የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ዓኢሻ ሆይ! ምስኪንን አትመልሺ፣ በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን (አስተናጋጂ)። ዓኢሻ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ። አቅርቢያቸውም። አላህ በትንሳኤ ቀን ያቀርብሻልና።" [ሶሒሑ ተርሚዚይ፡ 2352]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

ሴቶች በሰለፎች ዘመን
~
በሰለፎች (የጥንት ደጋግ ሙስሊሞች) ዘመን፣ ብዙ ሴቶች ቤታቸው ውስጥ ሆነው ማንነታቸውና ስማቸው ሳይታወቅ አልፈዋል። እኛ ማንነታቸውን ስላላወቅናቸው ግን የሚጎድልባቸው ነገር የለም። የፈጠራቸው ጌታ አላህ ያውቃቸዋልና።
እነዚያ ምርጥ ሴቶች በሱና ላይ በጥንካሬ ተኮትኩተው ያደጉ ነበሩ። የፈተና ማዕበል አልወዘወዛቸውም። እስኪ አንድ ድንቅ ታሪክ እንመልከት። ታሪኩ ስለ ዓሲም ቢኑ ዐሊይ አልዋሲጢይ የሚያወራ ነው። ጊዜው "ቁርኣን ፍጡር ነው" የሚል የጀህ ^ ሚያ እና የሙዕተዚላ ብልሹ እምነት የተንሰራፋበት ወቅት ነበር። ይህንን እምነት ያልተቀበለ ሰው ህይወትን እስከማጣት የሚደርስ ብዙ እንግልት የሚቀበልበት ሁኔታ ነበር።
ዓሲም ቢኑ ዐሊይ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሯቸው። በዚያን ጊዜ በአሕመድ ኢብኑ ሐንበል ላይ በደረሰው የጭካኔ ግርፋት ምክንያት፣ አባታቸው ተገድደው ለቢድዓ ሰዎች እጅ እንዳይሰጡና እንዳይሸነፉ ልጆቻቸው ሰግተዋል።
አባት ወደ ባግዳድ ለፈተና ተወስደዋል። ልጆች በዋሲጥ ከተማ ነበሩ። እነኚህ ሴቶች ልጆች ለአባታቸው ደብዳቤ ጻፉላቸው። በደብዳቤውም ላይ የሚከተለውን ጽሁፍ አካተቱ፡-
"አባታችን ሆይ! አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ቁርኣን ፍጡር ነው እንዲሉ ተገድደው እንደተገረፉ ሰምተናል። አደራ አላህን ፍራ! ለነሱ አትታዘዝ! በአላህ ይሁንብን! አንተ ለነሱ ተሸንፈህ በህይወት ከምትመጣልን፣ በአቋምህ ፀንተህ የሞትህ ዜና ቢመጣልን እንመርጣለን።" [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 9/264]
እቴ ሆይ! አደራ!
ከፍ በይ በሱና፣ እንደ ሰለፎችሽ፣ ፅኚ በተውሒድ ላይ
እንዳያታልልሽ፣ እንዳያዘናጋሽ፣ ኹራፊና ጠንቋይ!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሙዚቃ ነፃ አውጪ ግንባር
~
በሃገር ደረጃ ሙዚቃን ከ"ፅንፈኞች" ነፃ የማውጣት ዘመቻ የጀመረው ሐሰን ታጁ ነው። በመፅሀፍ፣ በጋዜጣ፣ በተለያዩ መድረኮች ብዙ ፍልሚያ አካሂዷል። አንዴ ሸገር ሬዲዮ ስለሙዚቃ የሀይማኖት ሰዎችን አቋም ለመስማት ፕሮግራም ሲያዘጋጅ ከኦርቶዶክስ በኩል አንድ ቄስ ቀርቦ 99 በመቶ ዘፈን በመፅሃፍ ቅዱስ የተወገዘ ነው ብሎ ፍርጥም ብሎ ሲሟገት ሐሰን ታጁ ኢስላምን ወክሎ ሙዚቃን ሐላል አድርጎ ረጅም ሀተታ ሰጠ። በሱ ትንታኔ የተደፋፈረው ጋዜጠኛ “እንግዲያው ሙዚቀኞቹን ቀጥታ ለመመልከት የምሽት ክበቦች መገኘትስ እንዴት ነው?” ብሎ ጠይቆት ነበር። የሴትና የወንድ ቅልቅል ስላለበት እዚያ መገኘት አይቻልም ብሏል ጥንቁቁ። ድንቄምi አነጋገሩ መቀላቀል ከሌለስ የሙዚቃ ባንዶች ላይ መገኘትም፣ መሳተፍም፣ መዝፈንም፣... ይፈቀዳል ይመስላል። “የምላስ ጣጣ” ፀሐፊ የዘፈን ጣጣ ሲያመጣ።
የሸገሩን ስብከት አደገኛ የሚያደርገው የቁርኣን አያዎችንና ሐዲሦችን ያለቦታቸው መጠቃቀሱ ነው። ይህ አካሄድ በተለይም አላዋቂዎች ዘንድ የሚፈጥረው አንድምታ ከባድ ነው። ምክንያቱም መድረክ ይዞ በኢስላም ስም የተናገረ ሁሉ ዓሊም የሚመስላቸው ብዙ ናቸውና። በተለይ በተለይ ደግሞ ስሜታቸውን የሚከተሉ የሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ምን አይነት አቀባበል እንደሚያገኝ ገምቱት። እነኚህ ስሜታውያን ስሜታቸውን የሚያስደስት ደሊል መሳይ ነገር ካገኙ የሌላኛውን ወገን ማስረጃ መስሚያ ጆሮ አይኖራቸውም።
የሐሰን አቀራረብ የሚገርም ነበር። ሙዚቃን በተመለከተ አንድ መካከለኛ እና ሁለት ፅንፈኛ አቋሞች አልሉ አለ። ያው “መካከለኛ” የሚለው እሱ ያለበትን ሙዚቃን የሚፈቅድበትን እንደሆነ ግልፅ ነው። ይሄ የሁልጊዜ አካሄዱ ነው። የቆመለትን ሰንካላ አካሄድ "ወሰጥ" የሚል ካፖርት ያለብስና የሚቃወሙትን ጠርዘኛ ተደርገው እንዲታዩ ይጥራል። የአስተሳሰብ ሽብር መፍጠር ነው አላማው። በሱ እይታ ሁለቱ ፅንፎች ምንና ምን ናቸው? አንዱ ያው ሙዚቃን ሐራም የሚለው ነው። ሌላኛው ፅንፍ ሐሰን ታጁ የራሱን ሀሳብ መካከለኛ ለማድረግ ሲል ብቻ የሚፈጥረው #ምናባዊ አቋም ነው።
በርግጥ የሐሰንን የሸገር ፈትዋ ጠበቅ አድርገን ከፈተሽነው የንግግሩ አንድምታ “ሙዚቃ ሐላል ነው” ከማለትም ይሻገራል። “እንዴት?” ማለት ጥሩ። ሙዚቃን ሐላል ለማድረግ ስለ ተፈኩር የሚያትቱ አያዎችን ጠቀሰ። “ሙዚቃ ማለት ውበትን ማድነቅ ነው” አለ። “ቁርኣን በዜማ ነው የሚቀራው፣ አዛንና ኢቃማ በዜማ ነው የሚደረጉት” አለ። ይሄ አነጋገር “ሐላል ነው” ከማለት ይዘላል። “ሐላል” ማለት “አጅርም” ወንጀልም የሌለው ነው። አዛንና ኢቋማ ማድረግ፣ በቁርኣን ድምፅን ማሳመርስ? የተወደዱ ተግባራት ናቸው። በርግጥ እሱ የፈለገው ዜማ በራሱ የተከለከለ አይደለም ለማለት ነው። ግን ስለተፈኩር ማውራቱን ምን አመጣው? ደግሞስ የአዛንና የቁርኣንን ዜማ ከዘፈን ዜማ ጋር ማነፃፀር አይቀፍም ወይ?
