Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
*የዱንያ ነገር!!*
~
ዐሊይ ብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–
"አምሳያ ያላገኘሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ደህይቶ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።
★ አልሐሰን ብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ሀብታም ሆኖ ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቼዋለሁ።"
||
ሱብሓነላህ!!
ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
♣️ ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
♣️ ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
♣️ ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍ .ጫፊ አረ .መኔ አለም ጠብባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።
® ይቺው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
♣️ በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
♣️ ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –
(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)
"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]
|||
ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ኢላሂ ልብ ስጠን!
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሽንት ቤትስ አንተ ነበርክ የምትሄድለት ወይስ እራሱ ነበር የሚሄደው?
በሱፊያ ኮተት የተጠለፋችሁ ወጣቶች ሆይ! እባካችሁን ጭንቅላታችሁን ለነዚህ ሰዎች አሳልፋችሁ አትስጡ። ተው አስተውሉ! የማንም መቀለጃ አትሁኑ። እንዴት ወደ ህክምና ቦታ መሄድ የነበረባቸው ሰዎች መጫወቻ ትሆናላችሁ? ግዴላችሁም ንቁ።
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
በሱፊያ ኮተት የተጠለፋችሁ ወጣቶች ሆይ! እባካችሁን ጭንቅላታችሁን ለነዚህ ሰዎች አሳልፋችሁ አትስጡ። ተው አስተውሉ! የማንም መቀለጃ አትሁኑ። እንዴት ወደ ህክምና ቦታ መሄድ የነበረባቸው ሰዎች መጫወቻ ትሆናላችሁ? ግዴላችሁም ንቁ።
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
أفْضَلُ الأعمالِ إِدخالُ السرورِ على المؤمِن؛ كسوتَ عورَتَه، وأَشبعتَ جوعتَهُ، أو قَضَيْتَ له حاجةً
“ከስራዎች ሁሉ በላጩ አንድን አማኝ ማስደሰት ነው። ይህም ነውሩን በመሸፈን፣ ረሃቡን በማብላት ወይም ጉዳዩን በመፈፀም ነው።”
አልባኒይ ሶሒሕ ነው ብለውታል። [አት-ተርጊብ፡ 2090]

የማንም ክብር ከተውሒድ በላይ አይደለም!
~
ከመካ በላይ ክቡር ቦታ የለም። ግና ነብዩ ﷺ እና ሶሐቦቻቸው ለተውሒድ ሲባል መካን ጥለው ተሰደዋል። ዝምድና ትልቅ ቦታ እንዳለው የሚታወቅ ነው። ግን ከተውሒድ በላይ ስላልሆነ ነው ነብዩ ﷺ ከአጎታቸው አቡ ለሀብ እና መሰል ዘመዶቻቸው ጋር መፋጠጣቸው። ዘርና ጎሳ ከተውሒድ በላይ አይደለም። ለዚያም ነው ከቁረይሽ ጋር በሰይፍ መሞሻለቃቸው። አንድነት ትልቅ የኢስላም እሴት ነው። ተውሒድን ገሸሽ ያደረገ አንድነት ከንቱ ስለሆነ ነው ነብዩ ﷺ "ሙሐመድ ህዝብ ለያየ" የተባሉት። ደግሞም የእውነትም ልዩነት ፈጥረዋል። በተውሒድና በሺርክ ሰበብ የተፈጠረ ስንጥቃት በዘርና በጎሳ ሽቦ አይጠገንም።
ተውሒድ የአላህ ሐቅ ነው። የአላህ ሐቅ ከነብያትም ከመላእክትም ክብርና ሐቅ በላይ ነው። ለዒሳ ያለንን አክብሮት ዒሳን በማምለክ እንደማንገልፀው ሁሉ ለሙሐመድ ያለንንም አክብሮት እሳቸውን በማምለክ አንገልፀውም። ዒሳን ማምለክ አይገባም ማለት ዒሳን መሳደብ እንዳልሆነው ሁሉ የቃጥባሬውን ዒሳን ማምለክ አይገባም ማለትም ስድብ ተብሎ ሊተረጎም አይገባም። የሁለቱ ደረጃ የተራራቀ ከመሆኑ ጋር።
የአንዳንዱ ግንዛቤ በጣም የተዛነፈ ነው። ክርስቲያኖች እንደሚያደርጉት ነብዩላህ ዒሳን፣ መርየምን፣ መልአኩ ጂብሪል (ገብርኤልን)፣ ሚካኢልን፣ ... ማምለክ አይቻልም ሲባል ወገኖቻችን እነዚህን ደጋጎች እየሰደባችሁ ነው አይሉም። ቃጥባሬን፣ አብሬትን፣ አልከሶን፣ ኑራሑሴንን፣ ጂላኒን፣ ዐሊ ጎንደርን፣ ደገርን፣ ጫሊን፣ ገታን፣ መጂትን፣ ነጃሺን ፣ አባድርን፣ ... ማምለክ አይቻልም ሲባል ግን "ወሊዮችን ሰደባችሁ" የሚል ክስ ያነሳሉ። እነ ዒሳ፣ እነ መርየም'ኮ እናንተ ከምትጠሯቸው ይበልጣሉ። እነሱን አታምልኩ ማለት ስድብ ሳይሆን እንዴት ነው ከነሱ በታች የሆኑ ወሊዮችን አታምልኩ ማለት ስድብ የሚሆነው?
በማርያም መማል ካልተቻለ በጂላኒ መማል አይገባም ሲባል ለምን ይጎረብጥሃል? "ገብርኤል ማረኝ"፣ "ሚካኤል ተከተለኝ" ማለት ካልተቻለ እንዴት አባድር፣ ጂላኒ ድረሱልኝ ማለት ይቻላል? የሺርክ ቡላና ዳለቻ አለው ወይ? ዒሳም፣ ሙሐመድም፣ ሌሎች ክቡራን ነብያትም (ሰላም በሁሉም ላይ ይሁን)፣ እንደ ኣሲያ፣ መርየም፣ ኸዲጃ፣ ዓኢሻ፣ ፋጢማ፣ እንዲሁም እንደ አቡበክር፣ ዑመር፣ ... ያሉ ደጋጎችም ዝናብ አይሰጡም። ለችግር አይደርሱም። ከመከራ አያወጡም። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፡-
{أَمَّن یُجِیبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَیَكۡشِفُ ٱلسُّوۤءَ وَیَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَاۤءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَـٰهࣱ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِیلࣰا مَّا تَذَكَّرُونَ}
{ወይስ ያ ችግረኛ በለመነው ጊዜ መልስ የሚሰጥ፣ ክፉንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት?) (ይህን የሚያደርግ) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለ ወይ?! ጥቂትን እንጂ አትገሰፁም!} [አነምል፡ 62]
ይህንን ማድረግ የሚችለው አንድ አምላክ ብቻ ነው። ይህንን የሚያደርግ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለ ወይ?! እኮ ማን?!
