tgoop.com/Zephilosophy/1103
Last Update:
2.ሌላኞቹ የተፈጣሪያዊነት አንድ አካል ተደርገው የሚቆጠሩት፣ ከ970 በኃላ ብቅ ያሉት ያንግ ኅርዝ ክሬሽኒስቶች(Young Earth Creationists) ናቸው። እነዚኞቹ እንደሚሉን ደግሞ የምድርን ሆነ በውስጧ ያሉ ፍጥሮችን ልደት እናከበራለን ካልን ከስድስት ሺህ የማያንስ፣ ከአስር ሺህ የማይበልጡ ሻማዎችን ማዘጋጀት አለብን፡፡ “የዩኒቨርስንም አብረን ማክበር አለበንና እድሜው ስንት ይሆን?' ብለን ከጠይቅናቸው፣ ከመካከላቸው ግማሾቹ እኩል እድሜ አላቸው ሲሉን ሌሎቹ በበኩላቸው ዪንቨርስ ትቅድማለች ይላሉ፤ ኾኖም የእድሜው ስሌት ግን ከ10 ሺህ በላይ እንደማይገፋ በሁለቱም ጎራ ያሉ ተከራካሪዎች ማንሳታቸው አይቀሬ ይሆናል። አሁን ያለችው ምድር ሆነ በውስጧ የያዘቻቸው ፍጡራን ቀድሞ በዘፍጥረት የመጀመሪያ ምዕራፎች ላይ የተፈጠሩት ናቸውን?' ብትሏቸው፣ ምላሻቸው አይደለም የሚል ነው፡፡ ለዚህ ምላሻቸው እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ኹነት ኢዩሱስ ወደ ምድር ሳይመጣ ከ2000- 3000 አመታት በፊት የተከሰተው የጥፋት ውሃን ነው፡፡ ከጥፋት ውሃ በኃላ ምድር እንደገና እንደ አዲስ ተፈጥራለች ማለት ይቻላል ይሉናል የዚህ እሳቤ(እምነት) አራማጆች፡፡ ጨምረውም ከጥፋት ውሃ በፊት የነበሩ፣ ነገር ግን ከኖህ መርከብ ላይ ሳይሳፈሩ የቀሩ ፍጡራን በሙሉ ጠፍተዋል ይሉንና፣ ዛሬ ላይ የሚገኙት ቅሪተ አካሎች አብዛኞቹ በዛን ወቅቱ የተቀበሩ ናቸው የሚል ድምዳሜያቸውን ያቀርቡልናል፡፡
3.ስለ ተፈጣሪያዊነት ያነሳነውን ሐሳብ የምናጠቃልለው በቅርብ ብቅ ያለውን ኢንተለጀንት ዲዛይን ክሬሺዝም (intelligent Design Creationism) አራማጆች ምን እንደሚሉን በማንሳት ይሆናል። የእዚህ እሳቤ አራማጆች እንደሚሉት የፀሐይ ዙረት ሥርዓት ጅማሬን እንዲሁም የፍጥረተ ዓለሙ እድሜ እና ዘመን ማስቀመጥ የሚቻል በፍጹም አይደለም። ስለዚህ ጉዳይ በቂ እውቀት የሆነው አዋቂ በሆነ አበጂ ኹሉም የተፈጠረ መሆኑን መረዳት ብቻ ነው። እንዲሁም የሕይወት ውስብስብ ኹደትን ከተመለከትን፣ የፍጥረተ ዓለሙ አፈጣጠር የታስቦት እና የታቅዶት ውጤት መሆኑን እንጂ የተፈጥሮ ምርጫ ፅንስ ሐሳብ እንደሚለው እንዳልሆነ እናውቃለን የሚል ድምዳሜ አላቸው፡፡ ታዲያ ፍጥረተ ዓለሙ በተነደፈለት ሥርዓት ሊጓዝ የሚችለው ኹሉም ፍጥረት የተፈጠረበትን ዓላማ ሲያሳካ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ይኽም የሚያሳየን በተፈጥሮ ምርጫ አሊያ በዝግመተ ለውጥ ፅንስ ሐሳብ መሰረት የተፈጠረ ፍጡር ሆነ የፍጡራን አካል አለመኖሩን ነውም ይላሉ፡፡ ይህን ድምዳሜያቸውን irreducible complexity ብለው ይጠሩታል፡፡
ቀጥሎ ደግሞ ስለ ዝግመተ ለውጥ እሳቤዎች እናያለን
@zephilosophy
BY ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
Share with your friend now:
tgoop.com/Zephilosophy/1103