ፍንዳታ ሙፍቲዎች
~
ለቅልቅሉ እንጂ - ዳንስ ካልታገደ
ሐራምነት ቀርቶ
ዘፈን ለተፈኩር - እንዲያ ከፈየደ
ምናለ ቢኖሩን - ከ’ኽቲላጥ የራቁ - የዳንስ ምሽቶች?i
ሙዚቀኛ ሸይኾች - አርቲስት ኸጢቦች?i
ምናለስ ቢኖሩን - “አንቱ” የተባሉ - ዘፋኝ ሰባኪዎች?i
ሰፋ ቦርቀቅ ያሉ - ተራማጅ ሙፍቲዎች?i
ዲጄ ሙአዚኖች - ኮሜዲያን ኢማሞች
ምንድን ነው ማካበድ - ምንድን ነው መወጠር?i
ባይሆን ይራቁ እንጂ - ከምላስ ጣጣና - ከትርፍ ንግግርi
አዋጅ በሬዲዮ - ገብር በጋዜጣ
አይበቃም ይደገም - በመፅሀፍ ይውጣ
ህዝቡ ለዘመናት - ተሸውዷልና
ይስማ ይዝፈን ይውጣ - ይጨፍር ይዝናናi
ተቃዋሚ ካለ - ጠባብ ነው ጠርዘኛ
ደሊል ከበዛ ግን - ይፈለጋል ዳኛ
“ልዩነት ረሕማ ነው” - እያለ 'ሚያስተኛ።
ሙሉ አልበሙ ቢቀር - በነጠላ ዜማ - መንፈስ የሚያድሱ
በተስረቅራቂ ድምፅ - በተውረግራጊ አካል - ሰው እያፈዘዙ
ምናለ ቢጣሩ - ልብን አለስልሰው - አይን እያስለቀሱ?i
ካልተቀላቀሉ - መጠጡን ካልጠጡ
ምናለስ ቢኖሩን - “ናይት ክለብ” ገብተው - እያቀነቀኑ “ፈትዋ” የሚሰጡ?i
በጊታር ታጅበው - ማሲንቆ እየመቱ - ጥበብ የሚያጠጡi
አታሞ እየመቱ - “ራፕ” እየዘለሉ - ሰውን የሚያቀኑi
ዘመናይ ቃዲዎች - ኢማሞች ዱዓቶች - ፅንፍ የሰለጠኑi
የታሉ ሞዴሎች - መቼ ነው የምናይ - ራቀብን ዘመኑ?i
“ዋቂዕ” የገባቸው - “ሒክማ” ያጠለቁ - ኡማን የሚያድኑi
ጥዑም ዜማ ሰምተው - ምላሽ የማይሰጡ
ከለዘብተኛው ወንዝ - “ገር” ውሀ ይጠጡi
ወደኛ ይውረዱ - ቡራኬ ይውሰዱi
ቀሽት ነው መንገዱ - ይመስጣል ሙዱi
መምሬንም ያዙ - በዚያው በመንገዱ
አካብደዋልና - ያው እንደለመዱi
ይህን ካልፈቀዱ - ይህን ካላግራሩ
“ዲኑ ገር ነው” ማለት - የታል ቁምነገሩ?i
ሙስሊሙ ወንድሜ - ዜማ የለቀቅከው
ሐራም ሲሉ ሰምተህ - የተሸማቀቅከው
ቀና በል ካንገትህ - ከኛ ጋር ሌላ ነው
ሌላው እንኳን ቢቀር - ቢያንስ ቢያንስ ሐላል ነውi
ሬዲዮ ጋዜጣው - መፅሀፍ የፃፍነው
የዚህ ሁሉ ልፋት - ትርፉ ምን ሊሆን ነው?
ስለዚህ ቀና በል - አዝናና እንዳትሰጋ
“ትርፍ ወሬ” ግን ቀንስ - እንዳትዘናጋ።
ሞዴሊስቷ እህቴ - ራቁት ኢኽቲላጥ ቢሉሽ
አንቺ እንኳን በሙያሽ - ኢስላምን አስጠራሽ
ጭንቀትሽ ግልፅ ነው - ያሳስባል በጣም
ቢሆንም ታገሺ - ተስፋ አይቆረጥም
የሚፈቅድ “ሙፍቲ” - ፈልገን ፈልገን - ፈልገን አናጣምii
(ኢብኑ ሙነወር፣ 2002)

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የአጥፊዎችን ስም በግልፅ ማንሳት
(መረጃ ለሚያከብሩ ብቻ!)
~
ዛሬ ዛሬ የቢድዐ አራማጆች ወይም ተሻጋሪ ጥፋት የሚያደርሱ አካላት ላይ ስማቸውን ጠቅሶ ምላሽ መስጠትን እንደ አፍራሽ ተግባር የሚቆጥሩ ብዙ ናቸው። እንዲያውም "ለምን ስም ሳትጠቅሱ ሃሳቡ ላይ ብቻ እርምት አትሰጡም?" ይላሉ። የሚገርመው እነዚህ "የሰው ስም አታንሱ" የሚሉ አካላት ራሳቸው የሚጠሉትን ሰው ትልቅ ዓሊም እንኳ ቢሆን ስሙን ጠርተው ከማብጠልጠል የማይመለሱ መሆናቸው ነው። ቢሆንም ዳኛችን እልህ ሳይሆን መረጃ መሆን አለበትና በመረጃ እንነጋገራለን።
በቅድሚያ በረባ ባልረባ ስም መጥቀስ እንደማይገባ ለመግለፅ እወዳለሁ። በተለይ ጥፋቱ ህዝብ ጋር ካልደረሰ፣ የተለየ ምክንያት ካልኖረ በስተቀር፣ ወይ በግል መምከር ወይ ሌሎችም እንዲማሩበት ስም ሳይጠቅሱት በደፈናው እርምት መስጠት የነብዩ ﷺ ሱና ነው። ነገር ግን ጥፋቱ አደባባይ ከወጣና ባለበት ቢትተው ህዝብ የሚጎዳ ከሆነ ባደባባይ ምላሽ ይሰጣል። ስለዚህ "በደፈናው ጥፋቱን ማረም ይሻላል ወይስ ስም ጠቅሶ እርምት መስጠት ይሻላል?" የሚለውን መገምገም ወግ ነው። ዛሬ እያየን ያለነው ግን ከነ ጭራሹ ስም ጠቅሶ መናገር ወንጀል እንደሆነ ሰፊውን ህዝብ የሚግቱ አካላትን ነው። አጥፊ በየትኛውም ሁኔታ ስሙ ሊነሳ አይገባም ማለት በኢስላም ታሪክ ፈፅሞ የሌለ፣ ከዐቅልም ያፈነገጠ፣ ከመረጃም የተኳረፈ አስተሳሰብ ነው።
1 - የዐቅል ማስረጃ፦
ሰዎች ላይ ዱንያቸውንም ይሁን ኣኺራቸውን የሚጎዳ ጥፋት የሚያደርስ አካል ስሙን ጠቅሰን ብናስጠነቅቅ ጉዳቱን ማስቀረት ወይም መቀነስ የሚቻል ከሆነ ይህንን ማድረግ እንደሚገባ የትኛውም ጤነኛ ዐቅል የሚገነዘበው ነው። ማንም የሚገነዘባቸው ምሳሌዎች ልጥቀስ፦
* ምሳሌ 1 - የምታውቁት ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት የሚሸጥ ፋርማሲ አለ እንበል። መድሃኒት ለመግዛት የወጣ ሰው ወደዚያ ሲሄድ ብታዩት ሃሜት እንዳይሆን ብላችሁ ዝም ትላላችሁ? ዝም ብትሉ በሚደርሰው ጉዳት ወንጀለኛ ትሆናላችሁ።
