tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5222
Last Update:
📌 ድንግልና ለምን "ዓይን" እንደተባለ የሚያውቅ ማን ነው ❓
❖ ድንግልና የአንድን ሰው ማንነት እስከ መወሰን ወይም ገልጦ እስከ ማሳየት የሚደርስ መሠረታዊ ምሥጢር እንድትይዝ ሆና በመፈጠሯ አይደለምን ? ዓይን ታያለች እርሷም ትታያለች፡፡
❖ አንቺ ሴት ከጋብቻሽ በፊት ድንግልናሽን ያጠፋሽው ከሆነ ስታገቢ ባልሽን በምን ታዪዋለሽ ? ድንግልና "ዓይን" ተብላለችና፤ ባልም ድንግልናውን ጠብቆ ካልኖረ ረቂቅ መነጽር ድንግልና የለውምና ሚስቱን በምኑ ይመለከታታል? ዛሬ ዛሬ ብዙ ባልና ሚስቶች በጥቃቅን አለመግባባቶች ለአንድ ቀን እንኳን ተያይተው የማያውቁ ያህል የሚሆኑትና የሚኳረፉት ምናልባት ድንግልናን መጠበቅ ስለቀረ ሕገ እግዚአብሔርም እየፈረሰ ስለመጣ ይሆን ? በማለት መጠየቅ አስተዋይነት ነው፡፡
❖ ድንግልና ሁሉን አርቆ የሚያሳይ ከፍተኛ ቦታ ነው፤ የኑሮ ደረጃቸውን በድንግልና ሆነው መርምረውና ተመልክተው ያገቡ ሰዎች አይጸጸቱም ማለትም አንድ ሰው ደረጃው ማግባትም ይሁን መመንኮስ በሚገባ ለይቶ ማወቅ የሚችለው ንጽሕናውን ጠብቆ ለመኖር ከቻለ ብቻ ነው፡፡
❖ መጽሐፍ ቅዱስ "የሰውነት መብራት ዓይን ናት፡፡ እንግዲህ ዓይንህ ጤናማ ብትሆን ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል ይላል፡፡
📖 ማቴ 22፥23
❖ እንደዚሁም ሁሉ በዓይን የተመሰለች ድንግልናም በሕገ ወጥነት በዝሙት ሥራ ከጠፋች አንደ ሰው ሰውነቱ ሁሉ እንደጨለመበት ሊያምን ይገባዋል፤ ምክንያቱም ድንግልና ሃይማኖትና ምግባር መሠረታቸውን ለቀው እንዳይናጉ የሚያደርግ ጽኑ መሠረት ነውና፤ ማለትም አመለካከት ፣ አነጋገርና አሠራር ሚዛናቸውን እንዳልሳቱ ከድንግልና አጠባበቅ አንጻር መናገር ይቻላል፤ ስለዚህ ድንግልና "ዓይን" ቢባል ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም፡፡
❖ ብዙ ጊዜ ድንግልና ለሴቶች የሚነገረው በጉልህ ምልክት የሚታወቀው በእነርሱ ስለሆነ ነው፤ ነገር ግን ድንግልና ለወንዶችም የጸና ተጠቃሽ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ "ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው ፣ ድንግሎች ናቸው" በማለት ከትቦ ይዟል፡፡
📖 ራዕ 14፥4
🔔 ንስሀ ግን የወደቁትን ታነሳለች ቀማኛውን መጽዋች፣ ዘማዊውንም ድንግል ታደርጋለች
📌 አዘጋጅ
® ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ
📌ምንጭ
✍️በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ
📚ሕይወተ ወራዙት
✍ "አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፤ ስለዚህ ተማር ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለና፤ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፤ አንድ ቀን ወደ ንስሐም ትመራሃለች"
📘ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
BY መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
Share with your friend now:
tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5222