"መብራቱን ይዛችሁ ጨለማው የት እንደሚገኝ ትፈልጋላችሁ።"
ኦሾ
..የቀጠለ
ብርሃን ሲኖር ጨለማ ይጠፋል፡፡ ጨለማ ጨርሶ የለምና የሚጠፋው ጨለማ አይደለም፡፡ ጨለማ የብርሃን አለመኖር ነው፡፡ የራስ ኩራት(የበላይነት ስሜት) ልክ እንደ ጨለማ ነው፤ ጨርሶ የለም፡፡ የራስ ኩራት የንቃት አለመኖር ነው፡፡
ስለዚህም ተመልከቱት እንጂ አጥፉት አልልም፡፡ ተመልካች፣ አስተዋይ ሁኑ. . .
ፖለቲከኛ ጭው ያለ የራስ ኩራተኛ ነው፤ ቅዱስ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው በጣም የባሰ የራስ ኩራተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ፖለቲከኛው በቀላሉ ሊታወቅ ይችላልና ቅዱሱ ከፖለቲከኛው የበለጠ አደገኛ ነው፡፡
የእኔ ጠቅላላ የህይወት ተግባር የሰውን መሰረታዊ ችግሮች ፈልጎ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡ የሰውን መሰረታዊ ችግሮች አንዴ ካወቅን መፍትሄ መፈለጉ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡
እኔ መሲህ ነኝ፣ እኔ አቫትራ ነኝ አልላችሁም ምክንያቱም እነዚህ የራስ ኩራት ወይም ራስን ከፍ የማድረግ ጨዋታዎች እንደሆኑ አውቃለሁ፡፡ እኔ እንደማንኛውም ሰው ተራ ወይም እንደ ማንኛውም ሰው ፍፁም ልዩ ነኝ፡፡
በህልውና ውስጥ አንዷ የሳር ሰበዝ ከትልቋ ኮከብ ጋር እኩል ጠቀሜታ እና ውበት አላት፡፡ በህልውና ውስጥ ተዋረድ የለም፡፡ ከፍተኛና ዝቅተኛ ብሎ ነገር የለም፡፡ እኔ ማንንም አልቃወምም፡፡ ነገር ግን የእኔ ዋና ስራ በሽታዎችን፣ እንቅፋቶችን በሙሉ ገልጦ ማሳየት ነው፡፡ ስለዚህም በእነዚህ ሳንካዎች አትያዙም፤ ነፃ ትሆናላችሁ ፤ ያለ ምንም እንቅፋት ከህልውና ጋር ትዋሃዳላችሁ፡፡ አንደኛው እንቅፋት ደግሞ ራስን ከፍ አድርጐ መመልከት ነው፡፡ እንደሚያታልላችሁ ካልነቃችሁ በብዙ መንገድ ይመጣባችኋል፡፡ እንደ ጥላ ጠንክሮ ሊከተላችሁ እና ነቅታችሁ ላታዩት ትችላላችሁ፡፡
በርግጥ ልታስወግዱት ከታገላችሁ እየጠነከረ ይሄዳል።ከአንድ ነገር ጋር ስትታገሉ የሚከሰተው ይህ ነው:: ወሲብ ሊሆን ይችላል፤ኢጎ ሊሆን ይችላል፡፡ ከመታገል በቀር ምን ልታደርጉት ትችላላችሁ? በሃይል ትገፉታላችሁ፤ ነገር ግን ወዴት ነው የምትገፉት የበለጠ በገፋችሁት ቁጥር የበለጠ ወደ ውስጣችሁ ይገባል ወደ ድብቁ ህሊና ጠልቆ የገባ ደግሞ ከንቃት ህሊና የበለጠ ሃይል አለው:: ድብቁ ህሊና ከንቁው ህሊና በዘጠኝ እጅ ይበልጣል፡፡ በንቃተ ህሊናችሁ ውስጥ ቢያንስ ምን እንዳለ ታውቃላችሁ:: ድብቁ አዕምሯችሁ ግን ጨለማ በመሆኑ በውስጡ ምን እንዳለ አታውቁም፤ ይሁንና ከንቁው ህሊና ዘጠኝ እጅ የሚልቅ ሃይል አለው፡፡ በማንኛውም ቅፅበት ንቁው ጥረታችሁን ሊውጠው ይችላል፡፡
ይህን ንቃት ነው የማስተምራችሁ:: ከራስ ወዳድነት፣ ከብስጭት፣ ከቅናት፣ ከጥላቻ ጋር አትታገሉ፡፡ ሃይማኖቶተኞች «ታገሏቸው፣ አጥፏቸው፣ ግደሏቸው፤ ጠላቶቻችሁ ናቸው›› እያሉ ይሰብኳችኋል፡፡ ልትገድሏቸው አትችሉም፣ ልታጠፏቸው አትችሉም፣ ልትታገሏቸው አትችሉም - በንቃት ልትመለከቷቸው እንጂ፡፡
ንቁ በሆናችሁ ቅፅበት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይጠፋሉ፡፡ በብርሃን ውስጥ ጨለማ አይኖርም፡፡
@zephilosophy

ለማንም የተፃፈ ደብዳቤ
[እነሆ የዘመንህ ቅዝምዝም ቅኔ...]
ይድረስ ላንተ ለማላውቅህ!!
እንደምን ነህ ማንም? ኑሮ እንዴት ይዞሃል? አለሁ እኔ ምንም ... አለሁ እንደምንም፡፡ አንተ ግን እንዴት ነህ? በሎሬት ፀጋዬ ሰላምታ ቅማንት ነህ ሽናሻ፣ አገው ነህ ወላይታ፣ ሃድያ ነህ ከምባታ... ወይስ ካህን ነህ አረመኔ፣ ገበሬ ነህ ወታደር፣ ባላባት ነህ ወይስ ገባር.. ክርስቲያን ነህ ወይስ ሙስሊም ወይስ ሌላ ወይስ ምንም... ብቻ ማንም ሁን፡፡ ማንም ሆይ ሰላምታዬ ላንተ ይሁን ብየሃለሁ፡፡ ብትመልስልኝ ደግ ባትመልስልኝ ግድ የለም፡፡
አንተስ እንደምን ነህ ላልከው... እኔማ ምን እሆናለሁ፡፡ በዮሐንስ አድማሱ ሰላምታ ያቀረብኩትን ሀሳብ አይሁድ ክርስቶስን በዕለተ ዓርብ ቸንክረው እንደሰቀሉት ሰቀሉት፡፡ ኋላም በማንም ስብሰባ ላይ ‹ጥላቻ፣ ብሔር፣ ጠባብነት፣ ድንበር፣ እምነት..." እንቶፈንቶ በተባለ ከፈን ከፍነው በአይቻልም በተባለ የሬሳ ሳጥን ዘግተው፣ በግብዝነት መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡›› እልሃለሁ፡፡
ከዚያም በኋላ እኔ ማንንም መሆንን ሸሽቼ ምንም ሆንኩ፡፡ እናም መንገዳችን ተለያየ፡፡ አንተ ወደ ኤማሆስ እኔ ወደ ቀራንዮ፡፡ አውቃለሁ ማንም ሆይ የኔ መንገድ ወደ ኤማሆስ መስሎ እንደሚታይህ አውቃለሁ፡፡ በዚህ እበልጥሃለሁ... እነሆ አንተ ከጥላቻህ፣ ከውምብድናህ፣ ከድንቁርናህ፣ ከድድብናህ፣ ከጅልግግናህ አዋጥተህ በሠራህልኝ ክንፌ ርቆ መብረር አቅቶኝ ስር ስርህ እውተፈተፋለሁ፡፡
ማንም ሆይ ግን አንተ እንደምንድን ነህ? ልክ ነህ እጠለሀለሁ፤ እንቅሃለሁ፤ .. እንደ ትንኝ፣ እንደ አንዳች፣ እንደ ኢምንት አይሃለሁ፡፡ምክንያቱም... ምክንያቱም... ምክንያቱም በጭካኔ ያለፍላጎቴ ዝንታለም የጠቀምከውን ዕድፋም ድሪቶ በላዬ ላይ ጭነህብኛልና፡፡ እናም ርቆ መብረሩ ቀረና አንተ ያወረስከኝን ድሪቶ መጥቀም ሆኗል ሥራዬ፡፡ ግን ደግሞ እወድሃለሁ፡፡ አንድ ዓይነት የጥላቻ ወይም የመውደድ ስሜት ጥርግርግ አድርጎ እንዲወስደኝ ከፈቀድኩማ ምኑን እኔን ሆንኩት? ምኑን ባንተ ዕድፋም ኑረት ተመራመርኩት? ምኑን ምንስ ሆነ?