* ምሳሌ 2 - አንድ የህክምና ትምህርት እንደሌለው የምታውቁት ሰው በፎርጂድ ወረቀት ክሊኒክ ቢከፍት አይናችሁ እያየ ህዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርስ ሃሜት ይሆናል ብላችሁ ዝም ትላላችሁ ወይስ አስፈላጊውን እርምጃ ትወስዳላችሁ? የሰዎች የኣኺራ ደህንነት ከዱንያዊ ህይወታቸው በላይ ነው።
* ምሳሌ 3 - የሰፈራችሁ አትክልት ቤት ሚዛን የሚቀሽብ እንደሆነ ብታውቁ ልጃችሁ ከዚያ እንዳይገዛ ትናገራላችሁ ወይስ ሃሜት እንዳይሆን በሚል በዝምታ ሐቃችሁ እየተወሰደ ዝም ትላላችሁ? ታዲያ የዲናችን ዋጋ ከቲማቲም ያነሰ ሆኖ ነው ወይ ቢድዐ የሚዘራ፣ ህዝብ የሚያሳስት ሰው ስሙ ሲነሳ የሚጎረብጠን? ብዙ ምሳሌዎችን መዘርዘር ቢቻልም በቀረቡት ልብቃቃ። "ጨዋ ጥቆማ ይበቃዋል።"
2 - የሐዲሥ ማስረጃ
ሀ - ፋጢማህ ቢንት ቀይስ - ረዲየላሁ ዐንሃ - ሁለት ሰዎች ለትዳር ጠየቋት፣ አቡ ጀህም እና ሙዓዊያህ። ጉዳዩን ለነብዩ ﷺ ስታማክራቸው እንዲህ አሏት ፡-
أَمَّا أَبُو جَهْمٍ، فَلَا يَضَعُ عَصَاهُ عَنْ عَاتِقِهِ، وَأَمَّا مُعَاوِيَةُ، فَصُعْلُوكٌ، لَا مَالَ لَهُ، انْكِحِي أُسَامَةَ بْنَ زَيْدٍ
“አቡ ጀህም ዱላውን ከትከሻው አያወርድም (ይማታል)። ሙዓዊያ ደግሞ ድሃ ነው፣ ገንዘብ የለውም። ይልቅ ኡሳመቱ ብኑ ዘይድን አግቢ።” [ሶሒሕ ሙስሊም: 3770]
ልብ በሉ! ሰዎቹን በሌሉበት ነው ስማቸውን ያነሱት። በአንዲት ሴት የትዳር ጉዳይ አስፈላጊ ሲሆን የሰዎችን ስም ማንሳት ከተቻለ፣ ዲንን የሚያጠለሹ፣ ወደ ቢድዐ የሚጣሩ ሰዎችን ስም ጠቅሶ ማስጠንቀቅ ደግሞ የበለጠ ተገቢ ነው።
ለ - እናታችን ዓኢሻህ - ረዲየላሁ ዐንሃ - እንዲህ ብላለች፦
قالت هِنْدُ امْرَأةُ أَبي سفْيَانَ للنَّبيِّ صلى الله عليه وسلم: إنَّ أَبَا سُفْيَانَ رَجُلٌ شَحِيحٌ وَلَيْسَ يُعْطِينِي مَا يَكْفيني وولَدِي إِلا مَا أَخَذْتُ مِنْهُ، وَهُوَ لا يَعْلَمُ؟ قَالَ: ((خُذِي مَا يَكْفِيكِ وَوَلدَكِ بِالمَعْرُوفِ
"የአቡ ሱፍያን ሚስት ሂንድ ለነብዩ ﷺ 'አባ ሱፍያን ስስታም ሰው ነው። እሱ ሳያውቅ የምወስድበት ካልሆነ በቀር ለኔና ለልጄ የሚበቃንን አይሰጠንም' አለቻቸው። 'ላንቺም ለልጅሽም የሚበቃ በልኩ ውሰጂ' አሏት።'' [አልቡኻሪይ፡ 5364] [ሙስሊም፡ 3532]
ልብ በሉ! የአቡ ሱፍያን ነውር በሌለበት ሲነሳ "ሃሜት ነው ተይ!" አላሏትም።
የነዚህን ሐዲሦች መልእክት ዋጋ ለማሳጣት ውሃ የማያነሳ ትንታኔ የሚሰጡ፣ በዱንያዊ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚገድቡ ሰዎች አሉ። ይሄ ግን ግልፅ ስህተት ነው። ጉዳዩን እኛ ስናነሳው ለማይዋጣቸው አካላት በሚያከብሯቸው ሸይኽ እንሞግታቸዋለን። ነወዊይ በታዋቂው ሪያዱ ሷሊሒን ኪታባቸው ላይ "باب مَا يباح من الغيبة" የሚል ሰዎችን በሌሉበት ነውራቸውን ማንሳት የሚቻልበት ሁኔታ ለማሳየት አንድ ርእስ ቋጥረዋል። በስሩም ሰዎችን ስማቸውን ማንሳት የሚቻልባቸው ስድስት ምክንያቶች እንዳሉ የዘረዘሩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አራተኛ ላይ የጠቀሱት እንዲህ የሚል ነው፦
الرَّابعُ: تَحْذِيرُ المُسْلِمينَ مِنَ الشَّرِّ وَنَصِيحَتُهُمْ
"ሙስሊሞችን ከነዚህ ሰዎች ክፋት ለማስጠንቀቅና ምክር ለመለገስ ነው።"
ዝርዝር የፈለገ ማብራሪያቸውን ይመልከት።
3 - የሰለፎች ፈለግ
ከነወዊይ ይልቅ ይበልጥ ክብደት ያለው ደግሞ የሰለፎች ፈለግ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ያሉ የሰለፎች ንግግሮች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ልብ በሉ! የምጠቅሳቸው አካላት ሁሉም ከሞቱ ከአንድ ሺህ አመት በላይ ያለፋቸው ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት ናቸው።
ሀ. ታቢዒዩ ሐሰን አልበስሪይ (110 ሂ.):- “ለቢድዐ ሰው ሃሜት የለውም! (ስሙ መነሳቱ ከሃሜት አይቆጠርም)። አመፁን ባደባባይ ለሚያወጣ አመፀኛም ሃሜት የለም” ብለዋል። [ሸርሑ ኡሱሊ ሱናህ፣ ላለካኢ፡ 1/158]
ለ. ታቢዒዩ ቀታዳህ ብኑ ዲዓማ አሰዱሲይ (117 ሂ.)