ፅሁፌን ብዙዎች በሚያመልኳቸው ጂላኒይ ንግግር እቋጫለሁ። እንዲህ ይላሉ፡-
“አንተ ችግርህን ለፍጡር የምታቀርበው ሆይ! ወደማይጠቅምህና ወደማይጎዳህ ፍጡር አቤት ማለትህ ምን ይፈይድሃል?! ብተመካባቸውና በጌታህ ሐቅ ላይ ብታጋራቸው ያርቁሃል። ከሱ ቁጣ ላይም ይጥሉሃል። … አንተ መሀይም! ፍጡርን በመማፀንህ ግልግልን እየተመኘህ አውቃለሁ ብለህ ትሞግታለህ!! … ወዮልህ! አላህ ከማንም የበለጠ ቅርብህ ሆኖ ሳለ ከሱ ሌላ ስትከጅል አታፍርም?!” [አልፈትሑ ረባኒይ ወልፈይዱ ረሕማኒይ፡ 117-118]
አታፍርም ወይ?! እፈር እንጂ!
=
የቴሌግራም ቻናል:-

ዐቅላችን ዐቅል እንዳያስተን
~
ዐቅል አላህ ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቅ ስጦታ ነው። የሰው ልጅ በዐቅል ያመዛዝናል፣ ያገናዝባል። ይሁን እንጂ ዐቅል በወሕይ ካልታገዘ ደካማ ነው። ስለዚህ ከዐቅል ይልቅ ቀዳሚው ወሕይ ነው፣ ቁርኣንና ሶሒሕ ሐዲሥ። ዐቅልን ፈራጅ ቀዳጅ ማድረግ እና ከወሕይ በላይ ማንገስ ዐቅልን ጣዖት አድርጎ መያዝ ነው የሚሆነው። ሸሪዐዊ ማስረጃን ገሸሽ በማድረግ "እኔኮ ዐቅል አለኝ፤ ሁሉንም በራሴ ነው የምወስነው" አይነት ልክፍት ከተሰማህ በራስ መኮፈስ፣ ዐቅልን ማምለክ ውስጥ ገብተሃል። ይሄ በዐቂዳ ጉዳይ ላይ ዐቅልን እናስቀድማለን የሚሉት የአሻዒራና የማቱሪዲያ ቡድኖች የወደቁበት ጥፋት ነው። ከዐቅል ጋር አይገጥሙም በሚል ሃሰተኛ ምክንያት ቁርኣንና ሐዲሥን በመግፋት የአላህን ሲፋት ሲያስተባብሉ ይታያሉ። ሌሎች በቀደዱላቸው እየፈሰሱ እንጂ ከዐቅል ጋር የማይሄደው የነሱ ፍልስፍና ነው።
በተጨማሪም ዛሬ ዛሬ አካዳሚ ትምህርት ገፋ ያደረጉ አንዳንድ አካላት ዐቅልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የሸሪዐ ጉዳዮች ላይ አፈንጋጭ አቋሞችን የሚያራምዱበት ሁኔታ አለ። አንዳንዶች የትምህርት ማእረጋቸው ብቅል ሆኖ ይፈትናቸዋል። አካዳሚ ስለተማሩ ብቻ ያላቅማቸው በየዘርፉ ጥልቅ የሚሉ የ'ርጎ ዝንብ ይሆናሉ። እየውልህማ አባኪያ!
1. ዐቅል በቂ ቢሆን ኖሮ ነብይ አይላክም ነበር። ነብይ የሚላከው ሰዎች የማያውቁትን መለኮታዊ ነገር ለማስተማር ነው።
2. ዐቅል በቂ ቢሆን ኖሮ ቁርኣን ባልወረደ ነበር። በዐቅል ብቻ ሌላው ህዝብ ቀርቶ ነብያችን ﷺ እንኳ የኢማንን ዝርዝር አያውቁም ነበር። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَكَذَ ٰلِكَ أَوۡحَیۡنَاۤ إِلَیۡكَ رُوحࣰا مِّنۡ أَمۡرِنَاۚ مَا كُنتَ تَدۡرِی مَا ٱلۡكِتَـٰبُ وَلَا ٱلۡإِیمَـٰنُ وَلَـٰكِن جَعَلۡنَـٰهُ نُورࣰا نَّهۡدِی بِهِۦ }
"እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲሆን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡" [አሹራ፡ 52]
3. ዐቅል ልክ እንደሌሎች የስሜት ህዋሳት ወሰን (limit) አለው። ጆሮ ድምፅ በራቀው ቁጥር መስማቱ እየቀነሰ እየቀነሰ ሄዶ መጨረሻ ላይ ይጠፋበታል። አይን ካጠገቡ ያለ ነገር በራቀ ቁጥር እያነሰ ሄዶ ከነ ጭራሹ ከእይታ ይሰወርበታል። አእምሮም እንደዚያው ነው። ሁሉን ነገር የመረዳት አቅም የለውም።
4. ዐቅል ከስህተትና ከጉድለት ፍፁም አይደለም። "ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት " የሚባለው ያለ ምክንያት አይደለም። ፍፁም የሆነው ማስረጃ ወሕይ ነው፣ መለኮታዊ ራእይ። ዐቅል በኋላ ታሪክ፣ በአስተዳደግ፣ በትምህርት፣ በልማድ፣ በአካባቢ፣ ... ተፅእኖ ስር ይወድቃል። በዚህ የተነሳ ነው አረዳዳችን የሚራራቀው። ይህም እውነታ ዐቅል ወጥ የሆነ መለኪያ እንደሌለው ያሳያል። ወጥ ቢሆን ኖሮ በህንድ ፍልስፍና፣ በግሪክ፣ በሮማ፣ በፋርስ፣ በቻይና፣ እንዲሁም በዛሬው የምእራቡ ዓለም እና በምስራቁ ዓለም ፍልስፍናዎች መካከል ልዩነቶች ባልተንፀባረቁ ነበር። የነዚህ ሃገራት ፈላስፎችም ለተውሒድ በተመሩ ነበር።.