ለመሆኑ የት ነህ? መተማ ነህ ጅማ? ደንቢዶሎ ነህ ደቡብ ወሎ? ነቀምቴ ነህ ዱርቤቴ? ጋምቤላ ነህ ዲላ? ወይስ አክሱም ወይስ ጭሮ? ወይስ ሌላ... ብቻ የትም ሁን፡፡ ሰላምታዬ ይድረስህ፡፡
ትገርመኛለህ ስታደንቅ በጅምላ፣ ስትተች በጅምላ፣ ስታመልክ በጅምላ፣ ስትበላ፣ ስትጠጣ፣ ስትደግፍ፣ ስትቃወም፣ በጅምላ ነው፡፡ ኸረ አሁን አሁንማ ስትሞትም በጅምላ ሆኗል፡፡ ስትሞትም ‹በስህተት› ሳይቀር በጅምላ ሆኖልሃል... ተነጥሎ መቆምን አታውቅበትም፡፡ ትፈራለህ፡፡ ምክንያቱም የተሰጠህ የዝንተ ዓለም አድፋም ድሪቶ መንጋነትን እንጂ ተነጥሎ መቆምን አላስተማረህማ፡፡
በየዕለቱ ደም ካዘለ ጭፍግግ ሰማይ ስር ግራ በተጋባ አውድ እንደሚታረዱ በጎች በሰልፍ እየተነዳህ እንደሆነ አያለሁ፡፡ሁልጊዜ ጭልፊት እንዳዩ እናት የሌላቸው መንጋ የዶሮ ጫጩቶች መጠለያ ፍለጋ በመንጋ ስትባዝን አይሃለሁ፡፡ አሳዛኙ ፍፃሜ ላይቀርልህ ነገር ይህ ሁሉ መሽቆጥቆጥ ለምንህ? ለምንህ? መልስ የለህም አውቃለሁ።
ማንም ሆይ ዛሬስ ስትበላ፣ ስትጠጣ፣ ስትሠራ ለብቻህ ወደ ውስጥ እያነባህ ታንጎራጉራለህ? ዛሬስ የሆነ ዓይነት ሰማያዊ ኃይል መጥቶ ከገባህበት የባርነት ቀንበር ያወጣህ ዘንድ በየዋህነት ታንጋጥጣለህ? ዛሬስ ያለ እቅድ መመራትህን አላቆምክም ይሆን?
በአድዋ ጦርነት ወቅት በጋሻና ጎራዴ ያሸነፍከውን ሠራዊት ከ40 ዓመታት በኋላም በጋሻና ጎራዴ እንደጠበቅኸው አትረሳውም መቼስ? ዛሬስ ባለህበት እየረገጥህ መሆኑ ታውቆሃል? ማንም ሆይ ያንተ ነገር ገና ያለቀለት አይመስልም፡፡ ነገርህ ህብሩ የተሳከረና የተወታተበ ነው፡፡ ነጻ ለመውጣት የቋመጥኸውን ያህል ሌሎችን ለመጨቆን ያቆበቆበ ድብቅ ማንነት እንዳለህም አያለሁ፡፡ ዘመኑን ለመቅደም ገና አልተዘጋጀህም፡፡
...ይቀጥላል
ያዕቆብ ብርሀኑ

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
ለማንም የተፃፈ ደብዳቤ [እነሆ የዘመንህ ቅዝምዝም ቅኔ...] ይድረስ ላንተ ለማላውቅህ!! እንደምን ነህ ማንም? ኑሮ እንዴት ይዞሃል? አለሁ እኔ ምንም ... አለሁ እንደምንም፡፡ አንተ ግን እንዴት ነህ? በሎሬት ፀጋዬ ሰላምታ ቅማንት ነህ ሽናሻ፣ አገው ነህ ወላይታ፣ ሃድያ ነህ ከምባታ... ወይስ ካህን ነህ አረመኔ፣ ገበሬ ነህ ወታደር፣ ባላባት ነህ ወይስ ገባር.. ክርስቲያን ነህ ወይስ ሙስሊም ወይስ…
የቀጠለ
ማንም ሆይ ነገር አረዘምኩብህ አይደል? በል ከአንተ አብራክ የወጣው ትንታግ ብዕረኛ ዮሐንስ አድማሱ በአንድ ወቅት ከፃፈልህ እና ቅድም ከቀነጨብኩልህ እንባ ቀረሽ ደብዳቤ ላይ የምትከተለዋን ላሥነብብህና ልሰናበትህ፡፡
ጽሑፉ ዮሐንስ አድማሱ በአንድ የመምህራን ስብሰባ ላይ የታዘበውና ለአንድ ወዳጁ (ምናልባት ጉዳዩን በሚገባ ለሚያውቅ ጓደኛው) የላከለት፣በብልህ ዘይቤ የተፃፈ ድንቅ ደብዳቤ ነው፡፡ የዮሐንስ ትዝብት፣ ምሬት ከአንድ ስብሰባ ባሻገር ሀገርን የሚያክል ምናልባት ሀገርን የሚወክል ነበር፡፡ እነሆኝ አንብቡት፡፡
‹‹ያቀረብነው ሀሳብ አይሁድ ክርስቶስን በዕለተ ዓርብ ቸንክረው እንደሰቀሉት በዕለተ ሰሉስ (ማክሰኞ ህዳር 5 የአቡዬ ዕለተ) ሰቀሉት፡፡ ኋላም በመምህራን ስብሰባ ላይ (ረቡዕ ህዳር 6 የኢየሱስ ዕለት) "ውሳኔ" በተባለ ከፈን ከፍነው ባይቻልም የሬሳ ሳጥን ዘግተው በግብዝነት መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡ ትንሳኤ ያለውም አይመስልም፡፡ ረቡዕ ዕለት በመምህራኑ ስብሰባ ጊዜ የነበረውን ግድየለሽነት፣ ግብዝነት፣ ተደጋጊነት፣ ንዝህላልነት በአንድ ቃል ሃላፊ ቢሥነት አታንሳው፡፡እንደተለመደው የተናገሩት በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡
የቀሩት ግን አፋቸው ቅርቃር የተቀረቀረበት የሚመስል አየር ለመሳብ አፍንጫቸውንና አፋቸውን ከመክፈት ከመዝጋት በቀር ከላይ አፋቸው ከታች አፋቸው አንዲት ቅንጣት ቃል አልተናገሩም፡፡ በተለይ ዕርር ትክን ያደረገኝ ይሄ ነው፡፡ የህሊና ብርሃናቸው የጠፋባቸው ይመስለኛል፡፡ ወይም በዘመናችን ያለው ትውልድ ተኮላሽቷል፡፡
አጋሰስ ትውልድ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ ምናልባት ተሳስቼ ይሆናል፣ ምናልባት የዚህ ዓለም ፈሊጥ የመኖር ወይም ከመኖር የሚገኘው ጥበብ አልተከሰተልኝ ይሆናል፡፡ የኑሮ ጥበብ ዝምታ ይሆን ነገሩ ብዙ ነው ህብሩም የተሳከረ፣ ስልቱ የተባ፣ አስተሳሰቡ የተዛባ ነው፡፡ እንኳን በዚህ ደብዳቤ በሌላም በሶስት አራት ደብዳቤ አይከተትም፡፡ ለዚች አገር እድል ፈንታዋ ፅዋ ተርታዋ ምን ይሆን? ብዬ አስባለሁ፡፡ እንጃ የምለምነው ግን የዕድሜ አተላ ሆና እንዳትቀር ነው፡፡ እኛስ ከፋም ለማም ደህና ኑሮ እንኖራለን፡፡ ይህ ስም የለሹ ሕዝብስ...››88
(ህዳር 7 1965ዓ.ም የተፃፈ ደብዳቤ ውስጥ የተቀነጨበ ምንጭ እስኪ ተጠየቁ)
ያዕቆብ ብርሀኑ
@zephilosiphy

ንጋት
ጠጠር ባኮፋዳ፣ ከባህር ዳር ለቅመው፣
ደሞ ዳግም ገድፈው፣
በድሜጥሮስ ኩፋል፣ ከባህረ-ሃሳብ
አቡሻህር ቆጥረው ፣
ዘመን የፈተቱ፣
ጊዜን የበለቱ፣
ከጨረቃ ሌሊት፣
ከጀምበርም መአልት፣
ቀን የፈተፈቱ፣
ምንኛ ዋተቱ!
ምንኛ ቃተቱ!
