Telegram Web
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የኔ ጀግና!
~
ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ኢስላምን ያጠለሹ፣ ሙስሊሞችን በአጉል ኮተቶች ጠፍረው ያሰሩ የሱፊያ ኮተቶችን የበጣጠሰ አንበሳ ነው። በጀሊሉ፣ በወሃቡ ፈቃድ የተሃድሶ ንቅናቄው የቀብር አምልኮትን ግንድ ከምድረ ሰዑዲያ ገንድሶታል። በመላው የሙስሊሙ አለም ያለውን የበሰበሰ የሱፊያ ሸክም አነቃንቆታል። ኧረ ክፉኛ ወዝውዞታል።

በዚህ የተነሳ ሱፊዮች ዘንድ እንደሱ የተጠላ ፍጡር የለም። የተፃፈ ኹጥባ ለማንበብ ሚንበር ላይ ወጥቶ የሚንገዳገደው ሁላ እየተነሳ "ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ጃሂ ል ነው" ሲል የምንሰማው ያለ ምክንያት አይደለም። ይገባናል፣ የሚያስጮሃችሁ ህመማችሁ ነው። "አሶራኹ ዐላ ቀድሪል አለም" እንዲል ዐረብ። "ጩኸት በህመም ልክ ነው!"

ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ እንዳንተ ሶደቃ ሲያባር እድሜውን አልፈጀም። ጋርዶ ጫት የሚቀረጥፍ ቦዘኔ አልነበረም። ሁሉን እንዳመጣጡ ያስተናገደ፣ ለቆመበት አላማ ቆርጦ የተነሳ፣ ከዚያም እስከ ደም ጠብታ የታገለ ቆራጥ ነበር፣ የጀግና ጀግና! የፅናት፣ የትጋት፣ የብቃት ተምሳሌት!

ዛሬ ግን ይሄ ነው የሚባል የዒልም ቅሪት የሌለው፣ ኢስላምን የግል ጥቅም መሸመቻ ያደረገ፣ ከሆዱ አሻግሮ መመልከት የማይችል ቦዘኔ ሁላ እየተነሳ "እሱ'ኮ ጃ ሂል ነበር" ይላል። እርሱ ጃሂ ል ከነበረ አንተ ጅህልና እራሱ ነህ!

"ወሃብዮች ዑለማእ አያከብሩም" የሚሉ አስ ^መሳዮች ሁላ በሸይኹ ላይ ምላሳቸውን ሲያሾሉ ማየት በስፋት የተለመደ ነው። ግማሹ "ተ 'ክ'^ ፊ'ር ነው" ይላል። ግማሹ "የሁዲ ነው" ይላል። ግማሹ "የእንግሊዝ ቅጥረኛ ነበር" ይላል። ሌላም ሌላም ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ውንጀላዎች አሉ። እናንተ ናችሁ ስለ ዑለማእ ክብር የምታወሩት? በጀግኖቻችን ክብር ላይ እየተረማመዱ ከዚያ የነሱን የጥፋት ሰባኪዎች እንድናከብርላቸው ይፈልጋሉ።
በሃገራችን በመውሊድ ሰበብ ስማቸው ገኖ ከሚታወቁ ቦታዎች ጋር ተቆራኝቶ ዝናቸው ከናኘ መሻይኾች ውስጥ #ብዙዎቹ የእውነት እንደሚባለው በዒልም የላቁ እንደነበሩ የሚያሳይ ማስረጃ ብትጠይቁ አስቂኝ ነገር ነው የምትሰሙት። "እስኪ ኪታባቸውን አሳዩን?" ብትሉ "የመውሊድ መንዙማ ፅፈዋል" ፣ "ማዲሕ ነበሩ። መድሕ አዘጋጅተዋል" ብለው የግጥም መድብል ይነግሯችኋል። ዒልም ማለት ግጥም መፃፍ ነው እነዚህ የዞረባቸው ዘንድ! በዚህ የግንዛቤ አቅምህ ነው ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብን በጅህልና የምትወርፈው?! አዎ መውሊድ ያገነናቸው ብዙ ስመ ገናናዎች አሉ። ከመውሊድ ጭፈራ ባለፈ ከነ ጭራሹ በቦታው ምንም አይነት የዒልም እንቅስቃሴ የሌለባቸው ብዙ ናቸው።
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
በአንድ የክፍለ ሀገር ከተማ ውስጥ በበዓል ጊዜ ታቦት የሚሸኘው ህዝብ ብዙ ሆኖ ነበር የሚታየው። ሙስሊም የሆነ ሰው እንዲህ አይነት በዓል ላይ መሳተፍ እንደማይቻል ሰፋ ያለ የማንቃት ስራ ከተሰራ በኋላ ታቦት የሚሸኘው በጣም ጥቂት ብቻ ቀረ። ያ ክስተት ሰው ላይ ግርምት ነበር የፈጠረው። ለካስ የሚያደምቃቸው ሌላው ነበር።

የሙና ሁኔታ እንደዚሁ ነው የሚሆነው። ብዙ ሰዎች ግን ይህንን የማንነት መተራመስ እንክብካቤ የሚሻ ትልቅ እሴት አድርገው ነው የሚገልፁት። ሱራፌልም የሚያስቀና ፍቅር እንደሆነ እየነገረን ነው። ችግሩ የሱራፌል አይደለም። በዚህ መልኩ የሚያስቡ ብዙ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች አሉ። ከዚያ ሙስሊም አስተማሪዎች እንዲህ አይነት ነገሮች መቀጠል ያለባቸው መልካም እሴቶች ሳይሆኑ ባስቸኳይ መቆም ያለባቸው የማንነት ቀውሶች እንደሆኑ ሲናገሩ እንደ አክራሪ ይታያሉ። ይሄ ወይ ሆነ ተብሎ የሚፈፀም መድፈቅና የራስን እምነት ሌሎች ላይ መጫን ነው። አለያ ደግሞ ለኃላፊነታቸው የሚመጥን ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎች የሚናገሩት ግልብ ንግግር ነው። እነዚህ አካላት መቻቻል እና የማንነት መደበላለቅ የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ሊለዩ ይገባል።

ዛሬ ላይ ብዙ ለውጥ ቢኖርም ታቦት የሚሸኙ፣ መስቀል፣ ጥምቀት የሚያከብሩ፣ ለግንቦት ልደታ ንፍሮ የሚቀቅሉ፣ ጷጉሜ ቅዱስ ምናምን እያሉ የተለያዩ እምነታዊ ተግባራትን የሚፈጽሙ፣ ፀበል የሚሄዱ፣ የጴንጤ ትርኢቶች ላይ የሚሳተፉ፣ ለወላድ "እንኳን ማርያም ማረችሽ"፣ "ማርያም በሽልም ታወጣሽ" የሚሉ፣ ወዘተ ብዙ ወገኖች አሉ። ስለዚህ አሁንም ብዙ ስራ አለብን ለማለት ነው።
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የመካ ሙ ሽ -ሪኮች የአላህን ፈጣሪነት አልካዱም!
~
ነቢዩ ﷺ የተላኩባቸው እነዚያ ሙ .ሽ -ሪኮች #አብዛኞቹ የሰማይ፣ የምድር ፈጣሪ አላህ እንደሆነ፣ የሁሉ ነገር ስልጣኑ በእጁ እንደሆነ፣ ዝናብ የሚሰጠው አላህ እንደሆነ ያምኑ ነበር። እነዚህ ባዶ ሙግቶች ሳይሆኑ የተረጋገጡ ሐቆች ናቸው። ቁርኣን ውስጥ ከሚገኙ በርካታ መረጃዎች ውስጥ #ጥቂቱን ብቻ ልጥቀስ።