5. ዐቅል አጥጋቢ መለኪያ ቢኖረው ኖሮ ዐቅልን እንከተላለን የሚሉት ጀህሚያዎች፣ ሙዕተዚላዎች፣ አሻዒሪዎችና ማቱሪዲያዎች ባልተለያዩ ነበር። ዐቅል በቂ አጥጋቢ መለኪያ ቢሆን ኖሮ ሌላው ቀርቶ በአንድ ቡድን ውስጥ እንኳ መለያየት ባልኖረ ነበር። አሻዒራን እንውሰድ። ሙፈዊዳ እና ሙአዊላ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ። ሁለቱ ተቃራኒ መንገዶች ናቸው። በሌላ በኩል የቀደሙት አሻዒራዎች የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ጨምሮ በርካታ የአላህን ሲፋት ያፀድቃሉ። የኋለኞቹ ያስተባብላሉ። ወደ ግለሰብ ዝርዝር ብንገባ ደግሞ ልዩነቱ ይሰፋል።
6. ዐቅል አስተማማኝ መለኪያ ቢሆን ኖሮ ግለሰቦች ከአንድ አቋም ወደ ሌላ ባልተገላበጡ ወይም በተለያዩ ከታቦቻቸው ላይ የተለያዩ አቋሞችን ባላንፀባረቁ ነበር። ኢብኑል ጀውዚን ምሳሌ መውሰድ ይቻላል። አንዴ ተእዊል፣ አንዴ ኢሥባት፣ ሌላ ጊዜ ተፍዊድ ላይ ተወዛውዘዋል።
7. ዐቅል በቂ መለኪያ ቢሆን ኖሮ በዐለም አቀፍ ደረጃ ፖለቲከኞች እና ኢኮኖሚስቶች ወጥና የጋራ መስመር መንደፍ በቻሉ ነበር። እውነታው ግን ሌላ ነው። የካፒታሊዝምና የሶሻሊዝም ፍጥጫ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። በሀገራችንም በ1960ዎቹ እና ሰባዎቹ እንደ አሸን የፈሉ የፖለቲካ ቡድኖች ሁሉም ለማለት በሚቀርብ ሶሻሊስቶች ነበሩ። ነገር ግን መማራቸውም ዐቅላቸውም ያላግባባቸው የሚጠፋፉ ቡድኖች ነበሩ።
ስለዚህ በዐቅል እያመሀኙ ከቁርኣንና ሐዲሥ ማስረጃዎች መራቅ ከራሱ ከዐቅል ጭምር መራቅ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ሲጀመር ጤነኛ ዐቅል ከትክክለኛ ወሕይ ጋር አይጋጭም። ስለሆነም ለወሕይ እጅ ለመስጠት መድረቅረቅ አይገባም። በዚህ ረገድ የኢማን የስኬት ማማ ላይ የደረሱትን የሰለፎችን አቋም እንመልከት፦
1. ዑመር ብኑል ኸጣብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
إياكم وأصحاب الرأي، فإنهم أعداء السنن، أعيتهم الأحاديث أن يحفظوها فقالوا بالرأي، فضلوا وأضلوا
“ከአስተያየት ባለቤቶች ተጠንቀቁ። ምክንያቱም እነሱ የሱና ጠላቶች ናቸው። ሐዲሦችን መያዝ ስለተሳናቸው በራሳቸው አስተያየት ወሰኑ፣ በመሆኑም እነሱም ጠመሙ፣ ሌሎችንም አጠመሙ።” [ኡሱል አል-ኢዕቲቃድ፣ አላለካኢይ፡ 57]
2. ዐሊይ ብኑ አቢ ጣሊብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
لو كان الدينُ بالرأي لكان أسفلُ الخفِّ أولَى بالمسحِ من أعلاهُ ، وقد رأيتُ رسولَ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلم يمسحُ على ظاهرِ خفَّيهِ
“ሃይማኖት በራስ አስተያየት የሚመራ ቢሆን ኖሮ፣ የጫማ ታችኛው ክፍል ከላይኛው ክፍል ይልቅ ለማበስ ቅድሚያ ይኖረው ነበር። ነገር ግን የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የጫማቸውን የላይኛው ክፍል ሲያብሱ ነው ያየሁት።” [አቡ ዳውድ፡ 162]
ስለዚህ የመፍትሄው ቁልፍ አቅምን ማወቅ ነው። ነፍሲያን መርገጥ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 22/1447)

ጥቂት ስለ ሰሞንኛው የሙዚቃ ግርግር
~
ሙዚቃ በተለይ በዚህ ዘመን በጣም ብዙ ነገር ነው አጭቆ የያዘው። አብዛኛው ይዘቱ የሴትን ልጅ አማላይ አካላዊ ገፅታ በመዘርዘር ላይ ያነጣጠረ ፆታዊ ቅስቀሳ ያዘለ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ሴቷ ስለ ወንዱ ስትዘፍንም እንዲሁ። ከዚያ ባሻገር ሙዚቃ ሃይማኖት አለበት። አድባሩ፣ ደብሩ፣ ገዳማቱ፣ "ቅዱሳኑ"፣ መፅሀፍ "ቅዱሳዊ" ይዘቶች፣ ወዘተ. እምነታዊ እሴቶች በሰፊው ይገኙበታል። ግጥሞቹ በአመዛኙ ጤነኛ አይደሉም። እንኳን ዘፈን ላይ ያለው እንዲሁ በሌጣውም ግጥም ብዙ ኮተት አለበት። (ሁሉንም እያልኩ አይደለም።) ያለ ምክንያት አይደለም አላህ እንዲህ ማለቱ፦
{ وَٱلشُّعَرَاۤءُ یَتَّبِعُهُمُ ٱلۡغَاوُۥنَ (224) أَلَمۡ تَرَ أَنَّهُمۡ فِی كُلِّ وَادࣲ یَهِیمُونَ (225) وَأَنَّهُمۡ یَقُولُونَ مَا لَا یَفۡعَلُونَ (226) }
"ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሏቸዋል። እነርሱ በ(ንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መሆናቸውን አታይምን? እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መሆናቸውን (አታይምን)?" [አሹ0ራእ፡ 224-226]
ሙዚቃን መፍቀድ ሙዚቃን ከማዳመጥ የከፋ ጥፋት ነው። በዚህ ረገድ ሆ ብሎ የተቆጣው ወገናችን አጉል ስልጡን ስልጡን ከሚሰራራቸው አካላት የተሻለ የዲን መቆርቆር፣ የበለጠ የሞራል ከፍታ እንዳለው በተግባር አሳይቷል። "መንጋ" ብለው ሊያጣጥሉት የሞከሩት የእውነት መንጋዎቹ እነሱ ናቸው። የቁርኣን አንቀፆችን፣ ሶሒሕ ሐዲሦችን፣ ህልቆ መሳፍርት የዑለማእ ንግግሮችን የተከተለ ነው ይሄኛው ''መንጋ"።
በተቃራኒው የቆመውስ መንጋ? ከዲኑ ክብር ይልቅ ለአንድ የተቃወመውን ሁሉ "ሴት" እያለ ለሚያጣጥል፣ በትእቢት ለተሞላ attention seeker ነው ሽንጣቸውን ገትረው እየተሟገቱ ያሉት። የክፋታቸው ክፋት የተቃውሞውን ድምፅ ለመበተን "የመዳ .ኺላ ተቃውሞ" እያሉ መቀባበላቸው ነው። ይሄ በተደጋጋሚ ድምፅ ለመበተን የሚጠቀሙት ስልት ነው። ጉዳዩ የቡድን ጉዳይ እንዳልሆነ ግልፅ ነው።
ደግሞ "ለምን አትወያዩትም?" ይላሉ። የሚገርመው ከፊሎቹ ሙዚቃ ሐራም ነው እያሉ ነው "ለምን አትወያዩትም?" የሚሉት። እናንተ ለምን አትወያዩትም? ነው ወይስ የህዝቡ ጩኸት አስፈርቷችሁ እንጂ የአቋሙ ተጋሪ ናችሁ? ለማንኛውም ልጁ ፈፅሞ ሊወያዩት የሚገባ አይደለም። ለምን?
