Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
Forwarded from Mitik Tesfaye
Forwarded from Mitik Tesfaye
Forwarded from Mitik Tesfaye
በመነን የሃገር ባህል ልብስ
ሽፎኖች
አፍሪካ ጨርቅ
ከፋይ
የፈለጉትን ዲዛይን መርጠው ማዘዝ ይችላሉ

ለማዘዝ በዚህ ስልክ ይደውሉ:-
0923251317 ምትክ ዲዛይን
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ ማስተላለፉ ተገለጸ

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

ምንጭ የኢኦተቤክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
#ኪዳነ_ምህረት_እጠራሻለሁ

በኃጢአት ብወድቅም ባንቺ እነሳለሁ
ስላለሽ ኪዳነ ተሰፋ አደርጋለሁ
ገብቶልሻል ኪዳን ኪዳነምህረት
ባንቺ ምልጃ ሊምር ይህን ሁሉ ፍጥረት
በአንቺ ንፅህና ዓለሙን ታርቆታል
ያንቺን ስጋ ለብሶ እኛን አድኖናል
ባጠባሸው ጡትሽ ማር በይው ይማረን
አሳስቢው ድንግል ሆይ ረሃብ ጥምሽን
ዛሬም ይምረናል በሰጠሽ ኪዳን
ከእግርሽ ስር ወድቀናል ድንግል አሰታርቂን
ኪዳን ቃልኪዳንሽ ዘውትር ይጠብቀን።
                   
                 ከእህተ ማርያም  
     


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
#የሰማዩን_ምስክር


ጨለማን ሰባሪ_ብርሃን ወጥቶብሻል
ሞትን የሚገድል_ትንሳኤን ወልደሻል
ንጽሕ መሶበ ወርቅ_ ድንግል ተብለሻል
ለከበረው ክብርሽ_ስግደት ይገባሻል።

የሰማዩ ምስክር_ የታየው በራማ
በምድራዊው ገነት_ እነሆ ተሰማ
የመልአኩን ብስራት_ኤልሳቤጥ ስትደግመው
በሆዷ ያለው ጽንስ_ ደስታ አዘለለው
መጥምቀ መለኮት_ክብሩ ከፍ ያለ ነው።

ለኛ ስለሰጠች _ የሕይወት እንጀራን
ሁሌም ለዘለአለም_ እንወዳታለን
የምስራቋ ደጃፍ_የወለደች ፀሐይ
የኤልሳዕ ማሰሮ_ የበረከት ሲሳይ።

የፍቅር የሰላም _ የምሕረት መገኛ
የምንመካብሽ _ ነይ ነይ ወደ እኛ
ናርዶስ ቀሲመታት_ በጎ መዓዛ ነሽ
የአማኑኤል ማደሪያ_ የለም የሚመስልሽ።

ጌታዬ ከሰጠኝ_ እናቴ እልሻለው
የመንገድ ስንቄ ነሽ_ እመካብሻለው
ለጠየኩሽ ሁሉ _ መልስ የምትሰጪኝ
እንዳልነዋወጥ_ በዐለቱ ትከይኝ።

በመከራ ጊዜ _ መሸሸጊያ ሆኖን
የመከራን ባሕር_ በፍቅሩ አሻግሮን
እንደበደላችን_ ሳያጠፋን ጌታ
አቆመን በደጁ_ ሞልቶን በእልልታ።

ከኛ የበረታችሁ _ አስቡን በጸሎት
በስጋ ፈተና _ እንዳይገለን ምቾች
በሄድንበት ሁሉ_ እንዲገጥመን ሰላም
ፍፃሜአችን እንዲያምር_አማልጅን ማርያም።

የተሰቀለውን _በገና  አውርዱ
መሰንቆ ክራሩን_ ከበሮ አሰናዱ
መቋሚያ ጽናጽል_ ይታደል ለሁሉም
በያሬድ ውብ ዜማ_በሚያስረሳ ዓለም
ተነሱ እንዘምር_ ለመድኃኒዓለም።

እንዲህ እናምናለን_ እንታመናለን
በተበተንበት በባዕዱ ምድር_ እንመሰክራለን
የሥላሴን ጥበብ_ ትውልድ እንዲረዳ
ይምጣና ይመገብ_ ከእናቱ ጓዳ
ኋላ ለጥያቄ እንዳይሆን_ እንግዳ ትጉኃን

በዝማሬው ጣዕም_ተሞልተን ደስታ
በተዋሕዶነቷም _ ነፍሳችን ተጽናንታ
በቃሉ ምስክር _ ቀርቦልን ማዕድ
በወልድ እናት ምልጃ _በሕይወት መንገድ
ከቅድስት ምድራችን _በመጡት
በደጀ ሰላሙ አለን_ ተሰብስበን።

