Telegram Web
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
~
የመውሊድ ደጋፊዎች ለዚህ ቢድዐ የሚያጣቅሱት ትልቁ ማስረጃ እነ እከሌ ደግፈውታል እያሉ ዑለማዎችን ማጣቀስ ነው። ሐቂቃው ግን እነዚህ ዓሊሞች ዛሬ መውሊድ ላይ በሚታየው መልኩ የፈቀዱ አለመሆናቸው ነው። ይሄውና አይታችሁ ታዘቡ፡-

1. አተዝመንቲ (682 ሂ.?)፡-

“የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” “መውሊድ …ፈፃሚው ደጋጎችን መሰብሰብ፣ በነብዩ ላይ ሶለዋት ማውረድ፣ ድሆችንና ምስኪኖችን ምግብ ማብላትን ካሰበ መልካም ቢድዐ ነው። በዚህ ልክና በዚህ ሸርጥ (መስፈርት) ከሆነ ይመነዳበታል። እንጂ ቂላቂሎችን መሰብሰብ፣ ዜማ ማዳመጥ፣ መደነስና ልብስ ማውለቅ … ካለበት አይወደድም። እንዲያውም ሊወገዝ የቀረበ ነው። መልካም ቀደምቶች ካልሰሩት ነገር ውስጥ መልካም የለም።” [አሲረቱ ሻሚያህ፡ 1/441-442]

ሁለት ነገሮችን ያዙ፦
አንድ፦ የመውሊድ በዓል በመልካም ቀደምቶች ዘመን እንደማይታወቅ።
ሁለት ፦ በጥፋት የታጀበ መውሊድ እንደማይደግፍ። ዛሬ ደግሞ እሱ ካወገዘው በላይ መውሊድ እጅግ በርካታ ሰቅጣጭ ጥፋቶችን ያጨቀ ሆኗል።

2. ኢብኑል ሓጅ (737 ሂ.)፦

“ትልልቅ ከሆኑ ዒባዳዎችና የዲን መገለጫዎች እንደሆነ በማመን ሰዎች ከፈጠሯቸው ቢድዐዎች የሚካተተው በረቢዐል አወል ላይ የሚሰሩት መውሊድ ነው። በርግጥም በርካታ ቢድዐዎችንና ክልክል ነገሮችን አጭቋል። ከዚህ ውስጥ ዘፈኖችን መጠቀማቸው ተጠቃሽ ነው። ከነሱ ጋር ከበሮ፣ ዋሽንትና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ይኖራሉ። በዚህም የዘፈን ድግስ አድርገውታል። አንተንም እኛንም አላህ ይዘንልንና ምን ያክል ንፁህ የሆነችዋን ሱና መፃረር እንዳለ፣ ምንኛ አስቀያሚ እንደሆነ፣ ምንኛ አስነዋሪ እንደሆነ፣ እንዴት ወደ ሐራም ነገሮች እንደሚጎትት ተመልከት። ንፁህ የሆነችዋን ሱና በተፃረሩ ጊዜ፣ መውሊድንም በፈፀሙ ጊዜ መውሊዱ ላይ ብቻ እንዳልተገደቡ አታይምን?! ይልቁንም የተወሱትን በርካታ ከንቱ ነገሮች ጨመሩበት። እድለኛ የታደለ ማለት ቁርኣንና ሱናን በመተግበርና ወደዚያ በሚያደርስ ነገርም ላይ እጆቹን ያሰረ ነው። እሷም ያለፉትን ቀደምቶች መከተል ነው፣ ሁሉንም አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸውና። ምክንያቱም እነሱ ከኛ የበለጠ ሱናን የሚያውቁ ናቸውና። ምክንያቱም ንግግርን ይበልጥ የሚያውቁ፣ ሁኔታንም ይበልጥ የሚረዱ ናቸውና። ልክ እንዲሁ እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ በመልካም የተከተላቸውን መከተል ይገባል። ከዘመናችን ሰዎች ባህሎችና ዝቃጭ ባህሎችን ከሚፈፅሙ ሰዎች ይጠንቀቅ።

ዘፈን ከኖረ እነዚህ ጥፋቶች በመውሊድ ተግባር ላይ የተደራረቡ ናቸው። ከሱ የፀዳ ሆኖ ምግብ ብቻ ካዘጋጀ በዚህም መውሊድን ካሰበና ወንድሞችን ወደሱ ከጠራ፣ ቀደም ብለን ከጠቀስነው ሁሉ ነፃ ከሆነ በኒያው ብቻ ቢድዐ ይሆናል። ምክንያቱም ይሄ በዲን ላይ ጭማሬ ነውና። ካለፉ ቀደምቶች ስራም አይደለምና። እናም እነሱ ከነበሩበት ተፃራሪ የሆነ ኒያ ከመጨመር ይልቅ ቀደምቶችን መከተል በላጭ ነው። ኧረ እንዲያውም ግዴታ ነው። ምክንያቱም እነሱ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሱና በመከተል፣ እሳቸውንና ሱናቸውን በማላቅ ከሰው ሁሉ በላጮች ነበሩና። ለነሱ ወደዚህ በመሽቀዳደም በኩል የቀዳሚነት ማእረግ አላቸው። ከነሱ ከአንዳቸውም መውሊድን እንዳሰበ አልተላለፈም። እኛም ለነሱ ተከታዮች ነን። ስለሆነም የበቃቸው ይበቃናል።” [አልመድኸል፡ 2/204-312]

ስለ ጭፈራና ማጨብጨብ ደግሞ እንዲህ ይላል፡- “የሆነ ሰው በ661 እንዲህ የሚል ጥያቄ አዘጋጅቶ ወደ አራቱም መዝሀብ ምሁራን ዘንድ አመራ፡- ‘ክቡራን የዲን መሪዎች የሆኑ ምሁራንና ሙስሊም ዑለማዎች አላህ እሱን ለመታዘዝ ያድላቸው፣ በውዴታውም ላይ ያግዛቸውና የሆኑ የሙስሊም ስብስቦች ወደሆነ ሃገር ሄዱና ወደ መስጂድ አመሩ። በውስጡም ማጨብጨብ፣ መዝፈንና አንዲሁም አንዳንዴ በእጃቸው አንዳንዴ በድቤዎችና በዋሺንቶች መጨፈር ያዙ። በሸሪዐ ይህን መስጂድ ውስጥ መፈፀም ይቻላልን? አላህ ምንዳችሁን ይክፈላችሁና ፈትዋ ስጡን ..’ የዚህን ጊዜ

* ሻፊዒያዎች፡- ‘እንዲህ አይነት መዝሙር መስማት የተጠላ ነው። ባጢል ነው የሚመስለው። ይህን የሚዘምር ሰው ምስክርነቱ ተቀባይነት አይኖረውም። ወላሁ አዕለም’ አሉ።
* ማሊኪያዎች፡- ‘በመሪዎች ላይ እነዚህን ተውበት አድርገው ወደ አላህ እስከሚመለሱ ድረስ ሊከለክሏቸውና ከመስጂድ ሊያስወጧቸው ግዴታ አለባቸው። ወላሁ አዕለም’ አሉ።
* ሐንበሊያዎች፡- ‘ይህን የሚሰራ ሰው ከኋላው አይሰገድም። ምስክርነቱ ተቀባይነት የለውም። ዳኛ ከሆነ ፍርዱ ተቀባይነት የለውም። ኒካሕ ካሰረም ኒካሑ ውድቅ ነው። ወላሁ አዕለም’ አሉ።
* ሐነፍያዎች፡- ‘የተጨፈረባት ምንጣፍ እስከምትታጠብ ድረስ አይሰገድባትም። የተጨፈረባት መሬትም አፈሯ ተቆፍሮ እስከሚወገድ ድረስ አይሰገድባትም። ወላሁ አዕለም’ አሉ።” [አልመድኸል፡ 3/99]

