tgoop.com/IbnuMunewor/7803
Last Update:
ጥቂት ስለ ሰሞንኛው የሙዚቃ ግርግር
~
ሙዚቃ በተለይ በዚህ ዘመን በጣም ብዙ ነገር ነው አጭቆ የያዘው። አብዛኛው ይዘቱ የሴትን ልጅ አማላይ አካላዊ ገፅታ በመዘርዘር ላይ ያነጣጠረ ፆታዊ ቅስቀሳ ያዘለ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ሴቷ ስለ ወንዱ ስትዘፍንም እንዲሁ። ከዚያ ባሻገር ሙዚቃ ሃይማኖት አለበት። አድባሩ፣ ደብሩ፣ ገዳማቱ፣ "ቅዱሳኑ"፣ መፅሀፍ "ቅዱሳዊ" ይዘቶች፣ ወዘተ. እምነታዊ እሴቶች በሰፊው ይገኙበታል። ግጥሞቹ በአመዛኙ ጤነኛ አይደሉም። እንኳን ዘፈን ላይ ያለው እንዲሁ በሌጣውም ግጥም ብዙ ኮተት አለበት። (ሁሉንም እያልኩ አይደለም።) ያለ ምክንያት አይደለም አላህ እንዲህ ማለቱ፦
{ وَٱلشُّعَرَاۤءُ یَتَّبِعُهُمُ ٱلۡغَاوُۥنَ (224) أَلَمۡ تَرَ أَنَّهُمۡ فِی كُلِّ وَادࣲ یَهِیمُونَ (225) وَأَنَّهُمۡ یَقُولُونَ مَا لَا یَفۡعَلُونَ (226) }
"ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሏቸዋል። እነርሱ በ(ንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መሆናቸውን አታይምን? እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መሆናቸውን (አታይምን)?" [አሹ0ራእ፡ 224-226]
ሙዚቃን መፍቀድ ሙዚቃን ከማዳመጥ የከፋ ጥፋት ነው። በዚህ ረገድ ሆ ብሎ የተቆጣው ወገናችን አጉል ስልጡን ስልጡን ከሚሰራራቸው አካላት የተሻለ የዲን መቆርቆር፣ የበለጠ የሞራል ከፍታ እንዳለው በተግባር አሳይቷል። "መንጋ" ብለው ሊያጣጥሉት የሞከሩት የእውነት መንጋዎቹ እነሱ ናቸው። የቁርኣን አንቀፆችን፣ ሶሒሕ ሐዲሦችን፣ ህልቆ መሳፍርት የዑለማእ ንግግሮችን የተከተለ ነው ይሄኛው ''መንጋ"።
በተቃራኒው የቆመውስ መንጋ? ከዲኑ ክብር ይልቅ ለአንድ የተቃወመውን ሁሉ "ሴት" እያለ ለሚያጣጥል፣ በትእቢት ለተሞላ attention seeker ነው ሽንጣቸውን ገትረው እየተሟገቱ ያሉት። የክፋታቸው ክፋት የተቃውሞውን ድምፅ ለመበተን "የመዳ .ኺላ ተቃውሞ" እያሉ መቀባበላቸው ነው። ይሄ በተደጋጋሚ ድምፅ ለመበተን የሚጠቀሙት ስልት ነው። ጉዳዩ የቡድን ጉዳይ እንዳልሆነ ግልፅ ነው።
ደግሞ "ለምን አትወያዩትም?" ይላሉ። የሚገርመው ከፊሎቹ ሙዚቃ ሐራም ነው እያሉ ነው "ለምን አትወያዩትም?" የሚሉት። እናንተ ለምን አትወያዩትም? ነው ወይስ የህዝቡ ጩኸት አስፈርቷችሁ እንጂ የአቋሙ ተጋሪ ናችሁ? ለማንኛውም ልጁ ፈፅሞ ሊወያዩት የሚገባ አይደለም። ለምን?