አወይ መጥቅዕ መና፣ ወይ አበቅቴ ከንቱ።
ዘመን አይፈረጥጥ፣ ጊዜም አይሸመጥጥ፣
ቀንም መሽቶ አይነጋ፤
ሰው ነው የሚጨልም፣ ሰው ነው የሚነጋ፡፡
ይስማዕከ ወርቁ
@zephilosophy
ጠጠር ባኮፋዳ፣ ከባህር ዳር ለቅመው፣
ደሞ ዳግም ገድፈው፣
በድሜጥሮስ ኩፋል፣ ከባህረ-ሃሳብ
አቡሻህር ቆጥረው ፣
ዘመን የፈተቱ፣
ጊዜን የበለቱ፣
ከጨረቃ ሌሊት፣
ከጀምበርም መአልት፣
ቀን የፈተፈቱ፣
ምንኛ ዋተቱ!
ምንኛ ቃተቱ!
አወይ መጥቅዕ መና፣ ወይ አበቅቴ ከንቱ።
ዘመን አይፈረጥጥ፣ ጊዜም አይሸመጥጥ፣
ቀንም መሽቶ አይነጋ፤
ሰው ነው የሚጨልም፣ ሰው ነው የሚነጋ፡፡
ይስማዕከ ወርቁ
@zephilosophy
---
የአንቺ አቅም
ይሄ ቀሽም መንገድ!
“ካለእሷ መራመድ አይችልም!” እያለ፣
“ከእሷ ውጪ መጓዝ አይችልም!” እያለ፣
“አቅጣጫ ካለእሷ አያውቅም!” እያለ፣
“ያለእሷ – ገደሉን፣
ዕንቅፋት፣ ድልድዩን – አይለይም!” እያለ፣
በእርምጃዬ መጠን ሀሜት ሲሰፍርልኝ፣
“መንገዴ አንቺ እንደሆንሽ”
ምነው ብትነግሪልኝ?
ሩሚ
@zephilosophy
የአንቺ አቅም
ይሄ ቀሽም መንገድ!
“ካለእሷ መራመድ አይችልም!” እያለ፣
“ከእሷ ውጪ መጓዝ አይችልም!” እያለ፣
“አቅጣጫ ካለእሷ አያውቅም!” እያለ፣
“ያለእሷ – ገደሉን፣
ዕንቅፋት፣ ድልድዩን – አይለይም!” እያለ፣
በእርምጃዬ መጠን ሀሜት ሲሰፍርልኝ፣
“መንገዴ አንቺ እንደሆንሽ”
ምነው ብትነግሪልኝ?
ሩሚ
@zephilosophy
መፍትሔ
በር መስኮት ዘግተህ፣
ቀዳዳዎች ደፍነህ፣
የለኮስከው ሻማ “በራ!”፣ “ጠፋ!” ካለ፤
ጠርጥር
ቤት ያፈራው ንፋስ ከጐጆህ እንዳለ?
በረከት በላይነህ
@zephilosophy
በር መስኮት ዘግተህ፣
ቀዳዳዎች ደፍነህ፣
የለኮስከው ሻማ “በራ!”፣ “ጠፋ!” ካለ፤
ጠርጥር
ቤት ያፈራው ንፋስ ከጐጆህ እንዳለ?
በረከት በላይነህ
@zephilosophy
አለም መቼ ተፈጠረች?
ኦሾ
እንደ ክርስትናና እስልምና ባሉ ሀይማኖቶች ዓለም የተፈጠረችው ከ6000 ዓመታት (4000BC+2000AC) በፊት እንደሆነ ያምናሉ፤ በሌላ በኩል ሳይንቲስቶች ደግሞ ይህች ምድር ከተፈጠረች በሚልየን የሚቆጠሩ ዓመታት ዕድሜ እንዳላት የሚያሳዩ ማረጋገጫዎች አግኝተናል ይላሉ። በምድር ውስጥ በቁፋሮ የወጡ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዕድሜ ያላቸው የእንስሳትና የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ተገኝተዋል ይላሉ።
ታድያ የመጨረሻው ጳጳስ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠይቀው ምን አሉ?
"ዓለም የተፈጠረችው ልክ መፅሐፉ እንደሚናገረው ነው፡፡"
ይህ ማለት ከስድስት ሺ ዓመታት በፊት ማለት ነው፡፡ ያሉት ማስረጃዎች ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ናቸው፡፡ህንድ ውስጥ ሰባት ሺ ዓመታት ያስቆጠሩ ከተሞችን አግኝተናል፡፡ ህንድ ውስጥ እንደ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ከሆነ ቢያንስ አስር ሺ ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠሩ ቬዳስ አግኝተናል፡፡ እንደ ሂንዱ ዕምነት ተከታዮች የእነኚህ ቬዳስ ዕድሜ ዘጠና ሺ ዓመታት ይሆናል። ምክንያቱም ቬዳስ ውስጥ ከዘጠና ሺ ዓመታት በፊት የነበሩ የአንዳንድ ኮኮቦች ምልክቶች ተገኝተዋል፡፡ ቬዳስ ውስጥ የተገኙት ኮኮቦች ዘጠና ሺ ካላስቆጠሩ ምን ተብለው ሊገለጹ ይችላሉ?
የጳጳሱ መልስ አስራሚ ነበር
«እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረው ከእነኚህ ነገሮች ጋር ነው፡፡ለእሱ የሚሳነው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር ዓለምን ከ6000 አመታት በፊት የፈጠረው በሚሊየን የሚቆጠሩ ዓመታት የኖሩ ከሚመስሉ የእንስሳት ቅሪተ አካል ጋር ነው፡፡››

ተፈጣሪያዊነት (Creationism)
እንዴትና ከየት መጣን?
ሰው እንዴት እና ከየት መጣ በሚለው ጉዳይ ላይ የሚነሱትን ሥነ መለኮታዊ እይታዎች፣ ፍልስፍናዊ እሳቤዎች፣ ሳይንሳዊ ግኝቶች እና የምርምር ውጤቶችን ከአጠቃላይ የተፈጥሮ አፈጣጠር ጋር በማቀናጀት ለመመልከት እንሞክራለን።
በዚህ መሰረት ለጥያቄችን ምላሽ የሚሰጡን በሁለት ዋነኛ ንዑስ ርእስዎች በመከፋፈል የሚቀመጡ ሲሆን እነሱም ተፈጣሪያዊነት (Creationism) እና የዝግመተ ለውጥ ጽንስ ሐሳብ (Evolution Theory) ናቸው፡፡
ተፈጣሪያዊነትን አጮልቀን ከተመለከትነው በሃይማኖት መጻሐፍት ላይ የሚገኙ ትረካዎችን እንደወረደ የሚቀበል እና ፈጣሪ ኹሉን ሲፈጥር መነሻው ምንም(ከባዶ) ነው የሚል እምነት ብቻ ያለው እንደሆነ በመረዳት እናበቃለን፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ እሳቤው በተለይም ከክርስትና እና ከአይሁድ ሃይማኖት አስተምህሮ ብቻ ጋር ሙሉ ለሙሉ ይገጥማል ብለን መደምደማችን አይቀሬ ይሆናል። ኾኖም “A History of Modern Creationism” እንዲሁም “scientific Creationism” በሚሉ ስራዎቹ ለሚታወቀው ሄነሪ ሞሪስ ይህ ስህተት ነው፤ ስህተት መሆኑን ለማስረዳት የሚያስችለው ደግሞ የተፈጣሪያዊነት ሶስት መልክ (በሶስት መከፈል) ነው ይለናል ሞሪስ፡፡ የመጀመሪያው ሳይንስን መሰረት ያደረገው ተፈጣሪያዊነት (Scientific Creationism) ሲሆን አፈጣጠርን በተመለከተ መሰረት የሚያደርገው ሳይንሳዊ ግኝቶችን ነው፡፡ ሌላኛው መጽሐፍ ቅዱሰን ብቻ የተመረኮዘ ተፈጣራዊነት (Biblical Creationism) ተብሎ ሲጠራ በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ ካለው የአፈጣጠር ትረካ ውጪ ሌላ አስረጂ አያስፈልግም የሚል ነው፡፡ ሶስተኛው በበኩሉ ሳይንሳዊ መንገድን ከመጽሐፍ ቅዱሱ የአፈጣጠር ትረካ ጋር ያጣመረ (Scientific Biblical Creationism) ነው፡፡ ይኽም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን የአፈጣጠር ትረካን ሳይንሳዊ ምርምሮች እና ግኝቶች እስካብራሩ እና እስካጠናከሩ ድረስ ፊት ሊሰጣቸው ይገባል የሚል እሳቤ ያለው ነው፡፡
የተፈጣሪያዊነት እምነት እና እሳቤን ይበልጥ ለመረዳት አራማጆችን በሶስት ጎራ ከፍለን መመልከቱ ይበጃል፡፡ እነሱም ኦልድ ኀርዝ ክሬሽኒስቶች (Old Earth Creationists)፣ ኢንተለጀንት ዲዛይን ክሬሺዝም (intelligent Design Creationism) እና ያንግ ኅርዝ ክሬሽኒስቶች(Young Earth Creationists) ናቸው፡፡
ይቀጥላል...

