Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖታችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ነገሮ አሉ። ከነዚህም ውስጥ:-
1. ድግምትና ጥንቆላ
በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሐሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ።
* ጥንቆላና ድግምት ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይ ^ጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይ ^ጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል} ብለዋል። [አሶሒሐ፡ 3387]
* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም” ብሏል። [ጠሃ፡ 69]
* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም} ብለዋል። [ሙስሊም፡ 5957]
2. የጳጉሜ ዱዓእ የሚል አጉል ፈጠራ
በአንዳንድ አካባቢዎች የጳጉሜ ዱዓእ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) የሚል እምነት አለ። ይሄ አጉል እምነት ነው። በጣም የሚገርመው ለዱዓእ የሚጣዱት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ብለዋል።
3. እንቁጣጣሽ ማክበር
ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-
* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡
ይህንን ስንል የሚጎረብጣቸው አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ይልቁንም የኛን እምነታዊ መገለጫ ካላንፀባረቃችሁ ብሎ ሌሎችን መወረፍ አክራሪነት ነው። እምነታችን በሌሎች ህዝቦች መለያ በሆኑ እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ስለ መውሊድ የሚሰጠው ትምህርት ለበዛባቸው!
~
ከመውሊድ ቢድዐ ስናስጠነቅቅ በዝቶባቸው የተንገሸገሹ አካላትን እያየን ነው። በቁርጥ ለመናገር በዚህ ጉዳይ ላይ ሐቂቃውን እንጂ የሰዎችን ስሜት መለኪያ አናደርግም። ሐቂቃው የት ላይ ነው?
1. የጥፋቱ አራማጆች ሳይታክቱ ወደ ቢድዐቸው እየተጣሩ እያየን ነው። የአጥፊዎቹ ስብከትና ውትወታ ሳይበዛበት ማስጠንቀቂያው የሚረብሸው የችግሩ ደጋፊ የሆነን አካል ነው።
2. እነዚህ አካላት ከቢድዐው የሚያስጠነቅቅ ትምህርት የሚበዛባቸው ለጉዳዩ የሚሰጡት የረባ ትኩረት ስለሌላቸው ነው። እነሱ ጧት ማታ ቢዝነሳቸውን ሲያስተዋውቁ፣ ድለላቸው ላይ ሲሰማሩ፣ አርቲ ቡርቲ የኳስና የፖለቲካ ወሬ ሲለቀልቁ ሳይበዛባቸው በቁርኣንና ሐዲሥ፣ በዑልማእ ንግግር የታጀበ ትምህርት የሚበዛባቸው ለደዕዋ የሚሰጡት ትርጉም የቀለለ ወይም የተዛባ በመሆኑ ነው።
3. ነብያችን ﷺ ዘወትር በየ ኹጥባቸው ላይ አይናቸው ቀልቶ፣ ድምፃቸው ጎልቶ፣ ቁጣቸው በርትቶ ደጋግመው ከቢድዐ ያስጠነቅቁ ነበር። [ሙስሊም፡ 867] ይሄ እንግዲህ ቢድዐው እንደዛሬው ገና ሳይንሰራፋ ማለት ነው።
ሌላም ሐዲሥ አለ። ሶሐቢዩ አቡ ኡማማ አልባሂሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ በደማስቆ መስጂድ አጠገብ በጦርነት የተገ ^ደሉ ኸዋ ^ ሪጆችን ጭንቅላቶች ተመለከቱና እንዲህ አሉ፦
كِلَابُ النَّارِ شَرُّ قَتْلَى تَحْتَ أَدِيمِ السَّمَاءِ، خَيْرُ قَتْلَى مَنْ قَتَلُوهُ ...
"የጀሀነም ው ^ ሾች! ከሰማይ በታች ከተገ ^ ደሉት ሁሉ የከፉ ናቸው። ከተገ ^ዳይ ሁሉ በላጩ እነሱ የገ. ደሉት ነው።" ...
አስተላላፊው አቡ ጋሊብ ለአቡ ኡማማ፡ "አንተ ግን ይህንን ያልከውን ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ሰምተሃልን?" ብለው ሲጠይቁ እንዲህ ብለው መለሱ፦
لَوْ لَمْ أَسْمَعْهُ إِلَّا مَرَّةً أَوْ مَرَّتَيْنِ أَوْ ثَلَاثًا أَوْ أَرْبَعًا - حَتَّى عَدَّ سَبْعًا - مَا حَدَّثْتُكُمُوهُ.
"አንድ ጊዜ፣ ሁለት ጊዜ፣ ሦስት ጊዜ፣ ወይም አራት፣ ... - ሰባት እስከሚቆጥሩ ድረስ - ይህን ያህል ጊዜ ብቻ እንጂ የሰማኋቸው ባልሆን ኖሮ ባልነገርኳችሁ ነበር!!" [ቲሪሚዚይ፡ 3000]
ምን ማለት ነው? ነብያችን ﷺ ከነዚህ የቢድዐ ኃይሎች ይህን ሁሉ ጊዜ ደግመው ደጋግመው ያስጠነቅቁ ነበር ማለት ነው። ልብ በሉ! በጊዜያቸው እነዚህ አካላት እንደ ቡድን ገና ያልመጡ ከመሆናቸው ጋር ነው በዚህ መልኩ የወተወቱት። ዛሬስ? የቢድዐ ባህር ውስጥ እየዋኙ ከዚያ ስለ ቢድዐው አትናገሩ ይላሉ። የተሞሉት ነገር ነው እንዲህ የሚያደርጋቸው። እስፖንጅ የያዘውን ነው የሚተፋው!!
ስለዚህ ደግመን ደጋግመን ከቢድዐ እናስጠነቅቃለን። በማስረጃ ብቻ!!

