Forwarded from أبو سلمان
የዐረብኛ_ቋንቋ_የመደበኛ_ትምህርት_ማስታወቂያ_ነሐሴ_2017_ዓ_ል.pdf
748.5 KB
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
እነኾ አል - ኢምቲያዝ የዐረብኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ማዕከል የ1ኛ ዙር የክረምት የዐረብኛ ትምህርት በመጠናቀቅ ላይ መኾኑን ተከትሎ በመደበኛ መርሓ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በመኾኑም ዐረብኛ ቋንቋን በደረጃ ሁለት እና ሶስት (Level II & III) መማር የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ ቀድማችሁ በመመዝገብ የዚህ ወርቃማ ዕድል ተጠቃሚ ትኾኑ ዘንድ ምዝገባ ላይ መኾናችኝን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
💐 መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም
በመደበኛ ፕሮግራም ትምህርት የምንሰጠው በሁለት መንገድ ነው።
🖌 ለአዲስ ጀማሪ ተማረዎች የሚሰጡ ኮርሶች:-
🌹 1ኛ ወሰነ ትምህርት
1/ ትምህርት ጥበብ (فن الدراسة)
2/ የንባብ ክሂል (مهارة القراءة)
3/ የአጻጻፍ ክሂል (مهارة الكتابة)
4/ የማዳመጥ ክሂል(مهارة الاستماع)
5/ የንግግር ክሂል (مهارة الكلام)
🌹2ኛ ተርም
1/ የዐረብኛ ሰዋሰው (علم النحو)
2/ የዐረብኛ የቃላት እርባታ (علم التصريف)
3/ የዐረብኛ አጻጻፍ ህግጋት (علم الإملاء)
🌹3ኛ ወሰነ ትምህርት
1/ የዐረብኛ የአነጋገር ዘይቤ መግቢያ (المدخل إلى البلاغة العربية)
2/ የማስተማር ሥነ ዘዴ(طرائق التدريس)
ደረጃ 2 ነው።
🖌 ተማሪዎቹ መሠረታዊ እውቀት ካላቸው ግን ከመጀመሪያው ጀምረው ክህሎቶችንና ህግጋቶችን አቀላቅለው የሚማሩ ይኾናል።
💐 ለበለጠ መረጃ ከላይ የተያያዘውን የpdf ዶሴ ማንበብ ትችላላችሁ።
ቻናላችንን ለመቀላቀል የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ👇👇👇
https://www.tgoop.com/+hZ1PJc9IJMswNjI8

የዐረብኛ_ቋንቋ_የበይነ_መረብ_ትምህርት_ማስታወቂያ_ነሐሴ_2017_ዓ_ል.pdf
742.3 KB
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
እነኾ አል - ኢምቲያዝ የዐረብኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ማዕከል የ1ኛ ዙር የክረምት የዐረብኛ ትምህርት በመጠናቀቅ ላይ መኾኑን ተከትሎ በመደበኛ መርሓ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በመኾኑም ዐረብኛ ቋንቋን በደረጃ ሁለት እና ሶስት (Level II & III) መማር የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ ቀድማችሁ በመመዝገብ የዚህ ወርቃማ ዕድል ተጠቃሚ ትኾኑ ዘንድ ምዝገባ ላይ መኾናችኝን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
💐 በበይነ መረብ(online) ፕሮግራም ትምህርት የምንሰጠው በሁለት መንገድ ነው።
🖌 ለአዲስ ጀማሪ ተማረዎች የሚሰጡ ኮርሶች:-
🌹 1ኛ ወሰነ ትምህርት
1/ የትምህርት ጥበብ (فن الدراسة)
2/ የንባብ ክሂል (مهارة القراءة)
3/ የማዳመጥ ክሂል(مهارة الاستماع)
4/ የንግግር ክሂል (مهارة الكلام)
🌹2ኛ ተርም
1/ የዐረብኛ ሰዋሰው (علم النحو)
2/ የዐረብኛ የቃላት እርባታ (علم التصريف)
3/ የዐረብኛ አጻጻፍ ህግጋት (علم الإملاء)
🌹3ኛ ወሰነ ትምህርት
1/ የዐረብኛ የአነጋገር ዘይቤ መግቢያ (المدخل إلى البلاغة العربية)
2/ የማስተማር ሥነ ዘዴ(طرائق التدريس)
ደረጃ 2 ነው።
🖌 ተማሪዎቹ መሠረታዊ እውቀት ካላቸው ግን ከመጀመሪያው ጀምረው ክህሎቶችንና ህግጋቶችን አቀላቅለው የሚማሩ ይኾናል።
💐 ለበለጠ መረጃ ከላይ የተያያዘውን የpdf ዶሴ ማንበብ ትችላላችሁ።
ቻናላችንን ለመቀላቀል የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ👇👇👇
https://www.tgoop.com/+VlaUOlzN2qcxYWM0

ኢብኑ ዐውን ረሒመሁላህ :
"ሱናን አደራችሁን! ሱናን አደራችሁን! ቢድዐዎችን ተጠንቀቁ!" ይሉ ነበር፣ እስከሚሞቱ ድረስ! [ሸርሑ ሱና፣ በርበሃሪይ ፡ 126]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

የሰው እዳ ወይም ብድር ያለበት ሰው በቻለ ጊዜ ከመመለስ ሊዘናጋ አይገባም። እዳ በጣም ከባድ ነገር ነው ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል :-
يُغْفَرُ لِلشَّهِيدِ كُلُّ ذَنْبٍ، إِلَّا الدَّيْنَ
"ለሸሂድ ሁሉም ወንጀሉ ይማርለታል፣ እዳ ሲቀር!" [ሙስሊም፡ 1886]
ጥለነው ለምንሄደው ዱንያ ብለን ኣኺራችንን እንዳናበላሽ።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
يُغْفَرُ لِلشَّهِيدِ كُلُّ ذَنْبٍ، إِلَّا الدَّيْنَ
"ለሸሂድ ሁሉም ወንጀሉ ይማርለታል፣ እዳ ሲቀር!" [ሙስሊም፡ 1886]
ጥለነው ለምንሄደው ዱንያ ብለን ኣኺራችንን እንዳናበላሽ።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
እዳ ገብቶ መክፈል ያቃተውን ሰው ጊዜ መስጠት ይገባል። ሐራም ላይም ቢሆን የትም ገብተህ አምጣ አይባልም። ይልቁንም ጊዜ መስጠት ይገባል። እዳውን መቀነስ ወይም ከእዳው ነፃ ማድረግ ደግሞ የበለጠ ሶደቃ ነው። አላህ እንዲህ ይላል ፦
{ وَإِن كَانَ ذُو عُسۡرَةࣲ فَنَظِرَةٌ إِلَىٰ مَیۡسَرَةࣲۚ وَأَن تَصَدَّقُوا۟ خَیۡرࣱ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ }
"የድህነት ባለቤት የሆነም (ባለዕዳ) ሰው ቢኖር እማግኘት ድረስ ማቆየት ይገባል። (ይቅር በማለት) መመጽወታችሁ ደግሞ ለእናንተ በላጭ ነው። የምታውቁ ብትሆኑ (ትሠሩታላችሁ)።" [አልበቀረህ: 280]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
{ وَإِن كَانَ ذُو عُسۡرَةࣲ فَنَظِرَةٌ إِلَىٰ مَیۡسَرَةࣲۚ وَأَن تَصَدَّقُوا۟ خَیۡرࣱ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ }
"የድህነት ባለቤት የሆነም (ባለዕዳ) ሰው ቢኖር እማግኘት ድረስ ማቆየት ይገባል። (ይቅር በማለት) መመጽወታችሁ ደግሞ ለእናንተ በላጭ ነው። የምታውቁ ብትሆኑ (ትሠሩታላችሁ)።" [አልበቀረህ: 280]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አራቱ መዝሀቦች
~
የፊቅህ መዝሀቦች አመሰራረት፣ መደራጀትና እድገት የተለያዩ ደረጃዎችን አሳልፏል። ነገሩን ለማሳጠር ያህል በዘመናት ሂደት ውስጥ እንደ የአውዛዒይ፣ የለይሢይ፣ የዟሂሪይ፣ ... መዝሀቦች እየከሰሙ አራት መዝሀቦች ቀርተዋል። እነዚህም የሐነፊያ፣ የማሊኪያ፣ የሻፊዒያ እና የሐንበሊያ መዝሀቦች ናቸው። በኢማሞቹ የዘመን ቅደም ተከተል መሰረት እንመልከት፡-
1. የሐነፊያ መዝሀብ:-
* ኢማሙ፦ አቡ ሐኒፋ አንኑዕማን ብኑ ሣቢት (80 - 150 ሂጅራ)
* መነሻ:- ዒራቅ - ኩፋ፣ ከዚያም በበግዳድ አድርጎ እየሰፋ ሄዷል።
* ዋና መለያ፦ ከቁርኣንና ሐዲሥ ቀጥተኛ ማስረጃ ባለፈ ከሌሎቹ መዝሀቦች በሰፋ መልኩ ግላዊ አስተያየት (ረእይ) እና ንፅፅር (ቂያስ) ይጠቀማል። በዚህ የተነሳ ከጥንት ጀምሮ የከረረ የዑለማእ ትችት አስተናግዷል።
* የተሰራጨባቸው ሃገራት፦ የባልካንና የካውካዝ ሃገራት፣ ቱርክ፣ ዒራቅ፣ ሶሪያ፣ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ቻይና፣ ወዘተ.። በዓለም ላይ ከሁሉም መዝሀቦች በበለጠ ከፍተኛ ስርጭት አለው። ለዚህም ምክንያቱ አብዛኛውን የሙስሊሙን ዓለም ረዘም ላለ ጊዜ የገዙት የ0ባሲዮች እና የኦቶማን ቱርኮች ጠንካራ ድጋፍ የነበረው በመሆኑ ነው።
2. የማሊኪያ መዝሀብ:-
* ኢማሙ፦ ማሊክ ብኑ አነስ (93 - 179 ሂጅራ)
* መነሻ:- ሒጃዝ - መዲና
* ዋና መለያ፦ ከቁርኣንና ሐዲሥ ቀጥተኛ ማስረጃ በተጨማሪ የመዲና ሰዎችን ልማድና ትውፊት እንደማስረጃ ይወስዳል። በዚህኛው ነጥብ የተነሳ የሚሰነዘርበት ነቀፌታ አለ።
* የተሰራጨባቸው ሃገራት፦ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት፣ ምእራብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ደቡባዊ ግብፅ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ሰሜን ናይጀሪያ፣ ሴኔጋል፣ ማሊ፣ ወዘተ.
3. የሻፊዒያ መዝሀብ:-
* ኢማሙ፦ ሙሐመድ ብኑ ኢድሪስ አሽሻፊዒይ (150 - 204 ሂጅራ)
* መነሻ:- ዒራቅ - በግዳድ፣ ኋላም ከግብፅ እየሰፋ ሄዷል።
* የተሰራጨባቸው ሃገራት፦ ሻም፣ ምስራቅ አፍሪካ፣ የመን፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣ ግብፅ በከፊል፣ ወዘተ. ። በስርጭት መጠኑ ከሐነፊያ መዝሀብ ቀጥሎ ሁለተኛ ላይ ይቀመጣል። ለዚህም አንዱ ምክንያት የአዩባውያን (ሶላሑዲን አል አዩቢይ እና ወራሾቹ) ጠንካራ ድጋፍ ስለነበረው ነው።
4. የሐንበሊያህ መዝሀብ ፦
* መሪው፦ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል፣ (164-241 ሂጅራ / 780-855 ዓ.ም.)
* የተመሰረተው :- ዒራቅ - በግዳድ
* የተሰራጨባቸው ሃገራት፦ በዋናነት የዛሬዋ ሰዑዲያ፣ በስሱ በግዳድ፣ ደማስቆ፣ የገልፍ ሃገራት፣ ወዘተ. ከሁሉም መዝሀቦች ዝቅተኛ ስርጭት አለው።
በሀገራችን
=
በዋናነት የሐነፊያ እና የሻፊዒያ መዝሀቦች የሚገኙ ሲሆን ሱዳን አዋሳኝ ቤኒሻንጉል ክልል የማሊኪያ መዝሀብ ይገኛል። ዛሬ ዛሬ ደግሞ የሰዑዲያ ዑለማኦችን ኪታቦች ተከትሎ በተደራጀ መልኩ ባይሆንም የሐንበሊያ መዝሀብ እየተንፀባረቀ ነው።
በአኢማዎቹ መካከል የነበረው ግንኙነት
* ኢማሙ አሕመድ የኢማሙ ሻፊዒይ ተማሪ ናቸው። ኢማሙ ሻፊዒይ ደግሞ የኢማሙ ማሊክ ተማሪ ናቸው።
ማሳሰቢያ
~
1. እነዚህ መዝሀቦች በፊቅህ ርእስ ያሉ የኢጅቲሃድ መስመሮችን የሚጠቁሙ እንጂ መሰረታዊ የ0ቂዳ ልዩነቶችን ለማሳየት የተቀመጡ አይደሉም።
2. እነዚህ አኢማዎች የተለየ መዝሀብ ለመመስረት ብለው አልተነሱም፣ በዚህም ላይ አልጣሩም። ይልቁንም እውቀታቸውን ለተማሪዎቻቸው አስተላለፉ። እያለ በሂደት ራሱን የቻለ ቅርፅ እየያዘ መጣ። እነዚህ መዝሀቦች ከነዚህ ኢማሞች በፊት አልነበሩም። በነብያችን ﷺ ዘመን ሶሐቦች ቀጥታ ከሳቸው ይማራሉ እንጂ ሐነፊ፣ ማሊኪ፣ ... የሚባል አልነበረም። በሶሐቦችና በታቢዒዮች ዘመንም ደግሞ ሰዎች ዲናቸውን በዘመኑ ከነበሩ አዋቂዎች ይማሩ ነበር እንጂ ሻፊዒይ፣ ሐንበሊይ፣ ... የሚባል አልነበረም። በተጠቀሱት አራቱ ኢማሞች ዘመንም ሆነ ከነሱ በፊት ሌሎች እጅግ በርካታ ኢማሞች ነበሩ። ሰዎች ሌሎችን ሁሉ ጥለው ከነዚህ ብቻ የሚማሩ፣ የነሱን መንገድ ብቻ የሚከተሉ አልነበሩም። እነሱ ራሳቸውም እኛን ብቻ ተከተሉ አላሉም። ይልቁንም ሰዎች ማስረጃን እንዲከተሉ ነው ያስተማሩት።
3. በነዚህ መዝሀቦች ውስጥ የሚገኙ ብይኖች ሁሉ ሙሉ በሙሉ የዋናዎቹ ኢማሞች ብቻ የሚባሉ አይደሉም። ይልቁንም በተማሪዎቻቸው ወይም ኋላ በመጡ የመዝሀቦቹ ተከታዮች የተቀመጡ ብዙ ነጥቦች አሉ።
4. ስርጭትን በተመለከተ በአንድ መዝሀብ በተለየ ሳይገደቡ፣ በማስረጃ እየመዘኑ ሚዛን የሚደፋውን የሚከተሉ፣ ወይም በዚህ መልኩ የሚጓዙ ዓሊሞችን ትንታኔ እየተመለከቱ የሚጓዙ ብዙ አሉ።
"ለምን የተለያዩ መዝሀቦች ኖሩ?"፣ "በነሱ ላይ ብቻ ታጥሮ መጓዝስ ግዴታ ነው ወይ?" የሚለውን በቀጣይ ክፍል እናያለን ኢንሻአላህ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 23/2017)

“በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ ደጋፊዎች ምርኩዝ
~
እጅግ ከሚገርሙ ነገሮች ውስጥ አንዱ መጤ ለሆነው መውሊድ ቁርኣንና ሐዲሥ የሚያጣቅሱ ሰዎችን ማየት ነው። ይሄ የሚያሳየው ሰዎቹ ምን ያክል ለቁርኣንና ሐዲሥ ተገቢ ክብር የማይሰጡ፣ ሐያእ የቀለላቸው እንደሆኑ ነው። መውሊድ በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ'ኮ፦
* ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት በሶሐቦቹ፣ በታቢዒዮቹ፣ በአትባዑ ታቢዒን፣ በታላላቅ ቀደምት ኢማሞች ይከበር ነበር።
* እናንተ እንደምትሉት በሙዞፈር እስከሚጀመር ስድስት ክ/ዘመን መቆየት ሳያስፈልገው በኸሊፋዎቹ ይፈፀም ነበር።
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ በዚህ ቢድዐ ላይ ውዝግብ ባልተነሳ ነበር።
* በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ ነቃፊ ዑለማዎች ቀርቶ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣ ዒራቂ፣ ተዝመንቲ፣… ያሉ የመውሊድ ደጋፊዎች ጭምር ቢድዐ ነው ብለው ባልደመደሙ ነበር። ቁርኣንና ሐዲሥ ውስጥ የሚገኝ ጉዳይ ቢድዐ ነው ይባላል'ንዴ?!