እንዴት እና ከየት መጣን?
.....የቀጠለ
1.ኦልድ ኀርዝ ክሬሽኒስቶች (Old Earth Creationists) እንደሚሉን ከሆነ ምድርን ጨምሮ ኹሉን የፈጠረው ፈጣሪ መሆኑ እርግጥ ኾኖ እድሜያቸውን በተመለከተ ግን የሥነ-ምድር ተመራማሪዎችን (geologist) እና
የሥነ-ፈለክ አጥኚዎች (astronomer) የሚያስቀምጡልንን ቁጥር ብንቀብል ይበጃል። ኦልድ ኀርዝ ክሬሽኒስቶች በአንድ ረድፍ አይቀመጥም፤ በሶስት እንጂ፤
የመጀመሪያው የ ዳግም ተፈጣሪያዊነት' (Gap or Restoration creationism) ሲሆን፣ እነዚህም ምድር ከባዶ አሊያም ከምንም አይደለም የተፈጠረችው፤ መጀመሪያ ቀድሞ ከነበረ እና ካረጀ ምድር ነው ተሻሽላ የመጣቹ የሚል ነው፡፡
በሁለተኛ ረድፍ የሚቀመጡት የቀን ቆጣሪ ተፈጣሪያዊነት (Day Age creationism) ተብሎ ሲጠራ፣ ይኽም የመጽሐፍ ቅዱስን ስድስቱ ቀናቶች በ24 ሰዓት አቆጣጠር መለካት ትልቅ ስህተት ነው የሚል ድምዳሜ አለው፡፡ አንዱ ቀን ሚሊዮን አሊያም ቢሊዮን ዓመት ሊሆን ይችላል ስለሚል የሚል መከራከርያ አለው፡፡ በዚህ ረድፍ የሚቀመጡት አራማጆች ይህን ለማለት ካስቻላቸው መሰረቶች ዋነኛው በአይሁዶቹ የዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ ያለው “ዮም "(ከአማርኛው ላይ ቀን እየተባለ የተገለጸው) የሚለው ቃል የትርጉም እኩሌታ ዘመን አሊያም ርዝመቱ የማይታወቅ "ጊዜ" የሚለው መሆኑ ነው
በመጨረሻ ረድፍ የሚገኝው (አቀማመጡ የጸሐፊው ኾኖ) “የተሸጋጋሪ ተፈጣሪያዊነት (progressive creationism) ነው፡፡ ይህን እሳቤ የሚከተሉት በበኩላቸው እንደሚሉት ተፈጥሮ አሁን የያዘውን ይዘት እና ቅርጽ ያገኝችው በአንዴ ጊዜ አይደለም፤ ኹደቱ ረጅም ዘመናትን የፈጀ ነው፡፡ ታዲያ ይህ በፈጣሪ ፍቃድ የተደረገ መሆኑ በፍጹም እንዳይረሳ ይሉናል።

2.ሌላኞቹ የተፈጣሪያዊነት አንድ አካል ተደርገው የሚቆጠሩት፣ ከ970 በኃላ ብቅ ያሉት ያንግ ኅርዝ ክሬሽኒስቶች(Young Earth Creationists) ናቸው። እነዚኞቹ እንደሚሉን ደግሞ የምድርን ሆነ በውስጧ ያሉ ፍጥሮችን ልደት እናከበራለን ካልን ከስድስት ሺህ የማያንስ፣ ከአስር ሺህ የማይበልጡ ሻማዎችን ማዘጋጀት አለብን፡፡ “የዩኒቨርስንም አብረን ማክበር አለበንና እድሜው ስንት ይሆን?' ብለን ከጠይቅናቸው፣ ከመካከላቸው ግማሾቹ እኩል እድሜ አላቸው ሲሉን ሌሎቹ በበኩላቸው ዪንቨርስ ትቅድማለች ይላሉ፤ ኾኖም የእድሜው ስሌት ግን ከ10 ሺህ በላይ እንደማይገፋ በሁለቱም ጎራ ያሉ ተከራካሪዎች ማንሳታቸው አይቀሬ ይሆናል። አሁን ያለችው ምድር ሆነ በውስጧ የያዘቻቸው ፍጡራን ቀድሞ በዘፍጥረት የመጀመሪያ ምዕራፎች ላይ የተፈጠሩት ናቸውን?' ብትሏቸው፣ ምላሻቸው አይደለም የሚል ነው፡፡ ለዚህ ምላሻቸው እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ኹነት ኢዩሱስ ወደ ምድር ሳይመጣ ከ2000- 3000 አመታት በፊት የተከሰተው የጥፋት ውሃን ነው፡፡ ከጥፋት ውሃ በኃላ ምድር እንደገና እንደ አዲስ ተፈጥራለች ማለት ይቻላል ይሉናል የዚህ እሳቤ(እምነት) አራማጆች፡፡ ጨምረውም ከጥፋት ውሃ በፊት የነበሩ፣ ነገር ግን ከኖህ መርከብ ላይ ሳይሳፈሩ የቀሩ ፍጡራን በሙሉ ጠፍተዋል ይሉንና፣ ዛሬ ላይ የሚገኙት ቅሪተ አካሎች አብዛኞቹ በዛን ወቅቱ የተቀበሩ ናቸው የሚል ድምዳሜያቸውን ያቀርቡልናል፡፡
3.ስለ ተፈጣሪያዊነት ያነሳነውን ሐሳብ የምናጠቃልለው በቅርብ ብቅ ያለውን ኢንተለጀንት ዲዛይን ክሬሺዝም (intelligent Design Creationism) አራማጆች ምን እንደሚሉን በማንሳት ይሆናል። የእዚህ እሳቤ አራማጆች እንደሚሉት የፀሐይ ዙረት ሥርዓት ጅማሬን እንዲሁም የፍጥረተ ዓለሙ እድሜ እና ዘመን ማስቀመጥ የሚቻል በፍጹም አይደለም። ስለዚህ ጉዳይ በቂ እውቀት የሆነው አዋቂ በሆነ አበጂ ኹሉም የተፈጠረ መሆኑን መረዳት ብቻ ነው። እንዲሁም የሕይወት ውስብስብ ኹደትን ከተመለከትን፣ የፍጥረተ ዓለሙ አፈጣጠር የታስቦት እና የታቅዶት ውጤት መሆኑን እንጂ የተፈጥሮ ምርጫ ፅንስ ሐሳብ እንደሚለው እንዳልሆነ እናውቃለን የሚል ድምዳሜ አላቸው፡፡ ታዲያ ፍጥረተ ዓለሙ በተነደፈለት ሥርዓት ሊጓዝ የሚችለው ኹሉም ፍጥረት የተፈጠረበትን ዓላማ ሲያሳካ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ይኽም የሚያሳየን በተፈጥሮ ምርጫ አሊያ በዝግመተ ለውጥ ፅንስ ሐሳብ መሰረት የተፈጠረ ፍጡር ሆነ የፍጡራን አካል አለመኖሩን ነውም ይላሉ፡፡ ይህን ድምዳሜያቸውን irreducible complexity ብለው ይጠሩታል፡፡
ቀጥሎ ደግሞ ስለ ዝግመተ ለውጥ እሳቤዎች እናያለን

የዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሀሳብ
በዝግመተ ለውጥ ፅንስ ሐሳብ ላይ ትልቅ አሻራውን ያኖረው ቻርልስ ዳርዊን "ሕይወት ላለቸው ነገሮች ኹሉ ቀዳሚቷ ምንጭ ማናት?" በሚለው ጉዳይ ላይ ያለውን ነገር እንመልከት፡፡ ይህ ሳይንቲስት ስለ ፍጥረታት ምንጭ ወዳጁ ለነበረው ጆሴፍ ሁከር በጻፈው ደብዳቤ ላይ ዛሬ ላይ በምድር ላይ ያለው ፍጡራን በሙሉ አንዱ እየጠፋ ሌላው እየዘለቀ እዚህ ላይ ይድረስ እንጂ መነሻው አንዲት ሴል ናት፡፡ ይቺ ሴል ከየት መጣች ለሚለው ጥያቄ የእኔን መላምት አስቀምጥ ካልከኝ ከኹሉ በፊት አንዲት ኩሬ የነበረች ሲሆን የተለያዩ ዓይነት ኬሚካሎች በውስጧ ይገኝ ነበር የሚል መነሻ አለው፡፡ ታዲያ በዚህች ኩሬ ላይ በሚያርፈው ጨረር እና በዛም የተነሳ በሚፈጠረው ሙቀት ምክንያት በተፈጠረ ኬሚካላዊ ለውጥ ሞሊኪሎች ተፈጠሩ የሚለው ቀጣዩ የመላምቱ ክፍል ነው፡፡ እነዚህ ሞሊኪሎች ደግሞ ያቺን ሴል ፈጠሩ፡፡ ሴሏ ወደ ህዋሳት፣ ህዋሳቶቹ ወደ የውሃ ላይ እንስሳት ተቀየሩ፡፡ ከእነዚህ የውሃ ላይ እንስሳት ደግሞ ግማሾቹ ወደ የብስ በመውጣት በየብስም ሆነ በውሃ ላይ መኖር የሚችሉ እንስሳት ሆኑ፡፡ በዚህም የተለያየ ባህሪ እንስሳቶቹ ሊይዙ ችለዋል ማለት ነው፡፡ አንዳንዶቹ መብረር የሚችሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ተሳቢ እንስሳት ሆነዋል፡፡ እንዲሁም የአራባብ ዘዴያቸው በዛው ተለያይቶ፤ ግማሾቹ በመውለድ ቀሪዎቹ እንቁላል በመጣል ሊራቡ ችለዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ጦጣ ተፈጠረ፤ ሰውም ከዛ ተገኘ፡፡' የሚል ሐሳብ ያለውን መላምቱን አስቀምጧል፡፡
በዝግመተ ለውጥ ፅንሰ ሐሳብ መሰረት ሕይወት ያላቸው ነገሮች ጥንተ ምክንያታቸው ከአንድ ሀረግ የሚመዘዝ ነው፡፡ ይኽም ማለት እንስሳት ሆነ እጽዋት ተያይዥነት ያለው አፈጣጠር አላቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የፅንሰ ሐሳቡ መሰረት ሕይወት ያላቸው ነገሮች በጊዜ ሂደት ከቀደምቶቻቸው ይልቅ በቅርጽ እና በባህሪ ለውጥ ይፈጠርባቸዋል የሚል ነው፡፡ ይህ ለውጥ ሊከሰት የሚችለው ታዲያ በረጅም ጊዜ ሲሆን፣ ለመከሰቱ ምክንያት የሆነውም በተፈጥሮ ምርጫ ኹነት ራሳቸውን እያራቡ ለመዝለቅ የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡ በሌላ አባባል የተፈጥሮ ምርጫ የዝግመተ ለውጥ ኹነት በፍጡራን ላይ እንዲፈጠር የሚያደርገው ኃይል ነው፡፡ እንስሳት ሆኑ እጽዋት በምድር ይሰነበቱ ዘንድ በተፈጥሮ አማካኝነት የሚከሰቱትን ፈተናዎችን በማለፍ መራባት አለባቸው። ከዚህ ጋር ተያይዥነት ያለውና በተፈጥሮ ምርጫ አማካኝነት በሚፈጠረው ዝግመተ ለውጥ ምክንያት ሕይወት ያላቸው ነገሮች ዘላቂነታቸውን ያስቀጥላሉ።
ከ5 ሚሊዮን ዓመት በፊት በተከሰተው ዝግመታዊ የአከባቢ ለውጥ ምክንያት የምድር ቅዝቃዜ ሲጨመርና የበረዶ ክምሮች መፈጠር ሲጀምሩ የአየር ኹኔታው ወደ ሞቃታማነት አጋደለ፤ በዚህ የተነሳ ደግሞ ጫካማነት ቀንሶ፣ ሳርማ እና ሜዳማ የምድር አካላት በዙ፡፡ ታዲያ በምስራቅ አፍሪካ ይገኝ የነበሩትና ከዛፍ ዛፍ እየተዘዋወሩ ከሚኖሩት Hominoidea' ከሚባሉ የእንስሳት ዝርያዎች መካከል የተወሰኑት በሁለት እግራቸው መራመድ የግድ ሆነባቸው፡፡ በሁለት እግር ለመሄድ በመሞከር ስሙ የሚጠራው አውስትራሎፒተከስ ተብሎ
የሚጠራው ሲሆን፣ የሰው ቀጥተኛ ቀደምት ዝርያ ነው ይሉታል የዘርፉ ተመራማሪዎች፡፡ የዚህ ዝርያ ቀዳሚ ደግሞ አውስትራሎፒተከስ አናሚሰስ ነው፡፡ ይኽም የ4 ሚሊዮን እድሜ ያለው እንደሆነ ይነገርለታል፡፡
በመቀጠል የመጣው ዝርያ ከ2-3ሚሊዮን ዓመት በፊት ይገኝ የነበረውና ሉሲ (ድንቅነሽ) የምትገኝበት አውስትራሎፒተከስ አፋርኒሰስ ነው፡፡ ከዚህ ዝርያ በኃላ የተከሰተው ሆሞ ሃብሊስ ነው፡፡ ይኽም የመጀመሪያው የሆሞ ዝርያ ሲሆን፤ የጭንቅላቱ መጠን ከቀደምቱ ይልቅ 200-300 ሴ.ሜ ይልቅ ነበር ይላሉ አጥኒዎቹ፡፡ ከሆሞ ሃብሊስ በኃላ ብቅ ያለው እሳትን እና ድንጋይን መጠቀም እንዲሁም ንግግር ጀመረ የሚባለው ሆሞ ኤርክተስ ነው፡፡ ይኽም ዝርያ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ ወደ ኤስያ እና አውሮፓ የተሰደደው፡፡ የሆሞ ኤርክተስ ተከታይ ኾኖ የምናገኝው ደግሞ የዛሬዎቹ ሰዎች የሚመደቡበት ሆኖ ሳፒያንስ ነው፡፡
ሌላኛው መከራከርያ በበኩሉ ቀጥተኛ የሰው ቀደምት የሚባል ነገር የለም የሚል ነው፡፡ ይህን መከራከርያ ኖኅ ሀራሪ “Sapienst A Brief History of HumanKind' በሚለው መጽሐፍ ላይ “Skeletons in the closet' በሚል ርእስ አጠር ባለ መልኩ አስቀምጦታል:: ይህ የታሪክ ፕሮፌሰር እንደሚለው “ጠቢቡ ሰው የደበቀው ሚስጥር አለ፤ ይህም በሆነ ወቅት ላይ ሥልጣኔ የማያቁ ዘመዶች ብቻ ሳይሆን ጥቂት የማይባሉ ወንድም እና እህቶችም እንደ ነበሩን ነው፡፡ ምንም እንኳን ላለፉት 10,000 ዓመት ሆሞ ሳፒያንስ ምድራችንን ተቆጣጥሮት ስለነበር ራሳችንን እንደ ብቸኛ ዘረ ሰብዕ አድረገን ስንቆጥር የነበረ ቢኾንም ከሆሞ ሳፒያንስ ውጪ ሌሎች የሰው ዝርያዎችም ነበሩ:: ሰው የሚለው ቃል ልከኛ ትርጓሜም “ሆሞ በሚባል ጀነስ የሚመደብ የሚል ነው፡፡”
ይቀጥላል...