ደዕዋ ላይ ላለኸው ወገኔ!
~
በአካባቢህ፣ በሰፈርህ የጥፋት ኃይሎች ጉልበት አውጥተውብሃል? ከጎንህ የሚቆም የሚርረዳህ አጋር አጥተሃል? በፍፁም በፍፁም እጅ እንዳትሰጥ። እንዳትርረታ። በቀላል የምትሰበር ከሆነ ሐቅን፣ ተውሒድን፣ ሱናን ትጎዳለህ። ታላቁ ዓሊም ሙሐመድ ብኑ ሷሊሕ አልዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡-
إنْ كنت وحيداً في بلدك تدعو إلى السنّة واتّباع السلف ؛ وكُثَرَ الأعداء الذين يدعون إلى مذهبهم الباطل ؛*
*فالواجب ألّا تنهزم ؛* لأنك إذا انهزمت فقد هزمت الحق ؛ بل اثبُت ؛ وما أرعبَ أعداءك إذا رأوك ثابتاً )).
“በሃገርህ ውስጥ ወደ ሱና እና የሰለፎችን መንገድ ወደ መከተል የምትጣራ ብቸኛ ሰው ብትሆን እንኳ፣ ወደ ጥፋት መንገዳቸው የሚጣሩ ጠላቶች ብዙ ቢሆኑም፣ ፈፅሞ መሸነፍ የለብህም። ምክንያቱም አንተ ተሸነፍክ ማለት፣ ሐቅ ተሸነፈ ማለት ነው። ስለዚህ ፅና። ጠላቶችህን አንተን ፅኑ ሆነህ እንደማየት የሚያስፈራቸው ነገር የለም።”
📚 [ሸርሑል ካፊየቲ-ሻፊያ፡ 1/201]
በአላህ ላይ ተወኩል ይኑርህ። የሌሎች መብዛት አያስደንግጥህ። ከጎንህ ሰው ብታጣ ባይተዋርነት አይሰማህ። የነብዩን ﷺ የደዕዋ ታሪክ በተግባር ኑረው። በአላህ ላይ ተስፋ አድርግ። ኢንሻአላህ ነገሮች ይቀየራሉ ብለህ ከልብህ ተግተህ ስራ። ባንዴ ውጤት አትጠብቅ። እወቅ! ጠብታ ውሃ ድንጋይ ትበሳለች። መንፈሰ ልፍስፍስ አትሁን። ፈተና አይስበርህ። ገና ለጀማሪዎች የምታስተምራት ሠላሠቱል ኡሱል ኪታብ መግቢያ ላይ ያለውን "አሶብሩ ዐለል አዛ ፊሂ" የሚለውን ከስጋህ ከደምህ ጋር አዋህደው። መቼስ አንተ የማትኖረውን ሐቅ ለሌላ ማሻገር ከባድ እንደሆነ አይጠፋህም። ባይሆን ለአካባቢህም ለጊዜህም የሚመጥን፣ ኃላፊነት ያለበት ሰው ሆነህ ተገኝ። አዋዋልህን አሳምር። የዋዛ ፈዛዛ ሰው አትሁን። "ጦር ሜዳ ውስጥ ከተገኘ ወርቅ ጦር ሜዳ ውስጥ የተገኘ ብረት የተሻለ ዋጋ አለው" ይባላል።

ደዕዋ ላይ ላለኸው ወገኔ
~
በደዕዋ ሂደትህ ላይ ጠላት አታብዛ። ከሁሉ ጋር አትጋጭ። በተለይ በአካባቢህ ደዕዋው ገና ዳዴ ላይ ከሆነ የማህበራዊ ሚዲያን ደዕዋ ወይም የተሻለ ድጋፍና መሰረት ያላቸውን አካባቢዎች አካሄድ ምሳሌ እንዳታደርግ። አቅምህን አገናዝብ። ደዕዋህን የፍጥጫ አታድርገው። የአካባቢህን ተጨባጭ ተረዳ። ተማሪዎችህ በችኮላ ለደዕዋው እንቅፋት እንዳይሆኑ ተቆጣጠር። ሁሉን ባንዴ አሳካለሁ ብለህ አታስብ። ብዙ ያሳደደ አንድ አይዝም።

ሁለት ሰዎች ብቻ በጀማዐ ሲሰግዱ ተከታዩ ከኢማሙ ትንሽ ወደ ኋላ መሆን ልክ ነውን?
~
ሁለት ሰዎች ብቻ ጀማዐ ሶላት የሚሰግዱ ከሆነ ተከታዩ ከኢማሙ ትንሽ ወደ ኋላ ሆኖ ሲቆም ማየት የተለመደ ነው። በርግጥ ይህንን የመረጡ ዓሊሞች አሉ። ይሁን እንጂ ትክክለኛው አፈፃፀም ተከታዩ ከኢማሙ ጋር እኩል ሆኖ መቆሙ ነው። ይሄ የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። አልሓፊዝ ኢብኑ ረጀብም እንዲህ ብለዋል፦
" الإمام إذا لم يأتم به غير واحد، فإنه يقيمه عن يمينه بحذائه، ولو كان صبيا لم يبلغ الحلم. وهذا كالإجماع من أهل العلم.