ዓሲም አልአሕወል እንዲህ ይላሉ፡- “ቀታዳ ዘንድ ተቀምጬ ነበር። ዐምር ብኑ ዑበይድ ስሙ ሲወሳ በክፉ አነሳው። 'ዑለማኦች አንዱ በሌላው ላይ እንደሚናገር አላውቅም ነበር' ስለው 'አሕወል ሆይ! አንድ ሰው ቢድዐ ሲያንፀባርቅ ሰዎች ይጠነቀቁት ዘንድ ስሙ ሊጠቀስ እንደሚገባ አታውቅም'ንዴ?' አለኝ።” [አልሚዛን፡ 5/330]
ሐ. ዐብዱላህ ብኑል ሙባረክ (181 ሂ.):-
በአንድ ወቅት “ሙዐላ ብኑ ሂላል ጥሩ ሰው ነበር በሐዲሥ ላይ ይዋሻል እንጂ” ይላሉ። በዚህን ጊዜ የሆነ ሱፊይ ሰማቸውና “የዐብዱረሕማን አባት ሆይ! እንዴት ሰው ታማለህ?” አላቸው። ኢብኑ ሙባረክ ታዲያ፡ “ዝም በል! ግልፅ ካላደረግን እውነትና ሃሰት እንዴት ይልለያል?!” አሉት። [አልኪፋያህ፡ 9]
መ. ዑቅባህ ብኑ ዐልቀማህ (204 ሂ.) እንዲህ ይላሉ፡-

“በአንድ ወቅት ከአርጣህ ብኑ ሙንዚር ጋር ነበርኩኝ። በቦታው ከነበሩ ሰዎች አንዱ ‘ከአህሉ ሱና ጋር እየተቀመጠ፣ እየተቀላቀላቸው ስለ ቢድዐ ሰዎች ሲወራ ግን ‘ተውን እንግዲህ ስማቸውን አታንሱ’ ስለሚል ሰው ምን ትላላችሁ’ ሲል ጠየቀ። አርጣህ፡ ‘እሱ እራሱ ከነሱ ነው። እንዳያታልላችሁ!’ አለ።
ይሄ የአርጣህ ንግግር አልተመቸኝምና ወደ አውዛዒይ ሄድኩኝ። አውዛዒይ እንዲህ አይነት ነገሮች ሲደርሱት ገላጭ ነበር። ጠየቅኩት። ‘አርጣህ እውነት ተናግሯል። ሐቁ እሱ ያለው ነው። ይሄ ሰውየ ስማቸው እንዳይነሳ ይከለክላል። ስማቸው ካልተገለፀ እንዴት ሰዎች ይጠነቀቋቸዋል?!’ አለ።” [ታሪኹ ዲመሽቅ፡ 8/15]
ሠ. ኢማሙ አሕመድ (241 ሂ.):-
ሙሐመድ ብኑ በንዳር፡ “በውኑ እኔ እከሌ እንዲህ ነው፣ እከሌ እንዲህ ነው ማለት ይከብደኛል” ቢላቸው፣ ኢማሙ አሕመድ፡ “አንተም ዝም ካልክ፣ እኔም ዝም ካልኩ መሀ .ይም የሆነ ሰው ጤነኛውን ከበሽ .ተኛው እንዴት ይለየው?!” ብለው መለሱላቸው። [አልፈታዋ፡ 28/231]
4 - ኢጅማዕ
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የአጥፊዎችን ስም ጠቅሶ መናገር የዑለማእ ኢጅማዕ እንዳለበት ኢብኑ ረጀብ ጠቅሰዋል። [አልፈርቅ በይነ ነሲሐ ወትተዕዪር፡ 25]
በድጋሜ የማስታውሰው ከነዚህ የሰው ስም አታንሱ ከሚሉ ሰዎች ውስጥ የሰው ስም የማያነሳ የለም። “ስም አታንሱ” የሚሉት የኛ በሚሉት አካል ላይ የሚሰጠውን ሂስ ዝም ለማሰኘት እንጂ አነሰም በዛ ራሳቸውም የሰው ስም ከማንሳት የሚቆጠቡ አይደሉም።
ሰላም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት ዐ4/2009)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ይሄ የአርጣህ ንግግር አልተመቸኝምና ወደ አውዛዒይ ሄድኩኝ። አውዛዒይ እንዲህ አይነት ነገሮች ሲደርሱት ገላጭ ነበር። ጠየቅኩት። ‘አርጣህ እውነት ተናግሯል። ሐቁ እሱ ያለው ነው። ይሄ ሰውየ ስማቸው እንዳይነሳ ይከለክላል። ስማቸው ካልተገለፀ እንዴት ሰዎች ይጠነቀቋቸዋል?!’ አለ።” [ታሪኹ ዲመሽቅ፡ 8/15]
ሠ. ኢማሙ አሕመድ (241 ሂ.):-
ሙሐመድ ብኑ በንዳር፡ “በውኑ እኔ እከሌ እንዲህ ነው፣ እከሌ እንዲህ ነው ማለት ይከብደኛል” ቢላቸው፣ ኢማሙ አሕመድ፡ “አንተም ዝም ካልክ፣ እኔም ዝም ካልኩ መሀ .ይም የሆነ ሰው ጤነኛውን ከበሽ .ተኛው እንዴት ይለየው?!” ብለው መለሱላቸው። [አልፈታዋ፡ 28/231]
4 - ኢጅማዕ
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የአጥፊዎችን ስም ጠቅሶ መናገር የዑለማእ ኢጅማዕ እንዳለበት ኢብኑ ረጀብ ጠቅሰዋል። [አልፈርቅ በይነ ነሲሐ ወትተዕዪር፡ 25]
በድጋሜ የማስታውሰው ከነዚህ የሰው ስም አታንሱ ከሚሉ ሰዎች ውስጥ የሰው ስም የማያነሳ የለም። “ስም አታንሱ” የሚሉት የኛ በሚሉት አካል ላይ የሚሰጠውን ሂስ ዝም ለማሰኘት እንጂ አነሰም በዛ ራሳቸውም የሰው ስም ከማንሳት የሚቆጠቡ አይደሉም።
ሰላም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት ዐ4/2009)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ደዕዋ ላይ ለተሰማራችሁ ወይም ሃሳቡ ላላችሁ ሁሉ!
~
ኢስላምን ማስተማር አቻ የሌለው ዘርፍ ነው። ከዐርሹ በላይ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلࣰا مِّمَّن دَعَاۤ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَـٰلِحࣰا وَقَالَ إِنَّنِی مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِینَ }
"ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ 'እኔ ከሙስሊሞች ነኝ' ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?" [አልፉሲለት፡: 33]
የሃገራችን ቁርኣንን የማስተማር ስልት በጣም ደካማ ነው። ወደ ገጠሩ ደግሞ ችግሩ ይብሳል። ስለዚህ ራሳችሁን በሚገባ አዘጋጁና ቁርኣንን አስተምሩ። ቁርኣንን ማስተማር :-
1- ከፍ ያለ ደረጃን ለመጎናፀፍ ወሳኝ ሰበብ ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
خَيْرُكُمْ مَنْ تَعَلَّمَ الْقُرْآنَ وَعَلَّمَهُ
"ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው።" [ቡኻሪይ ፡ 5027]
2. ቁርኣንን ማስተማር ትውልድ መገንቢያ ሁነኛ መንገድ ነው። ልጆች በዚህ እድሜያቸው ገና ሱስ አያውቁም። አእምሯቸው ከብልሹ አመለካከቶች ንፁህ ነው። ስለዚህ ቁርኣንን በጥሩ ሁኔታ ካስተማርናቸው በሂደት ከስር ጀምረን መሰረታዊ ትምህርቶችን በማስከተል ለመኮትኮት ሰፊ እድል እናገኛለን። የዒልም ጉጉት እንዲያድርባቸውም ማድረግ እንችላለን።
3. ወላጅ በአብዛኛው ለቁርኣን ልዩ ቦታ አለው። እኛ ልጆቹን በአካባቢው ካሉት በተሻለ መንገድ ካስተማርናቸው እና ፍሬው በግልፅ የሚታይ ከሆነ አጠቃላይ የደዕዋ አካሄዳችን ላይ እንቅፋት የመሆን እድሉ አናሳ ነው። ስለዚህ የአካባቢያችንን የዲን ግንዛቤ ለመቀየር እጅግ ትርጉም ያለው ስራ መስራት እንችላለን።
ነገር ግን እነዚህን ፍሬዎች ለማግኘት የማስተማር ስልታችን በአካባቢው ካሉት የተሻለ አያያዝ ያለው፣ ጥራት ያለው፣ በንፅፅር በአጭር ጊዜ ለውጥ የሚታይበት ሊሆን ይገባል። ቢቻል በርብርብ፣ ካልሆነ ለብቻችንም ቢሆን መስራት እንችላለን። የማስተማሩ ስራ በወንድም፣ በሴትም፣ በመስጂድም፣ በቤትም መሆን ይችላል። እናስብበት። አላህ ያግዘናል።

ሲጋራ ማጨስም፣ መነገዱም ሐራም ነው!