3. አልወንሺሪሲ (834 ሂ.)፡-

“ሙስሊሞች ዘንድ የተከበረ ቢሆንም ነገር ግን በሱ ውስጥ አንዳንድ ቢድዐዎች እስከሚፈፀሙበት ያደረሱት ጉዳዮች አሉ። ይህም በብዛት በዘፈን መሳሪያዎች መገኘትና በሌሎችም ያልተፈቀዱ ፈጠራዎች ምክንያት ነው። እሳቸውን ﷺ ማላቅ ሊሆን የሚገባው ሱናቸውን በመከተልና ፈለጎቻቸውን በመፈፀም ነው። እንጂ መልካም ቀደምቶች ዘንድ ያልነበሩ ቢድዐዎችን በመፍጠር አይደለም።” [አልሚዕያሩል ሙዕሪብ፡ 1/357-358]

4. ኢብኑ ሐጀር (852 ሂ.)፡-

የመውሊድ ደጋፊዎች የሚያጣቅሱት የኢብኑ ሐጀር ንግግር እንዲህ የሚል ነው፡- “የመውሊድ ተግባር መሰረቱ ቢድዐ ነው። በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች ከአንድም አልተላለፈም። ይህም ከመሆኑ ጋር ግን መልካም ነገሮችንም አፍራሾችንም ይዟል። በዚህ ተግባር ላይ አፍራሾቹን ርቆ መልካሞቹ ላይ ያነጣጠረ መልካም ቢድዐ ይሆናል። ካልሆነ ግን አይቻልም።” ” [አልሓዊ፡ 1/228]
አስተውሉ!
* መውሊድ ከኢብኑ ሐጀር ዘንድ ቢድዐ እንጂ ሱና አይደለም።
* “በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች (ሶሐቦች፣ ታቢዒዮችና አትባዑ ታቢዒን) ከአንድም አልተላለፈም” ማለቱ ደግሞ “ነብዩ ﷺ እና ሶሐቦቻቸው አክብረውታል” የሚሉ ቀጣ. ፊዎችን ወሽመጣቸውን የሚቆርጥ ነው።
* መውሊድ ውስጥ ጥፋቶች እንደሚገኙ መግለፁ የዛሬ መውሊድ ጨፋሪዎች ዘንድ የማይገኝ ምስክርነት ነው።
* አፍራሽ ነገሮቹ ካልተራቁ መውሊዱ እንደማይፈቀድ መናገሩ ደግሞ ከዛሬ መውሊድ አክባሪዎች ጋር ፈፅሞ እንደማይገጥም ማሳያ ነው።
እነዚህን ነጥቦች ያስተዋለ ሰው እንጥፍጣፊ ታክል ሚዛናዊነት ካለው ኢብኑ ሐጀርን ዛሬ ለሚፈፀመው መውሊድ ለማጣቀስ አይዳፈርም።

5. ሲዩጢ (911 ሂ.)፡-

“ሰዎች ተሰባስበው ከቁርኣን የተወሰነ ቢቀሩ፣ ስለ ነብዩ ﷺ ሁኔታ አጀማመርና ሲወለዱ የነበሩ ተአምራትን የሚያወሱ ዘገባዎችን ቢያወሱ ከዚያም ማእድ ቀርቦ ተመግበው ቢመለሱና በዚህ ላይ ምንም ካልጨመሩ ይሄ ባለቤቱ የሚመነዳበት ከመልካም ቢድዐ ነው።…” [አልሓዊ፡ 1/220-221]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ዛሬ እንደሚታየው በዚህ ላይ ብዙ ነገር ከተጨመረስ? ሌሎች ብልግናዎች ይቅሩና ጭፈራውን አስመልክቶ እራሱ እንዲህ ብሏል፦ “ከነዚህም (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሆነው በመስጂድ ውስጥ የሚፈፀም ጭፈራ፣ ዘፈን፣ ድቤ መምታት፣ ረባብና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ናቸው። ይህንን ከመስጂድ ውስጥ የፈፀመ ሊባረርና ሊደበደብ የሚገባው ጠማማ ሙብተዲዕ ነው። ምክንያቱም አላህ እንዲላቅ ያዘዘውን ነገር እያቃለለ ነውና። … (ከመስጂድ ውስጥ) የዘፈነ ወይም የጨፈረ ቅጣት የሚገባው የሆነ ጠሞ አጥማሚ ሙብተዲዕ ነው።” [ሐቂቀቱ ሱና ወልቢድዐ፡ 191]

6. አልሀይተሚ (974 ሂ.)፡-

“እኛ ዘንድ የሚተገበሩት ብዙዎቹ መውሊዶች እንደ ሶደቃ፣ ዚክር፣ በነብዩ ሶላትና ሰላም ማድረስና እሳቸውን ማወደስን የመሳሰሉ ብዙ ኸይሮች ያሉት ሲሆን እንዲሁም ሸርም ኧረ እንዲያውም ብዙ ሸሮችም ያሉበት ነው። ሴቶች ባእድ የሆኑ ወንዶችን ከመመልከት ያለፈ ሌላ ጥፋት ባይኖር እንኳን ይሄ እራሱ በቂ ጥፋት ነው። ከፊሎቹ (መውሊዶች) ሸር የለባቸውም። ግን ይሄ አልፎ አልፎ ነው ያለው። የመጀመሪያው አይነት የተከለከለ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም።” [አልፈታወል ሐዲሢያህ፡ 109]
አስተውሉ! የመውሊድ ደጋፊ ከመሆናቸው ጋር አብዛኞቹ መውሊዶች ብዙ ጥፋት ያለባቸው በመሆናቸው የተከለከሉ ለመሆናቸው ጥርጥር የለም እያሉ ነው።

7. ሙሐመድ ዒሊሽ (1217 ሂ.)፡-

“ለነብዩ ﷺ መውሊድ ማዘጋጀት የተወደደ አይደለም፣ በተለይ ደግሞ የድምፅ ቅላፄን ከፍ ዝቅ እያደረጉ እንደመቅራትና እንደ ዘፈን ያለ የተጠላ ነገር ካካተተ። በዚህ ዘመን ደግሞ ከዚህ ይቅርና ከዚህ የከፋ ከሆነም ነገር አይተርፍም።” [ፈትሑል ዐልዪል ማሊክ፡ 1/171]