መፅሀፍ - ጥያቄዎቹ
ደራሲ - ፍሬው ማሩፍ

የዝግመተ ለውጥን ፅንሰ ሐሳብ ላይ ከሚነሱት ጥያቄዎች መካከል አንዱ በተፈጥሮ ምርጫ ሂደት ውስጥ የጠፋው ጠፍቶ፣ የዘለቀው ዘልቆ ከቆዩት ፍጡራን መካከል በምን ምክንያት ይሆን እስከዛሬ ያልጠፋነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ሳይንስ ካስቀመጣቸው ምላሾች መካከል የተወሰኑትን እጅግ አጠር ባለ መልኩ ላስቀመጥ፡-
1. ገዳዮች ነበርን፡- አንትሮፖሎጂስቱ ራይሞንድ ዳርት(1893-1988) “ገዳዩ ጦጣ (killer ape theory) ተብሎ በሚጠራው ፅንስ ሐሳቡ ላይ ቀደምቶቻችን እጅግ አደገኛ እና ጨካኞች እንደነበሩ ይናገራል። ተመራማሪው እንደሚለው የመከላከል አቅማቸውን ችሎ ጥቃት ማድረስ የሚችል ሌላ ፍጡርም አልነበረም:: በእዚህም ከአሸናፊዎቹ ውስጥ አንዱ እየሆነን እስከዛሬ ዘልቀናል።
2. ምግብ እንከፋፋል ነበር፡- የእዚህ ፅንስ ሐሳብ አራማጅ ደቡብ አፍሪካያዊው
ኢዛ ግላይን(1937-1985) በ1971 “Whither Archaeology” በሚለው ጽሑፉ ላይ እንደሚለን እኛ ሰዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ ያገኘነውን መብል የመካፈል ባህሪ ነበረን። እንዲሁም ለምግብነት የሚውል ነገሮችን እንዴት እና የት እንደሚገኝ መረጃ እንለዋወጥም ስለነበር ሰው በተፈጥሮ ተመራጩ ሆኗል የሚል ድምዳሜ አለው። በተጨማሪም በእዚህ ልምዱ የተነሳ ቋንቋ ሊኖረን የቻለ ሲሆን፣ማኅበረሰባዊ የሆነ ባህሪንም የተላበሥነው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
4 አዳኞች ነን፡- ፍላጎቶቻችን ለሟማላት ያለን ጥረት፣ የማሰብ ችሎታችን፣ ስሜቶቻችን የመቆጣጠር አቅም እና ሌሎች ማኅበረሰባዊ የሆኑ አኗኗራችን ያገኘነው የማደን ዘዴን በማበጀታችን ነው፡፡ ይህን ያለው ደግሞ ሼርውድ ዋሽበርን(191-2000) የተባለ አንትሮፖሎጂስት ነው።
5. ወሲብ፡- በቀደምት ሰዎች ውስጥ የአንድ ለአንድ ግንኙነት መፈጠሩ በሰው ልጆች የዝግመተ ለውጥ ሂደት ላይ መዝለቅ እንዲችል ያደረገው ዋነኛው ክስተት ነው ይላል ሌላኛው አሜሪካያዊ ተመራማሪ ኦዎን ላቭጆይ። ከዛ ቀደም የነበሩት ወንዶች ወሲብ ለመፈፀም ከፈለጉ በሴቷ አከባቢ የተገኝ ሌላ ተገዳዳሪን በሙሉ መግደል አሊያም ማባረር ነበረባቸው፡፡ ኾኖም ሴቶቹ ይህንን ልምድ መቀየር አለበት ብለው በመወሰን ገላቸውን አሳልፈው የሚሰጡት ምግብ በቋሚነት ማቅረብ ለሚችሉ እና አብሮዋቸው ለሚቆዩት ብቻ እንዲሆን አደረጉ። በዚህም ምክንያት ወንዶቹ ወሲብን ለማግኝት ሲሉ ሙሉ ጊዜያቸውን ምግብ በመፈለግ ላይ ማዋል ጀመሩ። ከእዚህም የተነሳ ደግሞ ዘራችንን እንዳይጠፋ ሆነ። የዚህ ክስተት መፈጠር ሌላው ያስገኝልን በረከት ከወገባችን ቀና እንድንል ማድረጉ ነው፡፡ ምክንያቱም ወንዱ ወደ ሴቷ ሲሄድ ብዙ ምግቦችን በእጁ መሸከም ስለነበረበት ነው፡፡
6. በሁለት እግራችን መራመዳችን፡- የሳቫና ንድፍ ሀሳብ እንደሚያስቀምጠው በሁለት እግራችን ቆመን እንድንሄድ ያስገደደን የአየር ንብረት መለዋወጥ ነው፡፡ ከሶስት ሚሊዮን አመት በፊት በአፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ጫካዎች እንዲጠፉ እና ሳርማ መሬቶች እንዲበዙ አደረገ። ይህ ደግሞ በሳሮቹ መካከል በፍጥነት መራመድ እና ከሳሮቹ ቁመት በላይ ቀና እያሉ ጠላትን ለመጠበቅ እና ለማጥቃት አስገዳጅ ኹኔታን ፈጠረ። በተጨማሪም ውሃ እና ምግብ የሚገኝባቸው ቦታዎች የተራራቀ መሆን ሰው በፍጥነት መራመድ፣ ከቦታ ቦታ መዘዋወር ስላለበት በሁለት እግሮቹ መራመድ ግድ ሆነበት። በሁለት እግራችን መራመዳችን ዛሬን ለማየታችን አንዱ ሚስጥር ነው።
7. ማበራችን፡- የአሮዚና ሰቴት ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ኮርቲስ ማሬን እንደሚለን ከፍጡሯን ኹሉ ሰው በህብረት አጥቅቶ በመውረር የሚቀድመው አልነበረም፡፡ ይህ ህብረታዊነት ቀስ በቀስ የሥነ በራሂ (genetics) ባህሪያችንም ሆነ። ይኽም የጋራነት ኑሮችን አዳዲስ ኹነቶችንና ክስተቶችን በቶሎ እንድንለምድ ትልቅ አስተዋጽዖ በማድረጉ ከጥፋት ታደገን ይላል ተመራማሪው፡፡

እስልምና እና ተፈጣሪያዊነት
Eslamic creationism thought
የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንደሚሉት የሚታየው እና የማይታየውን ኹሉ የፈጠረው አላህ ነው፡፡ በሰማይ ሆነ በምድር ያሉ ፍጡራን በሙሉ መኖር የሚመሰከሩት ዋነኛው ነገርም ህልውናውን ነው፡፡ ፀሐይ ሆነች ጨረቃ እንዲሁም ከዋከብትን የተፈጠሩትም ሆነ የሚታዘዙት ለአላህ ነው፡፡ ፈጣሪ በዓለም ላይ ያሉ ፍጡራንን ተዛማች ጥንድ አድርጎ የፈጠረው ማለትም ሰማይ እና ምድር፣ ሞት እና ሕይወት፣ ደስታ እና ሀዘን፣ የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ አድርጎ ያበጀው የምንም እና የማንም ፈጣሪ እሱ እንደሆነ እንድንገነዘብ ዘንድ ነውም ይሉናል የሃይማኖቱ የሥነ መለኮት መምህራን፡፡ የሰማይን ከፍታ፣ የሌሊትን አጨላለም፣ የቀኑን መልክ፣ የምድር መዘርጋት በሙሉ የተደረገው በአላህ ይሁን ቃል ነው፡፡
እንደ እስልምና ሀይማኖት አስተሳሰብ አለም የተፈጠረችው በስድስት ቀን አፈጣጠር ትረካ ቢሆንም ብዙዎቹ የሀይማኖቱ መምህራን እንደሚሉት "ቀን" የሚለው ትርጉም የሰው የጊዜ አቆጣጠርን ("24 ሰዓት") አይገልፅም ይልቅ በአላህ የጊዜ አቆጣጠር ይወሰናል ይህም ማለት አንዱ ቀን ሚሊዮን አመታት ሊሆን ይችላል የሚል አስተምህሮ አለው።