1. {قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِیهَاۤ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ (84) سَیَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ (85) قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِیمِ (86) سَیَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ (87) قُلۡ مَنۢ بِیَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَیۡءࣲ وَهُوَ یُجِیرُ وَلَا یُجَارُ عَلَیۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ (88) سَیَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ (89)}
{“ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው የምታውቁ ከሆናችሁ?” በላቸው። “በርግጥ የአላህ” ይላሉ። “ታዲያ አትገሰፁምን?” በላቸው። “የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?” በላቸው። “በርግጥ አላህ ነው” ይላሉ። “እንግዲያው አትፈሩትምን?” በላቸው። “የሁሉ ነገር ስልጣኑ በእጁ የሆነው እሱ የሚጠብቅ በሱ ላይ የማይጠበቅ (የሆነው) ማን ነው? የምታውቁስ ከሆናችሁ?” በላቸው። “(ሁሉም) ለአላህ ነው” ይላሉ። “ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?” በላቸው።} [አልሙእሚኑን፡ 84-89]

2. {وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضَ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ لَیَقُولُنَّ ٱللَّهُۖ } ... {وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّن نَّزَّلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَحۡيَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ مِنۢ بَعۡدِ مَوۡتِهَا لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۚ}
{ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ “አላህ ነው” ይላሉ።} {ከሰማይም ውሃን ያወረደና በሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው ያደረጋት ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በርግጥም “አላህ ነው” ይላሉ።} [አልዐንከቡት፡ 61፣ 63]

3. {وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ خَلَقَهُنَّ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡعَلِيمُ}
{ሰማያትንና ምድርን ማን እንደፈጠረ ብትጠይቃቸውም በእርግጥ “አሸናፊውና አዋቂው (አላህ) ነው የፈጠራቸው” ይላሉ።} [ዙኽሩፍ፡ 9]

4. {وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَهُمۡ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۖ }
{ማን እንደፈጠራቸው ብትጠይቃቸውም “በእርግጥ አላህ ነው” ይላሉ።} [ዙኽሩፍ፡ 87]

እንዲያውም የመካ ጣኦ ^ታውያን ለአላህ አምልኮትም ይፈፅሙ ነበር። እርድና ሐጅን በምሳሌነት መውሰድ ይቻላል። ከዚህም አልፎ ጣኦ ^ታውያኑ ጣኦ .ቶቻቸው ከአላህ በታች እንደሆኑ ያውቁ ነበር። በማስረጃ ነው የማወራው።

1. {وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ}
{እነዚያም ከርሱ ሌላ ረዳቶችን የያዙት “ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጂ ለሌላ አንገዛቸውም” (ይላሉ።)} [ዙመር፡ 3]

2. {وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡ وَيَقُولُونَ هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ}
{ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን እና የማይጠቅማቸውን ያመልካሉ። “እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉም።} [ዩኑስ፡ 18]

ልብ በሉ! ወደ አላህ ለመቃረብ ነው ጣኦ .ቶችን የሚያመልኩት እያለን ነው።

ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ እንዲህ ይላሉ፡-
كَانَ الْمُشْرِكُونَ يَقُولُونَ: لَبَّيْكَ لَا شَرِيكَ لَكَ، قَالَ: فَيَقُولُ رَسُولُ اللهِ ﷺ: «وَيْلَكُمْ، قَدْ قَدْ» فَيَقُولُونَ: إِلَّا شَرِيكًا هُوَ لَكَ، تَمْلِكُهُ وَمَا مَلَكَ، يَقُولُونَ هَذَا وَهُمْ يَطُوفُونَ بِالْبَيْتِ
“አጋሪዎቹ 'ለበይከ ለአንተ ተጋሪ የለህም' ይሉ ነበር። ይህን ሲሉ የአላህ መልእክተኛ ﷺ {ወዮላችሁ በቃ በቃ!} ይሏቸው ነበር። እነሱ ግን 'የምትቆጣጠረው የማይቆጣጠርህ ላንተ የሆነ ተጋሪ ቢሆን እንጂ' ይላሉ። ይህን የሚሉት ከዕባን እየዞሩ (ጠዋፍ ሲያደርጉ) ነው።” [ሙስሊም፡ 1185]

እንደምታዩት ሰዎቹ በአላህ ፈጣሪነት ያምኑ ነበር። ዒባዳም ለሱ ይፈፅሙ ነበር። እንዲያውም ጣኦ .ቶቻቸው አላህ የሚቆጣጠራቸው ከሱ በታች የሆኑ እንደሆኑ በግልፅ እየተናገሩ ነው። ይሄ ሁሉ መረጃ እያለም “የለም! የመካ አጋ .ሪዎች ከነ ጭራሹ በአላህ አያምኑም ነበር” የሚል አለ። ቢገባችሁ ችግራችሁ ከቁርኣን ጋር ነው።

“እና የአላህን ፈጣሪነት የሚያምኑ ከነበሩ እንደ ከሃ .ዲ፣ አጋሪ ያስቆጠራቸው ምን ነበር?” ከተባለ ከምክንያቶቹ ውስጥ #አንዱ ሺርክ ነው። ሙሽ^ሪኮች ነበሩ። አላህን እንደሚያመልኩት ጣኦ .ቶቻቸውን ያመልካሉ። ለአላህ ሐጅ እንደሚያደርጉት በሐጁ ላይ ጣኦ .ቶቻቸውን ይጠራሉ። “የአላህ ባሪያ” ብለው ስም እንደሚያወጡት “የዑዛ ባሪያ” ብለው ስም ያወጣሉ። በአላህ እንደሚምሉት በጣ .ኦቶቻቸው ይምላሉ። ለአላህ እንደሚያርዱት ለጣኦ .ቶቻቸው ያርዳሉ። አላህን እንደሚወዱት ጣኦቶቻቸውን ይወዳሉ። ... ይሄ ተግባራቸው ነው ከነብዩ ﷺ ጋር ያፋጠጣቸው። ይሄ ተግባራቸው ነው ለአላህ ባላንጣ ማድረግ ተብሎ የተወገዘው። {ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን የሚይዝ አልለ። ልክ አላህን እንደሚወዱት ይወዷቸዋል} የሚለው የጌታችን ቃል ይህን ሀሳብ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

በተመሳሳይ ዛሬም ዒባዳዎችን ለአላህ እንደሚሰጠው ለፍጡሮች የሚሰጥና የሚማፀን ከሆነ የነዚያን ሙሽ .ሪኮች ተግባር ነው የፈፀመው። የዒባዳ ተውሒድ ከሌለ በአላህ ፈጣሪነትና ጌትነት ማመን ብቻውን ሙስሊም አያሰኝም፣ ከእሳትም አያድንም።
በመቅሪዚይ (845 ሂ.) ንግግር ፅሁፌን ልቋጭ፡- “ተውሒደ ሩቡቢያ እነዚያ አጋሪዎች ያልካዱበት ለመሆኑ ጥርጥር የለም። ይልቁንም ጥራት ይገባውና እሱ (አላህ) ብቻ የነሱም የሰማያትና የምድርም ፈጣሪ፣ ለአለማቱ ጥቅም ባጠቃላይ የቆመ እንደሆነ ያምኑ ነበር። ይልቅ የተቃወሙት የአምልኮትና የውዴታን ተውሒድ ነው።” [ተጅሪዱ ተውሒዲል ሙፊድ፡ 8]
ይሄ እንግዲህ የብዙሃኑ አጋሪዎች እምነት ነው። በጊዜው ከነበሩ ከሃ - ዲዎች ውስጥ የተወሰኑ ደህሪዮች ነበሩ፣ በፈጣሪ የማያምኑ። እነዚያን የሚመለከቱ መረጃዎችን ብቻ እየመዘዙ ሌሎችን አንቀፆችን መግፋት እራስን መሸወድ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጆችን አስር አመት ሲሆናቸው መኝታቸውን ለያዩዋቸው ብለዋል። ስለዚህ አላህ ባገራለት ልክ ሊለያያቸው ይገባል ማለት ነው። አንድ ክፍል ከሆነ ሁሉም የሚተኙት ሴቶችን አንድ ጥግ፣ ወንዶችን ሌላ ጥግ ማድረግ። በቂ ክፍል ካለ ሴቶችን የብቻ አንድ ክፍል፣ ወንዶችን ሌላ ክፍል ማድረግ። ከተቻለ ወንዶችን ከወንዶች፣ ሴቶችንም ከሴቶች ፍራሻቸው ቢለያይ ጥሩ ነው። አጉል መልካም ግምት ሊያዘናጋን አይገባም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ፖለቲካዊ ስጋቶችን ጠዋት ማታ ማስጠንቀቁን ከተውሒድ አስተምህሮት በላይ የሚያደርግ ሰው ማስተማር ሳይሆን መማር ነው ያለበት። የሙታን አምልኮን፣ መሰረታዊ የዐቂዳ ልዩነትን አቅልሎ በመመልከት በጥቃቅን ነገሮች ልንለያይ አይገባም የሚል ሰው መሰረታዊ የግንዛቤ ችግር ያለበት ሰው ነው። ተውሒድ የሌለበት አንድነት ዋጋ የለውም።