ስናጠቃልል ለመውሊድ ማጣቀሻ ተደርገው የሚነሱት ዓሊሞች ይህንን በብዙ ጥፋቶች የተሞላውን መውሊድ እንደማይደግፉ እናረጋግጣለን። በዚህ ላይ ፈቃጅ የሚባሉት ዓሊሞች ከተቃዋሚዎች የተለዩ አይደሉም። ስለዚህ ይሄ በብዙ ፀያፍ ነገሮች የታጀበው መውሊድ በኢጅማዕ የተወገዘ ነው ማለት ነው። ሸውካኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “ዛሬ የሚከሰተው የዚህ አይነቱ (ጥፋቱ የበዛበት) መውሊድ ግን በአንድ ድምፅ (ኢጅማዕ) የተከለከለ ነው።” [አልፈትሑ ረባኒ፡ 2/1087-1099]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 3/2014)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
በቢድዐ አንጃዎች ላይ ምላሽ መስጠት፣ የተሸወደባቸው አካላት እውነቱን እንዲለይ መጣር ትልቅ ጂሃድ ነው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦

" الراد على أهل البدع مجاهد حتى كان يحيى بن يحيى يقول : الذب عن السنة أفضل من الجهاد "

"የቢድዐ ባለቤቶች ላይ ምላሽ የሚሰጥ ሰው እንደ ሙጃሂድ (በአላህ መንገድ ላይ እንደሚታገል) ይቆጠራል። እንዲያውም የሕያ ኢብን የሕያ
'ሱናን (የነቢዩን መንገድ) መከላከል ከጂሃድ የበለጠ ነው' ይሉ ነበር።" [አልፈታዋ ፡ 4/13]

አጥፊዎቹን ዝም ብለው የእርምት ትምህርት ሲሰጥ ጊዜ በውስጥ ክፍፍል አትጠመዱ የሚሉ አካላትን ቦታ መስጠት አይገባም። አንድነት በዚህ መልኩ አይረጋገጥም። እነዚህ አካላት የተውሒድ ጉዳይ የሚያሳስባቸው አይደሉም። ተከታትላችሁ አረጋግጡ። የሙታን አምልኮውን፣ ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለም የሚለውን፣ የአላህን ሲፋት የሚያራቁተውን ሁሉ ዝም በሉ ይላሉ። እዚህ ላይ ዝም ካልን ከዚህ በኋላ ምን የቀረ ዲን አለ?!

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
4_5861896121495854515.pdf
357.9 KB
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ       ቀን 18/12/2017 E.C     
በ2018 የትምህርት ዘመን ዐረብኛ ቋንቋን በኤክስቴንሽን መርሃ ግብር በዲግሪ ደረጃ ለመማር ማመልከት (መመዝገብ)  ለሚፈልጉ ወንድሞችና እህቶች የማመልከቻው ጊዜው  ከነሐሴ 20/12/2017 -15/01/ 2018 ዓ.ል መኾኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
                                                                  
ስለዚህ መማር ለሚፈልጉ ወንድሞች እህቶች ይህ መረጃው ይደርሳቸው ዘንድ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ በተለያዩ ግሩፖች ሸር እናድርገው የኸይር በር እንሁን።

ስለዚህ ይኽን መረጃ:~

🌹ለደሴ፣
🌹ለኮምቦልቻ፣
🌹 ለሐይቅ
🌹 ለሐርቡ፣
🌹 ለደጋን፣
🌹 ለገርባ፣
🌹 ለባቲና፣
🌹 ለኸሚሴ ጀመዓዎች አሰራጩት !!!

የመመዝገቢያ መስፈርቶቹን ከዚህ ፒ ዲ ኤፍ(PDF) ውስጥ ማግኘት የምትችሉ መኾኑን እንገልጻለን፡፡


💐💐 ዐረብኛ ቋንቋ ለመማር ማመልከት ለሚፈልጉ ተማሪዎች ሲመጡ ሊይዟቸው የሚገቡ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው 💐💐

1/ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
2/ የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
3/ የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ካርድ፣
4/ የ11ኛና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
5/ የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ካርድ 2ቅጅና
6/ 2 ጉርድ ፎቶ ያስፈልጋችኋል።
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
أَوَ هكذا حُبُّ النبيِّ الهادي
طَبْلٌ و رقصٌ في ربوع بلادي؟

أبِِمثْلِ هذا يُحْتَفَى بـ(محمدٍ)
عِطْرِ الزمانِ وقِبلةِ القُصَّادِ؟

بِدَعٌ ودَرْوَشةٌ وجهلٌ مُطبقٌ
و خرائفٌ وُرِثَتْ من الأجدادِ

هل جاء (أحمدُ) كي يُربىَ أمةً
لتَهُدَّ عرشَ الهَزْلِ والإلحادِ؟

وتُحاصرَ الطاغوتَ في أوكارهِ
وتَدقَّ رأسَ الشركِ والأوغادِ؟

وتُقَدِّمُ الإسلامَ حلوا ناصعا
دينا جميلا كاملَ الأَبعادِ؟

أَمْ جاءَ يدعو الناس كى يتراقصوا
في يوم مولدهِ مع الإنشادِ؟؟

أَيُفَاخِرُ الهادي ملائكةَ السما
بمديح جُهَّالٍ وهَذْيِ الشادي؟

أيُسَرُّ (أحمدُ) بامتداحٍ كاذبٍ
والناس غَرقَى في لَظى الإفسادِ؟

أيسرُ بالحَلْوى نَلُوكُ صنوفَها
والقتلُ في كشميرَ في بغدادِ؟

أتطيبُ نفسُ المصطفى وبقدسِنا
جُرحٌ عميقٌ راسخٌ الأوتاد؟

لو أنَّ حُبَّ(محمدٍ) هو ما نَرَى
طَرَبٌ وحَلوَي رَنَّةُ الأعوادِ

وَوُرُودُ أضرحةٍ ونصبُ موالدٍ
وتمايلٌ بالرأسِ والأجسادِ

وتَنَكُرٌ لجراحِ إخوةِ دينِنا
مادام جُرحا لم يصل لبلادي

وتَنَصلٌ من جوعِ (صوماليةٍ)
مادام عندي مُؤنةٌ من زادِ

فلبئس هذا الحبُّ .حبٌّ كاذبٌ
نَصَّابُ يبغي مَسْحَة الزُّهَّادِ

كَرِهَ الرسولُ خروجكَم فلتخسأوا
في دُوركِم يا زُيَّفَ العُبَّادِ

حــُـبُّ النـبيِّ تَمَسُّكٌ بحــديثه
وكذا اتباعُ النصحِ والإرشاد ِ

حبُّ النبىِّ تَعَقـُّلٌ وتدبــرٌ
وشريعة بُنيت علي الإسنادِ

حبُّ النبىِّ تَحررٌ لعقولنا
من فاسدِ الموروثِ والأصفاد ِ

حبُّ النبيِّ تماسك وترابط
في وجه كل محارب ومعادي

حبُّ النبيِّ ريادةٌ وتقدمٌ
نحو العلا وصناعة الأمجادِ

حبُّ النبيِّ بِسيْرِنا في دَربِه
قدمٌ على قدمٍ بكل حيادِ

حبُّ النبيِّ سعادةٌ بقدومه
مَنْ غير (أحمدَ) مصدرُ الإسعادِ؟؟

لولاه كان الكون منزوعَ السَّنا
لولاه عِشنا في دُجَىً وفسادِ

فلتفرحوا ولتنشدوا لعيالكم
قُصوا حديثَ الغارِ للأحفادِ

إن السعادة بالحبيب عبادةُ
تُؤْتَى بكلِّ تأدبٍ ورشادِ

لا بابتداعٍ كــــاذبٍ ومُلَفـَّـقٍ
أسموه زورًا (حفلةَ الميلادِ)

…………………………………………
@ لا صوفية في الإسلام
በአንዳንድ አካባቢዎች መቃብር ውስጥ ጀናዛ ከተቀበረ በኋላ ዘወትር ደዕዋ ማድረግ የተለመደ ነው። ይህንን ልማድ በተመለከተ ዓሊሞች ምን ይላሉ?

ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ቀብሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ነቢያችን ﷺ ምክር የሰጡበትን ሁኔታ ሐዲሦችን ከጠቀሱ በኋላ ነገር ግን፣ ይህ ምክር ሰዎች ዘወትር የሚቀጥሉበት ቋሚ ልማድ መሆን የለበትም። ምክንያቱም በዚህ መልኩ አይደለምና የተገኘው። ቋሚ አድርጎ መያዝ ከሱና ጋር የሚገጥም አይደለም ይላሉ።

ምንጭ፦ https://www.tgoop.com/ibnhezam/19005
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦

"ማናችሁም አዋቂ ሆኖ አልተወለደም። እውቀት የሚገኘው በመማር ነው።" [አልኣዳቡ ሸርዒየህ፣ ኢብኑ ሙፍሊሕ፡ 1/35]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ግእዝን ለህፃናት ማስተማር አስገድዶ ማጥመቅ ነው!
~
ትናንት ጀምሮ የአማራ ክልል መስተዳድር ግዕዝን በክልሉ ባሉ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓመተ ልደት እንዲሰጥ ሊያስገድድ እንደሆነ የሚገልፅ ደብዳቤ ሲዘዋወር እያየን ነው። ይሄ ሲበዛ ነውረኛ አካሄድ ነው። ይሄ የራስን ማንነት በሌሎች ህዝቦች ላይ የመጫን አጉል ትምክህት ነው። ይሄ አሁንም ክልሉ ዘመናቸውን ባልዋጁ ጠባብ ጠርዘኞች እየተዘወረ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሁነኛ ማሳያ ነው።

በቅድሚያ ለማንም እንደማይሰወረው ግእዝ ጣእረ ሞት ላይ ያለ ቋንቋ ነው። የመጨረሻ እስትንፋሱ ላይ ስለሆነ እንደ ህዝብ ለማንም አይጠቅምም። ወንዝ አያሻግርም አልልም፣ እሱ ሩቅ ነገር ነው። ከጎረቤት ሃገር ቀርቶ ከጎረቤት ህዝብ ጋር አያገበያይም። ኧረ ከቤትህ ቀጥሎ ካሉት ከጎረቤትህ ሰዎች ጋር፣ ኧረ ከቤተሰብህ ጋር ለሰላምታ አይሆንም። እና በምን እዳቸው ነው ልጆቻችን ላይ የማይጠቅም ሸክም የሚጫንባቸው?

እንዲያውም ግእዝን ለህፃናት ማስተማር አይጠቅምም ብቻ ሳይሆን ጎጂ ነው። አዎ እንደ ሙስሊም ይጎዳናል። አስገድዶ ማጥመቅ ነው። ግእዝ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በማይነጠል መልኩ ተጣብቆ የተሰፋ ነው። የማስተማሪያ መሳሪያው እንዳለ "መፅሀፍ ቅዱስ" ነው። ይሄ ማለት የኦርቶዶክስ እምነትን በጨቅላ ሙስሊም ህፃናት ላይ መጫን ነው። ይሄ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የማይጠበቅ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ ነው። ትናንት በአፄው ዘመን አስኮላውን በግብረ ገብ ስም ክርስትና ማስተማሪያ፣ በጫና ማጥመቂያ ቦታ ስላደረጉት በርካታ ሙስሊም አልተማረም። ዛሬም ሙስሊሙን ከትምህርት ገበታ ለማራቅ የተጠነሰሰ ሴራ ነው።

ግእዝን በመደበኛ ትምህርት ውስጥ ለህፃናት ማስተማር ከሴኩላሪዝም ጋር አይሄድም። አዎ! ግእዝን ማስተማር ቀጥታ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ለመጨፍለቅ ማመሀኛ የሚደረገውን ሴኩላሪዝም መጣስ ነው። ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ስንት አይነት በደል እንደሚፈፀም አስቡ። አንዴ በሴኩላሪዝም ስም እምነታቸውን በግል እንዳያንፀባርቁ ይከለክላሉ። አሁን ደግሞ በቋንቋ በማስታከክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የግድ እንዲማሩ ሊደረጉ ነው። ይሄ እብሪተኝነት ነው። ይሄ የክልሉ ስልጣን በእጃችን ስለሆነ ያሻችንን ልናደርግባችሁ እንችላለን ምን ታመጣላችሁ ማለት ነው። ከፈለጋችሁ ለራሳችሁ ልጆች አስተምሩ። ያ ሲሆን ራሱ ለሙስሊሙም ህዝብ ልጆቹን በዐረብኛ የማስተማር አማራጭ ሊመቻችለት ይገባል።

ይልቅ ለልጆች ለምን የሚጠቅማቸውን አታስተምሩም? ልጆች አስራ ምናምን አመት ተምረው መቼ እንግሊዝኛ ይናገራሉ? እሱን አታስተካክሉም? መማር ካለባቸው ለምን ባቅራቢያቸው ያሉ ህዝቦችን ቋንቋ አይማሩም? ገዳም ውስጥ የአልጋ ቁራኛ የሆነ ቋንቋ ከሚማሩ ትግርኛ፣ አፋርኛ፣ ኦሮምኛ ቢማሩ የተሻለ ይጠቀማሉ። ከግእዝ ይልቅ ልጆች ዐረብኛ ቢማሩ የተሻለ ሃገራዊ ፋይዳ አለው። ዐረብኛ አለማቀፍ ቋንቋ ነው። ከ 20 ያላነሱ ዐረብ ሃገራት አሉ። በሌሎች ሙስሊም ሃገራት ውስጥ በሰፊው አለ። ዋና መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረትም አንዱ ኦፊሻል ቋንቋው ዐረብኛ ነው። ከዚህም ባሻገር እጅግ ሰፊ ወገናችን ዐረብ አገር ነው ያለው። ዐረብኛ ለኢትዮጵያ የውጭ ቋንቋ አይደለም። በሃገራችን ቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ የበርታ ህዝብ ዐረብኛ በሰፊው ይናገራሉ። በሃገር ውስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ለ0ረብኛ የቀረበ ሰፊ ህዝብ አለ። ስለዚህ ልጆች ዐረብኛ ቢማሩ ትርፉ ብዙ ነው። ዐረብኛ ቋንቋን ከኢስላም ጋር አያይዞ የሚፀየፍ አካል፣ ኢትዮጵያ የዐረብ ሊግ አባል ብትሆን የተሻለ ትጠቀማለች ብለው አንዳንዶች ሲፅፉ ከኢስላም ጋር አያይዞ የሚበረግግ አካል ግእዝን ካልተማራችሁ ብሎ ሙስሊሙ ላይ ሊጭን አይገባም።