* አንደኛ :- ትኩረት ነው የፈለገው። ችግሩ የግርታ ቢሆን ከአንድ ዓሊም ጋር ተጠግቶ ብዥታውን ማጥራት ይችል ነበር።
* ሁለተኛ :- ሰውየው ቀ .ጣ .ፊ ነው። የተቃወሙትን በጅምላ ትምህርት ሐራም የሚሉ፣ ቴሌቪዥን ሐራም የሚሉ፣ ... እያለ መግለፁ ለዚህ ማሳያ ነው። የተቃወመው አንድ ቡድን ነው ወይስ ሰፊው ህዝብ? ይሄ ምን ያህል መ .ሰሪ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
* ሶስተኛ :- የተቃወሙትን ሁሉ " ... ኩሉ ጀምዒን ሙአነሡ" እያለ "ሴቶች ናቸው" እያለ የሚያጣጥል በትእ ^ቢት የተወ .ጠረ ዋ .ል ^ጌ ነው። ከእንዲህ አይነት ሰው ጋር መወያየት እጅግ የተሳሳተ አካሄድ ነው። ድንገት ያሰባችሁ ካላችሁም ፈፅሞ እንዳታደርጉት። ከሱ ጋር ቀርባችሁ እንዳትግማሙ።
* አራተኛ :- የዘፈን ሐራምነት ለሰፊው ህዝብ ሲበዛ ግልፅ ነው። ታዲያ ምን ለማትረፍ ነው ውይይቱ? እናንተ ግር ካላችሁ ወይ በአራቱም አቅጣጫ ሂዳችሁ ያገኛችሁትን ዓሊም ጠይቁ። ካልሆነ ከሱው ጋር ሂዱና ተጨቃጨቁ። "አይ ለሱ እንዲመለስ አስበን ነው" ካላችሁ ወላሂ ይሄ ውሸት ነው። በንቀት የሚያንኳስሳቸውን ሰዎች ነው እንዴ የሚሰማው? የፈለገው ብዥታውን መዝራት፣ ጉራውን ማሳየት ነው። ከልቡ ምክር ከፈለገ የሚያጣጥላቸውን ሰዎች ሳይሆን የሚያከብራቸው ጋር አገናኙትና ይምከሩት።
በመጨረሻ ሚዛናዊ ሳትሆኑ ሚዛናዊ ለመምሰል ለምትጥሩ አካላት በአንድ ሰውኛ ዘይቤ መልክቴን ልቋጭ። ዝሆን ከጫካ ሸሸ ይባላል። "ምነው?'' ሲሉት "አንበሳ ጫካ ውስጥ ያሉትን ቀጭኔዎች ሁሉ ሊጨርስ ወስኗል" አለ።
"እና አንተ ዝሆን እንጂ ቀጭኔ አይደለህ! ለምን ትሻሻለህ?" አሉት።
''እሱን አውቃለሁ። ነገር ግን አንበሳ ዳኛ ያደረገው አህያን ነው። አህዮች ዳኝነቱን ሲይዙ አምልጡ" አለ።
እና ዳኝነታችሁ እንዲህ አይነት እንዳይሆን ጥንቃቄ አድርጉ። ቀዳሚው መቆርቆራችሁ ለዲን ይሁን። በዚህ በኩል ያየናቸው ከፊሎቹ (ኧረ አብዛኞቹ) መስአላውን የሚመዝኑበት አቅም የላቸውም። አቅማቸውን አውቀው ከዑለማኦች ኋላም አይሰለፉም። እንዲሁ ሲሉ ሰምተው "ኺላፍ ያለበት የፊቅህ ርእስ ነው" እያሉ ጉዳዩን እያቃለሉ በሌላ በኩል የሚቃወሙትን በከባባድ ቃላት ይወርፋሉ። ልጥፎቻቸውን ቼክ ብታደርጉ ለሐቁ ያሰሙት የረባ ድምፅ የለም። ያለ የሌለውን ታጥቆ ሙዚቃን ከ"ፅንፈኞች" ነፃ ሊያወጣ ዘመቻ ለወረደው "ተጋደላይ" ግን ሰፊ ርብርብ እያደረጉ ነው። እንዲህ ነው በፍትህና በመርህ ስም መቆመር።
እንደ ሁኔታው ልመለስበት እችላለሁ።

መርህ አልባ የመርህ ሰባኪዎች
~
"ዘምዘም ባንክ በወሰደው እርምጃ መርህና አሰራር አልተከተለም። ጥያቄያችን የጥቅምና የጉዳት ጉዳይ ሳይሆን የመርህ ጉዳይ ነው" የሚል ቃላቱ የተከሸነ ግን ቢከፍቱት ተልባ የሆነ መፈክር በዘመቻ መልክ ማስተጋባታቸውን ቀጥለዋልና አሁንም የተወሰነ ነገር ልበል። እውነት ለመናገር "ጩኸቱ ከፍየሏ በላይ ነው።" ከነዚህ አካላት ውስጥ ከፊሎቹ ዘመቻቸውን በመርህ ስም የሚያቀርቡት ብዙ ያልነቁባቸውን አካላት ከጎናቸው ለማሰለፍ እንጂ የልጁ አቋም ተጋሪዎች ናቸው። እንጂ ከመርህ የተፋቱት ራሳቸው ናቸው። መርህ አልባ ድስኩረኞች እንደሆኑ በተግባር እናያለን።
መርህ 1፦ ማንም ግለሰብ ከዲን በላይ አይደለም። ይሄ ለሙስሊሞች የማይሰወር ግልፅ የሆነ መርህ ነው። ይሄ ሰውዬ በዲን ላይ ግድፈት ሲፈፅም፣ በህዝብ መሀል ውዥንብር ሲነዛ እነዚህ የመርህ ቁማርተኞች አሁን የያዙትን ዘመቻ ሊከፍቱ ቀርቶ የረባ ድምፅ አላሰሙም። የታል "የመርህ " መፈክራችሁ? ወይስ የናንተ መርህ ስለ ዲን ደንታ የለውም? እንዲያውም የዘፈኑ ጉዳይ ተቀጣጠለ እንጂ የልጁ ትልቁ ጥፋት በዐቂዳ ጉዳይ የአፈን .ጋጩ የአሻዒራ ቡድን ተከታይ መሆኑ ነው። ይሄ ራሱ በቪዲዮ የለቀቀው ነው። ይህንን ሲያደርግ እነዚህ የመርህ ጠያቂዎች ኮሽታ አላሰሙም። እንዲያውም ከፊሎቹ እንከተለዋለን የሚሉትን ዘፈንን የሚያወግዘውን የሱፊያ፣ የሻፊዒያ እና የሐነፊያ መንገድ ጥለው ልጁን የደገፉት "ሱፊይ ነኝ"፣ "አሽዐሪይ ነኝ" ስላለ ነው። አስቡት እልህ የሰበሰባቸው አካላት ስለ መርህ ሲሰብኩ።
መርህ 2፦ ሐራም ማለት አላህ ሐራም ያደረገው ነው። ይሄ እንደ ፀሐይ ፍንትው ያለ መርህ ነው። የቁርኣንና የሐዲሥ መረጃ ጥሎ በረጅሙ የኢስላም ታሪክ የተንፀባረቁ ጥቂት ደካማ የኺላፍ ሃሳቦችን ይዞ ሲበጠብጥ አሁን አጉል የመርህ ሰዎች ለመምሰል የምትፍጨረጨሩትን ሩብ ያክል ተቃውሞ አሳይታችኋልን?
በዚህ አጋጣሚ ሰዑዲ ውስጥ የሆኑ ኢማሞች ሙዚቃን ሐላል ነው የሚል አቋም ሲያራምዱ እነ ሸይኽ ፈውዛን የከረረ አቋም ነበር ያንፀባረቁት። በመጨረሻም ከሚያሰግዱባቸው መስጂዶች ታግደዋል።
መርህ 3፦ በኢስላም የቀጣሪ እና የተቀጣሪ ውል በሁለቱም በኩል ነፃ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው፣ የቀደመ ሸርጥ ካልተቀመጠ በስተቀር። አንድ ድርጅት እንኳን ስጋት ኖሮት፣ ምክንያት ባይኖረውም ሰራተኛውን ሐቁን ሰጥቶ መሸኘት ይችላል። ሰራተኛውም ከድርጅቱ የመውጣት ነፃ ፈቃድ አለው። የማወራው ስለ ኢስላማዊ ህግ ነው። የምትጮሁት ጩኸት ምናልባት በሃገሪቱ ህግ ቢያስኬደው እንኳ ይሄ የሸሪዐ መሰረት ያለው አይደለም። ዘምዘም ባንክ ሰውየውን ያባር ወይም ይመልስ የሚለው ላይ አይደለም የኔ ጉዳይ። የትኛው ውሳኔው የተሻለ ነው የሚለውን ተቋሙ ይጨነቅበት። ጥያቄዬ ተቋሙ ያዋጣኛል ያለውን እንዳይወስን ማነው ጣልቃ የሚገባው የሚል ነው?
* "ህዝባዊ ስለሆነ ያገባናል" ከሆነ፣ እናንተን ከሌላው ህዝብ የተለየ ባለመብት የሚያደርጋችሁ ምን መሰረት አለ?
* በሸሪ0 ሚዛን ከሆነ መነጋገር የተፈለገው እንኳን ስጋት ኖሯቸው ዝም ብለውም መሸኘት ይችላሉ። ከዚህ አኳያ ማንም ተሳስተዋል ብሎ መረጃ መጥቀስ አይችልም። የቁርኣን የሐዲሥ መረጃ አለኝ የሚል ካለ ፈረሱም ይሄው ሜዳውም ይሄው?
መርህ 4፦ "አዶረሩ ዩዛል" የታወቀ መርህ ወይም ቃዒዳ ነው። የባንኩ ኃላፊዎች የሼር ሆልደሮቹን ንብረት በአማና የተረከቡ አካላት ናቸው። ለአንድ ተቀጣሪ ሲሉ የባንኩን ቅቡልነት አደጋ ላይ ቢጥሉ አማናቸውን አልተወጡም ማለት ነው። ስለዚህ "አካሄድህ ተቋማችንን ስለሚጎዳ ውላችን እዚህ ላይ ይቆማል" ቢሉ መርህ ጠበቁ እንጂ መርህ ጣሱ አይባልም። ስለሆነም ድርጅቱ፡ ደንበኞቹ መሀል ግርግር በመፍጠር የባንኩን መልካም ስም ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ አካላት ላይ ጠንካራ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰድን መርሁ ቢያደርግ የሚመሰገንበት እንጂ የሚወቀስበት አይደለም።
መርህ 5፦ ከእውነት በላይ መርህ የለም። ህዝቡ የሰውየውን ሙዚቃ መፍቀድ ያወገዘው by default እንደ ህዝብ ሙስሊሙ ዘንድ የሚታወቅ ሐቅ ስለሆነ እንጂ በወቅታዊ ጉትጎታ አይደለም። ሐቁ ይሄ ሆኖ ሳለ ልክ አንድ ቡድን በተለየ የተቃወመ እያስመሰሉ "መዳ - ኺላ" እያሉ ማቅረብ በምን ስሌት ነው ከመርህ ጋር የሚገናኘው? መርህ እየደፈጠጣችሁ ነው ስለ መርህ የምትደሰኩሩት? በቡድናዊ ስሜት አድፍጣችሁ ነው'ንዴ ስለ መርህ የምትሰብኩት? የቀበሮ ባህታውያን አትሁኑ እንጂ! "የቀበሮ ባህታዊ ከበግ መሀል ይፀልያል።"
ለመሆኑ መርህ ማለት እናንተ በፈለጋችሁት ቅርፅና መጠን የምትቆርጡት የቤት ውስጥ ሳሙና ነው'ንዴ? ወይስ ላሻችሁ የምትሰጡት ለደበራችሁ የምትነፍጉት የግል ንብረታችሁ ነው? የምትጮሁትን ኑሩት እንጂ! የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفۡعَلُونَ (2) كَبُرَ مَقۡتًا عِندَ ٱللَّهِ أَن تَقُولُوا۟ مَا لَا تَفۡعَلُونَ (3) }
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? የማትሠሩን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡" [አሶፍ: 2-3]
{ أَتَأۡمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلۡبِرِّ وَتَنسَوۡنَ أَنفُسَكُمۡ وَأَنتُمۡ تَتۡلُونَ ٱلۡكِتَـٰبَۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ }
"እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? (የሥራችሁን መጥፎነት) አታውቁምን?" [አልበቀረህ: 44]
* አያያዙን አይቼ ልመለስ እችላለሁ።

ለ0ብዱልጀሊል እና መሰሎቹ፣ ራሳችሁን ከሰቀላችሁበት ውረዱ!
