tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5166
Create:
Last Update:
Last Update:
አጠገብህ ልሆን ደሞ ርቅሀለሁ
ወይ ገብቼ አልሞቀኝ የመለኮት ክንድህ
ምን ያህል ይርቃል ልቤ ከመንገድህ
አለምንም ቀረብ
አምላኬንም ቀረብ
ደግሞ ጠጋ ማለት ደግሞ እሸሻለሁ
ሀጥያቴን አልተዉም መፅደቅም እሻለሁ
ምን ጉድ ነኝ ?
ምንጉድ ነኝ?
ምን ጉድ ነዉ ይሄ መሀል መሆን
ምን ድረስ ነዉ የሚያስጉዘኝ
እስከመጨረሻዉ መች ነዉ የምትይዘኝ
አይበቃኝም ወይ?
አይበቃኝም ወይ መሠባበሬ
ከቤቴ ይበልጣል የፍርሀት አጥሬ
ትዕቢቴ ልቤን አንቆ
የቱጋ ነዉ የምሰብረኝ?
እራቀብኝ ያ ደማስቆ
እምን ጋ ነዉ ምደነግጥ
በነዉሬ በኋጢያቴ
ወየዉልኝ ለጥጋቤ ወየዉልኝ ለትዕቢቴ
ድካም ለሊቱን እንባ እየጋተኝ
የሰበረኝን ይህንዓለም መጣል ያቃተኝ
በአንድ ሰዉነቴ ሁለት መልክ ያለኝ
ጌታዬ ንገረኝ እኔ የትኛዉ ነኝ?
✍ ኤልያስ ሽታሑን
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
#Join_and_Share🙏
BY መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
Share with your friend now:
tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5166