ሳጠቃልል ግእዝ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በታች ባለ ደረጃ ፈጽሞ በአስገዳጅ መልኩ ልጆች ላይ ሊጫን የማያገባው ቋንቋ ነው። በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ተማሪዎች በምርጫቸው ሊማሩት ይችላሉ። አሁን የቀረበው ህፃናት ላይ የመጫን ውሳኔ ግን የክልሉን ህዝብ ብዝሀነት ከግንዛቤ ያላስገባ ጨፍላቂ አሰራር ስለሆነ ሊቆም ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
"ቋንቋ መማር ምን ችግር አለው?" ይላሉ። ከመፅሀፍ ቅዱስ ገልብጠህ እያመጣህ፣ በቄስ እያስተማርክ ነው ችግር የሌለው? ከቁርኣን እየቀዱ የሚያስተምሩ ሸይኾች ቢመደቡባችሁ ዝም ልትሉ ነው? የክልሉ መንግስት ዐረብኛን በሁሉም ዞኖቹ ግዴታ ቢያደርግ ልትቀበሉ ነው? እየተዋወቅን! ያውም ዐረብኛ እና ግእዝ የሚወዳደሩ ካለመሆናቸው ጋር።

1. ዐረብኛ - በሁለት አህጉር ውስጥ በሚገኙ 22 ሀገራት፣ ከ332 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ይነገራል። በዓለም ላይ በተናጋሪ ብዛት 5ኛ ቋንቋ ነው።

* ግእዝስ? በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅፅር ግቢ ውስጥ ተጠልሎ ነው ያለው።

2. ዐረብኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የብዙ ዓለማቀፍና አህጉራቀፍ ተቋማት ኦፊሻል ቋንቋ ነው።
* ግእዝስ? ከሃይማኖታዊ ግልጋሎት ውጭ የየትኛውም ተቋማት ቋንቋ አይደለም።

3. ዐረብኛ የብዙ ሃይማኖት ቋንቋ ነው። ከሙስሊሞች ባሻገር ከ15 ሚሊዮን በላይ ዐረብ ክርስቲያኖች አሉ። አይሁድም ይገኛል።

* ግእዝስ? የኦርቶዶክ ተዋህዶ ክርስትና ብቻ!

እውነታው ይህ ቢሆንም በክልሉ 0ረብኛ ማስተማር በመንግስት ደረጃ እንደ ግእዙ ትእዛዝ ሊወጣበት ቀርቶ በፈቃድ ደረጃ እንኳ አልተፈቀደም። ለግል ትምህርት ቤቶች እንኳን አልተፈቀደም። ለህዝብም ለሀገርም የተሻለ ፋይዳ ያለውን ዐረብኛን ጥለው እንደ ህዝብ አንድ ቀበሌ ውስጥ እንኳ የማይነገርን ቋንቋ መማርን ግዴታ ማድረጋቸው ምክንያቱ ከቋንቋ ያለፈ እንደሆነ ግልፅ ነው። በዚያ ላይ ትምህርቱ በመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታጨቀ ሲሆንስ? በዚያ ላይ ትምህርቱን የሚሰጡት ቄሶች ናቸው። ለማን? እምነታቸውን በቅጡ ላልለዩ ጨቅላ ህፃናት! እንዴት ነው ታዲያ ችግር የሌለው?
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
የጥቅምት 7ቱ ጥቃት ከመፈጽጸሙ በፊት ኔታንያሁ ሁሉም ነገር ደርሶት እንደነበር የሚያጋልጡ የድምጽ ቅጂዎች ወጡ ይላል አልጀዚራ። ይሄ ነገር ከዚህ በፊትም ሌሎች ሚዲያዎች ብዙ የተነተኑት ነው። ብቻ የሚገርም ነው።

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
የሶሪያው መሪ አሕመድ አሽሸርዕ :-

"እኔ የጂሃ ^ዳዊ ድርጅቶችም ይሁን፣ የሙስሊም ወንድማማችነት (ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን) ንቅናቄም ይሁን የኢስላማዊ ቡድኖች ቅጥያ አይደለሁም። እንዲሁም 'የዐረብ ጸደይ' ቅጥያም አይደለሁም" ብሏል።

በዚህ ንግግሩ የተነሳ ብዙዎች በተለይም ኢኽዋኒዮች በሃይለኛ እያብጠለጠሉት ነው።

ሸይኽ አሕመድ አንነጃር ከዚህ የሸርዕ ንግግር ጋር አያይዘው እንዲህ አሉ፦

لا يمكن أن تقام دولة بفكر دواعش التكفير
فها هي حكومة سوريا تعلنها صراحة اليوم بأنها ليست على تنظيم جهادي ...ولا فكر قطبي...

"በዳዒሾች የ'ተ -ክ ^ ፊ -ር' አስተሳሰብ መሰረት መንግሥት ሊመሠረት አይችልም። ይሄው የሶሪያ መንግሥት ዛሬ በግልጽ እንደገለጸው፣ እሱ የጂሃ ^ዳዊ ድርጅት ወይም የ'ቁጥ ^ ቢ' አስተሳሰብ አካል እንዳልሆነ ግልፅ አድርጓል።"


=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሱፊያ እንደ ቡድን ቪዲዮው ላይ በተያያዘው አይነት የኹራፋት ቂሷ የተሞላ ነው። እከሌ ወልይ ጁሙዐ መካ - ሐረም ነበር የሚሰግዱት፣ ዐርሽ ላይ ነበር የሚሰግዱት፣ ቀብራቸውን ዘንዶና ነብር ነው የሚጠብቀው፣ የሆኑ ሰዎችን ረግመው ድንጋይ አደረጓቸው፣ እህል ያዘንቡ ነበር፣ መለይካ ነበሩ፣ ሲሞቱ ሌላ አገር ይወጣሉ፣ በፈቃዳቸው ነው የሚሞቱት፣ ... ማለቂያ የሌለው የውሸት ግሳንግስ!! አሁን ዐቅል ያለው ሰው በነዚህ ይሸወዳል? በተለይ ወጣት በነዚህ ሲሸወድ ያሳዝናል። በተለይ የተማረ ሰው!! መማር ለሂዳያ ዋስትና ይሆናል ማለቴ አይደለም። ግን ለማስተዋል በር ይከፍት ነበር ፣ ላደለው ሰው። ግን ምን ዋጋ አለው?

"ዐርሽ አደባባይ ያለው ህም ህም
የዘቡራ ልጅ ሰይድ ኢብራሂም!"

እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ቅጥ ^ፈት የሚናገሩ ሰዎች ወሊይ ተደርገው ሲያዙ አስቡት። አሳፋሪ!