እነዚህን እውነታዎች ይዘን ከዚያም እነዚህ አካላት ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናሉ ብለው የሚጠቅሷቸውን የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ብንመለከት ስራቸው አይን ያወጣ ማምታት እንደሆነ እንደመድማለን። ምክንያቱም የሚጠቅሷቸው አንቀፆችና ሐዲሦች መውሊድን የሚጠቁሙ ቢሆኑ ኖሮ በዚያ እንቁ ዘመን ይከበር ነበርና። በዚያ ዘመን መውሊድ አለመከበሩ እነዚህ አታላዮች ለአንቀፆቹ የሚሰጧቸው ትርጓሜዎች የተሳሳቱ ለመሆናቸው በቂ ማሳያ ነው።
ባጭሩ ለነዚህ አካላት የምንሰጣቸው ጥቅል ምላሽ የትኛውም የቁርኣን አንቀፅ ወይም የሐዲሥ ትርጓሜ ዋጋ የሚኖረው የቀደምቶችን ግንዛቤ የተከተለ ሲሆን ብቻ ነው። ሱብኪ አንዲትን የቁርኣን አንቀፅ ከሰለፎች አንድም ባልቀደመው መልኩ በመፈሰሩ የተነሳ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ ምላሽ ሲሰጡት እንዲህ ነበር ያሉት፡-
“ይሄ ተፃራሪ ይህቺን አንቀፅ የፈሰረበት መንገድ በርግጠኝነት ውድቅ ነው። ሐቅ ቢሆን ኖሮ (ቀደምቶቻችን) በእውቀትም፣ በተግባርም፣ በማመላከትም፣ በመምከርም ይቀድሙን ነበር። በየትኛውም አንቀፅ ወይም ሱና ላይ በሰለፎች ዘመን ያልነበረ፣ እነሱ ያላወቁትና ለህዝቡ ግልፅ ያላደረጉት የሆነን ትንታኔ መፍጠር አይቻልም። እንዲህ ማድረግ እነሱ በዚህ ላይ ሐቁን ዘንግተውና ከሱም አፈንግጠው ኖሮ ይሄ ዘግይቶ የመጣው ተቃዋሚ አግኝቶታል ማለት ነው።” [አሷሪሙል ሙንኪ፡ 247]
በነገራችን ላይ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣… ያሉ ዓሊሞች መውሊድ በሰለፎቹ ዘመን ያልነበረ ቢድዐ ነው ብለው በግልፅ ሲናገሩ አስተዋይ የሆነ ሰው ትልቅ የሚወስደው ቁም ነገር አለ። ይሄውም ለዚህ ቢድዐ ቁርኣንና ሐዲሥን ማጣቀስ ስህተት እንደሆነ። ይህንን ከያዝን በኋላ ሱፍዮች ለመውሊድ ቢድዐ ጠንካራ ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱትን አንድ የቁርኣን መልእክት እንመልከት፡-
{قُلۡ بِفَضۡلِ ٱللَّهِ وَبِرَحۡمَتِهِۦ فَبِذَٰلِكَ فَلۡيَفۡرَحُواْ هُوَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ}
{“በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ይደሰቱ። እርሱ ከሚሰበስቡት ሃብት በላጭ ነው” በላቸው።} [ዩኑስ፡ 58]
እና በዚህ ውስጥ መውሊድን የሚደግፍ ምን መልእክት አለ? ብትሉ “በአላህ እዝነትና ችሮታ እንድንደሰት ታዘናል፤ ከእዝነቶችና ችሮታዎቹ ሁሉ በላጩ ደግሞ የነብዩ ﷺ መወለድ ነው። ስለዚህ መውሊዳቸውን ማክበር በዚች አንቀፅ ውስጥ ተካቷል” ይላሉ።
መልስ፡-
=
አዎ አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ችሮታውና እዝነቱ ተብሎ የተጠቀሰው ምንድነው በሚለው ላይ “ቁርኣን”፣ “ዲን”፣ “ኢስላም”፣ “ኢማን”፣ “ከቁርኣን ሰዎች ማድረጉ”፣ “ሱናዎች”፣ “ጀነት” ወዘተ የሚሉ ተፍሲሮችን በቀዳሚነት ብናገኝም ነብያችንንም ﷺ የሚያካትት ይሆናል። ይህንን የሚጠቁም ተፍሲር ኢብኑል ጀውዚ፣ ሲዩጢና ኣሉሲ አስፍረዋል። በርግጥ ሶስቱም በቀዳሚነት ያሰፈሩት ይህንን አይደለም። ሱፍዮች ግን ቀዳሚዎቹን ጥለው እዚህ ላይ ነው የሚያነጣጥሩት። ቢሆንም ብዙም የሚያሳስብ አይደለም። መልእክቱ ጠቅላይ ነውና እዚህ ላይ ከተጠቀሱት ውጭ ባሉ የጌታችን ችሮታዎች ጭምር እንደሰታለን፣ እናመሰግነዋለንም። ነገር ግን፦
1. የአንቀጿ መልእክት በነብያችን ﷺ ላይ የተገደበ ባልሆነበት እንዲያውም ሌሎቹ ተፍሲሮች ቀዳሚ በሆኑበት ነጥሎ እሳቸውን ብቻ የታሰቡ አድርጎ ማቅረብ ማምታታት ነው።
2. በቁርኣን፣ በሐዲሥ፣ በኢስላም፣ በኢማን፣ ... ለመደሰት አመት መጠበቅ እንደማያስፈልገን ሁሉ በነብዩ ﷺ ለመደሰትም አመት መጠበቅ አያስፈልገንም። ይሄ ሱፍያዊ ፈጠራ ነው። አመት ጠብቆ ያልዘለለ ሰው በነብዩ ﷺ መልላክ አልተደሰተም ብሎ ማሰብም ቀሽም ስሌት ነው።
3. የአንቀጿ መልእክት ሙሉ በሙሉ ነብዩን ﷺ የሚገልፅ ነው ቢባል እንኳን አመት ጠብቃችሁ መውሊድ አክብሩ የሚል ጭብጥ በቅርብም በሩቅም የለም። እነዚህ አካላት ግን ካልተጨፈረ ካልተዘለለ ደስታ ያለ አይመስላቸውም። በዚያ ላይ የልደት ቀናቸው በቁርጥ አለመታወቁን ጨምሩበት።
4. የአንቀጿ መልእክት ለመውሊድ ማስረጃ ቢሆን ኖሮ ቀደምቶች እየተሰባሰቡ መውሊዳቸውን ያከብሩ ነበር። ይሄ ተግባር በዚያ ዘመን አለመፈፀሙ የቁርኣኑ መልእክት መውሊድን ፈፅሞ እንደማያካትት በቁርጥ ያስረዳል።