~
ሲጋራ ማጨስ አጫሹም ይሁን በቅርቡ ያሉ ሰዎችን ከባድ የጤና ጉዳት የሚያደርስ ሱስ ነው። ጎጂ ነገር በኢስላም ሐራም ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
وَلا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ
"ራሳችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ።" [አልበቀራ፡ 195]
ነብያችንም ﷺ "መጉዳትም መበቀልም የለም (አይፈቀድም)" ብለዋል። ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል (2341)። አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7517]
ስለሆነም ጎጂ ነገርን መጠቀምም በጎጂ ነገር መነገድም ሐራም ነው። ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"ለማንም ሰው ሲጋራ ሊሸጥ አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ሲጋራ የተከለከለ ነውና። አላህ አንድን ነገር ከከለከለ የሽያጭ ዋጋውንም ነው የሚከለክለው። እንዲሁም ሲጋራን መሸጥ በወንጀልና ወሰን በመተላለፍ ላይ መተባበር ነው።" [አሊቃኡ ሸህሪይ፡ 22/57]
ኢብኑ ባዝ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፦
"ሲጋራ ማጨሱም፣ መሸጡም፣ በሱ መነገዱም አይፈቀድም። በዚህ ላይ ከባድ ጉዳትና መጥፎ ፍፃሜ አለበትና።" [አልፈታዋ፡ 6/456]
ሲጋራ ለሌሎች መግዛትም አይፈቀድም። በሐራም ነገር መተባበርም አይቻልም። አላህ እንዲህ ብሏል፦
{ وَلَا تَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَ ٰنِۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِیدُ ٱلۡعِقَابِ }
"በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ። አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።" [አልማኢደህ: 2]

ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
~
ሙሐመድ ብኑ ዐሊ አሸውካኒ በ1250 ሂ. የሞቱ ታላቅ የመናዊ ዓሊም ናቸው፡፡ በሰፊው የሚታወቁ ስለሆኑ እሳቸውን በማስተዋወቅ ረጅሙን ፅሑፌን ይበልጥ ማስረዘም አልሻም፡፡ ሸውካኒ መውሊድ ላይ እጅግ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ዛሬ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው መውሊድ ተኮር ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑትን በመምዘዝ በሸውካኒ ንግግር ምላሽ እሰጣለሁ፡፡ ሙሉ ንግግራቸውን መመልከት የፈለገ ሰው “አልፈትሑ ረባኒ ሚን ፈታዋ አልኢማሚ ሸውካኒ” በተሰኘው የፈትዋ መድብላቸው ውስጥ ሁለተኛውን ጥራዝ ከገፅ 1087-1101 ድረስ መመልከት ይችላል፡፡ (ፅሑፉ ስለ ረዘመ ዐረብኛውን ማካተት አልቻልኩም፡፡)
1. መውሊድ የሸሪዐ መነሻ አለውን?
ሸውካኒ፡- “እስካሁን ድረስ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከኢጅማዕም፣ ከቂያስም (ንፅፅራዊ ምልከታም) መሰረት እንዳለው የሚያመላክት መረጃ አላገኘሁለትም፡፡” [ገፅ፡ 2/1087]
2. መውሊድን ሰለፎች ያውቁታል?
ሸውካኒ፡- “እንዲያውም ከዘመናት ሁሉ ምርጡ በሆነው (የሶሐቦች) ዘመንም፣ ከነሱ ቀጥሎ በነበሩትም፣ ቀጥሎ በነበሩትም (ዘመን) እንዳልነበር ሙስሊሞች ወጥ አቋም ይዘዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡)” [ገፅ፡ 2/1087]
3. ቢድዐ በመሆኑ ላይ ልዩነት አለ?
ሸውካኒ፡- “ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሙስሊሞች አንድ እንኳን የተቃወመ የለም፡፡” [ገፅ፡ 2/1088] “ይሄ ነገር ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሁሉም ሙስሊሞች ኢጅማዕ እንዳለበት አረጋግጠንልሃል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
4. መውሊድን በሚደግፉ መሻይኾች ማስፈራራት ያዋጣል?
ሸውካኒ፡- “በምርጡ ነብይ ﷺ የማያሻማ ምስክርነት ቢድዐ ሁሉ ጥመት እንደሆነ ተነግሮ ሳለ የመውሊድን ቢድዐ መሆን ካመነ በኋላ ይፈቀዳል የሚል ሰው የተናገረው ከንፁሁ ሸሪዐ ጋር የሚፃረር ንግግር ነው፡፡ ያለ አንድ ተጨባጭ እውቀታዊ መነሻ ቢድዐን ወደተለያዩ ክፍሎች ለከፈለ ሰው በጭፍን ከመከተል ያለፈ ነገርም የለውም፡፡ የትኛውንም አቋም ይቻላል የሚልን ሰው ይህንን ቢድዐ በተለየ የሚመለከት ማስረጃ ካቀረበ በኋላ እንጂ አንቀበለውም፡፡ … እንጂ ‘እከሌ እንዲህ አለ’፣ ‘እከሌ እንዲህ አይነት ኪታብ አዘጋጅቷል’ የሚል ባዶ ንግግር ፋይዳ የለውም፡፡ ሐቅ ከየትኛውም አካል ይበልጣልና፡፡” [ገፅ፡ 2/1088 - 1089]
“ከነሱ (ከፈቃጆቹ) ውስጥ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፡፡ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም፡፡” [ገፅ፡ 2/1094]
ኢብኑ ሐጀር እንዳደረገው የዓሹራን ፆም ማስረጃ ማድረግ፣ ወይም ሲዩጢ እንዳደረገው ከነብይነት በኋላ ለራሳቸው ዐቂቃ ማውጣታቸውን መመርኮዝ ቢድዐን የማፅናት ፍቅር እንዲህ አይነት ነገር ላይ እንደሚጥል ከሚያሳዩ አስገራሚ ነገሮች ውስጥ ነው፡፡ [ገፅ፡ 1095]
5. መውሊድ የብዙሃን ሙስሊሞች ድጋፍ ነበረውን?
ሸውካኒ፡- “በሰዎች ንግግሮች ላይ የምንመረኮዝ ከሆንና የእንቶ ፈንቶ ጅራቶችን የምንጨብጥ ከሆንን መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ‘ይፈቀዳል’ ባዮቹ ከሙስሊሞች በአቋም ያፈነገጡ ናቸው፡፡ …” [ገፅ፡ 2/1087-1089]
“ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1095–1099]
(አስተውሉ! ይህ እንግዲህ በሸውካኒ ዘመን ነው፡፡ የሞቱት በ1250 ሂ. ሲሆን ሁለት መቶ አመት ሊሞላቸው ጥቂት ነው የቀራቸው፡፡ ሱፊያ ደፋር ነውና የዛሬን የመውሊድ ጨፋሪዎች በመመልከት ሸውካኒን “ውሸታም ነው” እንዳይሉ እሰጋለሁ፡፡)
6. መውሊድ እንዴት ተስፋፋ?
