tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5128
Last Update:
ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን***በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን*** አግዓዞ ለአዳም
ሰላም***እም ይእዜስ
ኮነ***ፍስሃ ወሰላም
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!†††
#እንኳን_አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ዓመታዊ_የልደት_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን
በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ፤ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና ። እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኀዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር ። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለአለም ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም ሐሳባቸውን ተመለከተ ።ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለም ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው ። ነፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱም ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት፤ ቃሉ እውነት እንደሆነች እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ።የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው ። በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን ።
©ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፩
BY መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
Share with your friend now:
tgoop.com/Melikt_weg_gitim/5128