በመረዋ ድምጹ_ በሚስረቀረቀው
ሲሰማ አርነት_ተሰፋን በሚሰብከው
የአባቶችን ምክር_ትዕዛዝ በሚያከብረው
በረጋው አንደበት_ ከቴድሮስ ሰማነው
ኪዳነምሕረት_ በእቅፏ ታኑረው።


ከርስታችን ወተን_ ብንኖርም በእሩቅ
መተላለፋችን_ በስሙ እንዲፋቅ
ክብር ሞገስ ሆነን_ ስራው የሚያስደንቅ።

ሀይማኖት ከምግባር_የነፃነት በፍታ
የሚያስተምር  ፍቅር_ ጠዋትና ማታ
የወንጌል አርበኛ_ የሚያስር የሚፈታ
ደጀንን ሸለመን_ የሰራዊት ጌታ።

ለዘመኑ ሕመም_ መድኃኒት ያመርታል
የነፍስ ዶክተር  ነው _ትውልድ ይፈውሳል
ብሉይን  ከሐዲስ _ እያመሳጠረ
ስንቱን ሐሰተኛ_ ከቤት  አባረረ።

በጠላት ተከቦ_ ሲደፈር ተራራው
እንደ ተመረጡት_ በእውነት አብበው
ወንጌልን ተጫምቶ_  በብዕር ይሻገራል
በለበሰው ሞገስ_ ሁሉን ያስደምማል
___

@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
#ቀን....


አንዳንድ ቀን አለ፥ ሚያልፍ ማይመስል፤
ልብን 'ሚሰብር፥ተስፋን የሚያቆስል።
የእድሜ መጨረሻ፥ የሞት ቀን የሚያስመኝ፤
"ብንሄድ ይሻለናል"፥ በቅቶኛል የሚያሰኝ።

የቀን ክፉ አለ፥ ከአዙሪት የባሰ፤
ከመከራ ሚዘፍቅ፥ እየመላለሰ።
ዘላለም 'ሚመስል፥ አለ አስጨናቂ ቀን፤
አመትም ወራትም፥  ይዞ የማይለቀን።

ሲጨንቀው ሲጠበው፥ ሲጠፋው መድረሻ፤
መጠጊያ ሲያጣለት፥ ለሀዘኑ መርሻ።
ዛሬ ምን ልሆን ነው? ነገ ምን ይመጣል?
በጭንቀት ተዘፍቆ፥በሀሳብ ይሰምጣል።
መከራ ሲከበው፥ መልሶ መልሶ፤
ሀዘን ይቀመጣል፥ ሰው በራሱ ለቅሶ።

የሀጢያት ተራራ፥ ከቤቱ ቢያርቅህ፤
ዛሬ ቁራሽ ባይኖር፥ ባይሞላ መሶብህ።
የሰው እጅ ማየት፥ ሲያሳቅቅ ሲያደክምህ፤
እንደዚህ ሲሰማህ፥ አይሸበር ልብህ።

በሰው እጅ ከምትወድቅ፤
በእግዚአብሄር እጅ ውደቅ።
ከአምላክ አትጣላ፥ ከአምላክ አትኳረፍ፤
የማታውቀውን ቀን፥ ያውቃል ብለህ እለፍ፤

የተተወን የተረሳውን ሰው፥እግዚአብሔር ሲያስታውሰው፤
የተናቀን የተጣለውን ሰው፥እግዚአብሔር ሲያነሳው።
ወደ ቤትህ ስትመጣ፥የጠፋው ልጁ ስትገኝ፤
የሰው ፊት አይገርፍህም ፥ፍርፋሪም አትመኝ።
ከአባትህ ቤት ስትገባ፥ከአምላክ ስትታረቅ፤
የሰው ፊት አይፈጅህም፥ፀሀይህ መቼም አይጠልቅ።

አባታችን ሆይ፥
የምትኖር በሰማይ።
አትተወን እንጂ አንተ፥ የሰውስ አይደንቀንም፤
ያንተ ፀሀይ አትጥለቅ፥ የሰው እሳት አይሞቀንም።

ቀን ለጨለመበት፥ የደግ ቀን አንተ ስጥ፤
በወዳጄ ልብ ላይ፥ ፍቅርን ብቻ አስቀምጥ።




@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
#ልክ_እንደ_ገብርኤል


ልክ እንደ ገብርኤል ፤ ውስጡ ደስ ያላለው
እውነተኛ ሰላም ፥ በልቡ የሌለው
ባለበት ያልጸና ፤ ፍፁም የማያምን
ሰላም ለኪ ይበል ፤ እንደምን ማርያምን ።