وقد حكاه الترمذي فِي "جامعه" عَن أهل العلم من أصحاب النّبيّ - صلّى الله عليه وسلّم - فمن بعدهم، قالوا: إذا كان الرّجل مع الرّجل يقوم عن يمين الإمام. وحكاه ابن المنذر عَن أكثر أهل العلم... "
“አንድ ኢማም ከአንድ ሰው ውጭ የሚከተለው ከሌለ በቀጥታ ከቀኙ በኩል ሊያቆመው ይገባል። ለአቅመ ሃላፊነት ያልደረሰ ህፃን ቢሆን እንኳ። ይሄ የእውቀት ባለቤቶች ዘንድ ልክ እንደ ኢጅማዕ ነው። ቲርሚዚ በጃሚዐቸው ውስጥ ከነብዩ ﷺ ባልደረቦች እና ከነሱ በኋላ ከመጡ አዋቂዎች ጠቅሰውታል። አንድ ሰው ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ከሆነ ከኢማሙ ቀኝ ይቆማል ብለዋል። ኢብኑል ሙንዚርም ከብዙ የእውቀት ባለቤቶች ጠቅሰውታል።” [ፈትሑል ባሪ፡ 6/197 – 198]
ኢማሙል ቡኻሪ ረሒመሁላህ በሶሒሕ ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ የሚል ርእስ አስፍረዋል፦
" يَقُومُ عَنْ يَمِينِ الإمَامِ بحذائهِ سواءً، إذا كَاناَ اثْنَيْن".
“ከኢማሙ በቀኙ በኩል እኩል ሆኖ ይቆማል፣ ሁለት ከሆኑ።”
ከዚያም ተከታዩን የኢብኑ ዐባስን ረዲየላሁ ዐንሁማ ሐዲሥ አስፍረዋል፦
"بِتُّ فِي بَيْتِ خَالَتِي مَيْمُونَةَ، فَصَلَّى رَسُولُ اللَّهِ ﷺ العِشَاءَ، ثُمَّ جَاءَ فَصَلَّى أَرْبَعَ رَكَعَاتٍ، ثُمَّ نَامَ، ثُمَّ قَامَ، فَجِئْتُ فَقُمْتُ عَنْ يَسَارِهِ، فَجَعَلَنِي عَنْ يَمِينِهِ،... "
“ከየሹማዬ መይሙና ዘንድ አድሬ ነበር። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ዒሻእን ሰገዱ። ከዚያም (እቤት) መጡና አራት ረከዐዎችን ሰገዱ። ከዚያም ተኙ። ከዚያም ለሶላት ቆሙ። በግራቸው በኩል ቆምኩኝ። በቀኛቸው አደረጉኝ።...” [ቡኻሪ፡ 697]
“ይሄ የኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ ሐዲሥ እኩል ሆኖ መቆምን ይጠቁማል ወይ?” ከተባለ “አዎ” ነው መልሱ። ኢብኑ ሐጀር “ከቀኝ ጎናቸው አደረጉኝ” የሚለውን የኢብኑ ዐባስን ንግግር ሲያብራሩ “ጉልህ መልእክቱ እኩል ሆኖ መቆም ነው” ብለዋል።
የቡኻሪን ርእስ አስመልክተውም እንዲህ ብለዋል፦
በዚህ ርእስ አሰጣጣቸው የፈለጉት በሶላት ውስጥ ኢማምና ተከታይ ብቻቸውን ከተገኙ ተከታዩ ከኢማሙ በቀኝ ጎን እኩል ሆኖ ማለትም በመቆሚያው ቦታ ላይ መቀደምም ሆነ መዘግየት ሳይኖር እኩል መሆናቸው ነው።” [ፈትሑል ባሪ፡ 6/197]
.
በሌላ ዘገባ ላይም ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦
" أَتَيْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِنْ آخِرِ اللَّيْلِ، فَصَلَّيْتُ خَلْفَهُ، فَأَخَذَ بِيَدِي، فَجَرَّنِي، فَجَعَلَنِي حِذَاءَهُ، فَلَمَّا أَقْبَلَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى صَلاتِهِ، خَنَسْتُ، فَصَلَّى رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَلَمَّا انْصَرَفَ قَالَ لِي: مَا شَأْنِي أَجْعَلُكَ حِذَائِي فَتَخْنِسُ؟
فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ! أَوَيَنْبَغِي لِأَحَدٍ أَنْ يُصَلِّيَ حِذَاءَكَ، وَأَنْتَ رَسُولُ اللهِ الَّذِي أَعْطَاكَ اللهُ؟
قَالَ: فَأَعْجَبْتُهُ، فَدَعَا اللهَ لِي أَنْ يَزِيدَنِي عِلْمًا وَفَهْمًا... "
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ዘንድ የሌሊቱ መጨረሻ ላይ መጣሁኝ። ከኋላቸው ልሰግድ ቆምኩኝ። እጄን ይዘው በመጎተት ከሳቸው ጎን ትይዩ አቆሙኝ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶላታቸው ላይ ሲያተኩሩ ጊዜ ወደኋላ አልኩኝ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሰገዱ። ባጠናቀቁ ጊዜ፦ ‘ምነው? እኔ በጎኔ ሳደርግህ ወደኋላ ትላለህሳ?’ አሉኝ።
‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በአንተ ትይዩ ሆኖ ለማንስ ሊሰግድ ይገባዋልን? አንተ አላህ ያደለህ የአላህ መልእክተኛ ሆነህ ሳለ?’ አልኳቸው። ገረምኳቸው። እውቀትንና ግንዛቤን እንዲጨምረኝ አላህን ለመኑልኝ።” [አሶሒሐህ፡ 6/174 - 175]
ከጃቢርም ተመሳሳይ መልእክት ተላልፏል። [ሙስሊም፡ 3010]
በተጨማሪም ዐብዱላህ ብኑ ዑትባህ ብኒ መስዑድ እንዲህ ብለዋል፦
دخلت على عمر بن الخطاب رضي الله عنه بالهاجرة «فوجدته يسبح، فقمت وراءه. فقربني حتى جعلني حذاءه عن يمينه»
“ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ ቀትር ላይ ስገባ ሱና እየሰገዱ አገኘኋቸው። ከኋላቸው ቆምኩኝ። በቀኛቸው በኩል አድርገው አቀረቡኝ።” [ሙወጦእ ማሊክ፡ ሐዲሥ ቁ. 364]
በተጨማሪም ኢብኑ ጁረይጅ ረሒመሁላህ “ 'አንድ ሰው ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ሆኖ የሚሰግድ ከሆነ ከየት በኩል ነው የሚሆነው?' ብየ ዐጧእን ጠይቄ ነበር” ይላሉ።
ዐጧእ፦ “በቀኙ በኩል” አሉ።
ኢብኑ ጁረይጅ፦ “አብሮት እስከሚሰለፍ ድረስ በሱው አቅጣጫ ነው የሚሆነው? አንዱ ሌላውን ሳይቀደም?”