ኢስላም፣ ኢማን፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ ከቃላት ያልፋል። በተግባር ያልተገኘ ላ ኢላሀ ኢለላህ ባዶ መፈክር ነው። ከአላህ በስተቀር የሐቅ አምላክ የለም ብሎ የመሰከረ ሰው ምስክርነቱ በተግባር መገኘት አለበት። ላ ኢላሀ ኢለላህ እያለ ለጭንቅ ለመከራው እነ ጫሊን፣ አብሬትን፣ ቃጥባሬን፣ ገታን፣ አባድርን፣ ደገርን፣ ወዘተ. የሚማፀን ከሆነ በምላሱ የሚናገረው ከልቡ የለም። ባዶ መፈክር ምን ይሰራል?! እነዚህ አካላት ደካማ ፍጡሮች ናቸው። ከሞቱ በኋላ ቀርቶ በህይወት እያሉም ልጅና ዝናብ አይሰጡም። ቀጥታ ከአላህ መጠየቅ እየቻልክ ማርያምን፣ ገብረኤልን፣ ሚካኤልን እንደሚማፀኑ ኦርቶዶክሶች አትሁን። በኢስላም እየሱስን ብቻ ሳይሆን ሙሐመድንም ማምለክ አይቻልም። (ሰላም በሁለቱም ላይ ይሁን።)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ጥቂት ስለ ፌሚኒዝም
~
ፌሚኒዝም አጥፊ ወረርሽኝ ነው። ከማንም በላይ የሚጎዳው ደግሞ ቆሜላታለሁ የሚላትን ሴቷን ነው።
* በሃይማኖት ላይ እንድታቄም በማድረግ ኣኺራዋን ያበላሻል። ከዚህ በላይ ምንም ጉዳት የለም።
* በትዳር ላይ እንድትሸፍት ወይም ዋጋ እንዳትሰጥ በማድረግ ዱንያዋን ያበላሻል።
* ሁሉንም ወንድ አንድ አድርጋ እንድታይ በዳይ ድምዳሜ ላይ ያደርሳታል።
* ልጅ ወልዶ ማሳደግን እንደ ፀጋ ሳይሆን እንደ እዳ እንድትመለከት ያደርጋታል።
* ከእምነት፣ ከተፈጥሮ እና ከልማድ የወጣ የሴት ለሴት ፆታዊ ግንኙነት ውስጥ እንድትገባ ያደርጋታል።
* ያለ ጋብቻ ልጅ መውለድን ኖርማል አድርጋ እንድታይ ያደርጋታል።
* ሐያእና ግብረ ገብነትን እንደ ኋላቀርነት፣ ልቅነትን እንደ ንቃት እንድትመለከት ያደርጋታል።
* ፅንፍ ለረገጠ የወንድ ጥላቻ በማጋለጥ ለስነ ልቦና ቀውስ ይደርጋታል።
* ንቅናቄው ከጥንስሱ ጀምሮ ሴቶችን ከማራቆት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።
* በሴትነቷ ውስጥ ክብሯን ከመፈለግ ይልቅ ከተፈጥሮዋ የወጣ የወንድነት ትግል ውስጥ ያስገባታል፣ ወዘተ.

በብዛት የወጣትነት የእድሜ ክልል ላይ ያሉ ሴቶች በዚህ ንቅናቄ ላይ ያለው አደጋ ላይታያቸው፣ የሚሰጠው ምክርም ላይዋጣቸው ይችላል። ለዚያም ነው እያንዳንዷን ኮሽታ በጥርጣሬ፣ እያንዳንዷን ምክር በአሉታዊ መልኩ መተርጎም የሚቀናቸው። ለዚያም ነው ትዳር ላይ ትእግስት ያስፈልጋል ሲባል ተሽቀዳድመው "እና ትሙት ወይ?" የሚል ሙግት ውስጥ የሚገቡት። ለህይወቷ በሚያሰጋ ቤት ውስጥ በፍፁም ልትኖር አይገባም። ይሄ ቀርቶ አካላዊ ጉዳት ይደርስባታል ተብሎ ከተሰጋ በጊዜ የሚበጅ እርምጃ መውሰድ ይገባል። ከዚያ በመለስ ሲወራ ግን ትዳር ውስጥ ብዙ ውጣ ውረድ አለ። ሰው አብሮ ሲኖር ብዙ ነገር ያጋጥመዋል። ብስለትና ትእግስት ባለመኖራቸው ስንት ትዳር እንደሚፈርስ፣ ስንት ልጆች ለሰቆቋ እንደሚዳረጉ፣ "ምነው በታገስኩ!" የሚባልበት ስንትና ስንት ፀፀት እንደሚከተል የሚታወቅ ነው። ታዲያ ስለ ትእግስት መመካከርን ዘሎ አሉታዊ ትርጉም መስጠት ምን ማለት ነው?

ለፌሚኒዝም በሽታ ከሚያጋልጡ ሰበቦች

* ጨካኝ እና ያልተገራ የወንዶች አያያዝ ለሴቷ ዋና ገፊ ምክንያት ነው። ለንቅናቄውም ገበያ የሚፈጥር ትልቅ የትርክት ግብአት ነው።
* ዲንን አለመማር :- ትልቁ የችግሩ መንስኤ ይሄ ነው። የዲን ግንዛቤ ሲኖር መገፋት እንኳ ቢያጋጥም ሌላ ፅንፍ ከመርገጥ ይጠብቃል።
* የተቅዋ መሳሳት ወይም ከዲን መራቅ። የልብ ድርቀት ለብዙ በሽታ ያጋልጣል። በማይረቡ ጩኸቶች መጠለፍን ያስከትላል።
* የሰው ልጅ በተፈጥሮ በደለኛ ነው። ወንድ ሴትን ብቻ ሳይሆን ወንድ ወንድን፣ ሴት ወንድን፣ ሴት ሴትን ያለ ፆታ ልዩነት አንዱ ሌላውን ይበድላል። እያንዳንዷን ሴት ላይ የምትደርስን በደል በተለየ መልኩ ፆታዊ ትርጓሜ መስጠት ችግሩን ያውሰበስባል እንጂ መፍትሄ አያመጣም። ትኩረት መደረግ ያለበት ፍትህን ማስፈን፣ በደልን ከማንም ይምጣ፣ ማንም ላይ ይድረስ በጋራ መጋፈጥ ነው።
* ከፌሚኒዝም ንቅናቄ ጀርባ ያደፈጠውን ተንኮል አለማወቅ። ብዙ ምስቅልቅል ከደረሰ በኋላ ዘግይቶ መንቃት ለትልቅ ፀፀት ይዳርጋል።
* በሴቶች ስም የተደራጁ ብዙ አደረጃጀቶች የተቃወሰ አካሄድ የዚህ ወረርሽኝ ማስፋፊያዎች ናቸው። እንዲያውም እውነተኛ የሴትን ልጅ ህይወት ለማሻሻል የረባ ስራ የላቸውም።

መፍትሄዎች

* ወንዶች ለሴቶች ያላቸውን አያያዝ እንዲያስተካክሉ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ።
* በደሎችን በፆታ መነፅር ሳይሆን በፍትህ መነፅር በመመልከት ኃላፊነት ወስዶ ለማስተካከል መስራት።
* የሚደርሱ ከባባድ በደሎች ላይ እንዲሁ ለሚዲያ ፍጆታ ማዋል ሳይሆን አስተማሪ የሆነ ጠንካራ የእርምት እርምጃ መውሰድ።
* ሴቶችንም ወንዶችንም ዲናቸውን እንዲማሩ መስራት። ወዘተ.