~
0ብዱልጀሊል ዐሊ ካሳ የፃፈውን ፅሁፍ አየሁኝ። ፅሁፉ ድፍረትና ነውረኝነት የነገሰበት አሳፋሪ ፅሁፍ ነው። ከንግግሮቹ ውስጥ ጥቂት ሰበዞችን መዝዤ አያለሁ።
"እስከ አሁን ሙዚቃ ሃራም ነው ሃላል? ሙስተሃብ ነው ከርሃ? ወዘተ ዓይነት ሙግትም ፍላጎቱም የለኝም። እስክሞትም አይኖረኝም! So rubbish and irrelevant discussion." ብሏል።
መልስ፦ እውነት ከሙዚቃ ማስጠንቀቅ እሱ እንደሚለው ረብ የለሽ ስራ ነው? ይሄ ለብዙ ሙስሊሞች ባይሰወርም ለማስታወስ ያክል ጥቂት ልበል።
1. ከቁርኣን
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:-
{ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن یَشۡتَرِی لَهۡوَ ٱلۡحَدِیثِ لِیُضِلَّ عَن سَبِیلِ ٱللَّهِ بِغَیۡرِ عِلۡمࣲ وَیَتَّخِذَهَا هُزُوًاۚ أُو۟لَـٰۤىِٕكَ لَهُمۡ عَذَابࣱ مُّهِینࣱ }
"ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አልለ። እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው።" [ሉቅማን፡ 6]
በአንቀፁ ውስጥ "አታላይ ወሬ" የተባለው ዘፈን ነው። የቁርኣን ተፍሲር ሊቅ የሆኑት ሶሐቢዩ ኢብኑ ዐባስ “ይህ አንቀጽ ስለ ዘፈን የወረደ ነው” ብለዋል። [ተፍሲር አጦበሪ፡ 21/40] ታቢዒዩ ሐሰን አልበስሪይም እንዲሁ “ይህ አንቀጽ የወረደው ስለ ዘፈንና ስለ ሙዚቃ ነው” ብለዋል። [ተፍሲር ኢብኒ ከሢር፡ 3/451]
ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
“ሶሐቦችና ታቢዒዮች 'አታላይ ወሬ' ለሚለው የሰጡት ትርጉም ዘፈን መሆኑ ብቻውን በቂ ነው። ይህ ደግሞ ከኢብኑ ዐባስና ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁም) በትክክል የተዘገበ ነው። አቡ ሶሕባእ እንዲህ ይላሉ፡- ‘አላህ፡ ከሰዎች መካከል አታላይ ወሬን የሚገዙ አሉ’ የሚለውን የአላህን ቃል በተመለከተ ኢብኑ መስዑድን ጠየቅኩኝ። እርሳቸውም፡ ‘ከሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ በሌለው አላህ ይሁንብኝ! እሱ ዘፈን ነው’ በማለት ሶስት ጊዜ ደጋግመው ተናገሩ። ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ዘንድም እሱ ዘፈን መሆኑ ተረጋግጧል።” [ኢጋሰቱል ለህፋን፡ 1/258-259]
2. ከሐዲሥ
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
"ليكونن من أمتي أقوام يستحلون الحر والحرير والخمر والمعازف"
“ከህዝቦቼ ውስጥ ዝሙትን፣ ሐርን፣ የአልኮል መጠጥን እና የሙዚቃ መሣሪያዎችን የሚፈቅዱ ሰዎች ይመጣሉ።” [ቡኻሪ በተዕሊቅ ዘግበውታል፣ ቁጥር 5590] [አሶሒሐ፡ 1/1140] (በዚህ ሐዲሥ ላይ ስለሚያነሱት ብዥታ ሌላ ጊዜ ልመለስ እችላለሁ ኢንሻአለህ።)
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
“ይህ ሐዲሥ የሙዚቃ መሣሪያዎች የተከለከሉ መሆናቸውን ያመላክታል። በቋንቋ ሊቃውንት ዘንድ ‘መዓዚፍ’ ማለት የመዝናኛ መሣሪያዎች ማለት ነው። ይህ ስም ሁሉንም የሙዚቃ መሣሪያዎችን ያጠቃልላል።” [አልመጅሙዕ፡ 11/535]
3. ከሶሐቦች
ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
“በዚህ ጉዳይ ላይ ከሰህል ብኑ ሰዕድ አሳዒዲይ፣ ከዒምራን ብኑ ሑሶይን፣ ከ0ብዱላህ ብኑ ዐምር፣ ከ0ብዱላህ ብኑ ዐባስ፣ ከአቡ ሑረይራ፣ ከአቡ ኡማማ አልባሂሊይ፣ ከዓኢሻ፣ ከዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ፣ ከአነስ ብኑ ማሊክ እና ከሌሎችም (ረዲየላሁ ዐንሁም) ብዙ ሐዲሦች ተዘግበዋል። እነዚህ ሁሉ ወደ ክልከላ ያመላክታሉ።”
4. ከአራቱ አኢማዎች:-
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
“የአራቱ የፊቅህ መዝሃቦች (ኢማሞች) አቋም - የሁሉም - የሙዚቃ መሣሪያዎች ክልከላ ነው። …የአራቱ ኢማሞች ተከታዮችም በሙዚቃ መሣሪያዎች ጉዳይ ላይ ምንም አይነት አለመግባባት የላቸውም።” [አልመጅሙዕ፡ 11/576]
ሸይኹል አልባኒይም (ረሒመሁላህ) “አራቱ መዝሃቦች (ኢማሞች) ሁሉንም የመዝናኛ መሳሪያዎች (ሙዚቃ) መከልከል ላይ ተስማምተዋል” ብለዋል። [አሶሒሐ፡ 1/145]
በዚህ አጋጣሚ ሸይኹል አልባኒይ በዚህ ርእስ ላይ ብቻ የሚያጠነጥን "ተሕሪሙ ኣላቲ ጦርብ" የተሰኘ ምርጥ ኪታብ አላቸው። ማስረጃዎችን፣ በጉዳዩ ላይ የሚነሱ ብዥታዎችንና ምላሾችን የያዘ ስራ ነው።
ኢማም ማሊክምም “እኛ ዘንድ ይህንን የሚሰሩት ፋሲቆች (ከሃይማኖታዊ መንገድ ያፈነገጡ ሰዎች) ብቻ ናቸው” ብለዋል። [ተፍሲር አልቁርጡቢ፣ 14/55]
