tgoop.com/Zephilosophy/1105
Last Update:
..የቀጠለ
የዝግመተ ለውጥን ፅንሰ ሐሳብ ላይ ከሚነሱት ጥያቄዎች መካከል አንዱ በተፈጥሮ ምርጫ ሂደት ውስጥ የጠፋው ጠፍቶ፣ የዘለቀው ዘልቆ ከቆዩት ፍጡራን መካከል በምን ምክንያት ይሆን እስከዛሬ ያልጠፋነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ሳይንስ ካስቀመጣቸው ምላሾች መካከል የተወሰኑትን እጅግ አጠር ባለ መልኩ ላስቀመጥ፡-
1. ገዳዮች ነበርን፡- አንትሮፖሎጂስቱ ራይሞንድ ዳርት(1893-1988) “ገዳዩ ጦጣ (killer ape theory) ተብሎ በሚጠራው ፅንስ ሐሳቡ ላይ ቀደምቶቻችን እጅግ አደገኛ እና ጨካኞች እንደነበሩ ይናገራል። ተመራማሪው እንደሚለው የመከላከል አቅማቸውን ችሎ ጥቃት ማድረስ የሚችል ሌላ ፍጡርም አልነበረም:: በእዚህም ከአሸናፊዎቹ ውስጥ አንዱ እየሆነን እስከዛሬ ዘልቀናል።
2. ምግብ እንከፋፋል ነበር፡- የእዚህ ፅንስ ሐሳብ አራማጅ ደቡብ አፍሪካያዊው
ኢዛ ግላይን(1937-1985) በ1971 “Whither Archaeology” በሚለው ጽሑፉ ላይ እንደሚለን እኛ ሰዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ ያገኘነውን መብል የመካፈል ባህሪ ነበረን። እንዲሁም ለምግብነት የሚውል ነገሮችን እንዴት እና የት እንደሚገኝ መረጃ እንለዋወጥም ስለነበር ሰው በተፈጥሮ ተመራጩ ሆኗል የሚል ድምዳሜ አለው። በተጨማሪም በእዚህ ልምዱ የተነሳ ቋንቋ ሊኖረን የቻለ ሲሆን፣ማኅበረሰባዊ የሆነ ባህሪንም የተላበሥነው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
4 አዳኞች ነን፡- ፍላጎቶቻችን ለሟማላት ያለን ጥረት፣ የማሰብ ችሎታችን፣ ስሜቶቻችን የመቆጣጠር አቅም እና ሌሎች ማኅበረሰባዊ የሆኑ አኗኗራችን ያገኘነው የማደን ዘዴን በማበጀታችን ነው፡፡ ይህን ያለው ደግሞ ሼርውድ ዋሽበርን(191-2000) የተባለ አንትሮፖሎጂስት ነው።
5. ወሲብ፡- በቀደምት ሰዎች ውስጥ የአንድ ለአንድ ግንኙነት መፈጠሩ በሰው ልጆች የዝግመተ ለውጥ ሂደት ላይ መዝለቅ እንዲችል ያደረገው ዋነኛው ክስተት ነው ይላል ሌላኛው አሜሪካያዊ ተመራማሪ ኦዎን ላቭጆይ። ከዛ ቀደም የነበሩት ወንዶች ወሲብ ለመፈፀም ከፈለጉ በሴቷ አከባቢ የተገኝ ሌላ ተገዳዳሪን በሙሉ መግደል አሊያም ማባረር ነበረባቸው፡፡ ኾኖም ሴቶቹ ይህንን ልምድ መቀየር አለበት ብለው በመወሰን ገላቸውን አሳልፈው የሚሰጡት ምግብ በቋሚነት ማቅረብ ለሚችሉ እና አብሮዋቸው ለሚቆዩት ብቻ እንዲሆን አደረጉ። በዚህም ምክንያት ወንዶቹ ወሲብን ለማግኝት ሲሉ ሙሉ ጊዜያቸውን ምግብ በመፈለግ ላይ ማዋል ጀመሩ። ከእዚህም የተነሳ ደግሞ ዘራችንን እንዳይጠፋ ሆነ። የዚህ ክስተት መፈጠር ሌላው ያስገኝልን በረከት ከወገባችን ቀና እንድንል ማድረጉ ነው፡፡ ምክንያቱም ወንዱ ወደ ሴቷ ሲሄድ ብዙ ምግቦችን በእጁ መሸከም ስለነበረበት ነው፡፡
6. በሁለት እግራችን መራመዳችን፡- የሳቫና ንድፍ ሀሳብ እንደሚያስቀምጠው በሁለት እግራችን ቆመን እንድንሄድ ያስገደደን የአየር ንብረት መለዋወጥ ነው፡፡ ከሶስት ሚሊዮን አመት በፊት በአፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ጫካዎች እንዲጠፉ እና ሳርማ መሬቶች እንዲበዙ አደረገ። ይህ ደግሞ በሳሮቹ መካከል በፍጥነት መራመድ እና ከሳሮቹ ቁመት በላይ ቀና እያሉ ጠላትን ለመጠበቅ እና ለማጥቃት አስገዳጅ ኹኔታን ፈጠረ። በተጨማሪም ውሃ እና ምግብ የሚገኝባቸው ቦታዎች የተራራቀ መሆን ሰው በፍጥነት መራመድ፣ ከቦታ ቦታ መዘዋወር ስላለበት በሁለት እግሮቹ መራመድ ግድ ሆነበት። በሁለት እግራችን መራመዳችን ዛሬን ለማየታችን አንዱ ሚስጥር ነው።
7. ማበራችን፡- የአሮዚና ሰቴት ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ኮርቲስ ማሬን እንደሚለን ከፍጡሯን ኹሉ ሰው በህብረት አጥቅቶ በመውረር የሚቀድመው አልነበረም፡፡ ይህ ህብረታዊነት ቀስ በቀስ የሥነ በራሂ (genetics) ባህሪያችንም ሆነ። ይኽም የጋራነት ኑሮችን አዳዲስ ኹነቶችንና ክስተቶችን በቶሎ እንድንለምድ ትልቅ አስተዋጽዖ በማድረጉ ከጥፋት ታደገን ይላል ተመራማሪው፡፡
@zephilosophy
BY ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
Share with your friend now:
tgoop.com/Zephilosophy/1105