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 13/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Forwarded from Fuad Mohammed (فؤاد محمد)
هذا شرح لألفاظ في مسائل الموسيقى والغناء والمعازف لخصته من كتاب الرد على القرضاوي والجديع لعبد الله رمضان بن موسى

1- "المعازف" ليس من المشترك اللفظي وإنما لها معنى واحد باتفاق أهل اللغة وهو آلات اللهو والطرب والملاهي وهي التي تسمى بالآلات الموسيقية كالعود والطنبور والدفوف نص عليها أهل اللغة راجع العين، ولسان العرب والمصباح المنير والنهاية، والمغرب للخوارزمي، وتاج العروس، والقاموس المحيط، وتهذيب اللغة، وقال ابن تيمية كما في مجموع الفتاوى: "المعازف هي الملاهي كما ذكر ذلك أهل اللغة".
وإنما الاشتراك في كلمة "العازف" على وزن فاعل فإن لها معنيين أحدهما اللاعب بالمعازف وهي الآلات وثانيهما المغني (أي بالصوت المجرد دون آلات) جاء هذا في مختار الصحاح، والصحاح، ولسان العرب والقاموس المحيط وغيرها فلا بد من التدقيق في هذا لفهم حديث المعازف وبيان تدليس من يدعي أن من معاني المعازف الغناء.

تنبيه: واحد المعازف: عزف - على غير القياس- ومِعزَف ومعزفَة، راجع المعاجم السابقة.
ولفظ "العَزف" فيه اشتراك في المعنى أيضا فله ثلاثة معان:
- الآلات
- اللعب بالآلات
- الصوت
وتحرير محل النزاع:
أ- أن لفظ العزف الذي معناه الصوت أو اللعب بالآلات لا يجمع على معازف وإنما المعازف جمع للعزف الذي معناه الآلات نفسها فقط.
ب- أن العزف الذي معناه الصوت يأتي مضافا فيقال " عزف الرياح" و"عزف الدفوف" قال في تاج العروس: "عزف الرياح ,صواتها" وبهذا يتبين معناه.

وتحديد معنى اللفظ المفرد بالنظر إلى جمعه أمر معروف في اللغة ألا ترى أن "العود" لفظ مشترك بين الخشبة وآلة الغناء فإذا قصد به الخشبة جمع على "أعواد" وإذا قصد به الآلة جمع على "عيدان" قاله التلمساني في مفتاح الأصول بمعناه.

2- "الغناء" معناها "رفع الصوت وموالاته" راجع النهاية وتاج العروس ولسان العرب بألفاظ متقاربة فيها معنى الرفع والموالاة.
3- " المد" مد الحرف يمده مدا أي طوله (لسان العرب)
4- "الجَرْس" الصوت نفسه ويقال أجرس أي علا صوته ويقال جرس الحرف: نغمته (لسان العرب، تهذيب اللغة)
5- "النغمة" وجمعها نغْم ونغَم: جرس الكلمة -أي صوتها- وحسن الصوت قي القراءة وغيرها (مختار الصحاح، لسان العرب)
6- "التحزين" يقرأ بالتحزين أي يرقق صوته ( القاموس المحيط)

7- "السماع" معناه "الغناء والمسمعة المغنية" هكذا فسره أهل اللغة بأنه غناء بالصوت فقط دون الآلات الموسيقية جاء هذا في المحكم والمحيط الأعظم ومختار الصحاح وتاج العروس والمحيط في اللغة وغير ذلك فيطلق السماع عند العرب على الغناء بالصوت الطبيعي ولا يقصد به الغناء المصحوب بالمعازف ولذلك إذا أراد الفقهاء المعنى الأخير عبروا عنه بقولهم" السماع بآلة"

8- "التطريب" يقال طرب فلان في غنائه إذا رجع صوته وزينه والتطريب في الصوت مده وتحسينه (لسان العرب) والترجيع ترديد الصوت في الحلق كما سيأتي و"الطرب" الفرح والحزن وخفة تصيب الإنسان لشدة حزن أو فرح والعامة تخصه بالسرور راجع لسان العرب والمصباح المنير

9- " ترجيع الصوت "ترديده في الحلق كقراءة أصحاب الألحان" (لسان العرب) واللحن تطريب الصوت ومده كما سيأتي، روى البخاري عن عبد الله بن مفغل المزني قال: رأيت رسول الله صلى الله عليه وسلم يوم الفتح على ناقة له يقرأ سورة الفتح قال: فرجع فيه....." وقال معوية بن قرة -وهو من رواة الحديث- في كيفية ترجيع النبي صلى الله عليه وسلم قال :" آآآ ثلاث مرات"

10- "الإيقاع" اعتبار زمان الصوت، والوزنُ، وحركاتٌ متساوية الأدوار لها عودات متاولية، انظر الكشكول لبهاء الدين العاملي وجاء في المخصص في اللغة:"الإيقاع في الغنا بمنزلة العروض من الشعر "

11- من الألفاظ المهمة "اللحن" ويطلق على عدة معان منها:

أ- التطريب وتحسين الصوت في القراءة والشعر والغناء
ب- اللغة و النحو
ج- الخطأ في الإعراب فهو من الأضداد (قاله ابن الأثير )
واللحن من الأصوات المصوغة الموضوعة وهي التي يرجع فيها ويطرب (تاج العروس) وفي (جمهرة اللغة) "لحّن في قراءته إذا طرب فيها" وفي بعض طرق حديث عبد الله بن مفغل السابق جاء قول معاوية بن قرة (لولا أن يجتمع الناس لقرأت لكم بذلك اللحن) قال ابن حجر: "أي النغم"
فالألحان إنما هي بمد الصوت وتحسينه وترديده في الحلق وليس لها علاقة بالآلات الموسيقية في لغة العرب كما توهمه بعض المعاصرين من المجيزين للمعازف.

12- " الموسيقى" عرفها ابن القيم في الزاد" هي إيقاعات وحركات موزونة محدودة معدودة" وجاء في (الإمتاع والمؤانسة) لأبي حيان التوحيدي " الموسيقى التي هي معرفة النغم والإيقاعات والنقرات والأوزان" فهي كلمة في الأصوات الطبيعية التي تكون النغم وليست اسما للمعازف
https://www.tgoop.com/fuadorodurus
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የጀህ ^ሚያ ጥንስስ
~
በኢስላም ታሪክ የፈጣሪን መገለጫዎች (ሲፋት) ማራቆት የተጠነሰሰው በጀህ ^ሚያ ቡድን ነው። የዚህ ቡድን መስራቹ ጀዕድ ብኑ ዲርሃም ይባላል። ይሁን እንጂ ይህንን አስተሳሰብ ያሰራጨው ተማሪው ጀህም ብኑ ሶፍዋን በመሆኑ የተነሳ ጀህ ^ሚያ የሚለው የቡድኑ ስያሜ በሱ ስም ነው የተሰየመው።

ይህ የፈጣሪን መገለጫዎች (ሲፋት) የማራቆት እምነት ከሙሽ ^ሪኮች፣ ከሷቢአዎች፣ ከፈላስፋዎች፣ ከሂንዱይዝም ሱፊዮች እና ከአፈን ^ጋጭ የመፅሀፉ ሰዎች እንደሆነ ኢብኑ ተይሚያ ይገልፃሉ። [አልመጅሙዕ፡ 10/67] ስለዚህ ይህ አመላካከት ወደ ኢስላም ከመግባቱ በፊት ሌሎች ህዝቦች ዘንድ ይገኝ ነበር ማለት ነው። ይህንንም የሚያረጋግጥልን ይህ እምነት በታዋቂዎቹ የግሪክ ፈላስፎቹ እነ ፕላቶ፣ ኦርስቶትል፣ ሶቅራጥስ መፃህፍት ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ነው። እስክንድሪያዊው የሁ D ፋይሎ (40 ዓ.ል) ይህንን እምነት ቀጥታ ከግሪክ ፍልስፍና እየቀዳ መፃህፍት አዘጋጅቷል። ይሁን እንጂ በጊዜው iሁዶች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ነበር። ከነሱ ይልቅ በጊዜው በአካባቢው የነበሩ ክርስቲያኖች ነበሩ የተቀበሉት። ስራዎቹን ለትውልድ ያቆዩዋቸውና የተነተኗቸውም እነሱ ናቸው። የኋላ ኋላ ግን ስሙ እየናኘ ሲመጣ ስራዎቹ iሁዱም ክርስቲያኑም ዘንድ ተቀባይነት አገኝተዋል።

