ZEPHILOSOPHY Telegram 1092
"መብራቱን ይዛችሁ ጨለማው የት እንደሚገኝ ትፈልጋላችሁ።"
ኦሾ
..የቀጠለ

ብርሃን ሲኖር ጨለማ ይጠፋል፡፡ ጨለማ ጨርሶ የለምና የሚጠፋው ጨለማ አይደለም፡፡ ጨለማ የብርሃን አለመኖር ነው፡፡ የራስ ኩራት(የበላይነት ስሜት) ልክ እንደ ጨለማ ነው፤ ጨርሶ የለም፡፡ የራስ ኩራት የንቃት አለመኖር ነው፡፡

ስለዚህም ተመልከቱት እንጂ አጥፉት አልልም፡፡ ተመልካች፣ አስተዋይ ሁኑ. . .
ፖለቲከኛ ጭው ያለ የራስ ኩራተኛ ነው፤ ቅዱስ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው በጣም የባሰ የራስ ኩራተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ፖለቲከኛው በቀላሉ ሊታወቅ ይችላልና ቅዱሱ ከፖለቲከኛው የበለጠ አደገኛ ነው፡፡

የእኔ ጠቅላላ የህይወት ተግባር የሰውን መሰረታዊ ችግሮች ፈልጎ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡ የሰውን መሰረታዊ ችግሮች አንዴ ካወቅን መፍትሄ መፈለጉ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡
እኔ መሲህ ነኝ፣ እኔ አቫትራ ነኝ አልላችሁም ምክንያቱም እነዚህ የራስ ኩራት ወይም ራስን ከፍ የማድረግ ጨዋታዎች እንደሆኑ አውቃለሁ፡፡ እኔ እንደማንኛውም ሰው ተራ ወይም እንደ ማንኛውም ሰው ፍፁም ልዩ ነኝ፡፡

በህልውና ውስጥ አንዷ የሳር ሰበዝ ከትልቋ ኮከብ ጋር እኩል ጠቀሜታ እና ውበት አላት፡፡ በህልውና ውስጥ ተዋረድ የለም፡፡ ከፍተኛና ዝቅተኛ ብሎ ነገር የለም፡፡ እኔ ማንንም አልቃወምም፡፡ ነገር ግን የእኔ ዋና ስራ በሽታዎችን፣ እንቅፋቶችን በሙሉ ገልጦ ማሳየት ነው፡፡ ስለዚህም በእነዚህ ሳንካዎች አትያዙም፤ ነፃ ትሆናላችሁ ፤ ያለ ምንም እንቅፋት ከህልውና ጋር ትዋሃዳላችሁ፡፡ አንደኛው እንቅፋት ደግሞ ራስን ከፍ አድርጐ መመልከት ነው፡፡ እንደሚያታልላችሁ ካልነቃችሁ በብዙ መንገድ ይመጣባችኋል፡፡ እንደ ጥላ ጠንክሮ ሊከተላችሁ እና ነቅታችሁ ላታዩት ትችላላችሁ፡፡

በርግጥ ልታስወግዱት ከታገላችሁ እየጠነከረ ይሄዳል።ከአንድ ነገር ጋር ስትታገሉ የሚከሰተው ይህ ነው:: ወሲብ ሊሆን ይችላል፤ኢጎ ሊሆን ይችላል፡፡ ከመታገል በቀር ምን ልታደርጉት ትችላላችሁ? በሃይል ትገፉታላችሁ፤ ነገር ግን ወዴት ነው የምትገፉት የበለጠ በገፋችሁት ቁጥር የበለጠ ወደ ውስጣችሁ ይገባል ወደ ድብቁ ህሊና ጠልቆ የገባ ደግሞ ከንቃት ህሊና የበለጠ ሃይል አለው:: ድብቁ ህሊና ከንቁው ህሊና በዘጠኝ እጅ ይበልጣል፡፡ በንቃተ ህሊናችሁ ውስጥ ቢያንስ ምን እንዳለ ታውቃላችሁ:: ድብቁ አዕምሯችሁ ግን ጨለማ በመሆኑ በውስጡ ምን እንዳለ አታውቁም፤ ይሁንና ከንቁው ህሊና ዘጠኝ እጅ የሚልቅ ሃይል አለው፡፡ በማንኛውም ቅፅበት ንቁው ጥረታችሁን ሊውጠው ይችላል፡፡

ይህን ንቃት ነው የማስተምራችሁ:: ከራስ ወዳድነት፣ ከብስጭት፣ ከቅናት፣ ከጥላቻ ጋር አትታገሉ፡፡ ሃይማኖቶተኞች «ታገሏቸው፣ አጥፏቸው፣ ግደሏቸው፤ ጠላቶቻችሁ ናቸው›› እያሉ ይሰብኳችኋል፡፡ ልትገድሏቸው አትችሉም፣ ልታጠፏቸው አትችሉም፣ ልትታገሏቸው አትችሉም - በንቃት ልትመለከቷቸው እንጂ፡፡

ንቁ በሆናችሁ ቅፅበት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይጠፋሉ፡፡ በብርሃን ውስጥ ጨለማ አይኖርም፡፡

@zephilosophy

tgoop.com/Zephilosophy/1092
Create:
Last Update:

BY ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

Share with your friend now:
tgoop.com/Zephilosophy/1092

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

The SUCK Channel on Telegram, with a message saying some content has been removed by the police. Photo: Telegram screenshot. Users are more open to new information on workdays rather than weekends. Choose quality over quantity. Remember that one high-quality post is better than five short publications of questionable value. The imprisonment came as Telegram said it was "surprised" by claims that privacy commissioner Ada Chung Lai-ling is seeking to block the messaging app due to doxxing content targeting police and politicians. The optimal dimension of the avatar on Telegram is 512px by 512px, and it’s recommended to use PNG format to deliver an unpixelated avatar.
from us

Telegram ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
FROM American