Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
أَوَ هكذا حُبُّ النبيِّ الهادي
طَبْلٌ و رقصٌ في ربوع بلادي؟
أبِِمثْلِ هذا يُحْتَفَى بـ(محمدٍ)
عِطْرِ الزمانِ وقِبلةِ القُصَّادِ؟
بِدَعٌ ودَرْوَشةٌ وجهلٌ مُطبقٌ
و خرائفٌ وُرِثَتْ من الأجدادِ
هل جاء (أحمدُ) كي يُربىَ أمةً
لتَهُدَّ عرشَ الهَزْلِ والإلحادِ؟
وتُحاصرَ الطاغوتَ في أوكارهِ
وتَدقَّ رأسَ الشركِ والأوغادِ؟
وتُقَدِّمُ الإسلامَ حلوا ناصعا
دينا جميلا كاملَ الأَبعادِ؟
أَمْ جاءَ يدعو الناس كى يتراقصوا
في يوم مولدهِ مع الإنشادِ؟؟
أَيُفَاخِرُ الهادي ملائكةَ السما
بمديح جُهَّالٍ وهَذْيِ الشادي؟
أيُسَرُّ (أحمدُ) بامتداحٍ كاذبٍ
والناس غَرقَى في لَظى الإفسادِ؟
أيسرُ بالحَلْوى نَلُوكُ صنوفَها
والقتلُ في كشميرَ في بغدادِ؟
أتطيبُ نفسُ المصطفى وبقدسِنا
جُرحٌ عميقٌ راسخٌ الأوتاد؟
لو أنَّ حُبَّ(محمدٍ) هو ما نَرَى
طَرَبٌ وحَلوَي رَنَّةُ الأعوادِ
وَوُرُودُ أضرحةٍ ونصبُ موالدٍ
وتمايلٌ بالرأسِ والأجسادِ
وتَنَكُرٌ لجراحِ إخوةِ دينِنا
مادام جُرحا لم يصل لبلادي
وتَنَصلٌ من جوعِ (صوماليةٍ)
مادام عندي مُؤنةٌ من زادِ
فلبئس هذا الحبُّ .حبٌّ كاذبٌ
نَصَّابُ يبغي مَسْحَة الزُّهَّادِ
كَرِهَ الرسولُ خروجكَم فلتخسأوا
في دُوركِم يا زُيَّفَ العُبَّادِ
حــُـبُّ النـبيِّ تَمَسُّكٌ بحــديثه
وكذا اتباعُ النصحِ والإرشاد ِ
حبُّ النبىِّ تَعَقـُّلٌ وتدبــرٌ
وشريعة بُنيت علي الإسنادِ
حبُّ النبىِّ تَحررٌ لعقولنا
من فاسدِ الموروثِ والأصفاد ِ
حبُّ النبيِّ تماسك وترابط
في وجه كل محارب ومعادي
حبُّ النبيِّ ريادةٌ وتقدمٌ
نحو العلا وصناعة الأمجادِ
حبُّ النبيِّ بِسيْرِنا في دَربِه
قدمٌ على قدمٍ بكل حيادِ
حبُّ النبيِّ سعادةٌ بقدومه
مَنْ غير (أحمدَ) مصدرُ الإسعادِ؟؟
لولاه كان الكون منزوعَ السَّنا
لولاه عِشنا في دُجَىً وفسادِ
فلتفرحوا ولتنشدوا لعيالكم
قُصوا حديثَ الغارِ للأحفادِ
إن السعادة بالحبيب عبادةُ
تُؤْتَى بكلِّ تأدبٍ ورشادِ
لا بابتداعٍ كــــاذبٍ ومُلَفـَّـقٍ
أسموه زورًا (حفلةَ الميلادِ)
…………………………………………
@ لا صوفية في الإسلام
طَبْلٌ و رقصٌ في ربوع بلادي؟
أبِِمثْلِ هذا يُحْتَفَى بـ(محمدٍ)
عِطْرِ الزمانِ وقِبلةِ القُصَّادِ؟
بِدَعٌ ودَرْوَشةٌ وجهلٌ مُطبقٌ
و خرائفٌ وُرِثَتْ من الأجدادِ
هل جاء (أحمدُ) كي يُربىَ أمةً
لتَهُدَّ عرشَ الهَزْلِ والإلحادِ؟
وتُحاصرَ الطاغوتَ في أوكارهِ
وتَدقَّ رأسَ الشركِ والأوغادِ؟
وتُقَدِّمُ الإسلامَ حلوا ناصعا
دينا جميلا كاملَ الأَبعادِ؟
أَمْ جاءَ يدعو الناس كى يتراقصوا
في يوم مولدهِ مع الإنشادِ؟؟
أَيُفَاخِرُ الهادي ملائكةَ السما
بمديح جُهَّالٍ وهَذْيِ الشادي؟
أيُسَرُّ (أحمدُ) بامتداحٍ كاذبٍ
والناس غَرقَى في لَظى الإفسادِ؟
أيسرُ بالحَلْوى نَلُوكُ صنوفَها
والقتلُ في كشميرَ في بغدادِ؟
أتطيبُ نفسُ المصطفى وبقدسِنا
جُرحٌ عميقٌ راسخٌ الأوتاد؟
لو أنَّ حُبَّ(محمدٍ) هو ما نَرَى
طَرَبٌ وحَلوَي رَنَّةُ الأعوادِ
وَوُرُودُ أضرحةٍ ونصبُ موالدٍ
وتمايلٌ بالرأسِ والأجسادِ
وتَنَكُرٌ لجراحِ إخوةِ دينِنا
مادام جُرحا لم يصل لبلادي
وتَنَصلٌ من جوعِ (صوماليةٍ)
مادام عندي مُؤنةٌ من زادِ
فلبئس هذا الحبُّ .حبٌّ كاذبٌ
نَصَّابُ يبغي مَسْحَة الزُّهَّادِ
كَرِهَ الرسولُ خروجكَم فلتخسأوا
في دُوركِم يا زُيَّفَ العُبَّادِ
حــُـبُّ النـبيِّ تَمَسُّكٌ بحــديثه
وكذا اتباعُ النصحِ والإرشاد ِ
حبُّ النبىِّ تَعَقـُّلٌ وتدبــرٌ
وشريعة بُنيت علي الإسنادِ
حبُّ النبىِّ تَحررٌ لعقولنا
من فاسدِ الموروثِ والأصفاد ِ
حبُّ النبيِّ تماسك وترابط
في وجه كل محارب ومعادي
حبُّ النبيِّ ريادةٌ وتقدمٌ
نحو العلا وصناعة الأمجادِ
حبُّ النبيِّ بِسيْرِنا في دَربِه
قدمٌ على قدمٍ بكل حيادِ
حبُّ النبيِّ سعادةٌ بقدومه
مَنْ غير (أحمدَ) مصدرُ الإسعادِ؟؟
لولاه كان الكون منزوعَ السَّنا
لولاه عِشنا في دُجَىً وفسادِ
فلتفرحوا ولتنشدوا لعيالكم
قُصوا حديثَ الغارِ للأحفادِ
إن السعادة بالحبيب عبادةُ
تُؤْتَى بكلِّ تأدبٍ ورشادِ
لا بابتداعٍ كــــاذبٍ ومُلَفـَّـقٍ
أسموه زورًا (حفلةَ الميلادِ)
…………………………………………
@ لا صوفية في الإسلام
በአንዳንድ አካባቢዎች መቃብር ውስጥ ጀናዛ ከተቀበረ በኋላ ዘወትር ደዕዋ ማድረግ የተለመደ ነው። ይህንን ልማድ በተመለከተ ዓሊሞች ምን ይላሉ?
ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ቀብሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ነቢያችን ﷺ ምክር የሰጡበትን ሁኔታ ሐዲሦችን ከጠቀሱ በኋላ ነገር ግን፣ ይህ ምክር ሰዎች ዘወትር የሚቀጥሉበት ቋሚ ልማድ መሆን የለበትም። ምክንያቱም በዚህ መልኩ አይደለምና የተገኘው። ቋሚ አድርጎ መያዝ ከሱና ጋር የሚገጥም አይደለም ይላሉ።
ምንጭ፦ https://www.tgoop.com/ibnhezam/19005
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦
"ማናችሁም አዋቂ ሆኖ አልተወለደም። እውቀት የሚገኘው በመማር ነው።" [አልኣዳቡ ሸርዒየህ፣ ኢብኑ ሙፍሊሕ፡ 1/35]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
"ማናችሁም አዋቂ ሆኖ አልተወለደም። እውቀት የሚገኘው በመማር ነው።" [አልኣዳቡ ሸርዒየህ፣ ኢብኑ ሙፍሊሕ፡ 1/35]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ግእዝን ለህፃናት ማስተማር አስገድዶ ማጥመቅ ነው!
~
ትናንት ጀምሮ የአማራ ክልል መስተዳድር ግዕዝን በክልሉ ባሉ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓመተ ልደት እንዲሰጥ ሊያስገድድ እንደሆነ የሚገልፅ ደብዳቤ ሲዘዋወር እያየን ነው። ይሄ ሲበዛ ነውረኛ አካሄድ ነው። ይሄ የራስን ማንነት በሌሎች ህዝቦች ላይ የመጫን አጉል ትምክህት ነው። ይሄ አሁንም ክልሉ ዘመናቸውን ባልዋጁ ጠባብ ጠርዘኞች እየተዘወረ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሁነኛ ማሳያ ነው።
በቅድሚያ ለማንም እንደማይሰወረው ግእዝ ጣእረ ሞት ላይ ያለ ቋንቋ ነው። የመጨረሻ እስትንፋሱ ላይ ስለሆነ እንደ ህዝብ ለማንም አይጠቅምም። ወንዝ አያሻግርም አልልም፣ እሱ ሩቅ ነገር ነው። ከጎረቤት ሃገር ቀርቶ ከጎረቤት ህዝብ ጋር አያገበያይም። ኧረ ከቤትህ ቀጥሎ ካሉት ከጎረቤትህ ሰዎች ጋር፣ ኧረ ከቤተሰብህ ጋር ለሰላምታ አይሆንም። እና በምን እዳቸው ነው ልጆቻችን ላይ የማይጠቅም ሸክም የሚጫንባቸው?
እንዲያውም ግእዝን ለህፃናት ማስተማር አይጠቅምም ብቻ ሳይሆን ጎጂ ነው። አዎ እንደ ሙስሊም ይጎዳናል። አስገድዶ ማጥመቅ ነው። ግእዝ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በማይነጠል መልኩ ተጣብቆ የተሰፋ ነው። የማስተማሪያ መሳሪያው እንዳለ "መፅሀፍ ቅዱስ" ነው። ይሄ ማለት የኦርቶዶክስ እምነትን በጨቅላ ሙስሊም ህፃናት ላይ መጫን ነው። ይሄ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የማይጠበቅ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ ነው። ትናንት በአፄው ዘመን አስኮላውን በግብረ ገብ ስም ክርስትና ማስተማሪያ፣ በጫና ማጥመቂያ ቦታ ስላደረጉት በርካታ ሙስሊም አልተማረም። ዛሬም ሙስሊሙን ከትምህርት ገበታ ለማራቅ የተጠነሰሰ ሴራ ነው።
ግእዝን በመደበኛ ትምህርት ውስጥ ለህፃናት ማስተማር ከሴኩላሪዝም ጋር አይሄድም። አዎ! ግእዝን ማስተማር ቀጥታ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ለመጨፍለቅ ማመሀኛ የሚደረገውን ሴኩላሪዝም መጣስ ነው። ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ስንት አይነት በደል እንደሚፈፀም አስቡ። አንዴ በሴኩላሪዝም ስም እምነታቸውን በግል እንዳያንፀባርቁ ይከለክላሉ። አሁን ደግሞ በቋንቋ በማስታከክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የግድ እንዲማሩ ሊደረጉ ነው። ይሄ እብሪተኝነት ነው። ይሄ የክልሉ ስልጣን በእጃችን ስለሆነ ያሻችንን ልናደርግባችሁ እንችላለን ምን ታመጣላችሁ ማለት ነው። ከፈለጋችሁ ለራሳችሁ ልጆች አስተምሩ። ያ ሲሆን ራሱ ለሙስሊሙም ህዝብ ልጆቹን በዐረብኛ የማስተማር አማራጭ ሊመቻችለት ይገባል።
ይልቅ ለልጆች ለምን የሚጠቅማቸውን አታስተምሩም? ልጆች አስራ ምናምን አመት ተምረው መቼ እንግሊዝኛ ይናገራሉ? እሱን አታስተካክሉም? መማር ካለባቸው ለምን ባቅራቢያቸው ያሉ ህዝቦችን ቋንቋ አይማሩም? ገዳም ውስጥ የአልጋ ቁራኛ የሆነ ቋንቋ ከሚማሩ ትግርኛ፣ አፋርኛ፣ ኦሮምኛ ቢማሩ የተሻለ ይጠቀማሉ። ከግእዝ ይልቅ ልጆች ዐረብኛ ቢማሩ የተሻለ ሃገራዊ ፋይዳ አለው። ዐረብኛ አለማቀፍ ቋንቋ ነው። ከ 20 ያላነሱ ዐረብ ሃገራት አሉ። በሌሎች ሙስሊም ሃገራት ውስጥ በሰፊው አለ። ዋና መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረትም አንዱ ኦፊሻል ቋንቋው ዐረብኛ ነው። ከዚህም ባሻገር እጅግ ሰፊ ወገናችን ዐረብ አገር ነው ያለው። ዐረብኛ ለኢትዮጵያ የውጭ ቋንቋ አይደለም። በሃገራችን ቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ የበርታ ህዝብ ዐረብኛ በሰፊው ይናገራሉ። በሃገር ውስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ለ0ረብኛ የቀረበ ሰፊ ህዝብ አለ። ስለዚህ ልጆች ዐረብኛ ቢማሩ ትርፉ ብዙ ነው። ዐረብኛ ቋንቋን ከኢስላም ጋር አያይዞ የሚፀየፍ አካል፣ ኢትዮጵያ የዐረብ ሊግ አባል ብትሆን የተሻለ ትጠቀማለች ብለው አንዳንዶች ሲፅፉ ከኢስላም ጋር አያይዞ የሚበረግግ አካል ግእዝን ካልተማራችሁ ብሎ ሙስሊሙ ላይ ሊጭን አይገባም።
