tgoop.com/biranayetube/8477
Create:
Last Update:
Last Update:
ድንጋይ ከምንወረውርበት እናግዘው !😢🙏
የድሮ የስራ ባልደረባዬ ሶፎኒያስ ዋሲሁን በምን አይነት የህይወት ምዕራፍ ውስጥ እያለፈ እንዳለ እኔም የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረቦቹ በደንብ ያውቃሉ ። እርሱም ሻል ያለው ጊዜ ተናግሯል። ህመሙ የብዙ ችግሮች ድምር በመሆኑ በቀላሉ የሚድን አይደለም ።
ትናንትኔ እና ዛሬ እንዳንድ ወንድምና እህቶች ልጁ ያለበትን ወቅታዊ እውነት ሳያውቁም ይሁን አውቀው እንዲህና እንዲያ ያለ መልዕክት በሜሴንጀር ደረሰን በማለት የልጁን ጤንነት የበለጠ የሚያባብስ፤ እናቱንም ለበለጠ ጭንቀት የሚጥል መልዕክት እያስተላለፉ ነው::
በግሌ ይህ ትክክል አይመስለኝም:: አዕምሮው በጥቂቱ የሚታወክ ሰው ምንም አይነት መልዕክት ሊልክ ሊስትም ይችላል:: ጉዳዮ እንዴትስ ሆነ ምክንያቱ ምን ይሆን ?ብሎ መጠየቅ እንጂ ችግር የሚያባብስ ሀሳብ ማውጣቱ ትርጉም የለውም:: ቀድሞ ታመምኩ ታወኩ ላለ ሰው መድሀኒትና መዳኛ እንጂ ድንጋይ አይወረወርም:: እናም ሶፎንያስን እናድነው ፤ እናግዘው ። የምስኪን እናቱን ጭንቀት እንጋራ የኔ ሀሳብ ነው ::
(በታምሩ ማሞ)
BY Biranaye Tube

Share with your friend now:
tgoop.com/biranayetube/8477