ዐጧእ፦ “አዎ!”
ኢብኑ ጁረይጅ፦ “በመሃላቸው ክፍተት እስከማይኖር ድረስ?
ዐጧእ፦ “አዎ!” [ሙሶነፉ ዐብዲረዛቅ፡ ቁ. 3870]
ስለዚህ ሁለት ሆነው በሚሰግዱ ጊዜ ከኢማም ትንሽ ወደ ኋላ መቅረት ምንም እንኳ የደገፉት ዓሊሞች ቢኖሩም ማስረጃ የሚደግፈው ግን አይደለም። ይህንን ማድረግ የተወደደ ቢሆን ኖሮ ተጨባጭ መረጃ ከነብዩ ﷺ ይተላለፍ ነበር። ነገር ግን የለም። ከሶሐቦችም ይገኝ ነበር። ይህም የለም። መረጃ አለመኖሩ መሰረት እንደሌለው ያሳያል። እንደሚታወቀው ነብዩ ﷺ “ስሰግድ እንዳያችሁኝ ስገዱ” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 631] የሳቸው አሰጋገድ ውስጥ ደግሞ ከአንድ ተከታይ ጋር ብቻ ሆነው በሰገዱበት ላይ ትንሽ የተቀደሙበት አልተገኘም። ይልቁንም የተገኘው ከዚህ በተለየ እኩል ጎን ለጎን መቆም ነው። ይሄኛው አቋም ከዘመናችን ዓሊሞች ውስጥ የኢብኑ ባዝ፣ የአልባኒይ እና የኢብኑ ዑሠይሚን አቋም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-

አካባቢን፣ ዘርን፣ ቋንቋን፣ ... መሰረት ያደረገ ጥላቻ እና አጉል ውግንና የጃሂሊያ ባህሪ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
~
በርካታ የኢኽዋነል ሙስሊሚን አስተሳሰብ አራማጆች በመውሊድ ቢድዐ ላይ የሚደረገው ዘመቻ ክፉኛ ሲረብሻቸው ይታያሉ፡፡ አብዛኛው የመውሊድ አፈፃፀም ውስጥ ሺርክ እንዳለበት እያወቁ "ለምን በትንንሽ ነገሮች እንጨቃጨቃለን?" ይላሉ። የሺርክ ጉዳይ ለነሱ ከትንንሽ ነገሮች ውስጥ ነው። የተውሒድ ዋጋው ከነሱ ቡድናዊ አላማ በታች ነው። ራሳቸውን መካከለኛ ለማድረግ የመውሊድ ፅንፈኛ ደጋፊዎችን በስሱ ከነኩ በኋላ (እሱም ከስንት አንዴ ከኖረ ነው) ያለ የሌለ ሃይላቸውን መውሊድን በሚነቅፉት ላይ ነው የሚያደርጉት፡፡ መውሊድ ላይ የሚሰነዘረው ተቃውሞ ክፉኛ እንዲረብሻቸው የሚያደርጓቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል፡-
1. ኢኽዋነል ሙስሊሚን እንደ ቡድን መሰረቱ ሱፊያ ነው፡፡ የቡድኑ መስራች ሐሰን አልበና የሻዚሊያ ጦሪቃ ቅርንጫፍ የሆነው የ“ሐሷፊያ ጦሪቃ” ተከታይ የነበረ ሲሆን ራሱ እንደገለፀው “የሐሷፊያን አስተሳሰብ የጠገብኩ ሆኜ ወደ ደመንሁር ወረድኩ” ይላል፡፡ [ሙዘኪራቱ ዳዕዋ ወዳዒያ፡ 31 - 34] ከቡድኑ አመራሮች አንዱ የሆነው ሰዒድ ሐዋ “የኢኽዋነል ሙስሊሚን ንቅናቄ ራሱ ሱፊ ነው የመሰረተው፡፡ አሉታዊ ጎኖቹን በመተው የተሶውፍን እውነታ ወስዷል” ይላል፡፡ [ጀውለቱን ፊልፊቅሀይን፡ 154]
አንዳንዶች ይሄኛው አቋሙ ከመመለሱ በፊት የነበረበት ነው ቢሉም እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም። እስከ ፍፃሜው ተሶውፍ ላይ እንደዘለቀ ታላላቅ የኢኽዋን ቁንጮዎች መስክረዋል፡፡ ስለዚህ ዛሬ የኢኽዋን ፀሐፊዎች በተለያየ ስልት ከሱፍዮች የሚከላከሉት ከራሳቸው፣ ከመሪዎቻቸው እና ከቡድናቸው ለመከላከል ነው፡፡ ሱፍያ ተነካ ማለት ኢኽዋን ተነካ ማለት ነው፡፡ ሙስሊሞች ሱፍያን ተፀየፉ ማለት የኢኽዋን መሰረቱ ተናጋ ማለት ነው፡፡
አንዳንዶች “እነሱ ነፍስን ማጥራት ላይ የሚያተኩረውን፣ ንፁሁን ተሶውፍ ነው የተከተሉት” ይላሉ፡፡ እውነታው እንደዚያ እንዳልሆነና ተሶውፍን ከነሺርኩ ከነ ግሳንግሱ የሚያራምዱ እንደሆኑ በተከታዮቹ ነጥቦች የምናይ ይሆናል።
2. የቡድኑ መስራች ሐሰን አልበና ረቢዑል አወል አንድ ካለ ጀምሮ እስከ 12 ድረስ መውሊድን ያከብር እንደነበር ራሱ ፅፏል፡፡ [ሙዘኪራ፡ 58] ዛሬም ድረስ ለመውሊድ ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱ ኢኽዋኖችን የምናየው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡
3. በርካታ ሱፍዮች ዘንድ ነብዩ ﷺ ከመውሊዱ ጭፈራ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ነብዩ ﷺ ፈፅሞ ከእንዲህ አይነቱ የባእድ አምልኮ ድግስ ላይ አይገኙም፡፡ ይሄ ቅጥፈታዊ እምነት በኢኽዋነል ሙስሊሚን መስራቹ ሐሰን አልበናም ጭምር ሲስተጋባ የነበረ ነው፡፡ ይሄው እነ ሐሰን አልበና መውሊድ ላይ ሲያንጎራጉሯቸው ከነበሩ ስንኞች ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡-
هذا الحبيب مع الأحباب قد حضرا …
… لا شك أن حبيب القوم قد حضرا
“ይህ ወዳጃችን ከወዳጆች ጋር ተገኝቷል።
…
… ያለጥርጥር የሰዎቹ ወዳጅ ተገኝቷል፡፡” [ሐሰን አልበናህ ቢአቅላሚ ተላሚዘቲሂ ወሙዓሲሪሂ፡ 71-72]
ይህ እምነት ዛሬም ድረስ ከሱፍዮች ዘንድ በሰፊው ያለ ነው፡፡ በመውሊድ ጭፈራቸው መሃል መብራት አጥፍተው ነብዩ መጡ ይሉና “መርሐባ ነቢ መርሐባ! መርሐባ!” እያሉ ይዘፍናሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ታዳሚው እንዳለ ይቆማል፡፡ ክቡሩ ነቢይ ﷺ የነሱን በሺርክ የተጨማለቀ፣ በውዝዋዜ የታጀበ ድግስ ሊታደሙ መሆኑ ነው፡፡ “አይ ይሄ'ኮ ስማቸው ሲወሳ ለአክብሮት ያክል የሚፈፀም እንጂ ቦታው ላይ ይገኛሉ ተብሎ አይደለም” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ ቦታው ላይ ይገኛሉ የሚል እምነት እንዳለማ ይሄው የሐሰን አልበናን ንግግር አጣቀስኩልህ፡፡ በሃገራችንም በሰፊው የሚታወቅ እምነት ስለሆነ መወሻሸት አያስፈልግም፡፡ ደግሞስ በየደዕዋው ላይ፣ በየ መስጂዱ፣ በየ መድረኩ ስማቸው ሲወሳ ትቆማላችሁ እንዴ? ውሸት!
በነገራችን ላይ ነብዩ ﷺ በህይወት ሳሉ ማንም እንዲቆምላቸው አይወዱም ነበር፡፡ አነስ ብኑ ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “እነሱ (ሶሐቦች) ዘንድ ዱንያ ውስጥ እንደ ነብዩ ﷺ ሊያዩት የሚወዱት ሰው አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን መጥላታቸውን ስለሚያውቁ ለሳቸው አይቆሙም ነበር፡፡” [አሶሒሐ፡ 358]
ሌላ በነገራችን ላይ! ይህንን ነብዩ መጡ እያሉ መነሳትን - የሚሰማ ጠፋ እንጂ - ከመውሊድ አክባሪዎች ውስጥ ሳይቀር የኮነኑት ነበሩ፡፡ ሀይተሚ እንዲህ ይላል፡-“የዚህ አምሳያው ብዙዎች የነብዩ ﷺ ልደትና እናታቸው እሳቸውን መውለዷ ሲወሳ የሚያደርጉት መቆም ሲሆን ይህም ምንም አይነት መረጃ ያልመጣበት ቢድዐ ነው፡፡ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት እሳቸውን ﷺ ለማላቅ ነው፡፡ መሃይማኑ ከአዋቂዎቹ በተለየ በዚህ ድርጊታቸው ይታለፋሉ።” [አልፈታዋ አልሐዲሢያ፡ 58]
4. መውሊድን ያክል እጅግ በርካታ ቢድዐዎችን አቅፎ የያዘን ቢድዐ አቅልሎ ማቅረብ ቡድናዊ ስሜት እየጋረዳቸው እንጂ ላስተዋለ ሁሉ በቀላሉ የሚታይ ነው፡፡ በስፍራዎቹ የሚፈፀሙትን አላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል፣ በመስጂድ ውስጥ መጨፈር፣ መስጂዶችን በጫትና በተረፈ ምግብ ማቆሸሽ፣ ዝሙት፣ … ይቅርና ብዙ ከባባድ ሺርክ ይፈፀማል፡፡ ግና በርካታ ኢኽዋኖችን የሺርክ ጉዳይ ሲያስጨንቃቸው አይታይም፡፡ እንጂማ በነቢዩ ﷺ እና በ“ወልዮች” ላይ ብዙ ድንበር ይታለፋል፡፡ በመውሊድ ቦታዎች ላይ ብዙ አይነት ሺርክ ይፈፀማል፡፡ ለቀብር ሱጁድ ይወረዳል፡፡ ጦዋፍ ይደረጋል፡፡ ለበረካ እየተባለ የቀብር አፈር እየተበጠበጠ ይጠጣል፡፡ ከዘመናት በፊት ያለፉ ሙታኖችን ሰዎች ይማፀናሉ፡፡ ስለት ይፈፅማሉ፡፡ ያርዳሉ፡፡ በሺርክ የተሞሉ መንዙማዎች ይቀነቀናሉ፡፡
ይህን ሁሉ ጥፋት አጭቆ የያዘን ቢድዐ የሚያወግዙ ሰዎችን ነው እንደ ጠርዘኛ የሚስሉት፡፡ መውሊድ በመጣ ቁጥር ሰዎችን ከዚህ ጥፋት ስላስጠነቀቁ ነው ጨቅጫቃ የሚያደርጉት፡፡ “ረቢዕን የመጨቃጨቂያ ወር አደረጉት” ይላሉ፡፡ የጥፋቱን ጠንሳሾችና አራጋቢዎች እንዳላዩ እያለፉ ከሺርክና ቢድዐ የሚያስጠነቅቁ ሰዎችን ማብጠልጠል መንስኤው ምን እንደሆነ አይጠፋንም፡፡ እውነት ለህዝብ ብትቆረቆሩ ኖሮ ወገናችንን ከዚህ በሺርክ ከተወረረ በዓል ለማዳን ድርሻ በነበራችሁ ነበር፡፡ “ወላኪን ላ ሐያተ ሊመን ቱናዲ!”