ሸውካኒ፡- “ግና ቢድዐን በማፅናትም ሆነ በማጥፋት ላይ ንጉሳን ተፅእኖ አላቸው፡፡ ይህንን ቢድዐ (በሱኒው ዓለም ውስጥ) የፈጠረው ያ ንጉስ (ሙዞፈር) ሲሆን ኢብኑ ዲሕያ ደግሞ ‘አተንዊር ፊ መውሊዲል በሺር ነዚር’ የተሰኘ ኪታብ በማዘጋጀት አግዞታል፡፡ ሰውየው በዘገባ እውቀት ላይ የጠለቀ ከመሆኑም ጋር በዚህ ኪታቡ ግን ግልፅ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ለዚህ ስራው - ኢብኑ ኸሊካን እንደጠቀሱት - አንድ ሺህ ዲናር በንጉሱ መሸለሙ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የዱንያ ፍቅር ከዚህም በላይ ያደርሳል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
“የቢድዐ ስርጭት ከእሳት ስርጭት የፈጠነ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ መውሊድ፡፡ ምክንያቱም የመሃይማን ነፍሶች ጥግ የደረሰ መናፈቅን ይናፍቁታልና፡፡ በተለይ ደግሞ ከምሁራን፣ ከክቡራንና መሪዎች በርከት ያለ ሰው ከተካፈለበት በኋላ ይሄ ቢድዐ ወሳኝ ከሆኑ ሱናዎች ይመስላቸዋል፡፡ … እንደ መውሊድና አምሳያዎቹ ያሉ ለሐራም ነገሮች የሚያመቻቹ የጥፋት መዳረሻዎች መሃይሞች ፈጥነው እንደሚገቡባቸው አያጠራጥርም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ በዒልም፣ በክብርና በስልጣን ዝና ያለው ሰው መካፈል ሲታከልበት ሐራም ነገሮችን እንደ ፈጣሪ ትእዛዛት ሲፈፅሙ፣ በድንቁርናና በጥመት ሸለቆች ውስጥ ገብተው ሲዘባርቁ፣ “የተከበሩ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተገኝተዋል” እያሉ ከተቃውሞ ሲያመልጡ የባሰ ይሆናል፡፡
መሃይሙ ህዝብ ይቅርና አንዱ በዒልም ፍለጋ ላይ ገኖ የወጣ ሰው አንዳንድ የኢጅቲሃድ እውቀቶችን ለመማር ከፊቴ ተቀምጦ ነበር፡፡ በዚህ ወር ከተከናወኑ መውሊዶች ውስጥ በአንዱ አዳር ላይ እንደተካፈለ ሲነግረኝ ተቃወምኩት፡፡ አንገሸገሸኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ‘ሰዪዲ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተካፍለዋልኮ’ አለኝ፡፡ በነዚህ ታዋቂ ሰዎች ፊት የነበረውን አፈፃፀም ስጠይቀው እንዲህ አለኝ፡-
‘እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እየዘፈኑና እያዳመጡ መንዙማውን አንድ ዱርየ አነበበ፡፡ ከዚያም አንዱ ልክ ከእስር የተነሳ ይመስል አፈፍ ብሎ ተነስቶ “መርሐባ ያ ኑረ ዐይኒ፣ መርሐባ” (እንኳን መጣህ ያይኔ ብርሃን እንኳን መጣህ!) ሲል ታዳሚው በመላ ታዋቂዎቹን ጨምሮ ተከትለውት ቆሙ፡፡ እነሱ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቆሞ ማጓራት ያዘ፡፡ አንዱ ታዳሚ ደክሞት ቢቀመጥ ከታዋቂዎቹ ውስጥ አንዱ ንዴቱ ከፊቱ ላይ እየታየ ‘ተነስ! ጨዋታኮ አይደለም!’ ብሎ ጮኸበት፡፡ ቃል በቃል! የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚያች ሰዓት ከነሱ ዘንድ እንደደረሱ ጭራሽ አይጠራጠሩም፡፡ ከዚያም ተጨባበጡ፡፡ ከመሀይማን ከፊሎቹ በእጆቻቸው ሽቶ በመያዝ በፍጥነት ቀቡ፣ ተቀቡ፡፡ ልክ የሳቸውን ﷺ መገኘት ለመጠቀም፡፡’
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! የዲን ክብር የት ገባ?! ይህም ከጠፋ አይናፋርነት፣ ግብረ ገብነት፣ ህሊና የት ገባ?” [ገፅ፡ 2/1089-91]
7. መውሊድን የነብዩ ﷺ ቤተሰቦች ይደግፉታል?
መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች “ከኛ በላይ ነብዩን ﷺ የሚወድ ላሳር!” የሚሉ ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር የነብዩ ﷺ ዘሮች ሙእሚኖች ከሆኑ ለነብዩ ﷺ ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው፡፡ መውሊዱ የፍቅር መገለጫ ቢሆን ኖሮ ከማንም ቀድመው ባከበሩት ነበር፡፡ ግን ከነሱ የተገኘው መውሊድን ማክበር፣ ማስከበር፣ ለሱ ሽንጥን ገትሮ መሟገት ነውን?
ሸውካኒ፡- “ከነብዩ ﷺ ንፁሕ ቤተሰብም ይሁን ከተከታዮቻቸው ይህ ነገር እንደሚፈቀድ የተናገረ አንድም ፊደል አላገኘንም፡፡ እንዲያውም ይህቺ ቢድዐ ከተከሰተች ጀምሮ ወደ ጥፋቶች ከሚያሻግሩ አስቀያሚ መዳረሻዎች አንዷ እንደሆነች ንግግሮቻቸው ከሞላ ጎደል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1089]

“ከነብዩ ﷺ ቤተሰቦች እና ከተከታዮቻቸው ውስጥ ‘መውሊድ ይፈቀዳል’ ያለ አንድ እንኳን እንደሌለ ከተገለፀልህ ከነሱ ውጭ ያሉትን አቋም ልታውቅ ከፈለግክ ከሁሉም ሙስሊሞች ዘንድ ቢድዐ በመሆኑ ላይ ኢጅማዕ እንዳለ አረጋግጠንልሃል እንላለን፡፡” [ገፅ፡ 1091]
8. መውሊድ ውስጥ ሺርክ ወይም ሌላ ጥፋቶች ከሌሉበትስ ይፈቀዳል?
ሸውካኒ፡- “ ‘መውሊዱ ላይ ለምግብ መሰባሰብና ዚክር ብቻ ከሆነ ይፈቀዳል፣ አብረውት የሚያጅቡት ነገሮች ክልክል መሆናቸው ክልክልነቱን አያስይዝም’ የሚሉ ሰዎች ማመሀኛ ፉርሽነቱ ከዚህ ላይ ግልፅ ይሆንልሀል፡፡ ምክንያቱም እኛ እራስህ እንዳመንከው መውሊድ ቢድዐ ከመሆኑ ጋር በልምድ ከብዙ መጥፎ ነገሮች ጋር የተቆራኘና ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ ሆኗል እንላለንና፡፡ ደግሞም ከምግብና ከዚክር ውጭ ያሉ ነገሮችን የማያካትቱ መውሊዶችን ማግኘት ከቀይ ድኝ የበለጠ ፈታኝ ነው፡፡” [ገፅ፡ 2/1090-1091]
“የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ ጋር ሲነፃፀሩ ጥቂቶች ከመሆናቸው ጋር ለምግብና ለዚክር ብቻ በሚል መስፈርት ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡ ለብዙ ጥፋቶች መዳረሻ እንደሆነ ደግሞ ይሄው አሳውቀንሃል፡፡ ይህን ከግምት በማስገባት ላይ አንድም አይፃረርም፡፡ ዛሬ የሚከሰተው የዚህ አይነቱ (ጥፋቱ የበዛበት) መውሊድ ግን በወጥ ስምምነት የተከለከለ ነው፡፡” [ገፅ፡ 2/1098-1099]
“ወደ ጥፋት የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋትና ወደማይፈቀድ ነገር መንጠላጠያ ገመዶችን መቁረጥ ብዙሃን ምሁራን እርግጠኛ ከሆኑባቸው ወሳኝ ሸሪዐዊ መርሆዎች ውስጥ ነው፡፡ አንተ እራስህ እንጥፍጣፊ ሚዛናዊነት ቀርቶህ ከሆነ ይህንን ሐቅ አትክድም፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
9. መውሊድ የልዩነት መንስኤ ነውን?