ሳጠቃልል ግእዝ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በታች ባለ ደረጃ ፈጽሞ በአስገዳጅ መልኩ ልጆች ላይ ሊጫን የማያገባው ቋንቋ ነው። በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ተማሪዎች በምርጫቸው ሊማሩት ይችላሉ። አሁን የቀረበው ህፃናት ላይ የመጫን ውሳኔ ግን የክልሉን ህዝብ ብዝሀነት ከግንዛቤ ያላስገባ ጨፍላቂ አሰራር ስለሆነ ሊቆም ይገባል።

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
"ቋንቋ መማር ምን ችግር አለው?" ይላሉ። ከመፅሀፍ ቅዱስ ገልብጠህ እያመጣህ፣ በቄስ እያስተማርክ ነው ችግር የሌለው? ከቁርኣን እየቀዱ የሚያስተምሩ ሸይኾች ቢመደቡባችሁ ዝም ልትሉ ነው? የክልሉ መንግስት ዐረብኛን በሁሉም ዞኖቹ ግዴታ ቢያደርግ ልትቀበሉ ነው? እየተዋወቅን! ያውም ዐረብኛ እና ግእዝ የሚወዳደሩ ካለመሆናቸው ጋር።
1. ዐረብኛ - በሁለት አህጉር ውስጥ በሚገኙ 22 ሀገራት፣ ከ332 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ይነገራል። በዓለም ላይ በተናጋሪ ብዛት 5ኛ ቋንቋ ነው።
* ግእዝስ? በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅፅር ግቢ ውስጥ ተጠልሎ ነው ያለው።
2. ዐረብኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የብዙ ዓለማቀፍና አህጉራቀፍ ተቋማት ኦፊሻል ቋንቋ ነው።
* ግእዝስ? ከሃይማኖታዊ ግልጋሎት ውጭ የየትኛውም ተቋማት ቋንቋ አይደለም።
3. ዐረብኛ የብዙ ሃይማኖት ቋንቋ ነው። ከሙስሊሞች ባሻገር ከ15 ሚሊዮን በላይ ዐረብ ክርስቲያኖች አሉ። አይሁድም ይገኛል።
* ግእዝስ? የኦርቶዶክ ተዋህዶ ክርስትና ብቻ!
እውነታው ይህ ቢሆንም በክልሉ 0ረብኛ ማስተማር በመንግስት ደረጃ እንደ ግእዙ ትእዛዝ ሊወጣበት ቀርቶ በፈቃድ ደረጃ እንኳ አልተፈቀደም። ለግል ትምህርት ቤቶች እንኳን አልተፈቀደም። ለህዝብም ለሀገርም የተሻለ ፋይዳ ያለውን ዐረብኛን ጥለው እንደ ህዝብ አንድ ቀበሌ ውስጥ እንኳ የማይነገርን ቋንቋ መማርን ግዴታ ማድረጋቸው ምክንያቱ ከቋንቋ ያለፈ እንደሆነ ግልፅ ነው። በዚያ ላይ ትምህርቱ በመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታጨቀ ሲሆንስ? በዚያ ላይ ትምህርቱን የሚሰጡት ቄሶች ናቸው። ለማን? እምነታቸውን በቅጡ ላልለዩ ጨቅላ ህፃናት! እንዴት ነው ታዲያ ችግር የሌለው?

የጥቅምት 7ቱ ጥቃት ከመፈጽጸሙ በፊት ኔታንያሁ ሁሉም ነገር ደርሶት እንደነበር የሚያጋልጡ የድምጽ ቅጂዎች ወጡ ይላል አልጀዚራ። ይሄ ነገር ከዚህ በፊትም ሌሎች ሚዲያዎች ብዙ የተነተኑት ነው። ብቻ የሚገርም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
የሶሪያው መሪ አሕመድ አሽሸርዕ :-
"እኔ የጂሃ ^ዳዊ ድርጅቶችም ይሁን፣ የሙስሊም ወንድማማችነት (ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን) ንቅናቄም ይሁን የኢስላማዊ ቡድኖች ቅጥያ አይደለሁም። እንዲሁም 'የዐረብ ጸደይ' ቅጥያም አይደለሁም" ብሏል።
በዚህ ንግግሩ የተነሳ ብዙዎች በተለይም ኢኽዋኒዮች በሃይለኛ እያብጠለጠሉት ነው።
ሸይኽ አሕመድ አንነጃር ከዚህ የሸርዕ ንግግር ጋር አያይዘው እንዲህ አሉ፦
لا يمكن أن تقام دولة بفكر دواعش التكفير
فها هي حكومة سوريا تعلنها صراحة اليوم بأنها ليست على تنظيم جهادي ...ولا فكر قطبي...
"በዳዒሾች የ'ተ -ክ ^ ፊ -ር' አስተሳሰብ መሰረት መንግሥት ሊመሠረት አይችልም። ይሄው የሶሪያ መንግሥት ዛሬ በግልጽ እንደገለጸው፣ እሱ የጂሃ ^ዳዊ ድርጅት ወይም የ'ቁጥ ^ ቢ' አስተሳሰብ አካል እንዳልሆነ ግልፅ አድርጓል።"

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሱፊያ እንደ ቡድን ቪዲዮው ላይ በተያያዘው አይነት የኹራፋት ቂሷ የተሞላ ነው። እከሌ ወልይ ጁሙዐ መካ - ሐረም ነበር የሚሰግዱት፣ ዐርሽ ላይ ነበር የሚሰግዱት፣ ቀብራቸውን ዘንዶና ነብር ነው የሚጠብቀው፣ የሆኑ ሰዎችን ረግመው ድንጋይ አደረጓቸው፣ እህል ያዘንቡ ነበር፣ መለይካ ነበሩ፣ ሲሞቱ ሌላ አገር ይወጣሉ፣ በፈቃዳቸው ነው የሚሞቱት፣ ... ማለቂያ የሌለው የውሸት ግሳንግስ!! አሁን ዐቅል ያለው ሰው በነዚህ ይሸወዳል? በተለይ ወጣት በነዚህ ሲሸወድ ያሳዝናል። በተለይ የተማረ ሰው!! መማር ለሂዳያ ዋስትና ይሆናል ማለቴ አይደለም። ግን ለማስተዋል በር ይከፍት ነበር ፣ ላደለው ሰው። ግን ምን ዋጋ አለው?
"ዐርሽ አደባባይ ያለው ህም ህም
የዘቡራ ልጅ ሰይድ ኢብራሂም!"
እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ቅጥ ^ፈት የሚናገሩ ሰዎች ወሊይ ተደርገው ሲያዙ አስቡት። አሳፋሪ!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
"ዐርሽ አደባባይ ያለው ህም ህም
የዘቡራ ልጅ ሰይድ ኢብራሂም!"
እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ቅጥ ^ፈት የሚናገሩ ሰዎች ወሊይ ተደርገው ሲያዙ አስቡት። አሳፋሪ!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ከ“ወሃ * ብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
~
አንዳንዶች የመውሊድ ቢድዐን ማውገዝ የተጀመረው በቅርብ ጊዜ ይመስላቸዋል። ለዚያም ነው የተቃወማቸውን ሁሉ "ወሃ ^ ቢ" የሚሉት። ይሄ ሙግት ባዶ እንደሆነ ለማሳየት ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ መምጣት በፊት የነበሩ ይህንን የመውሊድ ቢድዐ የኮነኑ ዑለማዎችን እጠቅሳለሁ።
1. ኢብኑ ተይሚያህ (728 ሂ.)፡- የሳቸውን አቋም ራሱን ችሎ ስለዳሰስኩት በዚህ ሊንክ ከፍተው ማየት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/GnB9vMNEKaWpx9h9/?mibextid=oFDknk
2. ታጁዱን ዑመር ብኑ ዐሊይ አልፋኪሃኒይ (734 ሂ.)፡-
መውሊድን አጥብቀው የኮነኑ ሲሆን በዚህ ላይ አንድ ኪታብ ፅፈዋል። እንዲህ ይላሉ፡- “ለዚህ መውሊድ በቁርኣንም በሱናም መነሻ አላውቅለትም። በኢሰላም ላይ ተምሳሌት የሆኑትና የቀደምቶችን ትውፊቶች አጥብቀው የያዙ ከሆኑት የሙስሊሙ ህዝብ ምሁራኖች ከአንዳቸውም ተግባሩ አልተወሰደም። ይልቁንም ቦዘኔዎች የፈጠሩት ቢድዐ ነው! ሆዳ ^ሞች ያተረፉበት የሆነ የነፍስ ዝንባሌ ነው። … ይሄ (መውሊድ) ግን ሸሪዐው አልፈቀደውም። ሶሐቦችም ታቢዒዮችም አልሰሩትም። እስካወቅኩት ድረስ ዲን የተላበሱ ዑለማዎችም አልሰሩትም። ይህ ነው ከሱ ከተጠየቅኩ ከአላህ ፊት የምመልሰው። የተፈቀደ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም በዲን ውስጥ ፈጠራ መፍጠር በሙስሊሞች ኢጅማዕ የተፈቀደ አይደለምና። ስለዚህ የተጠላ ወይም የተከለከለ ከመሆን ውጭ የቀረ የለም። የዚህን ጊዜ ወሬያችን ሁለት ክፍሎች ይኖሩታል ማለት ነው፣ ሁለት የተለያዩ ሁኔታዎች ጋር:-
አንዱ፡- አንድ ሰው ከራሱ ገንዘብ ለባለቤቱ፣ ለጓደኞቹና ለቤተሰቡ የሚያዘጋጀው ነው። በዚህም ጉባዔ ላይ ምግብን ከመብላት ላያልፍና ወንጀሎችን የማይፈፅሙ ከሆነ ነው። ይህንን ነው የተጠላ ቢድዐና አስቀያሚ ነገር እንደሆነ የገለፅነው። ምክንያቱም የዘመናት መብራት፣ የሃገራት ውበት የሆኑት ምሁራኖችና የኢስላም ሊቃውንት የሆኑት ቀደምት የአላህ ታዛዦች አልሰሩትምና።
ሁለተኛ፡- ወንጀል የሚቀላቀለውና (ይህን ቢድዐ ለማክበር ገንዘብ ለመሰብሰብ) ትኩረት የሚበረታበት ነው። አንዳንዱ ነፍሱ የተንጠለጠለ ሆኖ፣ ከግፉ ህመም የተነሳ ልቡን እያሳመመው የሆነ ስጦታን ነገር እስከሚሰጥ የሚደርስበት ነው። ዑለማዎችን አላህ ይማራቸውና ‘እፍረት አስይዞ ገንዘብን መውሰድ በሰይፍ እንደመውሰድ ነው’ ይላሉ።
በተለይ ደግሞ በዚህ ላይ ከጠገቡ ሆዶች ጋር እንደ ድቤና ዋሽንት ያሉ በከንቱ መሳሪያዎች የታጀበ ዘፈን ካለ፣ እንዲሁም ወንዶች ከወጣቶችና ከዘፋኝ ሴቶች ጋር መቀላቀል ከኖረ ወይ ከወንዶቹ ጋር ተቀላቅለው ወይ ደግሞ ከከፍታ ላይ ዘልቀው፣ እየተጣጠፉ በመጨፈር፣ ከዛዛታ ውስጥ መስመጥና አስፈሪውን (የቂያማ) ቀን መዘንጋት የሚደረስበት ነው።
ልክ እንዲሁ ሴቶች ብቻቸውን ሲሰባሰቡ ያለምንም ሀፍረት ድምፃቸውን በዘፈንና በዜማ ከፍ ያደርጋሉ። ከተለመደው የቁርኣን አቀራርና ዚክር አልፈው ከሸሪዐው ይወጣሉ። የላቀው ጌታ {ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና} ማለቱን ይዘነጋሉ። ይሄ ክልክል በመሆኑ ላይ ሁለት ሰዎች አይወዛገቡበትም። ስርኣት ያላቸው አስተዋዮች በጥሩ አያዩትም። ይሄ የሚፈቀደው የሞቱ ቀልቦችን ከያዘና ወንጀልንና ሃጢኣትን ከሚያበዙ ሰዎች ዘንድ ነው። እንዲያውም ልጨምርህና እነሱ እንደ ዒባዳዎች እንጂ እንደ መጥፎና ክልክል ነገሮች አይደለም የሚቆጥሩት። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ‘ኢስላም እንግዳ ሆኖ ነው የጀመረው። እንግዳ ሆኖም ይመለሳል።’ ... ይህ እንግዲህ ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ረቢዐል አወል ወር የሞቱበትም ከመሆኑ ጋር ነው። መደሰቱ በሱ ውስጥ ከማዘን ቅድሚያ የሚሰጠው አልነበረም።” [አልመውሪድ ፊ ዐመሊል መውሊድ፡ 2-8]
3. ኢብኑል ቀዪም (751 ሂ.)፡-
“ኢስራእ ነብዩ ﷺ ከታደሏቸው ታላላቅ ትሩፋቶች ከመሆኑም ጋር ያንን ጊዜ ወይም ያንን ቦታ በሸሪዐዊ ዒባዳ መለየት አልተደነገገም። እንዲያውም ወሕይ መውረድ የጀመረበት የሒራእ ዋሻ ከነብይነታቸው በፊት ያተኩሩበት የነበረ ከመሆኑ ጋር ከነብይነት በኋላ ራሳቸውም መካ ላይ በቆዩ ጊዜ፣ እንዲሁም ከሶሐቦች አንድም ያሰበው የለም። ወሕይ የወረደበት ቀንም እንዲሁ በዒባዳም ይሁን በሌላ ተለይቶ አልተያዘም። ወሕዩ የተጀመረበት ቦታም ይሁን ዘመኑ እንዲሁ በምንም ነገር ተለይቶ አልተያዘም። የሆኑ ቦታዎችን ወይም ጊዜዎችን ከራሱ በዒባዳዎች ለዚህና መሰል አላማ የለየ ሰው የመፅሐፉ ሰዎች አምሳያ ሆኗል። እነዚያ የመሲሕን (የዒሳን) ሁኔታዎች፣ ጊዜዎችና መሰባሰቢያዎች በዓላት አድርገው እንደያዙት። ለምሳሌ የልደት ቀኑን፣ የጥምቀት ቀኑንና መሰል ሁኔታዎቹን ለይተው እንደያዙት። ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዱየላሁ ዐንሁ የሆኑ ሰዎችን ወደ አንድ ቦታ ለሶላት ሲቻኮሉ ያዩዋቸዋል። ‘ምንድነው ይሄ?’ ሲሉ ጊዜ ‘የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሰገዱበት ቦታ ነው’ አሉ። ‘የነብዮቻችሁን ፋናዎች መስገጃዎች አድርጋችሁ ልትይዟቸው ትፈልጋላችሁን? ከናንተ በፊት የነበሩት ሰዎች የጠፉት በዚህ ነው። እዚያ እያልለ ሶላት የደረሰበት እዚያው ይስገድ። ያለበለዚያ ግን ጉዞውን ይቀጥል’ አሉ።” [ዛዱል መዓድ፡ 1/59]