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ከ“ወሃ * ብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
~
አንዳንዶች የመውሊድ ቢድዐን ማውገዝ የተጀመረው በቅርብ ጊዜ ይመስላቸዋል። ለዚያም ነው የተቃወማቸውን ሁሉ "ወሃ ^ ቢ" የሚሉት። ይሄ ሙግት ባዶ እንደሆነ ለማሳየት ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ መምጣት በፊት የነበሩ ይህንን የመውሊድ ቢድዐ የኮነኑ ዑለማዎችን እጠቅሳለሁ።

1. ኢብኑ ተይሚያህ (728 ሂ.)፡- የሳቸውን አቋም ራሱን ችሎ ስለዳሰስኩት በዚህ ሊንክ ከፍተው ማየት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/GnB9vMNEKaWpx9h9/?mibextid=oFDknk

2. ታጁዱን ዑመር ብኑ ዐሊይ አልፋኪሃኒይ (734 ሂ.)፡-

መውሊድን አጥብቀው የኮነኑ ሲሆን በዚህ ላይ አንድ ኪታብ ፅፈዋል። እንዲህ ይላሉ፡- “ለዚህ መውሊድ በቁርኣንም በሱናም መነሻ አላውቅለትም። በኢሰላም ላይ ተምሳሌት የሆኑትና የቀደምቶችን ትውፊቶች አጥብቀው የያዙ ከሆኑት የሙስሊሙ ህዝብ ምሁራኖች ከአንዳቸውም ተግባሩ አልተወሰደም። ይልቁንም ቦዘኔዎች የፈጠሩት ቢድዐ ነው! ሆዳ ^ሞች ያተረፉበት የሆነ የነፍስ ዝንባሌ ነው። … ይሄ (መውሊድ) ግን ሸሪዐው አልፈቀደውም። ሶሐቦችም ታቢዒዮችም አልሰሩትም። እስካወቅኩት ድረስ ዲን የተላበሱ ዑለማዎችም አልሰሩትም። ይህ ነው ከሱ ከተጠየቅኩ ከአላህ ፊት የምመልሰው። የተፈቀደ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም በዲን ውስጥ ፈጠራ መፍጠር በሙስሊሞች ኢጅማዕ የተፈቀደ አይደለምና። ስለዚህ የተጠላ ወይም የተከለከለ ከመሆን ውጭ የቀረ የለም። የዚህን ጊዜ ወሬያችን ሁለት ክፍሎች ይኖሩታል ማለት ነው፣ ሁለት የተለያዩ ሁኔታዎች ጋር:-

አንዱ፡- አንድ ሰው ከራሱ ገንዘብ ለባለቤቱ፣ ለጓደኞቹና ለቤተሰቡ የሚያዘጋጀው ነው። በዚህም ጉባዔ ላይ ምግብን ከመብላት ላያልፍና ወንጀሎችን የማይፈፅሙ ከሆነ ነው። ይህንን ነው የተጠላ ቢድዐና አስቀያሚ ነገር እንደሆነ የገለፅነው። ምክንያቱም የዘመናት መብራት፣ የሃገራት ውበት የሆኑት ምሁራኖችና የኢስላም ሊቃውንት የሆኑት ቀደምት የአላህ ታዛዦች አልሰሩትምና።

ሁለተኛ፡- ወንጀል የሚቀላቀለውና (ይህን ቢድዐ ለማክበር ገንዘብ ለመሰብሰብ) ትኩረት የሚበረታበት ነው። አንዳንዱ ነፍሱ የተንጠለጠለ ሆኖ፣ ከግፉ ህመም የተነሳ ልቡን እያሳመመው የሆነ ስጦታን ነገር እስከሚሰጥ የሚደርስበት ነው። ዑለማዎችን አላህ ይማራቸውና ‘እፍረት አስይዞ ገንዘብን መውሰድ በሰይፍ እንደመውሰድ ነው’ ይላሉ።

በተለይ ደግሞ በዚህ ላይ ከጠገቡ ሆዶች ጋር እንደ ድቤና ዋሽንት ያሉ በከንቱ መሳሪያዎች የታጀበ ዘፈን ካለ፣ እንዲሁም ወንዶች ከወጣቶችና ከዘፋኝ ሴቶች ጋር መቀላቀል ከኖረ ወይ ከወንዶቹ ጋር ተቀላቅለው ወይ ደግሞ ከከፍታ ላይ ዘልቀው፣ እየተጣጠፉ በመጨፈር፣ ከዛዛታ ውስጥ መስመጥና አስፈሪውን (የቂያማ) ቀን መዘንጋት የሚደረስበት ነው።

ልክ እንዲሁ ሴቶች ብቻቸውን ሲሰባሰቡ ያለምንም ሀፍረት ድምፃቸውን በዘፈንና በዜማ ከፍ ያደርጋሉ። ከተለመደው የቁርኣን አቀራርና ዚክር አልፈው ከሸሪዐው ይወጣሉ። የላቀው ጌታ {ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና} ማለቱን ይዘነጋሉ። ይሄ ክልክል በመሆኑ ላይ ሁለት ሰዎች አይወዛገቡበትም። ስርኣት ያላቸው አስተዋዮች በጥሩ አያዩትም። ይሄ የሚፈቀደው የሞቱ ቀልቦችን ከያዘና ወንጀልንና ሃጢኣትን ከሚያበዙ ሰዎች ዘንድ ነው። እንዲያውም ልጨምርህና እነሱ እንደ ዒባዳዎች እንጂ እንደ መጥፎና ክልክል ነገሮች አይደለም የሚቆጥሩት። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ‘ኢስላም እንግዳ ሆኖ ነው የጀመረው። እንግዳ ሆኖም ይመለሳል።’ ... ይህ እንግዲህ ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ረቢዐል አወል ወር የሞቱበትም ከመሆኑ ጋር ነው። መደሰቱ በሱ ውስጥ ከማዘን ቅድሚያ የሚሰጠው አልነበረም።” [አልመውሪድ ፊ ዐመሊል መውሊድ፡ 2-8]

3. ኢብኑል ቀዪም (751 ሂ.)፡-

“ኢስራእ ነብዩ ﷺ ከታደሏቸው ታላላቅ ትሩፋቶች ከመሆኑም ጋር ያንን ጊዜ ወይም ያንን ቦታ በሸሪዐዊ ዒባዳ መለየት አልተደነገገም። እንዲያውም ወሕይ መውረድ የጀመረበት የሒራእ ዋሻ ከነብይነታቸው በፊት ያተኩሩበት የነበረ ከመሆኑ ጋር ከነብይነት በኋላ ራሳቸውም መካ ላይ በቆዩ ጊዜ፣ እንዲሁም ከሶሐቦች አንድም ያሰበው የለም። ወሕይ የወረደበት ቀንም እንዲሁ በዒባዳም ይሁን በሌላ ተለይቶ አልተያዘም። ወሕዩ የተጀመረበት ቦታም ይሁን ዘመኑ እንዲሁ በምንም ነገር ተለይቶ አልተያዘም። የሆኑ ቦታዎችን ወይም ጊዜዎችን ከራሱ በዒባዳዎች ለዚህና መሰል አላማ የለየ ሰው የመፅሐፉ ሰዎች አምሳያ ሆኗል። እነዚያ የመሲሕን (የዒሳን) ሁኔታዎች፣ ጊዜዎችና መሰባሰቢያዎች በዓላት አድርገው እንደያዙት። ለምሳሌ የልደት ቀኑን፣ የጥምቀት ቀኑንና መሰል ሁኔታዎቹን ለይተው እንደያዙት። ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዱየላሁ ዐንሁ የሆኑ ሰዎችን ወደ አንድ ቦታ ለሶላት ሲቻኮሉ ያዩዋቸዋል። ‘ምንድነው ይሄ?’ ሲሉ ጊዜ ‘የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሰገዱበት ቦታ ነው’ አሉ። ‘የነብዮቻችሁን ፋናዎች መስገጃዎች አድርጋችሁ ልትይዟቸው ትፈልጋላችሁን? ከናንተ በፊት የነበሩት ሰዎች የጠፉት በዚህ ነው። እዚያ እያልለ ሶላት የደረሰበት እዚያው ይስገድ። ያለበለዚያ ግን ጉዞውን ይቀጥል’ አሉ።” [ዛዱል መዓድ፡ 1/59]