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ ፀሎትን ለማድረስ
ከፈጣሪው ታርቆ ፤ በእግዚአብሔር መቅደስ
በፊቱ የማይቆም ፤ ያለ አንዳች ማቋረጥ
ማርያም ፊት ለመቆም ፤ እንደምን ይመረጥ ።

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ በቀንና በሌት
ዘወትር ሳያስታጉል ፤ የማይቆም ማህሌት
አብሮ የማይሰለፍ ፤ ከመላእክት ወገን
እንደምን ይችላል ፤ ማርያምን ማመስገን።

አቤል ታደለ


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
#ዐረገ_በእልልታ


የተዋሐደውን ሥጋ ፤
የከፈለበትን ዋጋ ፤
አልተወውም በመቃብር ፤
ከፍ አደረገው በክብር ፤
የአዳምም ፀጋ ፤ ከቀድሞ በለጠ
በዘባነ ኪሩብ ፤ ሰው ልጅ ተቀመጠ ።
ዛሬ በደመና ፤ ሰማይ ተቀበለው
ትላንትና ዮሴፍ ፤ እንደ ጠቀለለው ።
ዛሬ በአባቱ ቀኝ ፤ ከበረ ክርስቶስ
ትላንት እንደ ቆመ  ፤ በቅጥረ ጲላጦስ።
ዛሬ በመለከት ፤ ዐረገ በእልልታ
ትላንትና ህማም ፤ የዋለበት ጌታ።
ዛሬ ዘመሩለት ፤ መላእክት አጅበው
ትላንትና ጭፍሮች ፤ ያፌዙበት ከበው።
ዛሬም ቢሆን ፥ ወደ ሰማይ ፤ ነገም ቢሆን ትላንትና
እንደ ኢየሱስ ፥ ከፍ አይልም ፤ ዝቅ ያላለ በትህትና ።

እንኳን ለጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል አደረሳችሁ አደረሰን

አቤል ታደለ



@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
#ቅድስት_እናት


ይቺ ቅድስት እናት _ ቃልን ወሰነችው
በከብቶቹ ግርግም_ ወልዳ ታቀፈችው
በመጠቅለያም_ጠቀለለችው።

ለደቱንም ዘር_ አልቀደመውም
የዳዊት ሥር ነው_መድኃኒአለም
በመወለዱም ድንግልናዋን_አልለወጠውም
የተዘጋች ደጃፍ_እናታችን ማርያም።

ቃል ከአብ _ ያለ ድካም ወጣ
የአዳም ልደቱ_ ደረሰለት ዕጣ
ከድንግልም ያለ _ሕማም ተወለደ
በእውነተኛው ብርሃን_ከሳሽ ተሰደደ።

ምጥ ሳያገኛት_ተሰማ እልልታ
ሰበአ ሰገል መጡ_ሊሰግዱ ለጌታ
እረኞች _ ዘመሩ ተሞልተው ደስታ።

ለአምላክነቱ አመጡለት _ዕጣን
ለንጉሥነቱ _ አቀረቡ ወርቁን
መድኃኒት ነውና _ ገለጡት ትንቢቱን
እነሆ አየነው_ ምስዋዕት ከርቤውን።

ግርማ ያለሽ_ድንግል የአሮን በትር
እናደንቅሻለን _ የሁላችን ክብር
ገናንነትሽን _ልንዘረዝር
በያሬድ ውብ ዜማ_ በዳዊት መዝሙር
ቆመናል ከደጅሽ_ ልንደረድር።

እንደ መልአኩ ገብርኤል_ ከላይ እንደመጣው
ልናመሰግንሽ _ ማርያም ግድ ነው
የባሕሪያችን መዳን_ካንቺ  ተገኘልን
በማሕጸንሽ ፍሬ_ሞት ተቀበረልን።

እንደ ሠርግ _ቤት ጉድፍ የሌለብሽ
መንፈስ ቅዱስ _ ያደረብሽ
የልዑል ኃይልም ማርያም ጸለለበሽ ።

ዘለአለም ነዋሪ_የነገስታት ንጉስ
ከኃጢአት ያዳነን_ ይመስገን ኢየሱስ
የልባችን ሰላም_ፍቅርህ በኛ ይንገስ።

ከአብ የተወለደ _ከአለም  በፊት የነበረ
አንዱ ቃል እራሱን ( ባሕሪዩን) ሰወረ
እንደምን ይረቃል_የሰማዩ  ምስጢር
የሱ ያደረገን_ ይመስገን እግዚአብሔር።