4. አቡል ዐባስ አሕመድ ብኑል ቃሲም አልቁባብ (778 ሂ.)፡-
በመውሊድ ቀን ልጆችን ሰብስቦ ሻማ ስለመለኮስ፣ በነብዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ስለማለት፣ ድምፁ ያማረውን ከውስጣቸው በመምረጥ አስር የቁርኣን ሱራዎችን እንዲያነብ ስለማድረግና ነብዩን ﷺ የሚያወድሱ ግጥሞችን ስለመነሸድ፣ በዚህ ሰበብም ወንዶችና ሴቶች መሰባሰባቸውን እንዲሁም አስተማሪው ሻማዎችን መቀበል የሚፈቀድለት ስለመሆኑ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ ነበር የመለሱት፡-
“የገለፅካቸው በሙሉ ቢድዐ የሆኑ መጤ ፈሊጦች ናቸው። ስለሆነም የግድ ሊቋረጡ ይገባል። እነዚህን ነገሮች የሚፈፅም ወይም በነዚህ ላይ የሚያግዝ ወይም እንዲቀጥሉ የሚተጋ ሰው በቢድዐና በጥመት ላይ ነው እየተጋ ያለው። እሱ ግን በድንቁርናው ሳቢያ በዚህ ተግባሩ የአላህ መልእክተኛን - ﷺ - የሚያከብርና መውሊዳቸውን የሚያከብር እንደሆነ ያስባል። እሱ ግን ሱናቸውን እየጣሰና ክልከላቸውን እየፈፀመ ነው። ይህንን በይፋ እየፈፀመ ዲን ያልሆነን እንግዳ ነገር እየፈጠረ ነው። እውነተኛ የሆነን ማክበር ቢያከብራቸው ኖሮ ትእዛዛቸውን ባከበረና በዲናቸው ውስጥ እንግዳ ነገር ባልፈጠረ ነበር። እንዲሁም አላህ {እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳይደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ} ሲል ካስጠነቀቀው ጋር ባልተላተመ ነበር።
አስተማሪው የሚቀበለውን (ስጦታ) በተመለከተ እነዚህን ቢድዐዎች፣ እነዚህን ነገሮች ስለሚያስፈፅም ከሆነ የሚሰጠው የሚቀበለው ነገር አስቀያሚ መሆኑ አይሰወርም። እነዚህን ነገሮች ምንም ሳይፈፅም እንዲሁ በዚህ ጊዜ የሚሰጠው ከሆነ ኢብኑ ሐቢብ ‘ለአስተማሪ በሙስሊሞች ዒድ ምንም አይወሰንለትም - ይህን መስራቱ የሚወደድ ቢሆን እንኳን’ ብለዋል። … ኢብኑ ሐቢብ ሸሪዐዊ በሆኑ በዓላት ላይ እንዲህ ካሉ ሸሪዐዊ ባልሆኑት ላይ እንዴት ሊሆን ነው?!” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዒ ወተሶውፍ፡ 128-129]
5. አቡ ኢስሓቅ አሻጢቢይ (790 ሂ.)፡-

Facebook
Ibnu Munewor
እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
~
ሰሞኑን ስለ መውሊድ ስፅፍ ደጋግመው ኢብኑ ተይሚያም ፈቅደዋል በማለት የተቆረጠ ንግግራቸውን በሃሳብ መስጫ ላይ ሲለጥፉ እያየሁ ነው። ኢብኑ ተይሚያን የመውሊድ ደጋፊ አስመስሎ ማቅረብ ብዙ ሱፍዮች ዘንድ የተለመደ ነው። የመውሊድ ነቃፊዎች ኢብኑ ተይሚያን ስለሚወዱ...
~
ሰሞኑን ስለ መውሊድ ስፅፍ ደጋግመው ኢብኑ ተይሚያም ፈቅደዋል በማለት የተቆረጠ ንግግራቸውን በሃሳብ መስጫ ላይ ሲለጥፉ እያየሁ ነው። ኢብኑ ተይሚያን የመውሊድ ደጋፊ አስመስሎ ማቅረብ ብዙ ሱፍዮች ዘንድ የተለመደ ነው። የመውሊድ ነቃፊዎች ኢብኑ ተይሚያን ስለሚወዱ...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
“ሰዎች ዘንድ በተለመደው መልኩ የሚከበረው መውሊድ መጤ የሆነ ቢድዐ መሆኑ የታወቀ ነው። ቢድዐ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። ስለሆነም ቢድዐን ለመፈፀም ገንዘብን መለገስ አይፈቀድም። በዚህ ላይ ኑዛዜ ከተላለፈም ተፈፃሚ አይደለም። እንዲያውም ቃዲው ሊያፈርሰው ይገባል።…” [ፈታዋ ሻጢቢይ፡ 203-204]
በተጨማሪም ስለቢድዐ ምንነት ካብራሩ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አሁንም ከነሱ (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሚካተተው (በዒባዳ ውስጥ) ተለይተው የተወሰኑ አፈፃፀሞችንና ሁኔታዎችን በቋሚነት መያዝ ነው። ለምሳሌ በአንድ ድምፅ በመሰባሰብ የሚደረግ ዚክር፣ የነብዩን ﷺ ልደት ቀን በዓል አድርጎ መያዝና እነዚህን የመሳሰሉትን ያካትታል።” [አልኢዕቲሷም፡ 1/53]
6. ኢብኑ ረጀብ (795 ሂ.)፡-
ሸሪዐው ዒድ ተደርጎ እንዲያዝ ያዘዘበትን ካልሆነ በስተቀር ሙስሊሞች ዒድ ሊይዙ አይፈቀድላቸውም። እነሱም (የታዘዙትም) ዒደል ፊጥር፣ ዒደል አድሓና የተሽሪቅ (ከዒደል አድሓ ቀጥሎ ያሉት ሶስቱ) ቀናት ናቸው። እነዚህ አመታዊ በዓላት ናቸው። የጁሙዐ ቀን ደግሞ ሳምንታዊ ዒድ ነው። ከዚህ ውጭ ያለን በዓልና ዐውደ- አመት አድርጎ መያዝ በሸሪዐችን መሰረት የሌለው ቢድዐ ነው። [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 118]
7. አቡ ዐብዲላህ አልሐፋር አልገርናጢይ (811 ሂ.)፡-