“ይህን ሁሉ ጉድ እያወቁ እንዴት ለመውሊድ ይሟገታሉ?” የሚሉ የዋሆች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ጉዳዩ ከራስ የመከላከል ጉዳይ ነው። የኢኽዋን ቡድን መስራች ሐሰን አልበናና ጭፍሮቹ መውሊድ ላይ ሲያቀነቅኑት ከነበሩ ዜማዎች ውስጥ እነዚህ ነበሩ፡-
هذا الحبيب مع الأحباب قد حضرا - وسامح الكل فيما قد مضى وجرى
“ይህ ወዳጃችን ከወዳጆች ጋር ተገኝቷል፡፡
#ያለፈ_የሆነውን_ሁሉ_ይቅር_ብሏል፡፡” [ሐሰን አልበናህ፡ 71-72]
ይሄ ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቁ ሺርክ አይደለምን? ከአላህ ውጭ ወንጀልን የሚምር አለ ወይ?! አላህ ምን እንዳለ አስተውሉ፡-
وَمَنْ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إلاَّ اللهُ
“ከአላህ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምረው ማነው?” [ኣሊ ዒምራን፡ 135]
ነብዩም ﷺ "አላህ ሆይ! ... ካንተ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምር የለም" ይላሉ። [አልቡኻሪይ፡ 8585] [ሙስሊም፡ 2705]
ኢኽዋን ለተውሒድ ደዕዋ እንቅፋት የሚሆነው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ጉዳዩ የሺርክና የቢድዐ ጉዳይ እንደሆነ እያዩ ''በትንንሽ ነገሮች አንጨቃጨቅ" እውነታውን የሚያስቀይሱበት ምክንያቱ ከዚህ የመነጨ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 28/2012)

ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር - አላህ ከክፉ ይጠበቃቸውና - እንዲህ ብለዋል፦
*إنّ فاقد التوحيد ميّت ولو كان يمشي على الأرض ومحقّق التوحيد هو الذي يحيا الحياة الحقيقية
*يقول الله -جلّ وعلا-: {أَوَ مَن كَانَ مَيْتاً فَأَحْيَيْنَاهُ} [الأنعام:١٢٢]. أي أحييناه بالإيمان والتوحيد"*
“ተውሒድ የሌለው ሰው፣ ምድር ላይ የሚንቀሳቀስ ቢሆን እንኳ፣ የሞተ ነው። እውነተኛውን ህይወት የሚኖረው ተውሒድን ያረጋገጠ ነው። የላቀውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
“ሙት የነበረና ሕያው ያደረግነው ሰው…” [አል-አንዓም፡ 122]
ይህም ማለት፡- “በኢማንና በተውሒድ ሕያው አደረግነው” ማለት ነው።
🎙️[“የተውሒድ ደረጃ በሙስሊም ህይወት ውስጥ” ከሚል ኹጥባ የተወሰደ።]

የሌሎችን የቅንጦት ህይወት መከታተል መዘዝ አለው
~
በዱንያ ቅንጦት የሚንደላቀቁ ሰዎችን ህይወት መከታተል፣ በቅንጦት ህይወታቸው ላይ መመስጠት ጉዳት አለው።
1ኛ፦ አላህ የዋለልንን ኒዕማ እንድንክድ ወይም እንድንንቅ በር ይከፍታል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
انْظُرُوا إِلَى مَنْ أَسْفَلَ مِنْكُمْ ، وَلاَ تَنْظُرُوا إِلَى مَنْ هُوَ فَوْقَكُمْ ، فَهُوَ أَجْدَرُ أَنْ لاَ تَزْدَرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ.
"ከናንተ በታች ወደሆኑት ተመልከቱ። እንጂ ከናንተ በላይ ወደሆኑት አትመልከቱ። ይሄ በናንተ ላይ ያለውን የአላህን ፀጋ እንዳታናንቁ ዘንድ የተገባ ነውና።" [ሙስሊም ፡ 7540]
2ኛ፦ በወንጀል ሃብት ያጋበሱ ወይም ባልተገባ መልኩ ገንዘባቸውን የሚያወጡ ሰዎችን የቅንጦት አኗኗር መከታተል፣ በቅንጦታቸው መመሰጥ የነሱን ሁኔታ መውደድን፣ እንደነሱ የመሆን ምኞትን ያወርሳል። ይሄ ደግሞ ቀጥታ ባልፈፀሙት ወንጀል ተጠያቂ መሆንን ነው የሚያስከትለው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
وَعَبْدٌ رَزَقَهُ اللَّهُ مَالًا وَلَمْ يَرْزُقْهُ عِلْمًا، فَهُوَ يَخْبِطُ فِي مَالِهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ، لَا يَتَّقِي فِيهِ رَبَّهُ، وَلَا يَصِلُ فِيهِ رَحِمَهُ، وَلَا يَعْلَمُ لِلَّهِ فِيهِ حَقَّهُ، فَهَذَا بِأَخْبَثِ الْمَنَازِلِ» قَالَ: " وَعَبْدٌ لَمْ يَرْزُقْهُ اللَّهُ مَالًا، وَلَا عِلْمًا فَهُوَ يَقُولُ: لَوْ كَانَ لِي مَالٌ لَعَمِلْتُ بِعَمَلِ فُلَانٍ، قَالَ: هِيَ نِيَّتُهُ، فَوِزْرُهُمَا فِيهِ سَوَاءٌ "
"አላህ ገንዘብን የሰጠው ነገር ግን እውቀትን ያልሰጠው ባሪያ አለ። ገንዘቡን ያለ እውቀት ያባክናል። በገንዘቡ ውስጥ ጌታውን አይፈራም፣ ዝምድናን አይቀጥልም፣ እንዲሁም የአላህን ሐቅ አያውቅም። ይህ ሰው በጣም መጥፎ በሆነ ደረጃ ላይ ይገኛል።”
ከዚያም እንዲህ አሉ፦
“ሌላ ደግሞ አላህ ገንዘብንም ሆነ እውቀትን ያልሰጠው ባሪያ አለ። ‘ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮ እንደዚያ ሰው እሠራ ነበር’ ይላል። ይህ ሰው የኒያውን (የሞኞቱን) ያገኛል። ስለዚህ፣ ሁለቱም ኃጢአታቸው (ወንጀላቸው) እኩል ነው።” [ሙስነድ አሕመድ፡ 18031]
ያ ብልሹ በሆነ መልኩ በዱንያ ፀጋ የሚቀናጣው በዱንያ እየተጣቀመ ነው። እዚያ ሳይደርስ በባዶ የሱን አይነት ህይወት የሚመኘው ግን በምኞቱ ብቻ ወንጀለኛ ስለሚሆን ከሁለት ያጣ ጎመን ነው የሚሆነው።
3ኛ፦ እንዲህ አይነት ህይወት ያላቸውን ሰዎች በፊልም፣ በድራማ መከታተል እነሱን መውደድን ሊያስከትል ይችላል። ልብ በሉ! ሰዎችን መውደድ በኸይርም ይሁን በሸር ጎታች ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
المَرْءُ مع مَن أحَبَّ
"ሰው ከሚወደው ጋር ነው።" [ቡኻሪ ፡ 6168] [ሙስሊም ፡ 2640]
4ኛ፦ ደግሞ ደጋግሞ በሌሎች ህይወት ላይ መመሰጥ ለምቀኝነት ሊያጋልጥም ይችላል።

ግዕዝ ለምን?
~
ግዕዝን የማስተማር አስፈላጊነቱ ምንድነው? በተደጋጋሚ የሚነሱ ማሳመኛ ነጥቦችን እንመልከት (ከአንድ ፖስት ላይ የወሰድኳቸው ናቸው)።
1/ "አብዝሃኞቹ በብራና ላይ የተፃፉ የኢትዮጲያ ሃገር በቀል የሆኑ እውቀቶች የተሰናዱባቸው ድርሳናት የተፃፉት በግእዝ ቋንቋ ነው።"
መልስ፦
ሀ - ሃገር በቀል የሆኑ እውቀቶች ምንድን ናቸው? በግዕዝ ድርሳናት ውስጥ ብቻ የሚገኙ ህዝብ የማያውቃቸው ሃገር በቀል እውቀቶች አሉ? እና እስከዛሬ ለምን ዝም አላችሁ? እውነቱን ለመናገር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናትን ለማዘጋጀት የሚጠይቁ ያልተጠኑ የግዕዝ ድርሳናት የሉም።
ለ - የምትሉት እውነት ከሆነ ይህንን የመመራመር እና ህያው ወደሆነ ቋንቋ የመተርጎሙ ኃላፊነት የምሁራን እንጂ የህፃናት አይደለም። በከፍተኛ ተቋማት የሚሰራ እንጂ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጥ አይደለም። ስለዚህ እነዚህን ህፃናትን እንዲያስተምሩ ከየገዳማቱ ልታመጧቸው የምታስቧቸውን ቄሶችና ዲያቆናት የጥናት አሰራር ስልጠና ስጧቸውና እዚያው ጨርሱ።
2/ "alternative medicines የሚባሉት የኢትዮጲያ ባህላዊ ህክምና የተመሠጠረባቸው የብራና ሰነዶችና ድርሳናት የተፃፉት በግእዝ ነው።"