5. ሰለፎች መውሊድን ያላከበሩት ስላልተመቻቸው ነው የሚለውን ሱፍያዊ ማምታቻ ለጊዜው ብንቀበል እንኳ ሰለፎቻችን ከተፍሲሮቻቸው ውስጥ ያሰፍሩት ነበር። ልብ በሉ የመውሊድ አክባሪዎች ከዘመናት በኋላ መጥተው መልእክቱን ጠምዝዘው ለዚህ ቢድዐ እስከሚጠቀሙበት ድረስ ይህቺን አንቀፅ ለመውሊድ መረጃ ያደረገ አንድ እንኳን የለም። ሙልሀም እንደሆኑ ከተመሰከረላቸው ዑመር፣ ቁርኣንን እንደወረደ መቅራት የፈለገ ከሱ ይምማር ከተባለላቸው ኢብኑ መስዑድ፣ ቱርጁማኑል ቁርኣን ከተባሉት ኢብኑ ዐባስ፣ ከቁርኣን ሰብሳቢዎቹ ዑስማንና ዘይድ ኢብኑ ሣቢት፣ ከነ ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ … የሙፈሲሮች ሸይኽ ከሚባሉት ከሙጃሂድ፣ ከነቀታዳ፣ ከነዶሓክ፣ ከነሻፊዒይ፣ ከነማሊክ፣ ከነ ጦበሪ፣... እንዴት ተሰወረ? እነዚህ ሁሉ ያላወቁትን ነው ከዚያ በኋላ የመጣ ትውልድ የሚያውቀው?!
6. በነዚህ ሰዎች ስሌት ከተሄደ የሶሐቦችንም መውሊድ ማክበር ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ሶሐቦች አላህ ለኡማው ከዋላቸው ፀጋዎች ውስጥ ናቸው። የነብዩ ﷺ ሚኒስትሮችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች ነበሩ። ሶሐቦች ለዚህ ኡማ ባለውለታ ናቸው። ቁርኣኑም ሐዲሡም ያለነሱ ወደኛ መድረስ አይችልም ነበር። ስለዚህ አላህ ለኛ ከዋለልን ውለታዎች፣ ከትሩፋቱ፣ ከእዝነቱ ናቸው። አላህ ደግሞ በትሩፋቱና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ስለዚህ የእያንዳንዱ ሶሐቢይ መውሊድ መከበር አለበት። በተለይ ደግሞ ኹለፋኡ ራሺዲን። ውለታቸውም ደረጃቸውም ከፍ ያለ ነውና። ኧረ እንዲያውም በአንቀጿ ውስጥ “ትሩፋቱ” ሲባል የተፈለገው ነብዩን ﷺ ለማለት ሲሆን “እዝነቱ” የሚለው ደግሞ “ዐሊይን ነው” የሚል ዘገባ ከኢብኑ ዐባስ እንደተላለፈ ኸጢብ እና ኢብኑ ዐሳኪር ገልፀዋል። [ሩሑል መዓኒ፡ 6/133]

ከነሱ ቀጥሎ የመጡት ታቢዒዮችም እንዲሁ እነሱስ ባይኖሩ ቁርኣኑ ሐዲሡ እንዴት ይደርሰን ነበር? አትባዑ ታቢዒንም እንዲሁ። እንዲያውም ነብዩ ﷺ የመጀመሪያዎቹን ትውልዶች ከሰው ሁሉ በላጭ እንደሆኑ ጠቅሰዋል። ለሙስሊሞች ያላቸው ውለታ ከባድ ነው። የአላህ ችሮታና እዝነቱ ናቸው። ስለዚህ በአንቀጿ መልእክት ውስጥ ይካተታሉ። ተገቢው አተረጓጎም ሐሰን ታጁ እንደሚለው እዝነትና ችሮታ የሚሉ ፅንሰ-ሀሳቦችን ሁሉንም ሊያካትት በሚችል መልኩ መረዳት ነው። ስለዚህ የነዚህን ሁሉ መውሊድ ማክበር አለብን። የዑለማዎችንም እንዲሁ። በቃ! እንዲህ ይሻላል? አገር ምድሩን ከኦርቶዶክስ በላይ በበዓል ማጥለቅለቅ? ቁርኣንን በግምት፣ በስሜት መተንተን የት እንደሚያደርስ አስቡት። መቋጫ የሌለው ውጥንቅጥ!! ዑለማዎች አንድ ሰው ቁርኣንን በግምት ተንትኖ ሐቁ ቢያጋጥመው እንኳን ወንጀለኛ ከመሆን አይተርፍም ይላሉ።
ስናጠቃልል {በአላህ ችሮታና በእዝነቱ በዚህም ይደሰቱ} የሚለውን ሰለፎች አመት ጠብቀው ለመውሊድ ሳይሰባሰቡ ሲፈፅሙት እንደኖሩት ዛሬም ያለ መውሊድ መፈፀም ይቻላል። ታዲያ ከአንቀጿ አንፃር የመውሊድ አስፈላጊነት ምኑ ላይ ነው? “የለም መልእክቷን በተግባር ለማስገኘት መውሊድ የግድ አስፈላጊ ነው” የሚል ካለ መውሊድ ከመጀመሩ በፊት ያለፉ ትውልዶች አንቀጿን ወይ አልተረዷትም፤ አለያ ደግሞ አልተገበሯትም እያለ እየከሰሳቸው ነው። ይሄ ከባድ ውንጀላ ነው። ሶሐቦች፣ ታቢዒዮች፣ አትባዑ ታቢዒንና በቅርብ የተከተሏቸው ትውልዶች ይህቺን አንቀፅ ባብራሩበት ውስጥ ከመውሊድ ጋር አያይዘው የፈሰሩበት አንድ ማስረጃ የለም። ነብዩ ﷺ ራሳቸውም ረቢዑል አወልን እየጠበቁ በቡድንም ይሁን በነጠላ ያከብሩ እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ ቀርቶ ሽታውም የለም። ስለዚህ የአንቀጿ መልእክት ለመውሊድ ማስረጃ እያደረጉ ያሉ አካላት በዚህ ትንታኔያቸው ከቁርኣንም፣ ከሐዲሥም፣ ከሰለፎች አረዳድም ያፈነገጡ ናቸው። ይህም አንቀጿን ለዚህ ቢድዐ ማዋል ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሆነ ያሳያል። ምክንያቱም አንቀጿ ውስጥ “ይደሰቱ” የሚለው ቃል ከሰለፍ እስከ ኸለፍ ባሉ የቁርኣን ተንታኞች ዘንድ በመውሊድ የተተካበት አጋጣሚ የለምና። ይህቺን አንቀፅ መነሻ በማድረግ ተጨማሪ ዒድ መደንገግ ይቻላል የሚል አንድም ጥንታዊ ሙፈሲር የለም፤ አንድም!!
