tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5221
Create:
Last Update:
Last Update:
#ልዩ_ምሥክር_ናት
እንደ ከዚህ ቀደም ፤ አብሳሪው መልአክ
ለሌሎች እንዳለው ፤ ከአርያም ሲላክ
ሠምቶሻል እግዚአብሔር ፤ የልብሽ መሻቱን
አላለም ለድንግል ፤ ሲጀምር ብሥራቱን ።
ምክንያቱም እሷ ፤
ለምና አታውቅም ፤ ሥለትም ተስላ
የፈጣሪ እናት ፤ እኔ ልሁን ብላ ።
ምክንያቱም እሷ ፤
እንደ ደናግላን ፤ ድንገት አሁን ካሁን
ጠብቃ አታውቅም ፤ ለመውለድ መሲሁን ።
ምክንያቱም እሷ ፤
እንደነ ኤልሳቤጥ ፤ ወይም እንደ ሐና
ልጅ እንኳን ለማግኘት ፤ አታውቅም ተማፅና ።
ምክንያቱም እሷ ፤
መሆኑ አልገባት ፤ እንድትሆን እልፍኙ
ገና በልጅነት ፤ ያረጋት መናኙ ።
ምክንያቱም እሷ ፤
በልቧ ጸንሳው ፤ መኖርን ነው እንጂ
መባል አታስብም ፤ አምላክን ውለጂ ።
ምክንያቱም እሷ ፤
ምረጠኝ ሳትለው ፤ ወዶ የመረጣት
አንዳችም ሳትሻ ፤ ሁሉ የተሰጣት
የእርሱ ድንቅ ሥራ ፤ ልዩ ምሥክር ናት ።
✍ አቤል ታደለ
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
JoinandShare🙏
BY መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
Share with your friend now:
tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5221