4. አቡል ዐባስ አሕመድ ብኑል ቃሲም አልቁባብ (778 ሂ.)፡-

በመውሊድ ቀን ልጆችን ሰብስቦ ሻማ ስለመለኮስ፣ በነብዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ስለማለት፣ ድምፁ ያማረውን ከውስጣቸው በመምረጥ አስር የቁርኣን ሱራዎችን እንዲያነብ ስለማድረግና ነብዩን ﷺ የሚያወድሱ ግጥሞችን ስለመነሸድ፣ በዚህ ሰበብም ወንዶችና ሴቶች መሰባሰባቸውን እንዲሁም አስተማሪው ሻማዎችን መቀበል የሚፈቀድለት ስለመሆኑ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ ነበር የመለሱት፡-

“የገለፅካቸው በሙሉ ቢድዐ የሆኑ መጤ ፈሊጦች ናቸው። ስለሆነም የግድ ሊቋረጡ ይገባል። እነዚህን ነገሮች የሚፈፅም ወይም በነዚህ ላይ የሚያግዝ ወይም እንዲቀጥሉ የሚተጋ ሰው በቢድዐና በጥመት ላይ ነው እየተጋ ያለው። እሱ ግን በድንቁርናው ሳቢያ በዚህ ተግባሩ የአላህ መልእክተኛን - ﷺ - የሚያከብርና መውሊዳቸውን የሚያከብር እንደሆነ ያስባል። እሱ ግን ሱናቸውን እየጣሰና ክልከላቸውን እየፈፀመ ነው። ይህንን በይፋ እየፈፀመ ዲን ያልሆነን እንግዳ ነገር እየፈጠረ ነው። እውነተኛ የሆነን ማክበር ቢያከብራቸው ኖሮ ትእዛዛቸውን ባከበረና በዲናቸው ውስጥ እንግዳ ነገር ባልፈጠረ ነበር። እንዲሁም አላህ {እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳይደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ} ሲል ካስጠነቀቀው ጋር ባልተላተመ ነበር።

አስተማሪው የሚቀበለውን (ስጦታ) በተመለከተ እነዚህን ቢድዐዎች፣ እነዚህን ነገሮች ስለሚያስፈፅም ከሆነ የሚሰጠው የሚቀበለው ነገር አስቀያሚ መሆኑ አይሰወርም። እነዚህን ነገሮች ምንም ሳይፈፅም እንዲሁ በዚህ ጊዜ የሚሰጠው ከሆነ ኢብኑ ሐቢብ ‘ለአስተማሪ በሙስሊሞች ዒድ ምንም አይወሰንለትም - ይህን መስራቱ የሚወደድ ቢሆን እንኳን’ ብለዋል። … ኢብኑ ሐቢብ ሸሪዐዊ በሆኑ በዓላት ላይ እንዲህ ካሉ ሸሪዐዊ ባልሆኑት ላይ እንዴት ሊሆን ነው?!” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዒ ወተሶውፍ፡ 128-129]

5. አቡ ኢስሓቅ አሻጢቢይ (790 ሂ.)፡-
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
“ሰዎች ዘንድ በተለመደው መልኩ የሚከበረው መውሊድ መጤ የሆነ ቢድዐ መሆኑ የታወቀ ነው። ቢድዐ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። ስለሆነም ቢድዐን ለመፈፀም ገንዘብን መለገስ አይፈቀድም። በዚህ ላይ ኑዛዜ ከተላለፈም ተፈፃሚ አይደለም። እንዲያውም ቃዲው ሊያፈርሰው ይገባል።…” [ፈታዋ ሻጢቢይ፡ 203-204]

በተጨማሪም ስለቢድዐ ምንነት ካብራሩ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አሁንም ከነሱ (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሚካተተው (በዒባዳ ውስጥ) ተለይተው የተወሰኑ አፈፃፀሞችንና ሁኔታዎችን በቋሚነት መያዝ ነው። ለምሳሌ በአንድ ድምፅ በመሰባሰብ የሚደረግ ዚክር፣ የነብዩን ﷺ ልደት ቀን በዓል አድርጎ መያዝና እነዚህን የመሳሰሉትን ያካትታል።” [አልኢዕቲሷም፡ 1/53]

6. ኢብኑ ረጀብ (795 ሂ.)፡-

ሸሪዐው ዒድ ተደርጎ እንዲያዝ ያዘዘበትን ካልሆነ በስተቀር ሙስሊሞች ዒድ ሊይዙ አይፈቀድላቸውም። እነሱም (የታዘዙትም) ዒደል ፊጥር፣ ዒደል አድሓና የተሽሪቅ (ከዒደል አድሓ ቀጥሎ ያሉት ሶስቱ) ቀናት ናቸው። እነዚህ አመታዊ በዓላት ናቸው። የጁሙዐ ቀን ደግሞ ሳምንታዊ ዒድ ነው። ከዚህ ውጭ ያለን በዓልና ዐውደ- አመት አድርጎ መያዝ በሸሪዐችን መሰረት የሌለው ቢድዐ ነው። [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 118]

7. አቡ ዐብዲላህ አልሐፋር አልገርናጢይ (811 ሂ.)፡-

“የመውሊድ ሌሊት መልካም ቀደምቶች ማለትም የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ለአምልኮት የሚሰባሰቡባት አልነበሩም። ከአመቱ ሌሊቶች ተጨማሪ ስራም አይሰሩባትም ነበር። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዲከበሩ በተደነገገው መልኩ እንጂ አይከበሩምና። እሳቸውን ማላቅ ከትልልቅ ወደ አላህ መቃረቢያዎች ነው። ነገር ግን ልቅናው ከፍ ወዳለው አላህ እሱ በደነገገው መልኩ እንጂ (በሌላ) መቃረብ አይፈቀድም። ሰለፎች ከሌሎች ሌሊቶች በተለየ ምንም የሚጨምሩ እንዳልነበሩ መረጃው በሷ (በተወለዱበት ቀን) ላይ መለያየታቸው ነው። ለምሳሌ እሳቸው ﷺ የተወለዱት በረመዳን ነው ተብሏል፣ በረቢዕ ነውም ተብሏል። በዚህም ላይ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ አራት የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል። ከፍጡራን ሁሉ በላጭ የሆኑት በመወለዳቸው ሳቢያ በማለዳዋ የተወለዱባት ሌሊት ዒባዳ የሚጠነሰስባት ብትሆን ኖሮ ውዝግብ ሳይከሰትባት በሰፊው በታወቀች ነበር። ነገር ግን ጭማሬ የሆነ ማላቅ አልተደነገገባትም።