የሰውን አፈጣጠር ከቅዱስ ቅራዓን አንፃር ምን መልክ እንዳለው ሳጠና ከገረመኝ ነገሮች አንዱ የሰዎች መልክ(የቆዳ ቀለም መለያየት) ምክንያት ምን እንደሆነ ያገኝውት ምላሽ ነው፡፡
"መልካችን የተለያየው፣ የቆዳ ቀለማችን አንድ
ያልሆነው አደም የተፈጠረበት አፈር አንድ ዓይነት ባለመሆኑ ነው።"ይላሉ
“አላህ አደምን ከወሰዳቸው የምድር አፈር አይነቶች ኹሉ ፈጠረው፡፡ የአደም ልጆችም በዚህ የምድር አፈር አይነት (መልክ) የተለያዩ ሆነው መጡ፡፡ ከነሱም ውስጥ ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ በዚህ መሀል የሆነም በመሆን መጡ...” (አቡ ዳዉድ 4695፣ ቲርሚዚይ 2955)

ፍልስፍናን እወዳለሁ' የሚል ግለሰብ እንደ ሃይማኖት ጠይ፣ በሌላ በኩል ሃይማኖቴን እጠብቃለው የሚለው ደግሞ ጥበብ የማይወድ፣ ፍልስፍናን' የሚሸሽ ወይንም ሊጠየቁ እና ሊመረመሩ ያልተገቡ እሳቤዎችን “አሜን” ብሎ የተቀበለ ሞኝ አድርጎ ሲወሰድና ሲታሰብ አይገባውም፡፡ ስህተት ነው። ዓማኝ መሆን ፍልስፍናን ከመውደድ የሚያግድበት አንዳችም ምክንያት የለውም፡፡ እንዲሁም አንድ ግለሰብ የፍልስፍና ወዳጅ ሰለሆነ ብቻ ኢ-አማኝ እና እምነትን የጅሎች መጫወቻ ካርድ አድርጎ የሚቆጥር ነው ብሎ መውሰድም ተገቢ አይደለም፡፡እንዲሁም ኢ-አማኝ ስለሆነም ምግባረ - ብልሹ ነው ተብሎ ሊታሰብ አይገባውም።
@zephilosophy
@zephilosophy
የፍልስፍና ምንነት
ፍልስፍና የሰው ልጅ አካባቢውንና የራሱን ማንነት የሚረዳበት መንገድ ነው፡፡ ግምታዊ፣ ባህላዊ፣ ሳይንሳዊ ወይም ሐይማኖታዊ ከሆነው የግንዛቤ መንገድ በተለዬ ሁኔታ ነገሮችን ለመረዳትና ለመግለጽ የሚረዳ የእውቀት አይነት ነው ።
ከዚህ በተጨማሪ ፍልስፍና የምንለው የሰው ልጅ ማወቅ የሚፈልገውን ነገር ሙከራ ሣያደርግ፣ ልኬትንና ስሌትን ሣይጠቀም በህሊናዊ የመረዳትና የማመዛዘን ሁኔተ ብቻ ተጠቅሞ ነገሮችንና ሁኔታዎችን ለማወቅ የሚያስችለው መንገድ ነው::
የፍልስፍና እውቀት የተመሠረተው በህሊና የመገንዘብ አቅም ላይ ነው፤ በአጭሩ የፍልስፍና እውቀት ህሊናዊ እውቀት ነው፡፡ ህሊናዊ እውቀት የሚገኘው ደግሞ በህሊናዊ ተግባር (rational enterprise) ነው፡፡
በህሊናዊ ተግባር እውነትን ከሀሰት፣ ትክክል የሆነውን ስህተት ከሆነው መለየት የሚያስችለን አዕምሯዊ ሥራ ነው፡፡ አዕምሮ ሠራ የምንለው መጠየቅ ሲጀምር ነው፡፡ ሲመራመር ነው፤ እውነትን ሲፈልግ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ህይወቱን የሚመራ ሰው ፈላስፋ እንለዋለን፡፡
ሚለር ተመሣሣይ ሀሳብ አላቸው::
“ፍልስፍና ህሊናዊ ተግባር በመሆኑ በአመለካከቶቻችን ሥር ሊኖሩ የሚችሉ ድንቁርናን፣ ጭፍን አምላኪነትን፣ ወገንተኛነትን፣ የሌሎችን ሀሳብ በጭፍን መከተልን ፤ አዕምሮቢስነትን ለማስወገድ ይሻል።የምንከተላቸው ሀሳቦቻችን መጠየቅ ፤ መመርመርና በማስረጃና በአመክንዮ መደገፋቸውን መፈተሽ ያስችለናል።
ፍልስፍና እውነትን ይፈልጋል፣ ትርጉምን ይፈልጋል፣ ሰው እየኖረበት ያለውን የኑሮ ዘይቤውን ጠንካራና ደካማ ጐኑን፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን፣ መልካሙንና መጥፎውን ለመለየት ዕለት ዕለት ይፈልጋል፡፡ ፈላስፋም ፍለጋ ካልወጣ የኖረ ያህል አይሰማውም፤ ህሊናው እውነትን በመፈለግ ሱስ የተለከፈ ነው፤ ለፈላስፋ መኖር ማለት እውነትን ማወቅ ማለት ነው፡፡
ለዚህ ይመስላል ሜሪ ግሬስ (Mary Grace) የተባሉ ፈላስፋ የካቫኑ (John F.. Kavanaugh) የሚለውን ጽሑፍ ተመስርተው የሚከተለውን ለመናገር የተገደዱት፡፡
"ፍልስፍና ሰዎች ደስ ብሏቸው እንዲኖሩ መነቃቃት ይፈጥርላቸዋል፤ ብዙ መጠየቅ፣ መመለስ፣ መረዳት፣ መማር ያለብህ ነገር አለ በሚል አስተሳሰብ ተገፋፍተው መኖር እንዲችሉ ያደርጋቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምንም እንኳ ሥቃይ የሚፈጥሩ ፈተናዎች በየመንገዱ ላይ ቢኖሩም ፍልስፍናን መከተልና መያዝ ዋጋው ከፍ ያለ፣ አስደሳች፣ ህሊና የሚሰጠው ሃሴትም ተወዳዳሪ የሌለው ነው፡፡
የፍልስፍናን ምንነት ለመረዳት ባደረግሁት ጥረት በብዙ ነገር ብስለትን (ዕድገትን) እንደጨመርሁ አምናለሁ፤ እናም ራሴን ከፍልሰፍና ውጭ አደርጌ ማሰብ የማልችል ነገር ሆኖብኛል፡፡"
ትለናለች
ለመሆኑ ፈላስፋ ምን አይነት ባህሪ አለው?
ይቀጥላል

የፈላስፋ ህይወት በምን ይገለፃል?
የአማርኛው መዝገበ ቃላት “ፈለሰፈ” እንዲሁም “ፍልሰፋ” የሚሉትን ቃላት ልዩ ልዩ ብልሃትንና ጥበብን ከአእምሮ እያመነጨ አስገኘ፣ ያልነበረውን የጥበብ ሥራ ፈጥሮ አገኘ፣ ያልተገለጠውን (ያልታወቀውን) እንዲታወቅ አደረገ፣ ጥበብን(እውቀትን) ወደደ በማለት ትርጉም ሰጧቸዋል፡፡
የሚከተሉት ባህሪዎች ደግሞ ፈላስፋዎች የሚኖሩትን ህይወት ሊያመለክቱ የሚችሉ ዋና ዋና መገለጫዎች ናቸው።
1.ፈላስፋዎች የእውቀት ሱሰኞች ናቸው፤ አዲስን ነገር ለማወቅ የተራቡ ናቸው:: ነጋም መሸም ያው ነው - እውቀትን መፈለግ የጊዜ ገደብ የለውም፡፡ ለፈላስፋ ጊዜ፣ ቦታ፣ ሁኔታ እውቀት ማስገኘት አለባቸው፡፡ ለፈላስፋ እውቀት በልተው የማይጠግቡት የሚጣፍጥ ምግብ ነው፣ ጠጥተው የማይረኩት ጣፋጭ ወይን ጠጅ ነው፡፡ ሰዎች፣ ተፈጥሮ. ሌላም ሌላም... እግዚአብሔርም ይሁን ለፈላስፋ ሁሉም እውቀት ናቸው፡፡ ተፈጥሮ የያዘችው የሚያስደምም ህብርና ሥርዓት ምስጢር ማወቅ ጉጉታቸው መጠን የለውም፡፡ የሰውን ግላዊ፣ ማኅበራዊና ተፈጥሯዊ ማንነቱን፣ ተስፋውንና ጭንቀቱን ለማወቅ ሥሥት ያደረባቸው ናቸው፡፡ ፈላስፋ ለማንም አይገዛም ቢባል የተጋነነ አይሆንም፣ ግለ - ታሪካቸው ይመስክራልና፡፡ ነገር ግን ለማንም የማይረታው ልቦናቸው ለአንድ ነገር ተሸናፊና ባሪያ ነው - ለእውቀት!
