tgoop.com/Zephilosophy/1102
Last Update:
እንዴት እና ከየት መጣን?
.....የቀጠለ
1.ኦልድ ኀርዝ ክሬሽኒስቶች (Old Earth Creationists) እንደሚሉን ከሆነ ምድርን ጨምሮ ኹሉን የፈጠረው ፈጣሪ መሆኑ እርግጥ ኾኖ እድሜያቸውን በተመለከተ ግን የሥነ-ምድር ተመራማሪዎችን (geologist) እና
የሥነ-ፈለክ አጥኚዎች (astronomer) የሚያስቀምጡልንን ቁጥር ብንቀብል ይበጃል። ኦልድ ኀርዝ ክሬሽኒስቶች በአንድ ረድፍ አይቀመጥም፤ በሶስት እንጂ፤
የመጀመሪያው የ ዳግም ተፈጣሪያዊነት' (Gap or Restoration creationism) ሲሆን፣ እነዚህም ምድር ከባዶ አሊያም ከምንም አይደለም የተፈጠረችው፤ መጀመሪያ ቀድሞ ከነበረ እና ካረጀ ምድር ነው ተሻሽላ የመጣቹ የሚል ነው፡፡
በሁለተኛ ረድፍ የሚቀመጡት የቀን ቆጣሪ ተፈጣሪያዊነት (Day Age creationism) ተብሎ ሲጠራ፣ ይኽም የመጽሐፍ ቅዱስን ስድስቱ ቀናቶች በ24 ሰዓት አቆጣጠር መለካት ትልቅ ስህተት ነው የሚል ድምዳሜ አለው፡፡ አንዱ ቀን ሚሊዮን አሊያም ቢሊዮን ዓመት ሊሆን ይችላል ስለሚል የሚል መከራከርያ አለው፡፡ በዚህ ረድፍ የሚቀመጡት አራማጆች ይህን ለማለት ካስቻላቸው መሰረቶች ዋነኛው በአይሁዶቹ የዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ ያለው “ዮም "(ከአማርኛው ላይ ቀን እየተባለ የተገለጸው) የሚለው ቃል የትርጉም እኩሌታ ዘመን አሊያም ርዝመቱ የማይታወቅ "ጊዜ" የሚለው መሆኑ ነው
በመጨረሻ ረድፍ የሚገኝው (አቀማመጡ የጸሐፊው ኾኖ) “የተሸጋጋሪ ተፈጣሪያዊነት (progressive creationism) ነው፡፡ ይህን እሳቤ የሚከተሉት በበኩላቸው እንደሚሉት ተፈጥሮ አሁን የያዘውን ይዘት እና ቅርጽ ያገኝችው በአንዴ ጊዜ አይደለም፤ ኹደቱ ረጅም ዘመናትን የፈጀ ነው፡፡ ታዲያ ይህ በፈጣሪ ፍቃድ የተደረገ መሆኑ በፍጹም እንዳይረሳ ይሉናል።
ይቀጥላል...
@zephilosophy
BY ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
Share with your friend now:
tgoop.com/Zephilosophy/1102