የጀህም እና የፋይሎ የማራቆት (ተዕጢል) ፍልስፍናዎች በጣም መቀራረብ አላቸው። (The Philosophy of the the Kalam, Wolfson P. 222) እንዴት? የፋይሎ እምነት ወደ ሙስሊሙ ዓለም የተሰራጨው በደማስቋዊው ዮሐንስ አማካኝነት ነው። ዮሐንስ ክርስቲያን ነው። አንዳንድ ኦሬንታሊስቶች በአስማእ ወሲፋት እና በቀደር ጉዳይ የመጡ እንግዳ የሆኑ የዒልመል ከላም እምነቶችን ወደ ሙስሊሞች ያስገባቸው ይህ ሰው እንደሆነ ገልፀዋል። ዮሐንስ ፍልስፍናን በጥልቀት ያጠና ሰው ነው። ከሙስሊሞች ጋር በነበረ ጦርነት ተማርኮ በእውቀቱ የተነሳ ደማስቆ ላይ ለቤተ መንግስት ቅርብ ነበር። ዮሐንስ ኢስላምንም በሚገባ አጥንቷል። ዘመኑ ከጀዕድ ብኑ ዲርሃም ጋር ይገናኛል። ጀህም በሞት ሲቀጣም በህይወት ነበር። ጀዕድ ብኑ ዲርሃም ደማስቆ ውስጥ ከቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነበር የሚኖረው። እና ፍልስፍናውን በከፊልም ቢሆን ከዮሐንስ እንደ ቀዳው ይታሰባል። በከፊል ደግሞ ከአባን ብኑ ሰምዓን።

ከዚህም በተጨማሪ ይህ የማራቆት እምነት ሐራን አካባቢ የነበሩ ሷቢአዎች እና ሱመኒያ የተሰኙ በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የሂንዱይዝም ሱፍዮች ዘንድም ነበር። ጀዕድ መነሻው ከሐራን እንደመሆኑ ተፅእኖው ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሊሆን ይችላል። ጀህምም ከሱመኒያዎች ጋር ውይይት ለማድረጉ ተጨባጭ መረጃዎች አሉ።

ጠንሳሹ ጀዕድ ብኑ ዲርሃም እና ተማሪው ጀህም ብኑ ሶፍዋን በዚሁ ጥፋታቸው የተነሳ በሞት የተቀጡ ቢሆንም በኢስላም ታሪክ እንደ ጀህ ^ሚያ ዛሬ ድረስ ያልለቀቀ ከባድ የዐቂዳ ነውጥ የፈጠረ የለም። ዋና ዋናዎቹ የጀህ ^ሚያ አመላካከቶች ምን ምን ናቸው?

1- በመሰረታዊ የዲን ክፍሎች ላይ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃዎች አይቀበሉም። ከዚህ ይልቅ ዐቅል ነው መረጃ የሚሆነው የሚል ከንቱ ሙግት አላቸው።
2- ለአላህ ሲፋትን ማፅደቅ ከፍጡር ጋር ማመሳሰል ነው በሚል መነሻ ስሞቹንና መገለጫዎቹን (አልአስማእ ወሲፋት) ይክዳሉ።
3- የአላህን ከፍጡራን በላይ መሆን ያስተባብላሉ። እንዲያውም ጀህም ብኑ ሶፍዋን የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚጠቁመውን አንቀፅ ብችል ከቁርኣን ላይ ፍቄ አወጣው ነበር እስከማለት ደርሷል። [ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ፣ አልቡኻሪይ፡ 20]

4- በአላህ ሲፋት ላይ የያዙትን የማራቆት ዐቂዳ ያልተቀበሉ ሰዎችን አመሳሳዮች (ሙሸቢሀ) ናቸው በማለት ከኢስላም ያስወጣሉ። [አረድ ዐለልጀህሚያ፣ አሕመድ፡ 104]
5- ኢማን ማለት አላህን ማወቅ ብቻ ነው ይላሉ። ማወቅ ብቻ!! [አልኢማን፣ አቡ ዑበይድ፡ 31-32] [መቃላቱል ኢስላሚዪን፣ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ፡ 279]
ትክክለኛው ትርጓሜ ኢማን የልብ እምነትን፣ የምላስ ምስክርነትን እና የአካላት ተግባርን የሚያካትት ነው።

6- ቁርኣንን የአላህ ንግግርና ሲፈቱ አድርገው ሳይሆን ፍጡር ነው ብለው ያምናሉ። [መቃላቱል ኢስላሚዪን፣ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ፡ 280]
በዚህም የተነሳ ቁርአን ላይ የሰፈረውን ሐቂቃ በመካድ አላህ ሙሳን አላናገረም ይላሉ።
7- በብዙ የቁርኣንና የሐዲሥ መረጃዎች የተረጋገጠውን በኣኺራ ሙእሚኖች አላህን ያያሉ የሚለውን ዐቂዳ ይክዳሉ። [አልጉንያ፣ ጀይላኒይ፡ 114]

8- በቀደር ጉዳይ የሰው ልጅ የራሱ መሻትና ምርጫ የለውም ወንጀሉን ጭምር በአላህ ተገዶ ነው የሚፈፅመው የሚል የጀብር ዐቂዳ አላቸው። [መቃላቱል ኢስላሚዪን፣ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ፡ 279]
የሰው ልጅ ድርጊቶቹ ሁሉ ልክ እንደ ቁመቱ፣ እንደ መልኩ በፈጣሪ የተሰጠው እንጂ የራሱ ምርጫ የለውም ይላሉ።

9- በሲራጥ፣ በሚዛን፣ በቀብር ቅጣት፣ በሸፋዐ አያምኑም። [አተንቢህ ወርረድ፣ አልሚለጢ፡ 106፣ 118፣ 128]
10- ጀነትና ጀሃነም ይጠፋሉ ብለው ያምናሉ። [ኪታቡል ዐርሽ፣ ኢብኑ አቢ ሸይባ፡ 49]

በነዚህ ጥፋቶቻቸው የተነሳ የዚህ ቡድን ተከታዮች እንደ ሙስሊም አይቆጠሩም ብለዋል ሰለፎች። ከነዚህ የጀህ ^ሚያ ጥፋቶች ውስጥ ብዙዎቹ ዛሬ አሕ ^ባሾች ዘንድ በሰፊው ይገኛሉ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 14/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Forwarded from Fuad Mohammed (فؤاد محمد)
حديث المعازف ودلالته على التحريم مع ذكر شبهة مشهورة للمجيزين حوله


«لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ ‌يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ وَلَيَنْزِلَنَّ أَقْوَامٌ إِلَى جَنْبِ عَلَمٍ يَرُوحُ عَلَيْهِمْ بِسَارِحَةٍ لَهُمْ يَأْتِيهِمْ يَعْنِي الْفَقِيرَ لِحَاجَةٍ فَيَقُولُوا ارْجِعْ إِلَيْنَا غَدًا فَيُبَيِّتُهُمُ اللهُ وَيَضَعُ الْعَلَمَ وَيَمْسَخُ آخَرِينَ قِرَدَةً وَخَنَازِيرَ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ.» أخرجه البخاري

هذا الحديث صريح في تحريم المعازف وهي آلات الملاهي كالعود والطنبور وغير ذلك وسبق بيانه في المنشور الأول.

ووجه الدلالة: أنه قال (يستحلون) أي "يجعلون الحرام حلالا" قاله الصنعاني في سبل السلام، و "أن المعازف هي آلات اللهو كلها لا خلاف بين أهل اللغة في ذلك" قاله ابن القيم في إغاثة اللهفان.