* አንደኛ :- ትኩረት ነው የፈለገው። ችግሩ የግርታ ቢሆን ከአንድ ዓሊም ጋር ተጠግቶ ብዥታውን ማጥራት ይችል ነበር።
* ሁለተኛ :- ሰውየው ቀ .ጣ .ፊ ነው። የተቃወሙትን በጅምላ ትምህርት ሐራም የሚሉ፣ ቴሌቪዥን ሐራም የሚሉ፣ ... እያለ መግለፁ ለዚህ ማሳያ ነው። የተቃወመው አንድ ቡድን ነው ወይስ ሰፊው ህዝብ? ይሄ ምን ያህል መ .ሰሪ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
* ሶስተኛ :- የተቃወሙትን ሁሉ " ... ኩሉ ጀምዒን ሙአነሡ" እያለ "ሴቶች ናቸው" እያለ የሚያጣጥል በትእ ^ቢት የተወ .ጠረ ዋ .ል ^ጌ ነው። ከእንዲህ አይነት ሰው ጋር መወያየት እጅግ የተሳሳተ አካሄድ ነው። ድንገት ያሰባችሁ ካላችሁም ፈፅሞ እንዳታደርጉት። ከሱ ጋር ቀርባችሁ እንዳትግማሙ።
* አራተኛ :- የዘፈን ሐራምነት ለሰፊው ህዝብ ሲበዛ ግልፅ ነው። ታዲያ ምን ለማትረፍ ነው ውይይቱ? እናንተ ግር ካላችሁ ወይ በአራቱም አቅጣጫ ሂዳችሁ ያገኛችሁትን ዓሊም ጠይቁ። ካልሆነ ከሱው ጋር ሂዱና ተጨቃጨቁ። "አይ ለሱ እንዲመለስ አስበን ነው" ካላችሁ ወላሂ ይሄ ውሸት ነው። በንቀት የሚያንኳስሳቸውን ሰዎች ነው እንዴ የሚሰማው? የፈለገው ብዥታውን መዝራት፣ ጉራውን ማሳየት ነው። ከልቡ ምክር ከፈለገ የሚያጣጥላቸውን ሰዎች ሳይሆን የሚያከብራቸው ጋር አገናኙትና ይምከሩት።
በመጨረሻ ሚዛናዊ ሳትሆኑ ሚዛናዊ ለመምሰል ለምትጥሩ አካላት በአንድ ሰውኛ ዘይቤ መልክቴን ልቋጭ። ዝሆን ከጫካ ሸሸ ይባላል። "ምነው?'' ሲሉት "አንበሳ ጫካ ውስጥ ያሉትን ቀጭኔዎች ሁሉ ሊጨርስ ወስኗል" አለ።
"እና አንተ ዝሆን እንጂ ቀጭኔ አይደለህ! ለምን ትሻሻለህ?" አሉት።
''እሱን አውቃለሁ። ነገር ግን አንበሳ ዳኛ ያደረገው አህያን ነው። አህዮች ዳኝነቱን ሲይዙ አምልጡ" አለ።
እና ዳኝነታችሁ እንዲህ አይነት እንዳይሆን ጥንቃቄ አድርጉ። ቀዳሚው መቆርቆራችሁ ለዲን ይሁን። በዚህ በኩል ያየናቸው ከፊሎቹ (ኧረ አብዛኞቹ) መስአላውን የሚመዝኑበት አቅም የላቸውም። አቅማቸውን አውቀው ከዑለማኦች ኋላም አይሰለፉም። እንዲሁ ሲሉ ሰምተው "ኺላፍ ያለበት የፊቅህ ርእስ ነው" እያሉ ጉዳዩን እያቃለሉ በሌላ በኩል የሚቃወሙትን በከባባድ ቃላት ይወርፋሉ። ልጥፎቻቸውን ቼክ ብታደርጉ ለሐቁ ያሰሙት የረባ ድምፅ የለም። ያለ የሌለውን ታጥቆ ሙዚቃን ከ"ፅንፈኞች" ነፃ ሊያወጣ ዘመቻ ለወረደው "ተጋደላይ" ግን ሰፊ ርብርብ እያደረጉ ነው። እንዲህ ነው በፍትህና በመርህ ስም መቆመር።
እንደ ሁኔታው ልመለስበት እችላለሁ።
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7803