መልስ፦
ሀ - ይህም ውሸት ነው። ግዕዙ ላይ ዋጋ ያለው የህክምና እውቀት ቢኖር መሪጌታዎች በድግምትና መተት ማስታወቂያ ባላጥለቀለቁን ነበር።
ለ - እውነት ነው ቢባል እንኳ ይህንን የማጥናት ኃላፊነቱ የህፃናት ሳይሆን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ነው።
3/ "በብራና ላይ ተፅፈው የተቀመጡ ሃገር በቀል የስነ ህዋና የስነ ፈለክ ወርጅናሌ ሃሳቦች የተፃፉት በግእዝ ነው።"
መልስ፦
ኧረ እየታፈረ! በዚህ ዘመን እንዲህ ዓይነት ህፃናት የሚያሳምን ውሸት መዋሸት ለምን? ሳይንሳዊ ውጤቶች ካሉ ለምን እስከዛሬ ደበቃችኋቸው? እውነትስ ቢሆን ይህንን የማጥናት ኃላፊነቱ የህፃናት ሳይሆን የኢትዮጵያ የህዋ ሳይንስ ማዕከልኮ ነው።
4/ በእንግሊዝና በአሜሪካ ሙዚየሞች ውስጥ ከኢትዮጲያ ተዘርፈው የተወሰዱ ( በተለይ ከመቅደላ የተዘረፉት) ለቁጥር የሚታክቱ የብራና ላይ መፅሃፍት የተፃፉት በግእዝ ነው ፤
መልስ፦
ለቁጥር የሚታክቱ? ይህም ውሸት ነው። ቢኖር እንኳ ከገድላትና ዜና መዋዕል አይዘልም። ጥቂት ከተገኘ አንድ ተቋም ጥናቱን ለጨርሰው ይችላል።
5/ "ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ መነሻ የሆኑ አንዳንድ እሳቤዎች ከኢትዮጲያ የግእዙ የስነ ቁጥር (mathematics) ፅንሰ ሃሳብ እንደተወሰዱ ይነገራል። "
በግዕዝ የተደበቀ ህክምና፣ ህዋ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ የምትሉትን ቀልድ ተውት። የማይካደው ነገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሃገር ምስረታ ላይ፣ የፅህፈት ስራን በማዳበር ላይ (መነሻው ከኦርቶዶክስ በፊት ቢሆንም) ትልቅ አስተዋጽዖ አላት። ይህንን መካድ አይቻልም። ታሪክ ግን ታሪክ ነው። ሙገሳ ሙገሳውን እየመረጡ መውሰድ አይቻልም። በሃገሪቱ ታሪክ ላይ ጉልህ ሚና ያላት ተቋም አዎንታዊ ነጥቦችን ብቻ እየመረጡ ማስተጋባት ሐቀኛ የታሪክ አዘጋገብ አይደለም። ስለዚህ ለሃገሪቱ ኋላቀርነት፣ ህዝቦች ላይ ለደረሱ ጭቆናና ብዝበዛ፣ ለደረሱ ውድመቶችና ፍጅቶች ድርሻ እንዳላት ማመን ይገባል። ታሪክ ጣፈጠም መረረ እውነተኛ ክስተቶችን የምንዘግብበት እንጂ እንደ ብፌ ደስ ያሰኘንን እየመረጥን የምናነሳበት አይደለም።
እቅጩን ስንነጋገር ግዕዝን ማስተማር ምንም ዓይነት የህክምናም የቴክኖሎጂም የሌላ ዘመናዊ ስልጣኔ እድገትም ሆነ የተደበቀ እውቀት አያመጣም። የህዝብ ለህዝብ ትስስርም አይጨምርም። የሃገርን ሃብት ምንም እሴት በማይጨምር ነገር ከማባከን ዉጭ ለኢኮኖሚ እድገት ምንም አይነት አስተዋፅዖ የለውም። ሌላው ቀርቶ የረባ ሃይማኖታዊ ትርፍም አያመጣም። ይልቁንም ነፍጥ ያነሱ ተዋጊዎችን ልባቸውን ለማማለል ይውል ካልሆነ በስተቀር እንዲህ አይነት የጉልበት ፖሊሲ ጥላቻ ነው የሚያመጣው። ይልቁንም ላይሳካ ነገር እንዲህ አይነት የረባ ዋጋ የሌለው ቋንቋ ለመመለስ አጉል ከመዳከር የሃገር ውስጥ ቋንቋዎችን ወይም ለሚሰደዱ ዜጎቻችን የሚጠቅሙ የውጭ ቋንቋዎችን ማስተማር ነው የሚሻለው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
إنَّ اللَّهَ يَغَارُ، وإنَّ المُؤْمِنَ يَغَارُ، وَغَيْرَةُ اللهِ أَنْ يَأْتِيَ المُؤْمِنُ ما حَرَّمَ عليه
"አላህ ይቀናል። አማኝም ይቀናል። የአላህ ቅናቱ አማኝ የሆነ ሰው ሐራም የተደረገበትን ነገር መፈፀሙ ነው።"
[አልቡኻሪ፡ 5223] [ሙስሊም፡ 2761]

ጭፈራ የነገሰበት የሱፍያ እምነት ከክርስትና ጋር ብዙ የሚመሳሰልበት ነገር አለው።
1⃣ ሁለቱም በምልጃ ስም በ "ቅዱሳን" ላይ ወሰን በማለፍ ፍጡር እየተማፀኑ በፈጣሪ ሐቅ ላይ ሺርክን (ማጋራትን፣ ባእድ አምልኮን) ይፈፅማሉ።
2⃣ ሁለቱም ጭፈራና መዝሙርን እንደ አምልኮ በመቁጠር በቤተ እምነቶች ውስጥ ይጨፍራሉ።
3⃣ ሁለቱም በየ ሃገራቸው የሚገኙ አጉል ባህላትን እምነታዊ ሽፋን በመስጠት ሃይማኖትን ያጠለሻሉ።
4⃣ ሁለቱም ገና ወይም መውሊድ ያከብራሉ።
5⃣ ሁለቱም ከመፅሀፋዊ ማስረጃ ይልቅ
ሸይኾቻቸውን / ቄሶቻቸውን በጭፍን ይከተላሉ።