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 23/2014)
=
የቴሌግራም ሊንክ፦

በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
~
በመውሊድ በዓላት የተነሳ የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይረከሳል፡፡ ይሄ ደግሞ አላህ እንዲህ ሲል ከሃ ^ዲዎችን ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡-
(وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَیۡتِ إِلَّا مُكَاۤءࣰ وَتَصۡدِیَةࣰۚ)
"በቤቱ (በከዕባ) ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡" [አልአንፋል፡ 35]
የአራቱም መዝሀብ ተከታዮች ይህንን ድርጊት ያወግዛሉ፡፡ በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ “ወደ አላህ እቃረባለሁ፣ ዒባዳ ነው” የሚል እምነት አደገኛ ብል ^ግና ነው፡፡ እንዲያውም ይሄ ከክርስቲያኖች የተኮረጀ ጥመት ነው፡፡ ዛሬም ዝላይና ጭፈራን አምልኮት ያደረጉት እነሱ ናቸው፡፡ ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው፡፡ ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው፡፡ እንዲያውም ኢብኑል ጀውዚይ እንዲህ ብለዋል፡-
وقد نفر جماعة من المتصوفة خلقًا من الخلق عن الكسب، وأوحشوا بينهم وبينه، وهو دأب الأنبياء والصالحين، وإنما طلبوا طريق الراحة، وجلسوا على الفتوح، فإذا شبعوا، رقصوا، فإذا انهضم الطعام، أكلوا، فإذا لاحت لهم حيلة على غنيٍّ، أوجبوا عليه دعوةً، إما بسبب شكر، أو بسبب استغفار. وأَطَمُّ الطامات ادعاؤهم أن هذا قربةٌ! وقد انعقد إجماع العلماء أن من ادعى الرقص قربة إلى الله تعالى، كفر،
“በርግጥም ብዙ ሱፍዮች በርካታ ህዝቦችን ስራ ከመስራት አርቀዋል፡፡ በሱ (በስራ) እና በነሱ መካከል ባይተዋርነትን አንግሰዋል፡፡ እሱ (ስራ) የነብያትና የደጋጎች ፈለግ ነው፡፡ እነዚህ የፈለጉት ግን የእረፍትን መንገድ ነው፡፡ በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ ምግቡ ሲፈጭ ይበላሉ፡፡ በሃብታም ላይ የሆነ ብልጠት ሲገለጥላቸው በምስጋና ወይም በንስሃ ስም ግብዣ እንዲያዘጋጅ ግድ ያደርጉበታል፡፡ ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው እንደሚከ ^ፍ -ር በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]
ኢማሙ ማሊክ፡- “እኛ ዘንድ ሱፍያ የሚባሉ ሰዎች አሉ፡፡ በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ፡፡ ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ” ሲሏቸው
“ህፃናት ናቸው?” ብለው ጠየቁ፡፡
“አይደሉም” አሏቸው፡፡
“እብ ^ዶች ናቸው?” ሲሉ
“አይደሉም፡፡ ሸይኾች ናቸው” አሏቸው፡፡
“እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም” አሉ፡፡ [ተርቲቡል መዳሪክ: 2/53]
አቡበክር አጦርጡሺይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“የሱፍያ አካሄድ ቦዘኔነት፣ መሀይምነትና ጥመት ነው፡፡ ኢስላም ማለት የአላህ ቁርኣንና የመልእክተኛው ሱና እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ዳንስና ውዝዋዜ የመጀመሪያ የፈጠሩት የሳሚሪይ ባልደረቦች ናቸው (በነብዩ ሙሳ ዘመን)፡፡ ያኔ ድምፅ ያለው የወይፈን አካልን አምላክ ሲያደርግላቸው ጊዜ መጥተው ዙሪያውን ይጨፍሩና ይወዛወዙ ነበር፡፡ ማለትም ጭፈራ የከሃዲዎችና የወይፈን አምላኪዎች ሃይማኖት ነው፡፡ የነብዩ ﷺ እና የሶሐቦቻቸው ጉባኤ ልክ ከራሳቸው ላይ ወፍ ያረፈ እስከሚመስል መረጋጋት ነበራቸው፡፡ እነዚህን (ጨፋሪ) ሰዎች አሚሩ መስጂድ ውስጥም ይሁን ሌላ ቦታ (ጭፈራቸውን) ከመፈፀም ሊከለክላቸው ይገባል፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ከነሱ ጋር ሊካፈል፣ በጥፋትም ላይ ሊያግዛቸው አይፈቀድለትም፡፡ የማሊክም፣ የአቡ ሐኒፋም፣ የሻፊዒይም፣ የአሕመድም፣ የሌሎችም ሙስሊም ምሁራን መዝሀብ ይህን ነው የሚያዝዘው፡፡” [ተፍሲሩል ቁርጡቢይ፡ 11/238]
ይህንን ይዘን በየመውሊዱ መስጂድ ውስጥ በጫት ጠንብዘው ድቤ እየደለቁ፣ ለፉጨት የቀረበ ድምፅ እያወጡ፣ ቀረርቶ በመሰለ ድምፅ እያላዘኑ የሚወዛወዙ የጠመጠሙ መሃይ -ማንን አስቡ፡፡ ከአላህ ቤት ጭፈራ ዲን ሆኖ ሲቀርብ ተመልከቱ፡፡ አላሁል ሙስተዓን!
=
የቴሌግራም ቻናል፦

አምራለሁ ብላ ተኩላ፣ አይኗን አጠፋች ቸኩላ!