وهو حديث صحيح صححه الأئمة الحفاظ على مر العصور فصححه البخاري وأبو بكر الإسماعيلي وابن حبان وابن الصلاح وابن جماعة وابن تيمية وابن القيم وابن كثير وابن الملقن والحافظ العراقي وابن رجب والعيني وابن الوزير والصنعاني وشعيب الأرنؤوط، والألباني وقال" فهل يدخل في عقل مسلم أن يكون المخالفون كابن حزم ومن جرى خلفه- وليس فيهم مختص في علم الحديث- هل يعقل أن يكون هؤلاء على صواب وأولئك الأئمة على خطأ؟(هل يستوي الذين يعلمون والذين لا يعلمون)(إن في ذلك لذكرى لمن كان له قلب أو ألقى السمع وهو شهيد)" انتهى

ذكر الشبهة المشهورة حول هذا الحديث
قال المجيزون إن هذا الحديث إنما يدل على تحريم المعازف بدلالة الاقتران ودلالة الاقتران ضعيفة عند جمهور الأصوليين فلا دلالة فيه على تحريم المعازف.

ج: أن هذا كذب على الأصوليين وذلك لأن الأصوليين فرقوا بين المعطوفات ولم يحكموا عليها بحكم واحد فقالوا إذا كان المعطوف ناقصا بأن لم يذكر فيه الخبر كقولك (زينب طالق وعمرة) أو كان المعطوفات مفردات كما هو في هذا الحديث فإن دلالة الاقتران في هذين النوعين توجب المشاركة في الحكم بإجماع الأصوليين ولا خلاف بينهم في ذلك وممن حكى هذا الإجماع الزركشي في البحر المحيط والشوكاني في إرشاد الفحول وعلاء الدين البخاري في كشف الأسرار والقرافي في نفائس الأصول وقال " نص النحاة على أن المعطوف يجب مشاركته للمعطوف عليه في أصل الحكم الذي سيق الكلام لأجله" ، ونص على صحة هذه القاعدة ابن حزم - الذي يتشبث به المجيزون_ في كتابه الإحكام.

تنبيه: دلالة الاقتران إذا كانت بين جملتين تامتين كل منهما مبتدأ وخبر أو فعل وفاعل كقوله تعالى ( كلوا من ثمره إذا أثمر وآتوا حقه يوم حصاده) فإن المعطوف والمعطوف عليه جملتان تامتان لأن الجملة الأولى وهي (كلوا من ثمره إذا اثمر) عطف عليها الجملة الثانية وهي (آتوا حقه يوم حصاده) فهذا النوع من دلالة الاقتران هو الذي لا يوجب الاشتراك في الحكم عند جمهور الأصوليين لأن الأكل من الزكاة يوم حصاده ليس واجبا كإيتاء زكاته وإنما "عطف واجبا على مباح" قاله ابن النجار في شرح الكوكب المنير.

وأما حديث المعازف ففيه عطف المفردات وبيانه أنه ورد في صحيح البخاري بلفظ( ليكونن من أمتي أقوام يستحلون الحر والحرير والخمر والمعازف) فهي كلها مفردات كما هو واضح وليست جملا بدليل أننا لو حذفنا عبارة (يستحلون الحر) فلا يكون لهذه المفردات المتبقية أي معنى لأن الكلام يصبح هكذا( ليكونن من أمتي أقوام الحرير والخمر والمعازف) وهذا ليس كلاما ذا معنى فلذلك اتفقوا على أن دلالة الاقتران في مثل هذا توجب الاشتراك في الحكم.

وبهذا يتبين أن دلالة الاقران في حديث المعازف حجة بإجماع الأصوليين وأما ابن حزم فإنه موافق للعلماء في أصل القاعدة -وإنما أتي في إباحة المعازف من تضعيفه بخطإ ظاهر لحديث المعازف الذي صححه أهل الصناعة الحديثية كما سبق.

مستفاد من كتاب الرد على القرضاوي والجديع

https://www.tgoop.com/fuadorodurus
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
~
ሰሞኑን ስለ መውሊድ ስፅፍ ደጋግመው ኢብኑ ተይሚያም ፈቅደዋል በማለት የተቆረጠ ንግግራቸውን በሃሳብ መስጫ ላይ ሲለጥፉ እያየሁ ነው። ኢብኑ ተይሚያን የመውሊድ ደጋፊ አስመስሎ ማቅረብ ብዙ ሱፍዮች ዘንድ የተለመደ ነው። የመውሊድ ነቃፊዎች ኢብኑ ተይሚያን ስለሚወዱ "በሚያከብሩት ሰው አፋቸውን እናስይዛቸው" ነው ስሌቱ። ይሄ የሚያዋጣ ሂሳብ አይደለም።
ይሄ ኢብኑ ተይሚያን የመውሊድ ደጋፊ የማድረግ አካሄድ ቀድሞም ከፊል ሱፊዮች ዘንድ የሚታወቅ ቢሆንም ሐሰን ታጁ በመውሊድ መፅሀፉ ላይ ከጠቀሰው በኋላ የሚያነሱት በዝተዋል። ሐሰን ታጁ ቆርጦ ቀጥል ነው። ትንሽ መደገፊያ ካገኘ በምርኩዝ ዝላይ ከሰው ግቢ ይገባል። የንግግሩ መምታታት ሁሉ አያሳስበውም። ከኢብኑ ተይሚያ በፊት መውሊድን የተቃወመ የለም እያለ ዞሮ ኢብኑ ተይሚያን የመውሊድ ደጋፊ ያደርጋቸዋል። ከዚህም አልፎ ሸይኽ ፈውዛን ከመውሊድ ነቃፊ ዑለማኦች ውስጥ ኢብኑ ተይሚያን በመጥቀሳቸው "ሙደሊስ" (አምታች) ይላቸዋል። የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ነው ነገሩ! በራሱ መታወቂያ ሌሎችን ይከስሳል። ንግግሩ እንደሚጋጭም አይገባውም። ውሸታም ጥሩ የማስታወስ ችሎታ ያስፈልገዋል ይባላል። ካልሆነ ንግግሩ ይጋጫል። ሐሰን ታጁ እንዲህ ነበር ያለው፦

“ሸኽ እብን ተይሚያህም ቢሆን ያነሱት ሀሳብ ወደ ተቃውሞ ደረጃ ከፍ የሚል አይደለም፡፡ ‘እቅቲዳኡ ሲራጦል ሙስተቂም’ ከተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ መውሊድ የሚያወጡ ሰዎች ‘አንድም ከክርስቲያኖች ጋር ለመመሳሰል፣ አለበለዚያም ለነብዩ ፍቅር ነይተው የነብዩን ፍቅር ሊያስቡ ይችላሉ’ ካሉ በኋላ ‘ለነብዩ ባላቸው ፍቅር በድርጊታቸው አጅር (ምንዳ) ያገኛሉ’ ሲሉ ይደመድማሉ፡፡” [መውሊድ፡ 93-94]

አድበስብሶ ያቀረበው የኢብኑ ተይሚያ ንግግር ይሄውና፦
وكذلك ما يحدثه بعض الناس، إما مضاهاة للنصارى في ميلاد عيسى عليه السلام، وإما محبة للنبي ﷺ، وتعظيمًا. والله قد يثيبهم على هذه المحبة والاجتهاد، لا على البدع- من اتخاذ مولد النبي صلى الله عليه وسلم عيدًا.
“ልክ እንደዚሁ በዒሳ ዐለይሂ ሰላም ልደት ከክርስቲያኖች ጋር ለመፎካከር ሲሉ ወይም ደግሞ ነብዩን ﷺ ለመውደድና ለማክበር ሲሉ አንዳንዶች የሚፈጥሩትም ከዚሁ ነው። አላህ በዚህ (ለሳቸው) ባላቸው ውዴታና ጥረት ሊመነዳቸው ይችላል። የነብዩን ﷺ ልደት በዓል አድርገው በያዙበት በቢድዐው ግን አይደለም!”
ልብ በሉ! ተግባሩን ቢድዐ እንደሆነ ገልፀዋል። ሁለተኛ ምናልባት ለነብዩ ﷺ ባላቸው ውዴታና ጥረት ቢሆን እንጂ በመውሊድ ቢድዐ አጅር አያገኙም ነው ያሉት። እንጂ ተግባሩ የተወገዘ እንደሆነ ደጋግመው አስረግጠዋል።