“የመውሊድ ሌሊት መልካም ቀደምቶች ማለትም የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ለአምልኮት የሚሰባሰቡባት አልነበሩም። ከአመቱ ሌሊቶች ተጨማሪ ስራም አይሰሩባትም ነበር። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዲከበሩ በተደነገገው መልኩ እንጂ አይከበሩምና። እሳቸውን ማላቅ ከትልልቅ ወደ አላህ መቃረቢያዎች ነው። ነገር ግን ልቅናው ከፍ ወዳለው አላህ እሱ በደነገገው መልኩ እንጂ (በሌላ) መቃረብ አይፈቀድም። ሰለፎች ከሌሎች ሌሊቶች በተለየ ምንም የሚጨምሩ እንዳልነበሩ መረጃው በሷ (በተወለዱበት ቀን) ላይ መለያየታቸው ነው። ለምሳሌ እሳቸው ﷺ የተወለዱት በረመዳን ነው ተብሏል፣ በረቢዕ ነውም ተብሏል። በዚህም ላይ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ አራት የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል። ከፍጡራን ሁሉ በላጭ የሆኑት በመወለዳቸው ሳቢያ በማለዳዋ የተወለዱባት ሌሊት ዒባዳ የሚጠነሰስባት ብትሆን ኖሮ ውዝግብ ሳይከሰትባት በሰፊው በታወቀች ነበር። ነገር ግን ጭማሬ የሆነ ማላቅ አልተደነገገባትም።
የጁሙዐ ቀን ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጭ ቀን እንደሆነችና በበላጭ ቀን የሚፈፀመው በላጩ ነገር ፆም እንደሆነ አታውቅምን? ሆኖም ግን ነብዩ ﷺ ከትልቅ ልቅናው ጋር ከጁሙዐ ቀን ፆም ከልክለዋል። ይህም በየትኛውም ጊዜ ይሁን በየትኛውም ቦታ ካልተደነገገ በስተቀር አምልኮት መፍጠር እንደማይቻል ያመለክታል። ካልተደነገገ አይፈፀምም። ምክንያቱም የዚች ህዝብ ኋለኛው ክፍል ከቀዳሚው የተሻለ የተቀና ነገር አያመጣምና። ይሄ በር ቢከፈትማ የሆኑ ሰዎች መጥተው ወደ መዲና የተሰደዱበትም ቀን ‘አላህ በሱ ኢስላምን ያላቀበት ቀን ነው’ በማለት ሊሰባሰቡበትና ሊያመልኩበት ነው። ሌሎች ደግሞ ተነስተው ኢስራእ ያደረጉባት ሌሊት ‘ልኬታው የማይገመት የሆነ ልቅና የተጎናፀፉባት ሌሊት ነች’ በማለት አምልኮት ሊፈጠር ነው። እናም (እንዲህ ከተከፈተ) የሆነ ወሰን ላይ ሊቆም አይቻልም። መልካም ሁሉ ያለው አላህ ለሳቸው የመረጣቸውን መልካም ቀደምቶች በመከተል ነው። የሰሩትን እንሰራለን። የተውትን እንተዋለን። ይሄ ከተረጋገጠ በዚች ሌሊት ላይ መሰባሰቡ በሸሪዐው ተፈላጊ እንዳልሆነ ግልፅ ይሆናል። …
ይህቺ ሌሊት ደግሞ በሱፍዮች መንገድ ነው የምትዘጋጀው። በዚህ ዘመን የሱፍዮች መንገድ በዲን ውስጥ ከተፈጠሩ አስቀያሚ ነገሮች ውስጥ ነው። ምክንያቱም የጉባዔ ስርአታቸው ዘፈንና እንቶ ፈንቶ ነውና። ይሄ ነገር በነዚህ ጊዜያት ከሚፈፀሙ የላቁ መቃረቢያዎች እንደሆነና ይህ የወልዮች መንገድ እንደሆነ ለአላዋቂ ሙስሊሞች ያስተምራሉ። በሌሊትና በቀን ውስጥ ግዴታ የሆኑባቸውን ህግጋት በቅጡ የማያውቁ መሃይማን ሰዎች ናቸው። ይልቁንም አላዋቂ ሙስሊሞችን ለማጥመም ሸይ ^ጧን ምትኮች ካደረጋቸው ውስጥ ናቸው። ለሰዎች ከንቱ ነገሮችን ይሸላልማሉ። ወደ አላህ ዲንም ከሱ ያልሆነን ነገር ያስጠጋሉ። ምክንያቱም ዘፈንና እንቶ ፈንቶዎች ከዛዛታና ከጨዋታ ውስጥ ናቸውና። እነሱ ግን ወደ አላህ ወሊዮች ያስጠጉታል። እነሱም በዚህ ላይ ገንዘብን ያለ አግባብ ለመብላት ይዳረሱ ዘንድ እየዋሹባቸው ነው።…” [ዑለማኡል መግሪብ፡ 128]
8. ኢብኑ ነሐስ (814 ሂ.)፡-
“አውዳመታትና በዓላት ውስጥ ከተፈጠሩት ውስጥ በከፊል ማውሳት” በሚል ንኡስ ርእስ ስር “ከነዚህ ውስጥ በወርሃ ረቢዐል አወል ሰዎች የፈጠሩት የመውሊድ ተግባር ነው” ይላሉ። በውስጡ ካሉ ቢድዐዎችና ጥፋቶች እንኳን ቢፀዳ ከቢድዐነት እንደማያልፍ ካጣቀሱ በኋላ ሰዎች መውሊድን ለማዘጋጀት የሚያነሳሷቸው ምክንያቶች ብለው የተወሰኑ ነጥቦችን አንስተዋል። ከነዚህም ውስጥ፡-
- ከሚጠሯቸው ቃዲዎች፣ መሪዎች፣ መሻይኾችና ከመሳሰሉት ጋር ለመተዋወቅ በማለም የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንድ መሻይኾች ደግሞ ሰዎች በመውሊድ ምክንያት በእርዳታ መልክ ወይም በስጦታ መልክ ወይም ሃፍረት ይዞት ወይም ደግሞ ከእኩዮቹ ጋር ለመፎካከር ሲል ከሚያመጡት ነገር የሚተርፈውን ለራሳቸው ለመጠቀም በማለም መውሊድን የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንዱ ክፉ ምላስ ያለውና ቁጡ ይሆንና ደካሞችን በመጥለፍና ምላሱንና ምግባሩን የሚፈሩ ሰዎችን በማጥመድ አላማውን የሚያሳካ አለ። … [ተንቢሁል ጋፊሊን ዐኒል አዕማሊል ጃሂሊን፡ 499]
9. ቃዱ ሺሃቡዲን ደውለት ኣባዲ አልሐነፊይ (894 ሂ.)፡-
“በያመቱ መጀመሪያና በረቢዐል አወል ወር መሃይማን የሚሰሩት ተግባር ከምንም የሚቆጠር ነገር አይደለም። የሳቸው ﷺ ልደት ሲወሳ ይቆማሉ። ሩሐቸው ትመጣና ትካፈላለች ይላሉ። ይሄ ሙግታቸው ውድቅ ነው። ይሄ እምነት ሺርክ ነው።” [ፈታወ ሸይኽ ሸምሲል ሐቅ አዚምኣባዲ፡ 166]
እንግዲህ ተመልከቱ። እነዚህ በሙሉ በ1206 ሂ. ከሞቱት ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ - ረሒመሁላህ - ዘመን ቀድሞ መውሊድን ያወገዙ ዑለማዎች ናቸው። ከዚህ በኋላ መውሊድን የሚቃወሙት ከ200 አመት ወዲህ የመጡ “ወሃ*ቢዮች” ናቸው ማለት ራስን ማታለል ካልሆነ በስተቀር ምን ትርጉም ይኖረዋል?