~
በውስጣችን ያሉ ችግሮች ብዙ ዓይነት ናቸው። እነዚህን ችግሮች መተራረማችን የልእልናችን መሰረት ነው። "በላጭ ህዝብ ሆናችሁ" የሚለው ሰማያዊ አዋጅ ስር ለዚህ ብልጫ ሁለት ምሰሶዎች ናቸው የተጠቀሱት። ከኢማን በተጓዳኝ የተጠቀሰው በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነው። የመተራረም እሴት በሌለበት ህዝባዊ አንድነት አይኖርም።
እግር ከወርች ጠፍረው ካሰሩን ችግሮች ውስጥ ታዲያ አንዱ ዘረኝነት ነው። የሚጎመዝዛቸው ቢኖሩ እንኳ በዚህ ጉዳይ ላይ ደጋግመን መነጋገር አለብን። በርእሱ መነሳት ውስጡ የሚደፈርሰው የችግሩ ሰለባ ነው። ዘረኝነት የእልፎችን ህይወት እየነጠቀ፣ ንብረት እያወደመ፣ ትዳር እያፈረሰ፣ ደዕዋ እያደናቀፈ ነው። ዘረኝነት የብዙዎችን ዐቂዳ እየናደ ነው። በዘረኝነት የተነሳ ከላ ኢላሀ ኢለላህ ገመድ ይልቅ ለዘር ትስስር ቅድሚያ እየተሰጠ ነው። ዘረኝነትም አይነት አለው። ላ ኢላሀ ኢለላህ የሚልን ሙስሊም ቋንቋው ስለተለየ ብቻ ያለምንም በደል ከሌላ ጋር ተሰልፎ መቅጠፍ በርግጠኝነት ነፍስ ማጥፋት ከሚባለው እጅግ ሰቅጣጭ ጥፋት የራቀ ጥፋት ነው። ይሄ ወደ ክህ ^ደት የሚሻገር ወንጀል ነው።
እንዲህ አይነትን ጥፋት ማውገዝና ማስተማር የሁሉም ኃላፊነት ቢሆንም የተሻለ ውጤት ለማምጣት ግን ሁሉም በራሱ ዘር ላይ ቢሰራ የተሻለ ነው። ምክንያቱም መካሪው ከሌላ ዘር ሲሆን ምክርን ከመቀበል ይልቅ በዘር ጥላቻ መፈረጅ ነው የሚታየው። መካሪው የራስ ሲሆን ግን ችግሩ ባይጠፋም ይቀንሳል። ስለዚህ የኦሮሞውን ኦሮሞው፣ የአማራውን አማራው፣ የትግሬውን ትግሬው፣ የአፋሩን አፋሩ፣ የስልጤውን ስልጤው፣ የጉራጌው ጉራጌውን፣ ... ሲናገረው የተሻለ ይሆናል። ሌላው ላይ እንደሚደረገው ተናጋሪውን በዘር ጥላቻ መፈረጅ አይኖርም። እንዲያ የሚያደርግ ቢኖር እንኳ ገበያ አያገኝም። ይሄ ወሳኝ ጉዳይ ግን ባለቤት አጥቷል። ዱዓቱ መሻይኹ ሁሉ የዘረኝነትን አደጋ ለራሱ ወገኖች እያስተማረ አይደለም። እንዲያውም በዚህ ኃላፊነት ላይ የሚጠበቀው አካል የቫይረሱ ተሸካሚ፣ የበሽታው አስተላለፊ እየሆነ ነው። ይሄ ለወገን መቆርቆር ሳይሆን ሞት ነው፣ የሞት ሞት!! የገዛ ወገንን ዲኑን መጉዳት፣ ኣኺራውን ማጨለም።
በሌላ በኩል ቀደም ብየ እንደገለፅኩት ሁላችንም አንድ ህዝብ ነንና እከሌ ጋር የተከሰተውን ችግር ብሄራቸው ስለተለየ ብቻ ሌሎች ዝም ይበሉ እያልኩ አይደለም። ነገር ግን አንድ ጥንቃቄ ያስፈልገናል። ብዙ ጊዜ እንደሚስተዋለው መነቃቀፍችን፣ መተራረማችን ብሽሽቅ የተጫጫነው ሊሆን አይገባም። የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ እንዳይሆንም መጠንቀቅ አለብን። የሆነ ጥፋት በአንድ "የሌላ" ብሄር ሰው ሲፈፀም ሆ ብለን ተነስተን ከአጥፊው አልፈን ሌሎቹንም በጅምላ ስንጎነትል ብንውል፤ ነገ "ከኛ" የሆነ በሽተኛ ተነስቶ ፀያፍ ቃል ሲናገር "እነሱም" በተራቸው በጅምላ ይነሳሉ። ጉዳዩ ከምክክር ይልቅ ብሽሽቅና ፉክክር ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ ከጅምላ ፍረጃ ልንርቅ ይገባል። ችግሩንም ላንቀርፍ የችግሩ አካል ያልሆኑ ወገኖቻችንን ወይ ወደ ጠርዝ እንገፋቸዋለን። ወይ ያለ ጥፋታቸው እናሸማቃቸዋለን። ችግራችንን እንፈታለን ብለን ይበልጥ እንዳናወሳስበው መጠንቀቅ ይገባል። ችግር የምንፈታበት መንገድ የጋራ ቤታችንን ባገናዘበ መልኩ መሆን አለበት። "ትኋን በዛ ብየ ቤቴን አላቃጥልም" የሚባል ድንቅ ብሂል አለ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 15/ 2015)

📢 አስደሳች ዜና 🆕
⭐️ታላቅ የቁርአን ሒፍዝ ምርቃት ፕሮግራም⭐️
⏩መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዐሪ የቁርአን ሒፍዝ ማእከል በበጋና በክረምት ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን እሁድ ነሀሴ 25/20117 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በደማቅ ፕሮግራም እንደሚያስመርቅ ስናበስረዎ በታላቅ ደስታ ነው ።
🔈በፕሮግራሙም ላይ የተላያዩ መሻዪኾችና ኡስታዞች የሙሐደራ ግብዣ ይኖራቸዋል ።
በመሆኑም እርሶ የፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል ።
🗂አድራሻ: አጠና ተራ እፎይታ የገቢያ ማእከል አዳራሽ
❗️ማሳሰቢያ: የ አዳራሽ መግቢያ ምንም አይነት ክፍያ ስለሌለው ቦታ ሳይሞላባቹህ ቀድማቹህ እንድትገኙ ሰንል እናሳስባለን .
☹️😭🙁🙁🙁🙁🙁🙁
✉️ የመርከዙ የቴሌግራም አድራሻ
⤵️
https://www.tgoop.com/merkezabumussa1

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
“ሶሐቦቼን የተሳደበ አላህ ከእዝነቱ ያርቀው” ብለዋልና። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5111]
=
ቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
“ሶሐቦቼን የተሳደበ አላህ ከእዝነቱ ያርቀው” ብለዋልና። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5111]
=
ቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የመውሊድ አደጋዎች
~
ከመውሊድ ቢድዐ የምናስጠነቅቀው መነዛነዝ ስለሚያምረን፣ በአጉል ቡድንተኝነት ተነሳስተን ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን እነዚህ አደጋዎች ስላሉበት ወገናችን እንዲነቃ በማሰብ ነው።
1. መውሊድን ማክበር የነብዩን ﷺ እና የምርጥ ትውልዶቻቸውን ፈለግ መጣስ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَتَّبِعۡ غَيۡرَ سَبِيلِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصۡلِهِۦ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرًا)
{ቅኑም መንገድ ከተገለፀለት በኋላ መልእክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከአማኞቹም መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሰው በተሾመበት ላይ እንሾመዋለን። ጀሀነምንም እንከተዋለን። መጨረሻይቱም ከፋች።} [አኒሳእ፡ 115]