የጁሙዐ ቀን ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጭ ቀን እንደሆነችና በበላጭ ቀን የሚፈፀመው በላጩ ነገር ፆም እንደሆነ አታውቅምን? ሆኖም ግን ነብዩ ﷺ ከትልቅ ልቅናው ጋር ከጁሙዐ ቀን ፆም ከልክለዋል። ይህም በየትኛውም ጊዜ ይሁን በየትኛውም ቦታ ካልተደነገገ በስተቀር አምልኮት መፍጠር እንደማይቻል ያመለክታል። ካልተደነገገ አይፈፀምም። ምክንያቱም የዚች ህዝብ ኋለኛው ክፍል ከቀዳሚው የተሻለ የተቀና ነገር አያመጣምና። ይሄ በር ቢከፈትማ የሆኑ ሰዎች መጥተው ወደ መዲና የተሰደዱበትም ቀን ‘አላህ በሱ ኢስላምን ያላቀበት ቀን ነው’ በማለት ሊሰባሰቡበትና ሊያመልኩበት ነው። ሌሎች ደግሞ ተነስተው ኢስራእ ያደረጉባት ሌሊት ‘ልኬታው የማይገመት የሆነ ልቅና የተጎናፀፉባት ሌሊት ነች’ በማለት አምልኮት ሊፈጠር ነው። እናም (እንዲህ ከተከፈተ) የሆነ ወሰን ላይ ሊቆም አይቻልም። መልካም ሁሉ ያለው አላህ ለሳቸው የመረጣቸውን መልካም ቀደምቶች በመከተል ነው። የሰሩትን እንሰራለን። የተውትን እንተዋለን። ይሄ ከተረጋገጠ በዚች ሌሊት ላይ መሰባሰቡ በሸሪዐው ተፈላጊ እንዳልሆነ ግልፅ ይሆናል። …

ይህቺ ሌሊት ደግሞ በሱፍዮች መንገድ ነው የምትዘጋጀው። በዚህ ዘመን የሱፍዮች መንገድ በዲን ውስጥ ከተፈጠሩ አስቀያሚ ነገሮች ውስጥ ነው። ምክንያቱም የጉባዔ ስርአታቸው ዘፈንና እንቶ ፈንቶ ነውና። ይሄ ነገር በነዚህ ጊዜያት ከሚፈፀሙ የላቁ መቃረቢያዎች እንደሆነና ይህ የወልዮች መንገድ እንደሆነ ለአላዋቂ ሙስሊሞች ያስተምራሉ። በሌሊትና በቀን ውስጥ ግዴታ የሆኑባቸውን ህግጋት በቅጡ የማያውቁ መሃይማን ሰዎች ናቸው። ይልቁንም አላዋቂ ሙስሊሞችን ለማጥመም ሸይ ^ጧን ምትኮች ካደረጋቸው ውስጥ ናቸው። ለሰዎች ከንቱ ነገሮችን ይሸላልማሉ። ወደ አላህ ዲንም ከሱ ያልሆነን ነገር ያስጠጋሉ። ምክንያቱም ዘፈንና እንቶ ፈንቶዎች ከዛዛታና ከጨዋታ ውስጥ ናቸውና። እነሱ ግን ወደ አላህ ወሊዮች ያስጠጉታል። እነሱም በዚህ ላይ ገንዘብን ያለ አግባብ ለመብላት ይዳረሱ ዘንድ እየዋሹባቸው ነው።…” [ዑለማኡል መግሪብ፡ 128]

8. ኢብኑ ነሐስ (814 ሂ.)፡-

“አውዳመታትና በዓላት ውስጥ ከተፈጠሩት ውስጥ በከፊል ማውሳት” በሚል ንኡስ ርእስ ስር “ከነዚህ ውስጥ በወርሃ ረቢዐል አወል ሰዎች የፈጠሩት የመውሊድ ተግባር ነው” ይላሉ። በውስጡ ካሉ ቢድዐዎችና ጥፋቶች እንኳን ቢፀዳ ከቢድዐነት እንደማያልፍ ካጣቀሱ በኋላ ሰዎች መውሊድን ለማዘጋጀት የሚያነሳሷቸው ምክንያቶች ብለው የተወሰኑ ነጥቦችን አንስተዋል። ከነዚህም ውስጥ፡-

- ከሚጠሯቸው ቃዲዎች፣ መሪዎች፣ መሻይኾችና ከመሳሰሉት ጋር ለመተዋወቅ በማለም የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንድ መሻይኾች ደግሞ ሰዎች በመውሊድ ምክንያት በእርዳታ መልክ ወይም በስጦታ መልክ ወይም ሃፍረት ይዞት ወይም ደግሞ ከእኩዮቹ ጋር ለመፎካከር ሲል ከሚያመጡት ነገር የሚተርፈውን ለራሳቸው ለመጠቀም በማለም መውሊድን የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንዱ ክፉ ምላስ ያለውና ቁጡ ይሆንና ደካሞችን በመጥለፍና ምላሱንና ምግባሩን የሚፈሩ ሰዎችን በማጥመድ አላማውን የሚያሳካ አለ። … [ተንቢሁል ጋፊሊን ዐኒል አዕማሊል ጃሂሊን፡ 499]

9. ቃዱ ሺሃቡዲን ደውለት ኣባዲ አልሐነፊይ (894 ሂ.)፡-

“በያመቱ መጀመሪያና በረቢዐል አወል ወር መሃይማን የሚሰሩት ተግባር ከምንም የሚቆጠር ነገር አይደለም። የሳቸው ﷺ ልደት ሲወሳ ይቆማሉ። ሩሐቸው ትመጣና ትካፈላለች ይላሉ። ይሄ ሙግታቸው ውድቅ ነው። ይሄ እምነት ሺርክ ነው።” [ፈታወ ሸይኽ ሸምሲል ሐቅ አዚምኣባዲ፡ 166]

እንግዲህ ተመልከቱ። እነዚህ በሙሉ በ1206 ሂ. ከሞቱት ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ - ረሒመሁላህ - ዘመን ቀድሞ መውሊድን ያወገዙ ዑለማዎች ናቸው። ከዚህ በኋላ መውሊድን የሚቃወሙት ከ200 አመት ወዲህ የመጡ “ወሃ*ቢዮች” ናቸው ማለት ራስን ማታለል ካልሆነ በስተቀር ምን ትርጉም ይኖረዋል?

(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 17/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
የአደባቸው ቅለት በዚህ ልክ ነው። ያመናቸውን ገደል ይከታሉ። በርግጠኝነት በዚህ ዓይነት መንገድ ጀነት እንደማይገኝ ግልፅ ነው። አላማቸው ዱንያ ነው። አላማቸው አጉል ዝና ፍለጋ፣ ከሌሎች መሰሎቻቸው አንፃር በልጦ፣ ጎልቶ መታየት ነው። አላማቸው ሞኛሞኝ ተከታያቸውን ማለብ ነው። ተውሒድን ያልታጠቀ ሰው ደግሞ አይነቃባቸውም፡፡

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
2025/09/11 21:36:00
Back to Top
HTML Embed Code: