tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5129
Create:
Last Update:
Last Update:
#ማርያም_ተወለደች
በዚች እለት
ከሐናና ከኢያቄም ፤ እድሜያቸው ካረጀ
ልዑል ለማደሪያው ፤ መቅደስ አዘጋጀ
ከዕሴይ የዘር ግንድ ፤ እቤቱን አነፀ
ከማይነቅዝ እንጨት ፤ ታቦቱን ቀረፀ።
በዚች እለት
እንደ እንግዳ ደራሽ ፤ ድንገት ያላየናት
አስቀድሞ ትንቢት ፤ የተነገረላት
በሊባኖስ አድባር ፤ ተወለደች ሴት ልጅ
ፊቷ የሚያበራ ፤ ከፀሐይ ሰባት እጅ ።
በዚች እለት
በነፍስም በሥጋ ፤ ነውር የሌለባት
መልክና ደም ግባት ፤ የተባበረላት
ጸጋን የተመላች ፤ በዕንቁ ያጌጠች
የመመኪያችን ዘውድ ፤ ማርያም ተወለደች።
ታዲያ ይህችን እለት ፤
እንዴት እናክብራት ፤ በምን ያህል ድምቀት
አይደለም የሌላ ፤ የተራ ሰው ልደት
እንዴት ባለ ቅኔ ፤ ጠቢቡስ ያገልግል
ልደቷ ብቻውን ፤ ድንቅ ነው የድንግል።
እንኳን አደረሳችሁ!
✍️ አቤል ታደለ @abeltadele
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gitim
BY መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

Share with your friend now:
tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5129