2. መውሊድ “ዒባዳ ነው” ብሎ የሚያስብ ሰው “ዲኑ ሙሉእ ነው” የሚለውን ጌታ እያስተባበለ፣ ነብዩ ﷺ አደራቸውን አልተወጡም እያለ እየሞገተ ነው። ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፡- “በኢስላም ውስጥ መልካም ናት ብሎ የሚያስባትን ቢድዐ የፈጠረ ሰው ሙሐመድ ﷺ ተልእኳቸው ላይ ሸፍጥ ሰርተዋል ብሎ እየሞገተ ነው። ምክንያቱም አላህ {ዛሬ ለናንተ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ} ብሏልና።” [ዳሪሚይ፡ 141]
ነብዩ ﷺ በመሰናበቻው ሐጅ ላይ “አጥብቃችሁ ከያዛችሁት ከሱ በኋላ የማትጠሙበትን ነገር በርግጥም ትቼላችኋለሁ፣ የአላህን ኪታብ። እናንተ ስለኔ ትጠየቃላችሁና ምንድን ነው የምትሉት?” ሲሉ ሶሐቦችም “አንተ በርግጥም እንዳደረስክ፣ አደራህን እንደተወጣህና እንደመከርክ ነው የምንመሰክረው” አሉ። ይህኔ አመልካች ጣታቸውን ወደ ሰማይ እያነሱ ከዚያም ወደ ሰዎቹ እየጠቆሙ “ጌታዬ ሆይ! መስክር” አሉ ሶስት ጊዜ በመደጋገም። [ሙስሊም፡ 3009]
3. የመውሊድ ቢድዐን የሚፈፅም ሰው የማይመነዳበትን ከንቱ ልፋት እየለፋ ነው ያለው። ነብዩ ﷺ “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እሱ (ስራው) ተመላሽ (ውድቅ) ነው” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 3/69] [ሙስሊም፡ 4590]
4. ይህን ቢድዐ የሚፈፅም ሰው ጥመት ላይ ነው። ነብዩ ﷺ “መጤ የሆኑ ነገሮችን ተጠንቀቁ። መጤ ፈሊጥ ሁሉ ፈጠራ ነው። ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ ወደ እሳት ነው” ብለዋል። [ኢርዋኡል ገሊል፡ 608]
5. መውሊድ የሚያከብርና እንዲከበር የሚሟገት ሰው ከሸሪዐዊ ነፀብራቆች ውስጥ አንዱ የሆነውን ነብዩን ﷺ የመውደድ ፅንሰ-ሀሳብን እያዛባ ነው። እሳቸውን ስለመውደድ፣ ስለማክበርና ስለመከተል የሚያትቱ ብዙ የቁርኣን አያዎችን፣ ሐዲሦችንና የሰለፎች ንግግሮችን ቀደምቶቻችን ባልተረዱት መልኩ በመተንተን እነሱ ላልፈፀሙት ቢድዐ ማስረጃ በማድረግ ነብዩን ﷺ መውደድ ማለት መውሊድን ማክበር፣ በሶለዋት ስም መጨፈር ተደርጎ እንዲሳል ተደርጓል። ይህ ምን ያክል እሳቸውን የመውደድ ሸሪዐዊ ነፀብራቅ እየተዛባ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
6. መውሊድን ማክበር በአንድምታ ቀደምቶቻችንን በነገር መውጋት አለበት። ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ከኛ በበለጠ ነብዩን ﷺ የሚወዱ ከመሆናቸው ጋር መውሊድን አላከበሩም። ዛሬ መውሊድን የሚያከብረው የነብዩ ﷺ ወዳጅ፣ የሚቃወመው ደግሞ የሳቸው ጠላት ተደርጎ እየተሳለ ነው። በነዚህ ሰዎች አረዳድ መሰረት ቀደምት ሰለፎች ነብዩን ﷺ “አይወዱም ነበር” ማለት ነው። ይሄ አደገኛ ነገር ነው። እነዚያ ለነብዩ ﷺ ሲሉ አጥንታቸውን የከሰከሱ፣ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ ቤታቸውን ያፈረሱ፣ ገንዘባቸውን የለገሱ ሶሐቦች መውሊድን ስላላከበሩ እሳቸውን “አይወዱም” ቢባል ማን ያምናል?!
7. መውሊድ በአብዛኛው ከባባድ የሆኑ ሺርኮች ይፈፀሙበታል። ቀብር ጦዋፍ የሚያደርጉ፣ ለቀብር ሱጁድ የሚወርዱ፣ ለቀብር የሚሳሉ፣ የቀብር አፈር ለበረካና ለፈውስ የሚወስዱ፣ በጥብጠው የሚጠጡ፣ ስለት የሚወስዱ፣... አሉ። መንዙማዎቹ እራሳቸው በሺርክ የታጨቁ ናቸው። {አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም።} [አኒሳእ፡ 48]
8. መውሊድ ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል አለበት። የነብይን ልደት በዓል አድርጎ መያዝ ክርስቲያናዊ ሱና ነው። ክርስቲያኖች ገናን የሚያከብሩት የዒሳ ልደት ነው በሚል እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ነብዩ ﷺ “ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል። [ኢርዋኡል ገሊል፡ 1269]
9. መውሊድ ውስጥ ብዙ አይነት ድንበር ማለፍ አለ። በነብዩ ﷺ ላይ፣ በሌሎችም ሙታኖች ላይ ድንበር ማለፍ ይፈፀማል። ይሄ በእለቱ በሚነበቡ ግጥሞች፣ መንዙማዎችና ዶሪሖች ላይ በሰፊው የሚንፀባረቅ ነው። ነብዩ ﷺ ግን “ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ ዒሳን ድንበር አልፈው እንዳወደሱት አታወድሱኝ” ይላሉ። [ጋየቱል መራም፡ 123]
አንዳንዶች በድፍረት የመውሊድ ሌሊት ከለይለተል ቀድር የበለጠ ነው ብለው እስከሚሞግቱ ደርሰዋል። [አልመዋሂቡ ለዱንያህ፡ 1/135] ሱብሓነላህ! ይህ ሁሉ የሚባለው እንግዲህ የተወለዱበት ቀን አወዛጋቢ ከመሆኑ ጋር ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው የተወለዱት በሌሊት እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ በሌለበት ነው። በዚያ ላይ የተወለዱበት ጊዜ ከ 14 ከፍለ-ዘመናት በፊት ያለፈ እንጂ እንደ ለይለተል ቀድር በያመቱ የሚመላለስ አይደለም። ዐልዩል ቃሪ (1014 ዓ. ሂ.) “(የለይለተል ቀድር) በላጭነት ዒባዳ በሷ ውስጥ በላጭ ስለሆነ እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም። ይህም {መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር በላጭ ናት} በሚለው ቁርኣናዊ ምስክርነት ነው። ለመውሊዳቸው ግን ይህቺ ብልጫ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከሙስሊሙ ህዝብ ዑለማዎች ከአንድም አትታወቅም!!” ይላሉ። [አልመውሪዱ ረዊይ፡ 97]
10. መውሊድን ከኢስላማዊ በአላት ውስጥ ማካተት ሁለት አመታዊ በዓል ያደረጉልንን ነብይ ትእዛዝ መጣስ ነው። ነብዩ ﷺ መዲና ሲገቡ ነዋሪዎቿ የሚጫወቱባቸው ሁለት ቀናት ነበሯቸው። “ምንድን ናቸው እነዚህ ሁለት ቀናት?” ሲሉ ጠየቁ። “በጃሂሊያው ጊዜ እንጫወትባቸው ነበርን” አሉ። ይህኔ “የላቀው አላህ ከነሱ በላጭ በሆኑ ሁለት ቀናት ተክቶላችኋል። እነሱም የአድሓ ቀን እና የፊጥር ቀን ናቸው” አሉ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1039]
11. የመውሊድ በዓልን ማክበር ለሌሎች የቢድዐ በዓላት በር መክፈት ነው። የወልዮች ልደት እያሉ በመቃብር ዙሪያ ለሚልከሰከሱ፣ የልጆች አመታዊ ልደት ለሚያከብሩ ሰዎችና ለሌሎችም ምርኩዝ ማቀበል ነው።