ሌላም ቦታ ከዚሁ ጋር የሚቀራረብ እንዲህ የሚል ንግግር አላቸው፡-
فتعظيم المولد، واتخاذه موسمًا، قد يفعله بعض الناس، ويكون له فيه أجر عظيم لحسن قصده، وتعظيمه لرسول الله ﷺ، كما قدمته لك أنه يحسن من بعض الناس، ما يستقبح من المؤمن المسدد.
“መውሊድን ማላቅና ህዝባዊ በዓል አድርጎ መያዝ አንዳንድ ሰው በጥሩ ኒያና የአላህ መልእክተኛን ﷺ በማላቁ ሲሰራው ምንዳ ሊኖረው ይችላል። እንዳሳለፍኩልህ የተቃና አማኝ ቢያደርገው #የሚያስፀይፍ የሆነ ነገር አንዳዱ ሰው ጋር ግን እንደ በጎ ይቆጠራል።”

ንግግራቸውን በጥሞና ላስተዋለ መውሊድ ከሳቸው ዘንድ ፀያፍ እንደሆነ በቀላሉ ይደርስበታል፡፡ ምንዳ እንደሚያገኝ የተናገሩት የድርጊቱን ጥፋትነት ለማያውቅ ነው፡፡ ያውም በጥሩ ኒያውና በውስጡ ባሉ ሸሪዐዊ ተግባራት እንጂ በቢድዐው አጅር ያገኛል አላሉም። ቢድዐውንማ ደጋግመው ኮንነውታልኮ! ለምሳሌ ያህል፡

1- ከመጀመሪያው ንግግራቸው አያይዘው እንዲህ ይላሉ፡-

“ሰዎች በልደት ቀናቸው ላይ ከመወዛገባቸው ጋር። በጎ ቢሆን እንዲሰራ የሚያደርገው ሁኔታ ከመኖሩና ከልካይ ነገር ካለመኖሩም ጋር ሰለፎች ግን ይህንን አልሰሩትም። ይሄ ሙሉ ለሙሉ ወይም ሚዛን በሚደፋ መልኩ በጎ ቢሆን ኖሮ ሰለፎች ረዲየላሁ ዐንሁም ከኛ ይልቅ ለሱ የተገቡ ነበሩ። ምክንያቱም ለአላህ መልእክተኛ ﷺ ከኛ የበለጠ ወዳጆችና አክባሪዎች ነበሩና። እነሱ በመልካም ነገር ላይ ይበልጥ የጓጉ ነበሩ። በተሟላ መልኩ እሳቸውን መውደድና ማላቅ የሚገኘው እሳቸውን በመከታተል፣ በመታዘዝና ነገራቸውን በመከተል፣ በስውርም በግልፅም ፈለጋቸውን ሕያው በማድረግ፣ የተላኩበትን በማሰራጨትና በልብም በእጅም በምላስም በዚህ ላይ በመታገል ነው። ይህቺ ናት ከሙሃጂሮችና ከአንሷሮች የሆኑት እነሱንም በመልካም የተከተሉት የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች መንገድ። [ኢቅቲዳኡ ሲራጢል ሙስተቂም፡ 2/115-116፣ 123-126]

2- በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፡-
“በዓላት ከሃይማኖታዊ ድንጋጌዎች ውስጥ አንድ ድንጋጌ ናቸው። ስለሆነም በነሱ ላይ አዲስ መፍጠር ሳይሆን መረጃን መከተል የግድ ይላል። ለነብዩ ﷺ በተለያዩ ቀናት የተፈፀሙ ኹጥባዎች፣ ቃል-ኪዳኖችና ጦርነቶች አሏቸው። ለምሳሌ የበድር ጦርነት፣ የሑነይን፣ የኸንደቅ ጦርነት፣ የመካ መከፈት፣ የስደታቸው ጊዜ፣ መዲና መግባታቸው፣ የዲን መሰረቶችን ያወሱባቸው በርካታ ድስኩሮች አሏቸው። ይሁን እንጂ ይሄ እንዲህ አይነት ቀናትን በዓላት አድርገው እንዲይዙ አላስገደደም። እንዲህ አይነቱን የሚሰሩት ክርስቲያኖች ናቸው። የዒሳ የተለያዩ ክስተቶች የተፈፀሙባቸውን ቀናት በዓላት አድርገው የሚይዙ የሆኑት። ወይም ደግሞ የሁ .ዶች ናቸው (እንዲህ አይነቱን የሚሰሩት።) ዒድ ሸሪዐ ነው። አላህ የደነገገውን ሊከተሉት ይገባል። ያለበለዚያ ግን ከዲን ያልሆነ ነገር በዲን ውስጥ አይፈጠርም።”

3. ሌላም እንዲህ የሚል ንግግር አላቸው፡-
“በዚህ ርእስ ስር መጥፎ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ ሌሎቹ በዓላትና ቢድዐዊ የሆኑት ዓውደ-አመታት ናቸው” ካሉ በኋላ ዘለግ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። [አልኢቅቲዳእ፡ 2/81-82]

4. የኢብኑ ተይሚያ ንግግር እየቆራረጡና እየቀጣጠሉ የሚንጠላጠሉ አካላትን ይበልጥ ወሽመጣቸውን መቁረጥ አስፈላጊ ስለሆነ ሌላም የሸይኹን ንግግር ልጨምር። በያመቱ የነብዩ ﷺ መውሊድ ሌሊት ላይ ኺትማ ስለሚያደርግ ሰው “ይሄ የተወደደ ነው ወይስ አይደለም?” ተብለው ተጠይቀው እንዲህ ብለው ነበር የመለሱት፡-
وَأَمَّا اتِّخَاذُ مَوْسِمٍ غَيْرِ الْمَوَاسِمِ الشَّرْعِيَّةِ كَبَعْضِ لَيَالِي شَهْرِ رَبِيعٍ الْأَوَّلِ الَّتِي يُقَالُ: إنَّهَا لَيْلَةُ الْمَوْلِدِ أَوْ بَعْضِ لَيَالِيِ رَجبٍ أَوْ ثَامِنَ عَشَرَ ذِي الْحِجةِ أَوْ أَوَّلِ جمْعَةٍ مِنْ رَجبٍ أَوْ ثَامِنِ شَوَّالٍ الَّذِي يُسَمِّيهِ الْجهَّالُ عِيدَ الْأَبْرَارِ فَإِنَّهَا مِنْ الْبِدَعِ الَّتِي لَمْ يَسْتَحِبَّهَا السَّلَفُ وَلَمْ يَفْعَلُوهَا.
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
“ሸሪዐዊ ያልሆኑ ክብረ በዓላትን ክብረ-በዓል አድርጎ መያዝ ግን ‘የመውሊድ ሌሊት’ የሚባሉትን የተወሰኑ የረቢዐል አወል ሌሊቶችን ወይም የረጀብ ሌሊቶችን ወይም ደግሞ ዙልሒጃ አስራ ስምንትን ወይም ደግሞ የረጀብ የመጀመሪያ ጁሙዐን ወይም ደግሞ መሃይማን ‘የደጋጎች ዒድ’ እያሉ የሚጠሩትን ሸዋል ስምንትን የመሰሉ እነዚህ ሰለፎች እንደሚወደዱ ያልገለጿቸውና ያልተገበሯቸው ቢድዐዎች ውስጥ ናቸው።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 25/298]

