tgoop.com/IbnuMunewor/7811
Create:
Last Update:
Last Update:
የአህመድ ሻኪር እና የፕሮፌሰር ኪስተር ታሪክ
~
ፕሮፌሰር ኪስተር እ $ራ -ኤ 'ላዊ የ ሁ ^D ነው። ለረጅም ጊዜ በሐዲሥ ጥናት ላይ ተሰማርቶ የቆዬ የ75 ዓመት አዛውንት። የግብፃዊውን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ አሕመድ ሻኪር የጥናት ውጤቶች አሳዶ ያነባል። አንዴ ኪታባቸውን ሲያነብ በሐዲሥ ምርምራቸው (ተሕቂቅ) ላይ ስህተት አገኘባቸው። ወዲያውኑ ይህንን የሚጠቁም ደብዳቤ ጻፈላቸው። ሸይኽ አሕመድ ሻኪር ለደብዳቤው እንዲህ የሚል ምላሽ ፃፉለት :-
“Y ^ሁ 'ዶች ወዳረ ^ከ - ሱት ቅዱስ ምድር፣
ለፕሮፌሰር ኪስተር።
ሰላም ቅኑን መንገድ ለተከተለ ይሁን።
በመቀጠል፣
ደብዳቤህ ደርሶኛል። በውስጡ ያለውንም አንብቤያለሁ። አንተ ትክክል መሆንህን እና እኔ ደግሞ ስህተት መሆኔን ስነግርህ እያዘንኩ ነው። ነገር ግን የእውቀት አደራ ሆነብኝ።
አህመድ ሻኪር ነኝ።”
ለፕሮፌሰሩ የሸይኽ አሕመድ ሻኪር መልስ ደስታ ነበር የሰጠው። “ለኔ ከሸይኽ አሕመድ ሻኪር ደብዳቤ የተፃፈልኝ መሆኔ ይሄ ደረቴ ላይ ያረፈ ትልቁ ሜዳሊያዬ አድርጌ ነው የምቆጥረው'' ነበር ያለው። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር፣ ካሴት ቁጥር፡ 675]
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7811