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 17/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል:-

የአደባቸው ቅለት በዚህ ልክ ነው። ያመናቸውን ገደል ይከታሉ። በርግጠኝነት በዚህ ዓይነት መንገድ ጀነት እንደማይገኝ ግልፅ ነው። አላማቸው ዱንያ ነው። አላማቸው አጉል ዝና ፍለጋ፣ ከሌሎች መሰሎቻቸው አንፃር በልጦ፣ ጎልቶ መታየት ነው። አላማቸው ሞኛሞኝ ተከታያቸውን ማለብ ነው። ተውሒድን ያልታጠቀ ሰው ደግሞ አይነቃባቸውም፡፡
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ሐነፊይ፣ ... አትሁን
~
ከሱና ሰዎች አበይት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ የፈለገ ቢገንኑ ለዑለማዎች ጭፍን ወገንተኛ አለመሆን ነው። የፈለገ ብንወደው ማንም ቢሆን የተናገረው ሁሉ ልክ አይሆንም። ስለሆነም ለማንም ጭፍን ወገንተኛ ልንሆን አይገባም። ይህንን በተግባር ያስተማሩን ራሳቸው ዑለማዎቹ ናቸው። ለአብነት ያክል የአራቱን አኢማዎች ንግግሮች እዚህ ላይ ላስፍር፡-
[ሀ] አቡ ሐኒፋ፡-
1. “አንድ ሐዲሥ ትክክለኛ ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው።”
2. “ማስረጃዬን ያላወቀ ሰው በኔ ንግግር ፈትዋ ሊሰጥ ሐራም ነው።”
3. “እኛ ሰዎች ነን። አንድ ንግግር ዛሬ እንናገርና ነገ ከሱ እንመለሳለን።”
4. “የላቀውን አላህ መፅሐፍና የመልእክተኛውን ﷺ ንግግር የሚፃረር ንግግር ከተናገርኩኝ የኔን ንግግር ተውት።”
[ለ] ማሊክ፡-
1. “እኔ ሰው ነኝ። እስታለሁ፣ አገኛለሁ። ስለዚህ እይታየን ተመልከቱ። ቁርኣንና ሱና ጋር የገጠመውን በሙሉ ያዙት። ቁርኣንና ሱና ጋር ያልገጠመውን ተውት።”
2. “ከነብዩ ﷺ በስተቀር ንግግሩ የሚያዝለት ወይም የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም።”
3. “ከነብዩ ﷺ በኋላ ከንግግሩ የሚያዝና የሚተው ያልሆነ አንድም የለም። ነብዩ ﷺ ሲቀሩ።"
[ሐ] ሻፊዒይ፡-
1. “አንድ የነብዩ ﷺ ሱና የተገለፀለት ሰው ለማንም ንግግር ሲል እሷን (ሱናዋን) መተው እንደማይፈቀድለት ሙስሊሞች በሙሉ ኢጅማዕ አድርገዋል።”
2. “በኪታቤ ውስጥ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ሱና የሚፃረር ነገር ካገኛችሁ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሱና ተከተሉ። የኔን ንግግር ተውት።”
3. “ሐዲሥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው።”
[መ] አሕመድ፡-
1. “የአውዛዒይ አስተያየት (ረእይ)፣ የማሊክም አስተያየት፣ የአቡ ሐኒፋም አስተያየት ሁሉም አስተያየት ነው፣ እኔ ዘንድ። መረጃ ያለው ከነብዩ ﷺ እና ከሶሐቦቹ ቅሪት ዘንድ ነው።”
2. “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይን፣ ሠውሪይን በጭፍን አትከተል። እነሱ ከያዙበት ያዝ።”
እነዚህንና መሰል ወርቃማ ንግግሮችን ከሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ “ሲፈቱ ሶላቲ ነቢይ” ኪታብ መግቢያ ላይ ማግኘት ይቻላል። እነዚህን ንግግሮች በአንክሮ እናስተውል። የህይወታችን ቋሚ መመሪያም እናድርጋቸው። “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይን፣ ሠውሪይን በጭፍን አትከተል” የሚለውን የኢማሙ አሕመድ ንግግር አስተውለነዋል? እነዚህን የኡማው ከዋክብት በጭፍን መከተል ካልተፈቀደ ከነሱ በእጅጉ የሚያንሱትንስ በጭፍን መከተል ይፈቀዳልን? ጤነኛ ከሆንን መልሱ አይጠፋንም። ርእሴ ላይ "ሐነፊይ አትሁን" ስል ትኩረቴ የሐነፊያ መዝሀብ አይደለም። ነጥቤ ከአራቱም አኢማዎች ጋር ይያያዛል። እናም በተመሳሳይ እንዲህ እንበል:-
- ኢብኑ ተይሚያንም፣ ኢብኑል ቀይምንም፣ ዘሀቢይንም፣ ኢብኑ ከሢርንም፣ … በጭፍን አትከተል።
- ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወህሃብንም፣ ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንንም፣ ዐብዱለጢፍ ኣሊ ሸይኽንም፣ ሰዕዲይንም፣ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂንም፣… በጭፍን አትከተል።
- ኢብኑ ባዝንም፣ አልባኒይንም፣ ኢብኑ ዑሠይሚንንም፣ ሙቅቢልንም፣… በጭፍን አትከተል።
- ፈውዛንንም፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድንም፣ ሙሐመድ አማን አልጃሚይንም፣ ረቢዕ አልመድኸሊይንም፣… በጭፍን አትከተል።
- በሰፈርህ፣ በአካባቢህ፣ በሃገርህ ያሉ መሻይኾችንም፣ ኡስታዞችንም የፈለገ ብትወዳቸው እንኳ በጭፍን አትከተል። የሐቅ መለኪያ ሚዛንም አታድርጋቸው። ማንም ይሁን ማን።
ልብ በሉ! ዑለማኦችን አታክብሩ አልተባለም። ትንታኔያቸውን አትጠቀሙም አልተባለም። የዚህ ፅሑፍ አላማ ግለሰቦችን የሐቅ መለኪያ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል ፈተና ማስጠንቀቅ ብቻ ነው። እንጂ የቁርኣንና የሐዲሥን ማብራሪያ የምንወስደው ከዑለማዎች እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ከመሆኑም ጋር ከማስረጃ ጋር የሚቃረን ፈትዋ ወይም ትንታኔ ሲገጥም ለሸሪዐዊ ማስረጃዎች ቅድሚያ መስጠት ይገባል ለማለት ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 07/2010)
=
የቴሌግራም ቻናል

አምልኮታዊ እርድ
~
ለአላህ እንጂ ለየትኛውም ፍጡር ሊሰጡ ከማይገባቸው የአምልኮት አይነቶች አንዱ እርድ ነው፡፡ ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡
{ فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَٱنۡحَرۡ }
"ስለዚህ ለጌታህ ስገድ። (ለሱም) እረድ።" [አልከውሠር፡2]
ከዚች የቁርኣን አንቀፅ የምንረዳው ልክ ሶላት አምልኮት እንደሆነው ሁሉ እርድም አምልኮት እንደሆነ ነው፡፡ ልክ ሶላት ለፍጡር ቢሰገድ ከኢስላም የሚያስወጣ ሺርክ እንደሆነው ሁሉ፣ ከአላህ ውጭ ላለ አካል መቃረቢያ እርድ መፈጸምም እንዲሁ ከኢስላም የሚያስወጣ ሺርክ መሆኑን ነው፡፡
{ قُلۡ إِنَّ صَلَاتِی وَنُسُكِی وَمَحۡیَایَ وَمَمَاتِی لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَـٰلَمِینَ (162) لَا شَرِیكَ لَهُۥۖ وَبِذَ ٰلِكَ أُمِرۡتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡمُسۡلِمِینَ (163) }
" 'ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው' በል። 'ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ' (በል)።" [አንዓም፡ 162-163]
ልብ በሉ! እርድ ከሶላት ጋር ተቆራኝቶ መምጣቱ ዒባዳ እንደሆነ ያሳያል። ልክ ሶላት ለፍጡር ቢፈፀም ሺርክ እንደሆነው እርድን ለፍጡር መፈፀምም ሺርክ ነው።
ሐቁ ይህ ቢሆንም ነገር ግን ልክ ነብዩን ﷺ ሲያሰቃዩ የነበሩት አጋሪዎች ለጣኦቶቻቸውና ለጂኖች ያርዱ እንደነበረው ዛሬም በምላሳቸው “ላኢላሀ ኢለላህ” እያሉ ለጂኖችና ለሙታን የሚያርዱት እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በሀገራችን “ሙወከል”፣ “ራሄሎ” እያሉ ዶሮዎችን፣ ሙክቶችን እና ወይፈኖችን የተለያዩ ስያሜዎችን ሰጥቶ ለጂን ወይም ለዛር ማረድ የተለመደ ነው፡፡ የተለያዩ መጤ መሰባሰቢያ በአላትን ጠብቀው ከታወቁ መቃብሮች ዘንድ በመሄድ ከአላህ ውጭ ላሉ አካላት ፍየል፣ ከብትና ግመል የሚያርዱትም ቀላል አይደሉም፡፡ እንዲህ አይነቱ እርድ ግን ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቁ ሺርክ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን ተግባር የሚፈፅም ሰው የተረገመ እንደሆነ ነብዩ ﷺ እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል፡-
"لَعَنَ اللَّهُ مَنْ ذَبَحَ لِغَيْرِ اللَّهِ".
{የአላህ እርግማን ከአላህ ሌላ ላለ ባረደ ላይ ይሁን!} [ሙስሊም፡ 5240]
ማሳሰቢያ፡-
በዚህ ንኡስ ርእስ ስር እያወራን ያለነው አምልኮታዊ ስለሆነው፣ መቃረቢያ ወይም መጥጠበቂያ ታስቦ ስለሚፈፀመው እርድ እንጂ እንግዳ ለማክበር ታስቦ ቢታረድ እንዲያውም የሚበረታታ ነገር ነው፡፡ ሰው ለራሱ ለሚበላው ቢያርድም የተፈቀደ ነገር ነው፡፡ እርድ በጥቅሉ ለሶስት ይከፈላል፡፡
1. ሸሪአዊ እርድ፡- ሸሪዐው የሚያዘው ወይም የሚወደው የእርድ አይነት ሲሆን ለምሳሌ የሐጅ እርድ፣ የኡዱሒያህ እርድ፣ ለአላህ ስለትን ለመሙላት የሚፈፀም እርድ፣ የዐቂቃ እርድ፣ የሰርግ እርድ፣ ወደ አላህ መቃረቢያ የሶደቃ እርድ፣ እንግዳ ለማስተናገድ የሚታረድ እርድ በዚህ ስር የሚካተቱ ናቸው፡፡
2. የተፈቀደ እርድ፡- ለራስ ለመመገብ ወይም ለንግድ የሚታረድ የእርድ አይነት ሸሪዐው የሚፈቅደው የእርድ አይነት ነው።
3. የተከለከለ እርድ፡- ይሄኛው የእርድ አይነት ሸሪዐው የሚያወግዘው የእርድ አይነት ሲሆን እሱም ሁለት አይነት ነው።
* አንዱ ለጂን ወይም ለዛር፣ ለጣኦት፣ ለመቃብር እና ለመሳሰሉት የሚታረድ እርድ ሲሆን ይሄ ከኢስላም የሚያስወጣ አደገኛ ሺርክ ነው፡፡ ከላይ ስናወራ የነበረውም ስለዚህኛው አይነት እርድ ነው፡፡
* ሁለተኛው የተከለከለው የእርድ አይነት ለምሳሌ የቢድዐ በአላትን ለማክበር የሚታረድ እርድ፣ በሺርክ ቦታዎች ላይ ለአላህ የሚታረድ እርድ እና የመሳሰሉት ከዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ እነዚህኞቹ የእርድ አይነቶች ሺርክ ባይሆኑም በሸሪዐው ግን የተወገዙ ናቸው፡፡ በነብዩ ﷺ ዘመን አንድ ሰው ‘በዋናህ’ በተባለ ቦታ ግመል ሊያርድ ስለት ተሳለና ስለሁኔታው ነብዩን ﷺ ሲጠይቃቸው የዘመነ-ጃሂሊያህ ጥፋቶች ይፈፀሙበት የነበረ ቦታ አለመሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ነው እርዱን እንዲፈፅም የፈቀዱለት፡፡ [አሶሒሐህ፡ 2872]

ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
كلما كان الرجل أعظم إخلاصاً
كانت شفاعة الرسول أقرب إليه
"የአንድ ሰው ኢኽላሱ ይበልጥ በላቀ ቁጥር የመልእክተኛው ሸፋዐ ይበልጥ ለሱ የቀረበ ይሆናል።"
[መጅሙዑል ፈታዋ: 11/528]

በሽተኛን በምንጠይቅ ግዜ መልካም ንግግር መናገር!
ከአብደላህ ቢን ዓባስ (رضي الله عنه) ተይዞ፡ ነቢዩ (ﷺ) በሽተኛን በሚጠይቁ ግዜ እንዲህ ይሉ ነበር፦
﴿لا بَأْسَ، طَهُورٌ إنْ شاءَ اللَّهُ﴾
“አይዞህ! ምንም አይደለም። ምንአልባትም አላህ ከፈቀደ (ይህ በሽታ) የወንጀልህ ማበሻ ሊሆን ይችላል።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5662
☑ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
Telegeram፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
Whatsup፦ https://bit.ly/486xnrS
Facebook፦ https://bit.ly/41zEZkk
Instagram፦ https://bit.ly/4arMbTx
X፦ https://bit.ly/41tIUPv
Youtube፦ https://bit.ly/3UTTSwh
Tik tok፦ https://bit.ly/442V9nM