5. ሌላም ልጨምር፡-
“… የሆኑ ሰዎች ልክ እንደ መደበኛ ሱናዎች ቋሚ ልምድ አድርገው ሳይዙ በሆኑ ሌሊቶች ግዴታ ላልሆነ ሶላት ቢሰባሰቡ ይሄ አይጠላም። ነገር ግን ወቅት በዞረ ቁጥር አብሮ የሚዞር ልምድ አድርጎ መያዙ የተጠላ ነው። ሸሪዐን መቀየር እንዲሁም የተደነገገውን ካልተደነገገው ጋር ማመሳሰል አለውና። እንዲህ አይነቱ ቢፈቀድ ኖሮ በረፋድ ወቅት ወይም በዙህርና በዐስር መካከል ሌላ ሶላት እንዲፈፀም ወይም በሸዕባን ተራዊሕ እንዲኖር ወይም በሁለቱ የዒድ ሶላቶች ላይ አዛን እንዲኖር ወይም ደግሞ በበይተል መቅዲስ ካለው ቋጥኝ ዘንድ ሐጅ እንዲኖር መፍቀድ ነበር። ይሄ የአላህን ዲን መቀየርና መለወጥ ነው። በመውሊድ ሌሊትና በሌሎችም ላይ ልክ እንዲሁ ነው የሚባለው።”
ከምን አይነት ጥፋቶች ጋር አብረው እንደቆጠሩት ተመልከቱ። ቀጠሉ፡-
“የተጠላ ቢድዐ ማለት በሸሪዐው እንደሚወደድ ያልተገለፀ ሲሆን እሱም አላህ ያልፈቀደበትን መደንገጉ ነው። የሆነን ነገር ከአላህ ድንጋጌ ሳይኖር ዲንና መቃረቢያ ያደረገ ሰው ጠማማ ሙብተዲዕ ነው። እሱን ነው ነብዩ ﷺ ‘ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው’ ሲሉ የገለፁት። ፈጠራ የድንጋጌ ተቃራኒ ነው። ድንጋጌ ማለት ግዴታ በሆነ ትእዛዝ ወይም ተወዳጅ መሆንን በሚያመልክት ትእዛዝ አላህና መልእክተኛው ያዘዙት ነው። ልክ ለተራዊሕ በአንድ ኢማም እንደመሰባሰብ፣ ቁርኣንን በአንድ መፅሐፍ መሰብሰብ፣ አፈንጋጮችንና ኸዋሪጆችን እንደመዋጋት ያለና ይህን የመሳሰለ በሳቸው ዘመን ያልተፈፀመ ነገር ቢሆን እንኳን። አላህና መልእክተኛው ያልደነገጉት እርሱ ፈጠራ ነው፣ ጥመት። ለምሳሌ ልክ የሶላት ወቅቶችን፣ የጁሙዐና የበዓላት ቀናትን ደንጋጊው እንደወሰነው በሱ ውስጥ ለዒባዳ በመሰባሰብ የሆነን ቦታ ወይም የሆነን ጊዜ ለይቶ እንደ መያዝ ማለት ነው።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 23/133-134]

6. መጤ የሆኑ በዓላትን በጅምላ የሚኮንኑባቸው ሌሎች ንግግሮችም አሏቸው። [አልኢቅቲዷእ፡ 2/115] [አልሙስተድረክ ዐላመጅሙዒል ፈታዋ፡ 3/132]

ከዚህ በኋላስ ኢብኑ ተይሚያን ለመውሊድ ለማጣቀስ ድፍረት ይኖራችሁ ይሆን? ለነገሩ ካፈርኩ አይመልሰኝ ነው የያዛችሁት። መቼስ የስሜትን ፈረስ በማስረጃ ልጓም መግታት አይቻል ነገር።

ደግሞም ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ደግፈውስ ቢሆን ኖሮ? ቅንጣት ታክል የሚቀይረው ነገር የለም። ለማንም ያለን አክብሮት ስህተቱን እንድንቀበል አያደርገንም። መውሊድ ኢብኑ ተይሚያ የደገፉትና የፈፀሙት ቢሆን እንኳ ኖሮ ከቢድዐነት የሚወጣ አልነበረም። አያይዤ የማነሳው ተግባሩ ቢድዐ መሆኑን ያላወቀ ሰው በቢድዐው ሳይሆን በኒያው አጅር ያገኛል የሚለው የኢብኑ ተይሚያ ንግግርም ውድቅ ነው። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ውድቅ ነው” ብለዋልና። [ሙስሊም፡ 1718] ራሳቸው ኢብኑ ተይሚያ ይህንን ደጋግመው ገልፀውታል። መጥፎ ስራ በመልካም ኒያ አጅር አያስገኝም። መልካም ኒያ መጥፎ ስራን መልካም አያደርግም። ሶሐቢዩ ኢብኑ ዑመርም - ረዲየሏሁ ዐንሁ - “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፣ ሰዎች መልካም ነው ብለው ቢያስቡትም” ብለዋል፡፡ [አልኢባናህ፡ 205] ታላቁ ሰለፍ የሕያ ብኑ የሕያ “ሱና ባልሆነ ነገር ውስጥ ተስፋና ምንዳ የለም” ብለዋል። [አልኢዕቲሷም፡ 1/199]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
ዐረብ ሃገር ያሉ እህቶቻችንን በሰበብ አስባብ በነገር የሚወጉ ሰዎች አሉ። ወንድሜ! የዐረብ ሃገር ሴት አገር በጀርባዋ የተሸከመች ባለ ውለታ ነች። የምታዝንላት እንጂ የምታብጠለጥላት አይደለችም። ደሟን፣ ላቧን ሰጥታ ለሃገር ለወገን የምትኖር ናት። ሻማ ሆነው ቀልጠው ለሌሎች የሚኖሩ አሳዛኝ ወገኖች ናቸው። ለቤተሰብ ሲሉ የራሳቸውን ህይወት ፊዳ ያደረጉ ምስኪኖች ናቸው። ቤት መስርቶ ለመኖር፣ ወልዶ ለመክበድ ባላቸው ጉጉት ባመኑት ተኩላ የሚበሉ የዋሆች ናቸው። ሰርቶ የማይለወጥ፣ ወስዶ የማይጠረቃ ወንድም እየጎተጎታቸው ለፍተው መና የሚቀሩት ብዙ ናቸው። አያሳዝኑም ታዲያ?

ደግሞም ብዙዎቹ እህቶች ባለቻቸው ጊዜ ዲናቸውን እየተማሩ ከሺርክ፣ ከቢድዐ፣ ከብዙ ሐራም ነገሮች የወጡ ናቸው። ባሉበትም ይሁን በሃገር ቤት ባሉ የኸይር ስራ ጥሪዎች ላይ ግንባር ቀደም ተሰላፊዎች ናቸው። አዎ! ሰዎች ናቸውና ያውም ብዙዎቹ ወጣቶች ናቸውና መሀላቸው ብዙ ክፍተቶች ያሉባቸው ሊታዩ ይችላሉ። ግን ማነው ከዚህ ነፃ የሆነው? ምን ሲባልስ ነው በጅምላ የሚፈረጁት? አላህ ስብራታቸውን ጠግኖ፣ ክፍተታቸውን ሞልቶ ለሃገር ለቤታቸው የሚበቁ ያድርጋቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድቤ መደብደብ
የለውም አደብ
~

በዚክርና በሶላት ወቅት ማጨብጨብ፣ ፉጨት፣ ማናፋት፣ መዝለል፣ ማቃሰት፣... የሙሽ ^ሪኮች ተግባር ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-

{ وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَیۡتِ إِلَّا مُكَاۤءࣰ وَتَصۡدِیَةࣰۚ }
{በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አልአንፋል፡ 35]

የሙስሊሞች ዚክር እና ሶለዋት ከዚህ ይለያል። እንዲህ ይላል:-

{ وَٱذۡكُر رَّبَّكَ فِی نَفۡسِكَ تَضَرُّعࣰا وَخِیفَةࣰ وَدُونَ ٱلۡجَهۡرِ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ بِٱلۡغُدُوِّ وَٱلۡـَٔاصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡغَـٰفِلِینَ }
''ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በሆነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው። ከዘንጊዎቹም አትኹን።" [አልአዕራፍ፡ 205]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
2025/09/13 17:19:16
Back to Top
HTML Embed Code: