፣ "የህግ የበላይነትን" የሚጥስ ተግባር ነው።
በቪዲዮው ላይ የሚታየው የቡድን ድብደባ፣ ማንኛውም ተጠርጣሪ በህግ ፊት የመዳኘት መብቱን የሚጋፋ አደገኛ የ"mob justice" ተግባር ነው።
የተጠርጣሪው ማንነትና የድርጊቱ ትክክለኛ አላማ ሳይጣራ አካላዊ ጥቃት ማድረስ ከሰብዓዊነት አንጻርም ተገቢነት የሌለው ተግባር ነው።
በቪዲዮው ላይ ክስ የቀረበበት ግለሰብ ድምጽ በግልጽ አይሰማም። ድርጊቱን ለመፈጸም ያነሳሳው ምክንያት ምን እንደሆነ፣ ትክክል መሆኑን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የተጠርጣሪውን ወገን መስማት አስፈላጊ ነው። አንዳንዶች ድርጊቱ ተንኮል ሊሆን እንደሚችል ምልከታ አላቸው።
BY Biranaye Tube

Share with your friend now:
tgoop.com/biranayetube/8489