12. የመውሊድ ኪታቦችና የመውሊድ ድግሶች በነብዩ ﷺ ስም በሚነገሩ የውሸት ቂሷዎች የታጨቁ ናቸው። “አብዛኛው በመውሊድ ደስኳሪዎች እጅ ያለው ውሸትና ቅጥፈት ነው” ይላሉ መውሊድ ደጋፊ የሆኑት ሰኻዊ። [አልመውሊዱ ረዊይ፡ 32] መልእክተኛው ﷺ ግን “በኔ ላይ ሆን ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ” ይላሉ። [ቡኻሪ፡ 1291] [ሙስሊም፡ 5]
13. በመውሊድ የቢድዐ ድግስ ላይ ነብዩ ﷺ “ከጭፈራው ይታደማሉ” የሚል ሰቅጣጭ እምነት አለ። የቅጥፈታቸው ቅጥፈት የመውሊዱ ሌሊት ላይ “ነብዩ መጡ” እያሉ ከተቀመጡበት መነሳታቸው ነው። በነገራችን ላይ ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኋላ ቀርቶ በህይወት እያሉ እንኳን ሲመጡ ሶሐቦች አይነሱላቸውም ነበር። [አሶሒሐ፡ 358] ሀይተሚ እንዲህ ይላል፡“የዚህ አምሳያው ብዙዎች የነብዩ ﷺ ልደትና እናታቸው እሳቸውን መውለዷ ሲወሳ የሚያደርጉት መቆም ሲሆን ይህም ምንም አይነት መረጃ ያልመጣበት ቢድዐ ነው።” [አልፈታወል ሐዲሢያህ፡ 58]

14. በመውሊድ በዓላት የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይረከሳል። ይሄ ደግሞ አላህ ከሃዲዎችን እንዲህ ሲል ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ ነው፡-
(وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ)
{በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አልአንፋል፡ 35]
ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር በአራቱም መዝሀብ የተወገዘ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው። ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው። ኢብኑል ጀውዚይ፡ “ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጭቷል” ብሏል። [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]
15. ብዙ የመውሊድ ዝግጅቶች የሴትና የወንድ ቅልቅል በብዛት አለባቸው። የብል -ግና መናሃሪያ እየሆኑም ነው። በእለቱ እቃ እያዞሩ የሚሸጡ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮንዶምና መሰል ነገሮችን እንደሚይዙ ተጨባጭ መረጃ አለ። በአንዳንድ አካባቢዎች ሴተኛ አዳሪዎች መውሊድ በሚከበርበት አካባቢ የተለያዩ ነገሮችን ለመሸጥ በሚል ሽፋን ጊዜያዊ ዳስ በመቀለስ ለጥፋት እንደሚሰማሩ ከሰበሰብኳቸው መረጃዎች አረጋግጫለሁ።
መቅሪዚይ በ790 ሂጅሪያ በዒማዱል አንባኒ በተዘጋጀው መውሊድ ላይ የታዘበውን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡- “ሜዳው በዓሊሞች እስከሚጨናነቅ ህዝብ ጎረፈ። በዚያች ሌሊት ሴቶችና ወጣቶች ከባለጌዎች ጋር በመቀላቀላቸው ምክንያት ብዙ አይነት ብልግናዎች ተፈፀሙ። ማለዳ ላይ ሌሊቱን የተጠጡ ከሃምሳ በላይ የአስካሪ መጠጥ እንስራዎች በዛውያው ዙሪያ በነበሩ እርሻዎች ውስጥ ተጥለው እንደተገኙ፣ በርካታ ደናግላንም ክብረ-ንፅህናቸው እንደተገሰሰ፣ በጣም ብዙ ገንዘብ የወጣባቸው ሻማዎችም እንደተለኮሱ እጅግ በርካታ መረጃ ወጥቷል። በማግስቱ ጧት አላህ የንፋስ ጥቃት ላከባቸውና ከቦታው የነበሩ ሰዎችን ፊታቸውን አፈር አለበሳቸው። ድንኳኖቹንም ቆራረጣቸው። አንድም ሰው ባህር መሳፈር አልቻለም። ከዚያን ጊዜ በኋላ መውሊድ አልተዘጋጀም።” [ዱረሩል ዑቁዲል ፈሪዳህ፡ 2/501]
16. የመውሊድ ጨፋሪዎች በውዝውዛኔና መሰል ነገሮች ሰውነታቸው ዝሎ ሌሊቱን ገፍተው ስለሚተኙ አብዛኞቹ የፈጅር ሶላትን የተወሰኑት ደግሞ ዙህርንም ጭምር አይሰግዱም። ለነገሩ ክፍለ - ሃገር ላይ አብዛኛው ታዳሚ ከነጭራሹ ሶላት ሰጋጅ አይደለም።
17. መውሊድ ለማክበር አገር አቋርጠው ረጃጅም ርቀቶችን የሚጓዙ ሰዎች ሞልተዋል። ነብዩ ﷺ ግን ለቢድዐ ቀርቶ ለአላህ ታስቦ ለሚፈፀመው አምልኮት እንኳን ከሶስቱ መስጂዶች (መስጂደል ሐራም፣ መዲና የነብዩ መስጂድ እና አቅሷ) ውጭ አገር አቋርጦ መጓዝ እንደማይገባ አሳስበዋል። [ቡኻሪ፡ 1189] [ሙስሊም፡ 3450] አገር አቋርጠው ያለ መሕረም የሚጓዙ ሴቶችም ቀላል አይደሉም። ነብዩ ﷺ ግን “ማንኛዋም ሴት ከቅርብ ወንድ ቤተሰቧ ጋር እንጂ እንዳትጓዝ” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 1862]
18. መውሊድ የልዩነት መንሰኤ ነው። ለዚህም መውሊድ በተቃረበ ቁጥር የሚነሳውን ውዝግብ መስማቱ ብቻ በቂ ነው። በመውሊድ ላይ ስላልተጋሯቸው ብቻ “ወሃ ~ ቢ”፣ “የነቢ ጠ ^ላት”፣ “ከአይ ^ ሁድ በከፋ ዲን ያበላሹ” እያሉ ሙስሊሞችን መወንጀል የተለመደ ዘመቻ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “ቢድዐ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው።” ስለዚህ ቢድዐው እስካለ ድረስ መለያየቱ አይቀርም። ሸውካኒይ እንዲህ ይላሉ፡- “ደግሞም ይሄ መውሊድ ከተከሰተ በኋላ ውዝግቡ ተጧጡፏል። በዚህም ላይ የሚፃፉት ኪታቦች ከከልካዩም ከፈቃጁም በዝተዋል። … ከነሱ ውስጥ እንደማይፈቀድ ቁርጥ አድርጎ የተናገረ ሲኖር ከነሱ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፣ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም።” [አልፈትሑ ረባኒ፡ 2/1091-1095]
ጥፋቶቹ እነዚህ ብቻ አይደሉም። ይህን ሁሉ ጉድ አጭቆ የያዘ ቢድዐ ከጥቃቅን ነገሮች ነውን? ህሊና ያለው ይፍረድ። በርግጥ ከነዚህ ጥፋቶች ውስጥ ከፊሎቹን የሚርቁ አሉ። ግና አንደኛ ጥቂት ናቸው። ሁለትኛ እነዚህ እራሱ ድግሳቸውን በሺርክ የተቀላቀለ መንዙማ ባዮችን ይጋብዙበታል። ከሺርኩ ቢጠራም ድርጊቱ በራሱ መረጃ የለውምና ከቢድዐነት አይዘልም። ሶስተኛ በጥፋት የተወረረውን መውሊድ ሊያወግዙ ቀርቶ የሚያወግዙትን የሚነቅፉ ናቸው። ስለሆነም ጥፋታቸው ከነዚያኞቹ ጥፋት ብዙም የራቀ አይደለም።
=
ኢብኑ ሙነወር

ታቢዒዩ ሶፍዋን ብኑ ሱለይማን እንዲህ ብለዋል፦
ليأتين على الناس زمان ، تكون هِمّةُ أحدهم فيه : بطنُهُ،
ودينُهُ : هواه.
"በሰዎች ላይ ሀሳባቸው ሁሉ ሆዳቸው፣ ሃይማኖታቸው ደግሞ ስሜታቸው የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል።"
[አልጁዕ፣ ኢብኑ አቢ ዱንያ ፡ 261]