የኪዳን ጽላት_ያለብሽ
የተሰወረ መና_የተሸከምሽ
የወርቅ መሶብ_ የምንልሽ
ደብተራ ድንኳን _አንቺ ነሽ
የጥበብን ወንጌል_ በክንድሽ የታቀፍሽ
አሳስቢ ድንግል ሆይ_  ለመሃሪው ልጅሽ
እናምናለንና  _ ሁሉ እንደሚቻልሽ


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
#ሁለት_ነበርን

ገነት ውስጥ ሆነን ስናምፅ ባንተ ላይ
ያንተን መንግሥት ሽተን ዙፋንህን ስናይ
ዕፀ በለስ በልተን ካንተ ስንጣላ
ሁለት ነበርን እንጂ አልነበረም ሌላ

ሁለት የአፈር ሥራ ሁለት ወንጀለኛ
ዘር ልተካ ሳይል ሳይበዛ አመፀኛ
እዚያው ብትመልሰው ከመጣበት አፈር
ማን ይጠይቅሃል ከፍቅርህ በስተቀር?

ሁለት ጆንያ አፈር መልሰህ ከመሬት
ሌላ ሰው ብትሠራ ሌላ አዲስ ፍጥረት
የማያምፅ አዳም ታዛዥዋን ሔዋኒት
ደግመህ ብትፈጥር ላንተ ምን አለበት?

ሸከላህን አክብረህ ሲሰበር ያልጣልከው
ሲያምጽብህ አይተህ በአየር ያልበተንከው
ከቶ ለምን ይሆን ዘሩን ያበዛኸው
እስኪገርፍህ ድረስ ፖልበት የሰጠኸው

ጠላትክን መግበህ እንዲህ የወደድከው
ምድርን ሙላ ብለህ በሁሉ ያነገስከው
ምራቁን የተፋው በአንተ ላይ ጨክኖ
ማጥፋት ስትችል ነው ገና ሁለት ሆኖ

ማን ነበር ከልካይህ ፈጥረህ እንዳታጠፋ
ምሕረትህ ነው እንጂ በዓለም የሰፋ
ቸርነትህ እንጂ ምድሪቱን የሞላ
አንተን የሚያስቆም ከቶ የለም ሌላ

“ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና" ሰቆ ኤር. 3:22

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 23 2017 ዓ.ም.

@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
የሰዉ ልጅ

በጭንቁ ማርያም ማርያም ይላል ምጡ
እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀና እና እያቄም
መስዋእቱ ቀረ እርግብ ና ዋኖስ
ልጇን ልትሰጥ ነዉ እናት ከሊባኖስ
የሊባኖስ ዝግባ ንፋስ የማይገፋዉ
ማርያም ስትወለድ እግዜር ዙፋን ሰፋዉ
እመ ብዙሀኗ

የሄኖክ የራሥ ወርቅ የኢሳያስ ትንቢቱ
የዳዊት የልጅ ልጅ የኖህ መርከቢቱ
እመ አምላክ አንቺ

ቤት የለዉም እና አዳም ወጥቶ ቀርቶ ከፈጣሪዉ ደጁ
ምንድነዉ ሚስጥሩ ቤት አልተወለዱም እናት እና ልጁ

ሚስጥሩ ነች እና ሰም እና ወርቅ ቃል
ቀራንዮን ያየ ሊባኖስን ያዉቃል
ሰዉ ሲጨንቀዉ ጊዜ ማርያም ማርያም ይላል
ምጥም እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀና እና እያቄም


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
#ማርያም_እስካለ


የበግ ለምድ ለበሶ ፤ አስመሳዩ ተኩላ
ከእናታችን ነጥቆ ፤ እኛንም ሊበላ
መስሎ ተቆርቋሪ ፤ የእውነት ጠበቃ
ፀሀይን ጋረደች ፤ ይለናል ጨረቃ ።
ደካማ ነው ብሎ ፤ ሺ ጊዜ ቢወድቅም
ማርያም እስካለ ፤ ሰይጣን ሰው አይንቅም።
የጥላቻ መርዙን ፤ በወንጌል አስታኮ
የኛንም ምስጋና ፤ ይለዋል አምልኮ ።
ደግነቷ እንጂ ፤ የጌታዬ እናቱ
ከክፉ ጠማማ ፤ ከእንደኛ አይነቱ
አለም ካሰመጠን ፤ በኃጢያት ማእበል
ባልተገባት ነበር ፤ ምስጋና መቀበል።


አቤል ታደለ


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim


#Join_and_Share🙏
2025/06/18 17:24:48
Back to Top
HTML Embed Code: