tgoop.com/biranayetube/8474
Last Update:
ዩቲዩብ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው
ዩቲዩብ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበበትን ክስ ተከትሎ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ፡፡
ባለቤትነቱ የጉግል ኩባንያ የሆነው ዩቲዩብ በፈረንጆቹ 2021 ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ለአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለማስረከብ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በዋሽንግተን ሁከት በተነሳበት ማግስት የዶናልድ ትራምፕን አካውንት ለቀናት ዘግቶ እንደነበር ይታወሳል።
በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ ከዩቲዩብ በተጨማሪ ኤክስ እና ፌስቡክ የፕሬዚዳንቱን አካውንት በጊዜያዊነት ማገዳቸው ይታወቃል።
ይህንን የኩባንያዎቹን ውሳኔ ተከትሎ ‘ፖለቲካዊ መድሎ ተፈፅሞብኛል’ በሚል ወደ ፍርድ ቤት ያመሩት ዶናልድ ትራምፕ ኩባንያዎቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስወሰን ችለዋል።
በዚህም ጥፋቱን አስቀድሞ ያመነው ዩቲዩብ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ኤክስ እና ፌስቡክ በፍርድ ቤት የሚወሰንባቸውን የገንዘብ ካሳ ለፕሬዚዳንቱ ይከፍላሉ ተብሏል፡፡
ትራምፕ ከዩቲዩብ ከሚያገኙት ካሳ 22 ሚሊየን ዶላሩን በናሽናል ሞል ትረስት ፈንድ አማካኝነት በነጩ ቤተመንግሥት ለሚገነባው አዲስ አዳራሽ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ነው የተባለው፡፡
ቀሪውን 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ደግሞ የአሜሪካ ኮንሰርቫቲቭ ሕብረትን ጨምሮ የዶናልድ ትራምፕን ክስ ለደገፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በድጋፍ መልክ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡
BY Biranaye Tube

Share with your friend now:
tgoop.com/biranayetube/8474