0ብዱልጀሊል ደግሞ ነውሩን እንደመሸፈን ደጋግሞ በማዳመጥ የሐፈዘውን የዘፈን ዝርዝር ለጥፎልናል። ይሄ ሊያፍሩበት የሚገባን ጥፋት ጀብድ አድርጎ መናገር ድርብ ወንጀል ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
كُلُّ أُمَّتي مُعافًى إلَّا المُجاهِرِينَ، وإنَّ مِنَ المُجاهَرَةِ أنْ يَعْمَلَ الرَّجُلُ باللَّيْلِ عَمَلًا، ثُمَّ يُصْبِحَ وقدْ سَتَرَهُ اللَّهُ عليه، فَيَقُولَ: يا فُلانُ، عَمِلْتُ البارِحَةَ كَذا وكَذا، وقدْ باتَ يَسْتُرُهُ رَبُّهُ، ويُصْبِحُ يَكْشِفُ سِتْرَ اللَّهِ عنْه
“ከህዝቦቼ ውስጥ ሁሉም ሰው ከሃጢአቱ ይቅርታ ይደረግለታል፣ ግልጽ የሚያወጣ ሲቀር። ግልጽ ከማውጣት የሆነው አንድ ሰው በሌሊት አንድን ስራ ሰርቶ (ወንጀል ሰርቶ) አላህ ደብቆለት ያደረ ቢሆንም፣ ጠዋት ሲሆን ‘እንዲህ እንዲህ አይነት ነገሮችን ሰራሁ’ ማለቱ ነው። ጌታው ደብቆለት ያደረ ሲሆን፣ እሱ ግን ጠዋት ሲሆን አላህ የሸፈነለትን ነገር ይገልጣል።” [ቡኻሪ፡ 6069] [ሙስሊም፡ 2990]
እሱ ግን በጥፋቱ እንደማፈር ራሱ አይፈቀድም የሚለውን የሙዚቃ ዓይነት ሳይቀር እንደሸመደደው ለሕዝብ እያሳየ ነው። እንዲህ አይነት በነውራቸው መከበር የሚሹ አካላትን አስመልክቶ "ባይብል" ላይ እንዲህ የሚል አለ:- “መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ #ክብራቸው_በነውራቸው_ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።” [ፊልጵስዩስ 3፥19]
ይህንን ማጣቀስ ችግር የሚመስላቸው ካሉ እመለስበታለሁ።
ከላይ ያሉትን መረጃዎች የጠቀስኩበት ዋና አላማ "እስከ አሁን ሙዚቃ ሃራም ነው ሃላል? ሙስተሃብ ነው ከርሃ? ወዘተ ዓይነት ሙግትም ፍላጎቱም የለኝም። እስክሞትም አይኖረኝም! So rubbish and irrelevant discussion" የሚለው የ0ብዱልጀሊል ንግግር ምን ያህል ጅህልናና ድፍረት የተሞላበት እንደሆነ እንዲታይ ነው። ቁርኣኑ፣ ሐዲሡ፣ ሶሐቦቹ እና አኢማዎቹ ትኩረት የሰጡት ጉዳይ እሱ ዘንድ ዛሬ ብቻ ሳይሆን እስከሚሞት ድረስ ረብ የለሽ ጉዳይ ነው። ስለ ዲን ጉዳይ ያለው የግንዛቤ መጠን ይሄ ነው። ወይ ቁርኣን ሐዲሥ ጠቅሶ በእውቀት አይፅፍ። ወይ አለማወቁን አውቆ አርፎ አይቀመጥ። በego ውጥርጥር ያለ፣ ስራው ሁሉ በ"እኔ" የተሞላ ነው። ተመልከቱ ይህንን ንግግሩን፦
"ሁሌም እንደምለው በተራ እና ፋይዳ በሌለው አጀንዳ አታድክሙን ነው!! በዙሪያችን ቋጥኝ ናዳ እየወረደ ጠጠር ላይ አታድክሙን!!"

አያችሁ አይደል በቁርኣን፣ በሐዲሥ የተወገዘ፣ ከበጣም ጥቂቶች ውጭ፣ ከጥንት እስከ ዛሬ ያሉ ዓሊሞች ትኩረት ሰጥተው ያወገዙትን ተግባር ትኩረት ሰጥቶ ማስተማርን ተራ እና ፋይዳ ቢስ እያለ ሲገልፀው?! የሐላልና የሐራም ርእስ ነው ረብ የለሽ ተብሎ የሚጣጣለው? ይሄ እንግዲህ ረብ የለሽ የሆኑ ሰዎች በትልልቅ ጉዳዮች ላይ ሲናገሩ የሚመጣ ጣጣ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"سيأتي على الناس سنوات خدّعات، يُصَدق فيها الكاذب ويُكذَّب فيها الصادق، ويُؤتمن فيها الخائن ويُخوَّن فيها الأمين، وينطق فيها الرويبضة"
قيل وما الرويبضة يا رسول الله ؟ .. قال: «الرجل التافه يتكلم في أمر العامة»
“በሰዎች ላይ የማታለል ዓመታት ይመጣሉ። ያኔ ውሸ .ታም ሰው እውነትኛ ተደርጎ ይወሰዳል፣ እውነትኛ ሰው ደግሞ ውሸ .ታም ተብሎ ይከሰሳል። ከ^ሃ .ዲ ታማኝ ይባላል፣ ታማኝ ደግሞ ከ ^ሃዲ ተብሎ ይጠረጠራል። ‘ሩወይቢዷ’ በወሳኝ ጉዳይ ላይ ይናገራል።”
ሰዎችም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሩወይቢዷ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁ።
እርሳቸውም፡ “የሰፊው ሕዝብ ጉዳይ ላይ የሚናገር ክብረ ቢስ ሰው ነው” አሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3650]
ይህንን ነው ዛሬ ላይ እያየን ያለነው። እንዲያውም ራሱ በቅርቡ የተጠቀመውን ቃል ልጠቀምና ይሄ "ስክነት አልቦ ድውይነት! የግመል ሽንትነት! የውሃ ላይ ኩበትነት!" ነው። እንዳሻው ሲሳደብ ዝም ያሉ የሒክማ ፖሊሶች ግምገማ ሊሰጡ ይመጣሉ አሁን።
ይቀጥላል፦
"ኦልሬዲ ዘፈን ለሚያዳምጥ ወይም ለማዳመጥ ለሚዳዳው ህዝብም የሙዚቃ ሃላል ነው ሃራም ነው ሙግት ምኑም የማያስደስት አጀንዳ ነው!" ብሏል።
አዎ! ይህን ሁሉ ሙዚቃ ለሐፈዘ ሰው የዘፈን ሐራምነት መነገሩ እንደማያስደስተው ሳይታለም የተፈታ ነው። ቀደም ብዬ፡ መርህ፣ መርህ እያሉ ከአደም ከሚከላከሉት ውስጥ ከፊሎቹ በመርህ ጭምብል ይመጣሉ እንጂ ዋና ምክንያታቸው ራሳቸው የሙዚቃ ደጋፊ መሆናቸው ነው ያልኩት ሁኔታቸውን ስለማውቅ ነው።