ሸውካኒ፡- “ደግሞም ይሄ መውሊድ ከተከሰተ በኋላ ውዝግቡ ተጧጡፏል፡፡ በዚህም ላይ የሚፃፉት ኪታቦች ከከልካዩም ከፈቃጁም በዝተዋል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
10. መውሊድ ውስጥ አስቀያሚ ጥፋቶች ከኖሩበትስ?
ሸውካኒ፡- “ሀሳቡ ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡ ለጥፋቶች መዳረሻ እንደሆነ ደግሞ በርግጥም አሳውቀንሃል፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ አንድም የሚወዛገብ የለም፡፡ የዚህ አይነቱ ዛሬ እየተከሰተ ያለው መውሊድ በዑለማእ ስምምነት ክልክል ነው፡፡ ርእሱ የፈቃጆቹን ንግግሮች እያቀረቡ ዘለግ ባለ መልኩ መመለስ የሚጠይቅ ቢሆንም ለጊዜው እዚህ ላይ ይበቃናል፡፡” ከዚያም በሙታን ላይ የሚፈፀመውን ሺርክና የጣኦት አምልኮ ጠቅሰው በጥብቅ ከኮነኑ በኋላ “እኛ ማስጠንቀቅና ማድረስ እንጂ ሌላ አቅም የለንም፡፡ ይህንን ይሄው አድርገናል፡፡ አላህ ሆይ! ለዲንህ ተቆጣ! ከነዚህ ቀብር አምላኪ ሸይጧኖች ቆሻሻም አፅዳው፡፡ ከነዚህ የጠንካራውን እምነት ንፅህና ካጠለሹ ቆሻሻዎችም አሳርፈን፡፡” [ገፅ፡ 1095–1101]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 25/2012)
=
የቴሌግራም ቻናል

ለዐረብ ሀገር ወንድምና እህቶች
~
① ከሁሉም በፊት ለዲናችሁ ቅድሚያ ስጡ። ከተውሒድ ጀምራችሁ ግንዛቤያችሁን በተለያዩ መንገዶች አስፉ። ለአላህ ምስጋና ይግባውና በዚህ በኩል ብዙ ወንድሞችና እህቶች ዘንድ ጥሩ ተነሳሽነት ይታያል።
② ለአሰሪዎቻችሁ ታማኞች ሁኑ። የሰው ሀላፊነት እስከተቀበላችሁ ድረስ አላህን ፈርታችሁ ሀላፊነታችሁን ባግባቡ ተወጡ። በሰዐትም፣ በስራም፣ በገንዘብም፣ በክብርም፣ በልጆችም የምትታመኑ ሁኑ። አማናን መወጣት ትልቅ ሃላፊነት ነው።
③ በተቻላችሁ ከአላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል ተጠንቀቁ። በጋራ የኪራይ ቤቶች ሊፈፀሙ ከሚችሉ አደጋዎች እራሳችሁን ጠብቁ።
④ እርስ በርስ ተዛዘኑ። ስራ ለሌለው ስራ በመፈለግ፣ ለተቸገረው በብድር ወይም እራስን በማይጎዳ መዋጮ ተጋገዙ።
⑤ ከወንጀለኞች ራቁ። ዐረብ ሀገር በርካታ ኢትዮጵያውያን በወንጀል ስራ ላይ መሰማራታቸው የሚታወቅ ነው። በነሱ ሳቢያ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይ በተደጋጋሚ ስማቸው ይጠፋል። የሚገርመው ብዙ ለነዚህ ወንጀለኞች ሽፋን የሚሰጡ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ነው። በነሱ ጥፋት አብራችሁ እንዳትጎዱ ተጠንቀቁ። እንዲያውም ለሌላ የሚተርፍ የተረጋገጠ ወንጀል ካያችሁ ለሚመለከተው አካል ጠቁሙ። ይሄ ለዲናችሁም ለገፅታችሁም ዋጋ አለው።
⑥ ቤተሰቦቻችሁን አትርሱ። ወላጅ ወላጅ ስለሆነ ብቻ ከባድ ሐቅ እንዳለው እሙን ነው። ከዚያም ባለፈ ስንት ፍዳቸውን አይተው አሳድገዋል። ዐረብ ሀገር ትሄዱ ዘንድ የተቸገሩላችሁም ብዙ ናቸው። እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ወላጆቻችሁን አትርሱ። በዚያ ላይ አንዳንዶቻችሁ ወደ ወላጆቻችሁ ልጅ የላካችሁ ትኖራላችሁ። በዚህን ጊዜ ሐቁ ድርብርብ ነውና ኣኺራችሁን እንዳታጨልሙ ተጠንቀቁ።
⑦ እራሳችሁን አትርሱ። የወጣችሁት እንጀራ ፍለጋ ነው። ከፋም ደላ የሰው ሀገር የሰው ነው። ህልማችሁ ቋጥሮ ወደ ሀገር ለመመለስ እንጂ በልቶ ለመውዛት፣ ለብሶ ለመድመቅ አይደለም። ለዚህ ደግሞ ብልጥ መሆን ያስፈልጋል። መስራቱን ቻሉበት። መያዙንም ቻሉበት። ወጭ ቀንሱ። ለቤተሰብ ስትልኩም አቅማችሁንም፣ ኑሯቸውንም፣ ሁኔታቸውንም እያገናዘባችሁ ይሁን። ለጎረምሳ ጫት መቃሚያና መንሸራሸሪያ አትላኩ። በዚህ ወንድሞቻችሁን ታበላሻላችሁ እንጂ አትጠቅሟቸውም። ገንዘባችሁንም አጥታችሁ ወንጀለኛም ትሆናላችሁ። ባጭሩ የምትሰሩትን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ ለማዋል ተጣጣሩ። ባዶ እጃችሁን ላለመግባት በተቻላችሁ ተጠንቀቁ። ችግር መጥፎ ነው። ቤተሰብ እንኳን እንዲገፋችሁ ያደርጋል። አገራችን ለባዶ እጅ ቀርቶ ለያዘም እየከበደ ነው።
⑧ እቅድ ይኑራችሁ። ለቆይታችሁ ገደብ አስቀምጡለት። በግምት አትኑሩ። ሁለት አመት ሰራርቼ አገሬ እገባለሁ ብለው ሃያ አመት የኖሩ አሉ። ከአላማ ካልተወጣ ክፋት አልነበረውም። እየባከኑ ሲሆን ግን ያሳዝናል። "ምን ይዤ ልግባ?" እያሉ እየተብከነከኑ መኖር ይጎዳል። ስለዚህ ገደብ ያለው እቅድ ይኑራችሁ። ለእቅዳችሁም በትጋት አስቡ፣ በትጋት ስሩ። መገናኘታችሁ እቅዳችሁን የሚያሰናክል፣ ለትርጉም የለሽ ወጭ የሚዳርግ ከሆነ ተራራቁ።
⑨ ሴቶች ሆይ! መንገደኛ አታግቡ። እስኪ አሁን ሂንዲ፣ ፓኪስታኒ፣ ባንጋሊ ማግባት ምን ይባላል? እንዲህ አይነቱ ትዳር ዘላቂ የመሆን እድሉ እጅግ የጠበበ ነው። ልጅ ከመጣም ከነ ጭራሹ አባቱ ጋር አይኖርም። ስለዚህ ለራስም ለልጅም ፈተና ነው።
(10) ለኸይር ስራ እጃችሁን ስትዘረጉ ጥንቁቅ ሁኑ። ኸይር አትስሩ አይባልም። ግን በትክክል ለታለመለት ግብ የሚደርስ መሆኑን ቢያንስ ሚዛን የሚደፋ ግምት ያዙ።
(11) ለትዳር ክብር ይኑራችሁ። ትዳርን መስፈርት በማያሟላ በተጨመላለቀ መልኩ ሳይሆን በሥርዓት ፈፅሙ። አትበዳደሉ። ኣኺራችሁን በማይጎዳ መልኩ በስርኣት ኑሩ። ለጋብቻ የተጋነነ ወጭ አታውጡ። ከሰሞንኛ ሆይሆይታ ይልቅ ለዘላቂው ትዳራችሁ ቅድሚያ ስጡ። መለያየት ግድ ካለም ባግባቡ ይሁን።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 4፣ 2013)

መቼም ቢሆን ከዒልም ፍለጋ ልንዘናጋ አይገባም። የትኛውም ቀናችን አነሰም በዛ የሆነ ነገር ልንሸምትበት ይገባል። በዚህ ሳምንት ምን ተምረናል? ምን አዳምጠናል? ምን አንብበናል? ለቀጣይስ ምን አስበናል? በዚህ ዓመት ስንት ኪታብ አየን? ለቀጣይስ ምን አሰብን? አነሰም በዛም ጊዜያችን ከዒልም ፍለጋ የተራቆተ ሊሆን አይገባም።
ጊዜ የለንም ብለን አንዘናጋ። እንደምንም ብለን ጊዜ እንስጥ። ተረጋግተን ተቀምጠን የምንከታተልበት ጊዜ ቢያጥረን ስራችንን እየሰራን ብዙ ደርሶችን፣ ደዕዋዎችን ማዳመጥ እንችላለን። በየቀኑ ከቤቱ ተነስቶ ስራ ቦታ የሚሄድ ሰው፣ ረጃጅም የወረፋ ሰልፍ ላይ የሚቆም ሰው፣ ... ፀጥታ ካለ ቁርአኑን መቅራት ይችላል። እሱ ባይመች ኪታብ ማንበብ፣ ዚክር ማድረግ፣ በኤርፎን ደርስ ማዳመጥ ይችላል። አንዴ ካስለመድነው ህይወታችን ጋር ይዋሃዳል። ቀላል የሚመስለን ጊዜ ብዙ ልንጠቀምበት እንችላለን።
ዋናው ነገር ውስጣችን ለመማር ዝግጁ ይሁን። የምር ካሰብንበት በየቀኑ የሆነ እውቀት መጨመር እንችላለን። ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም።
ዐብዱላህ ኢብኑል ሙባረክ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"አንድ ሰው እውቀትን ፍለጋ ላይ እስከሆነ ድረስ አዋቂ ከመሆን አይወገድም። እንዳወቀ ያሰበ እለት ያኔ አላዋቂ ሆኗል።" [አልሙጃለሳህ : 2/186]

በባለ ትዳሮች መሀል የሚገጥም መጠራጠር
~
ባሏን በሐራም የምትጠራጠር ሴት፣ ወይም ሚስቱን በሐራም ግንኙነት የሚጠራጠር ወንድ ሲያጋጥም በቅድሚያ "አላህን ፍሩ! አትጠራጠሩ!" በማለት አፍ ለማስያዝ ከመሞከር በፊት ሁኔታውን ማየት ያስፈልጋል። ለጥርጣሬ የሚጋብዝ ተጨባጭ መነሻ አለ ወይ?
* ሰበብ ካለ "አትጠራጠሩ " ሳይሆን የሚባለው "ለጥርጣሬ የሚጋብዘውን ክፍተት አስተካክሉ" ነው መሆን ያለበት። ሰበብ ባለበት ሁኔታ በችኮላ "እንዴት ሲባል ልጃችንን ትጠረጥራታለህ?/ ትጠረጥሪዋለሽ?" የሚል የቤተሰብ መከላከያ ኋላ ራሳችንን ሊያሳፍረን ይችላልና በቅድሚያ ሚዛናዊ ሆነን እንመልከት። አዋዋል፣ አነጋገር፣ የስልክ አጠቃቀም፣ ... ላይ ችግሮች ካሉ ፈርጠም ብሎ ማስተካከል ወይም እንዲስተካከል መስራት ይገባል።
* ጥርጣሬው መሰረት የሌለው ቅጥ ያጣ የባህሪ ችግር ከሆነ ያኔ "አላህን ፍሩ! ከጥርጣሬ ራቁ" ብሎ መገሰፅ ይገባል። አጉል ጥርጣሬ ህይወትን ፈተና ያደርጋል። ቤትንም ያፈርሳል።

በአካላችን ላይ የተገጠሙ ምስክሮች!
~
ኸይርም ይሁን ሸር ዛሬ ስለምንሰራው ሁሉ ነገ በቂያማ ቀን የአካል ክፍሎቻችን ምስክሮች ናቸው። የማይዛነፍ፣ በጉቦ የማይታለፍ፣ በዘመድ፣ በትውውቅ የማይሸወድ የፍትህ ችሎት አለ ነገ። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
{ یَوۡمَ تَشۡهَدُ عَلَیۡهِمۡ أَلۡسِنَتُهُمۡ وَأَیۡدِیهِمۡ وَأَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُوا۟ یَعۡمَلُونَ }
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)።" [አንኑር: 24]
{ ٱلۡیَوۡمَ نَخۡتِمُ عَلَىٰۤ أَفۡوَ ٰهِهِمۡ وَتُكَلِّمُنَاۤ أَیۡدِیهِمۡ وَتَشۡهَدُ أَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُوا۟ یَكۡسِبُونَ }
"ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል። እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ።" [ያሲን፡ 65]
በዚያ ቀን አካሎቻችን ብቻ አይደሉም። ምድርም በላዩዋ ላይ የተፈፀመባትን ሁሉ ትናገራለች። ምን ይታወቃል? እጃችን ላይ የሚውለው የሞባይል ስልክም ይመሰክርልን ወይም ይመሰክርብን ይሆናል። ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አልቡረዒይ - አላህ ይጠብቃቸውና - "የሞባይል ስልክ ለባለቤቱ በሰራው መልካም ወይም ክፉ ነገር ላይ በትንሣኤ ቀን ይመሰክራልን ወይ" ተብለው ተጠይቀው ነበር። ምላሻቸው እንዲህ የሚል ነው፦
"አላህ ያውቃል። ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሌሎች ምስክሮች አሉ። ዓይን ይመሰክራል፣ ጆሮ ይመሰክራል፣ በስልኩ ላይ የተንቀሳቀሱ ጣቶች ይመሰክራሉ። ስለዚህ ምስክሮች ብዙ ናቸው።"
ለዚያ ቀን ዛሬ ነው መዘጋጀት። ዛሬ ነው መጠንቀቅ። ዛሬ ነው መሰነቅ። መቼስ ሁላችንም ወደዚያው ጉዞ ላይ ነው። እዚህ ሰፈር በብዛት የሚዘዋወር አንድ የሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁላህ እንዲህ የሚል ስንኝ አለ፦
ሁሉም ይጓዛታል - ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን - ያለውን ስንቁን ይዞ።"

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لَا تُطْرُونِي كَمَا أَطْرَتِ النَّصَارَى ابْنَ مَرْيَمَ، فَإِنَّمَا أَنَا عَبْدُهُ، فَقُولُوا : عَبْدُ اللَّهِ وَرَسُولُهُ "
"ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ (ዒሳን) እንዳጋነኑ እኔን አታጋንኑ። እኔ የአላህ ባሪያው ነኝና፣ 'የአላህ ባሪያውና መልዕክተኛው' በሉኝ።" [አልቡኻሪይ ፡ 3445]
በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል፦
مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
"አንድን ሕዝብ የተመሳሰለ (የተከተለ) ከእነርሱ ነው (እንደነርሱ ይቆጠራል)።" [አቡ ዳውድ ፡ 4031]