2.ፈላስፋዎች ሌላው የሚታወቁበት ነገር ለሰው ልጅ እጅግ አሳቢዎች መሆናቸው ነው:: ከማንም በላይ ህብረተሰብ የሚሠቃይባቸው ችግሮች ይሰማቸዋል፡፡ ህብረተሰብን ለከፋ ህመም የዳረጉ ቁስሎች እነርሱንም ይጠዘጥዛቸዋል፡፡ ህብረተሰብ ገመናውን በይስሙላ ከበሮችና ወዳሴዎች መሸፈኑ ያንገበግባቸዋል፡፡ ለፈላስፋ የሰው ልጅ በእውነተኛ ማንነቱ መኖር እስካልቻለ ድረስ ህሊናቸው ረፍት አያገኝም፡፡ ሰው ተስፋ ያጣበት ነገር ፈላስፋን አንገቱን ያስደፋዋል፤ ከትካዜውም አይመለስም፡፡ ፈላስፋ ሰው ከሀዘኑ፣ ከጭንቀቱ፣ ከችግሩ የሚያወጣ እውቀት እስካላገኘ ድረስ የሚበላውን፣ የሚለብሰውን፣ የሚኖርበትን፣ ወዘተ እስኪረሳ ድረስ በሀሳብ ይናወዛል፡፡
የሰው ልጅ ተስፋ ማጣት ጩኸት በቀንም በሌሊትም በጆሮው ያቃጭልበታል፣ «ምን ልሁን? ተስፋ ቆረጥሁ፣ ታደገኝ እያለ የሚጠራው ይመስለዋል፤ ነፍሱ በህዝቡ ሰቆቃ መሃል ሁና ትዋትታለች፡፡ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓቶች በሰው ልጅ ላይ የሚያደርሱት በደል መታገስ የሚችልበት ጉልበት የለውም - ነፍሱ ከተበደሉት ጋር ናት - ሲያለቅሱ ታለቅሳለች፣ ሲታራዙ፣ ሲራቡ፣ ሲሰደዱ አብራቸው ትሰደዳለች፡፡
3.ፈላስፋነት አማጺነት ነው፡፡ፈላስፋ መጥፎ ሥርዓት ላይ አማጺ ነው፡፡ ተፈትኖና ተመርምሮ ባልተረጋገጠ አስተሳሰብና እምነት ጋር አብሮና ተመሣስሎ ላለመኖር እንቢተኛ ነው፡፡ በአጓጉል ማኀበራዊ ሥርዓቶች ተጨፍልቆ ላለመኖርና ራሱን ነፃ ለማውጣት ይጥራል፣ በራሱ ህሊና ለመምራትና የራሱን ማንነት ይዞ ለመገኘት ህሊናው በማይቀበላቸው እምነቶችና አስተሳሰቦች ላይ ያምፃል፡፡ ህሊናውንና ማንነቱን አሳልፎ ሳይሰጥ በተረዳውና በአመነው ነገር ላይ ብቻ ህይወቱን ለመምራት የስብዕና ጥንካሬ ያለው ፈላስፋ ነው፡፡
4.ፈላስፋ ራሱን የሚቀድስ ሰው ነው፡፡ ግለሰቦችና ማኅበራዊ ሥርዓቶች ከሚያደርሱት በደል ራሱን በእውቀት እያበቃ ተካፋይ ላለመሆን የእውነት መንገድን እየፈለገ የሚኖርና ከህብረተሰብ እድፍ ራሱን የሚያነፃ ፈላስፋ ነው፡፡ ስሜታዊነትን፣ አድሏዊነትንና ወገንተኛነትን ከህይወቱ በማስወገድ ስብዕናውን የሚቀድስና በእውቀት የቅድስና ህይወት መኖር የሚችል ፈላስፋ ነው፡፡ፈላስፋ ምድራዊ ለሆነው ማንነት (ለሥጋዊ ደስታ፤ ለክብር፣ ለዝናና ለሐብት) ብሎ ህሊናውን የማይሸጥ እና ላመነበት ነገር እስከ ሞት ፅዋ ድረስ የሚጋፈጥ ነው።
ረ/ፕሮፌሰር ዋለልኝ እምሩ

“የተነገራችሁን ሁሉ በቀጥታ እንደወረደ አምናችሁ አትቀበሉ፡፡ ከዚያ ይልቅ እውነትን በብልሃትና በንቃት ለማግኘት ሞክሩ፡፡ እውነት ሁልጊዜ ተሞክሮ ነው፡፡ የኔ እውነት የእናንተ ሊሆን አይችልም፤ እውነትን ልንጋራው አንችልም፡፡ እኔ የምሰጣችሁ ግንዛቤ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ እያንዳንዱ ሰው እውነትን ደጋግሞ በራሱ ማግኘት አለበት፡፡ ስለሆነም ለመመራመር፣ ለመጠየቅ፣ ለመሞከር ፣ለመተገበር ትጉ፡፡”
ኦሾ
@zephilosophy
ኦሾ
@zephilosophy
ብቸኝነትን የመረጥኩት....
ካህሊል ጂብራን
"ከአለም ተነጥለህ ብቻህን ለመኖር እንዴት መረጥክ ?"
ብዬ ጠየኩት
በሀሳብ ተውጦ በዝምታ ከቆየ በኋላ እንዲህ አለ
‹‹በፍጥረቶቹ መካከል እየኖርኩ እግዚአብሔርን ማምለክ እችል ነበር፤ ማምለክ ለብቻ ተነጥሎ መኖርን አይጠይቅምና! ሰዎችን የተውኳቸው እግዚአብሔርን ለማግኘት ስል አልነበረም፡፡ በአባትና በእናቴ ቤት ሆኜም አገኘው ነበር፡፡ ከሰዎች የተገለልኩበት ምክንያት ተፈጥሯቸው ከእኔ ተፈጥሮአዊ ባህርይ ጋር ስለተጋጨ እንዲሁም ህልማቸው ከህልሜ ጋር ባለመስማማቱ ነው፡፡
‹‹ብቸኝነትን የፈለግሁት ራሳቸውን ሽጠው በተመሳሳይ ዋጋ በመንፈሳዊም ሆነ በቁስ አካላዊ መስፈርት ከእነሱ ያነሰች ነገርን የሚገዙ ሰዎችን ፊት ላለማየት ስል ነው...
‹‹ብቸኝነትን የፈለግሁት የዕውቀትን መንፈስ በህልሞቻቸው ውስጥ አይተው ግባቸውን እንደመቱ ከሚያምኑት ከእነዚያ በራሳቸው ከሚረኩት ሰዎች እራሴን ለመሸሸግ ስል ነው...
‹‹ከማህበረሰቡ የሸሸሁት እውነትን ባያዩም መንፈሱን ባይገነዘቡትም እና ለዓላማቸው መሳካት ሲሉ ብቻ የእውነትን ፍሬ ነገር ሙሉ ለሙሉ እንዳገኙት አድርገው ከሚለፍፉት ለመራቅ ነው::
‹‹ከዓለም ተነጥዬ ብቸኝነትን የፈለግሁበት ምክንያት ትህትናን ደካማነት፣ ምህረትን ፍርሃት፣ ትምክህትን ደግሞ የጥንካሬ መገለጫ እንደሆነ አድርገው የሚያምኑትን ህዝቦች በይሉኝታ መቅረቡ አሰልችቶኝ ነው፡፡
‹ብቸኝነትን የመረጥኩት ነፍሴ ከነዚያ ፀሐይ፣ ጨረቃ እንዲሁም ከዋክብት በገንዘብ ካዝናዎቻቸው ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ እንደማይወጡና በእነሱ የአትክልት ስፍራዎች ውስጥ ካልሆነ በስተቀር እንደማይጠልቁ ፅኑ እምነት ካላቸው ጋር አብሮ መኖሩ ስላንገፈገፈኝ ነው...
‹‹እናም በዓይኖቻቸው ላይ ወርቃማ አቧራ እየጨመሩና ጆሮቻቸውን ትርጉም አልባ በሆኑ ወሬዎች እየሞሉ የህዝቦችንን ምድራዊ ዕጣ ፈንታ ከሚበጠብጡት የስልጣን ጥመኞች ሸሸሁ
‹‹እንደስብከታቸው የማይኖሩትን እና ህዝቦችን እነሱ የማይፈጽሙትን ነገር እንዲያደርጉ የሚመክሩትን (የሚያስገድዱትን) ቀሳውስት ለመሽሽ ስል ትቻቸው ሄድኩ...
‹‹ሰዎች ስልጣኔ ብለው የሚጠሩትን ትቼ እዚህ የምኖረው ስሮቹ መሬት ስር ተሸሽገው የተቆላለፉ ቅርንጫፎቹ ከደመናው በላይ ከፍ ብለው ፈክተው፣ የበቀሉት አበቦቹ ግን ስስት፣ ክፋት እና ሰቃይ የሆኑ ብልሹ የሆነ ጠንካራ አስቀያሚ ዛፍ ሆኖ ስላገኘሁት ነው፡፡
‹‹ብቸኝነትን የፈለግሁት እዚህ በውስጡ ለመንፈስ፣ ለልብና ለአካል የሚሆን ሙሉ ህይወት ስላለ ነው:: እናም የፀሐይ ብርሃን የሚያርፍባቸውና መጨረሻ የሌላቸው አበቦች መዓዛቸውን ወደ ህዋ የሚተነፍሱበት እንዲሁም ጅረቶች እያዜሙ ወደ ባህር የሚያቀኑበትን የሳር መስክ አግኝቻለሁ፡፡ የፀደይ ወራትን ትኩስ ግንዛቤ፣ የክረምትን ቀለመደማቅ ናፍቆት፣ የመኸርን ጣፋጭ መዝሙሮች እና የበጋ ወራትን ውብ እንቆቅልሽ ያገኘሁባቸውን ተራሮች ደረስኩባቸው፡፡ ወደዚህ ርቆ ወደሚገኝ ግዛት የመጣሁት የዓለምን ሚስጥሮች ለማወቅ ስለተራብኩ ነው፡፡
Book: Between night and morn
Author :Khalil Jibran