ችግራቸው ግን ከሙዚቃም ያልፋል። 0ብዱልጀሊልና መሰሎቹ ፡ ዑለማኦች፣ ዱዓቶች ምን ማስተማር፣ ምን መተው፣ መቼና የት መናገር እንዳለባቸው መስመር የሚያሰምሩ፣ አቅጣጫ የሚሰጡ የደዕዋ ዘርፍ ስምሪት ክፍል አዛዥ ናዛዥ መሆን ነው የሚፈልጉት። ከአካሄዳቸው በመነሳት ሰፊ ጊዜያቸውን ለፖለቲካ፣ ለዜና፣ ለፊልም፣ ለሙዚቃ እንዳደረጉ መረዳት ይቻላል። ድፍረታቸው ግን አንድ የቁርኣን አንቀፅ፣ አንድ የሐዲሥ መልእክት፣ አንድ የዑለማእ ጥቅስ ሳይዙ የደዕዋ አጀንዳዎችን ቅደም ተከተል ሊያስቀምጡ ነው የሚዳዳቸው። በዚህ መጠን ነው ልባቸው ያበጠው።
የቀለም ትምህርት ትንሽ ሲቀምሱ በዐቂዳውም፣ በሐላልና ሐራሙም ገብተው መፈትፈት ነው የሚፈልጉት። ሲበዛ ግልብ ናቸው። ራሳቸውን የሚያዩበት አይን ግን በጣም የተለየ ነው። አያውቁም። አለማወቃቸውንም አያውቁም። ህዝቡ እነሱ የሚጥሉለትን የአጀንዳ ፍርፋሪ ከመልቀም ውጭ የዑለማኦችን አስተምህሮት በመከተል ሊፅፍ፣ ሊናገር አይመቻቸውም። ይጎረብጣቸዋል። የዘፈን ዝርዝር ሲለጥፉ ሳያፍሩ፤ "የአይነ'ላህ ተቆርቋሪዎች" እያሉ በተውሒድ ላይ የሚሳለቁ ጥራዝ ነጠቅ ዋል ^ ጌዎች ናቸው። ሺርክና ቢድ0ን ማውገዝ፣ በተውሒድ እና በሱና ላይ ሰዎችን ማንቃት፣ ከአደገኛ አንጃዎች ህዝብን መጠበቅ፣ ህዝብ መሀል የተንሰራፉ 'ከባኢሮች' ላይ ግንዛቤ መስጠት ለነሱ ረብ የለሽ ልፋት ነው። የነሱ የሴራ ትንታኔ ተራራ ሲሆን የሌሎች ቃለ'ላህ፣ ቃለ ረሱሉ'ላህ ተራ ነገር ነው። በሌላ ዘርፍ ላይ ትንሽ ስራ ሲሰሩ የደዕዋውን ልጓም እኛ ካልያዝነው ነው የሚሉት። በሆነች ስራቸው ህዝብ ተደስቶ አክብሮ እራሱ ላይ ሲሰቅላቸው አናቱ ላይ ሊፀዳዱበት ሊዘባነኑበት ይፈልጋሉ። ማየት፣ መስማት፣ መማር ያለበትን ሁሉ ሊመርጡለት ይሻሉ። ለራሳችሁ ስትሉ አደብ ይኑራችሁ። ክብርን ያለመንገዱ የፈለገ ሰው አይከበርም። "ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ። ካልሆነ ድንጋይ ነህ ተብለህ ትወረወራለህ!!"

የአህመድ ሻኪር እና የፕሮፌሰር ኪስተር ታሪክ
~
ፕሮፌሰር ኪስተር እ $ራ -ኤ 'ላዊ የ ሁ ^D ነው። ለረጅም ጊዜ በሐዲሥ ጥናት ላይ ተሰማርቶ የቆዬ የ75 ዓመት አዛውንት። የግብፃዊውን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ አሕመድ ሻኪር የጥናት ውጤቶች አሳዶ ያነባል። አንዴ ኪታባቸውን ሲያነብ በሐዲሥ ምርምራቸው (ተሕቂቅ) ላይ ስህተት አገኘባቸው። ወዲያውኑ ይህንን የሚጠቁም ደብዳቤ ጻፈላቸው። ሸይኽ አሕመድ ሻኪር ለደብዳቤው እንዲህ የሚል ምላሽ ፃፉለት :-
“Y ^ሁ 'ዶች ወዳረ ^ከ - ሱት ቅዱስ ምድር፣
ለፕሮፌሰር ኪስተር።
ሰላም ቅኑን መንገድ ለተከተለ ይሁን።
በመቀጠል፣
ደብዳቤህ ደርሶኛል። በውስጡ ያለውንም አንብቤያለሁ። አንተ ትክክል መሆንህን እና እኔ ደግሞ ስህተት መሆኔን ስነግርህ እያዘንኩ ነው። ነገር ግን የእውቀት አደራ ሆነብኝ።
አህመድ ሻኪር ነኝ።”
ለፕሮፌሰሩ የሸይኽ አሕመድ ሻኪር መልስ ደስታ ነበር የሰጠው። “ለኔ ከሸይኽ አሕመድ ሻኪር ደብዳቤ የተፃፈልኝ መሆኔ ይሄ ደረቴ ላይ ያረፈ ትልቁ ሜዳሊያዬ አድርጌ ነው የምቆጥረው'' ነበር ያለው። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር፣ ካሴት ቁጥር፡ 675]

የህመምተኛ አሰጋገድ
~
* ሶላት ላይ መቆም ሩክን ነው፣ ዋና ክፍል። የቻለ ሰው ቆሞ ይሰግዳል። መቆም ያልቻለ ወይም መቆሙ ህመሙን የሚያባብስበት የሆነ ሰው ተቀምጦ ይሰግዳል። መቀመጥም ከከበደ ተኝቶ ይሰግዳል።
* መቆም የሚችል እና መቆሙ የማይጎዳው የሆነ ሰው ሱጁድ መውረድ ስላቃተው ብቻ ወንበር ላይ ተቀምጦ መስገድ የለበትም። ይልቁንም የሚችለውን ይፈፅምና ለማይችለው ጎንበስ እያለ ይሰግዳል።
* ሩኩዕንም ሱጁድንም በትክክል መፈፀም ያልቻለ ሰው ሱጁዱን ከሩኩዕ የበለጠ ዝቅ እያደረገ በማጎንበስ ይሰግዳል።
* ወንበር ላይ የሚሰግድ ሰው ጀማዐ ላይ የሚገኝ ከሆነ ሶፉን እንዴት ያድርግ?
- ከመነሻውም ተቀምጦ የሚሰግድ ከሆነ አቀማመጡን ነው ከሰጋጆች ሶፍ ጋር መስመር የሚያስይዘው።
- ቆሞ እየሰገደ ወንበሩን ለሩኩዕ እና ለሱጁድ ከሆነ የሚጠቀመው ወንበሩን ወደ ኋላ በማድረግ እግሩን ከሰጋጆች እግር ጋር አስተካክሎ ሶፍ ይጠብቅ። በዚህን ጊዜ አጉል ቦታ ሶፍ እንዳይቆርጥ ጥግ ይዞ ቢሰግድ የተሻለ ነው።
* እያንዳንዱን ሶላት በየወቅቱ መስገድ የሚከብደው ከሆነ ዙሁርና ዐስርን በአንድ ወቅት፣ መግሪብና ዒሻእን በአንድ ወቅት አድርጎ መስገድ ይችላል።
ወላሁ አዕለም።

ከሰገደ በኋላ ውዱእ እንዳልነበረው ወይም ጁኑብ እንደሆነ ያስታወሰ ሰው ሶላቱን እንደገና ይሰግዳል። ያለ ውዱእ የተሰገደ ሶላት ዋጋ የለውምና።
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور