Telegram Web
👉ድንቅ ዜና

🚧የአለማችን ትልቁ 3D ፕሪንተር ሙሉ የመኖሪያ ቤት በራሱ ፕሪንት ማድረጉ ተገለፀ።

💫በአሜሪካ ሜን ዩኒቨርስቲ ዉስጥ የተሰራው ይህ ፕሪንተር ከውስጡ በሚወጣ ቴርም ፕላስቲክ ፖሊመር አማካኝነት ግዙፍ ቤቶችን የመስራት አቅም አለው ተብሏል።

💥ቴክኖሎጂው በዚህ ከቀጠለ በቅርብ አመታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በማሽን ፕሪንት የተደረገ የመኖሪያ መንደር ማየታችን አይቀሬ ይመስላል።

የዜና ምንጭ AP

@etconp
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👉እንወያይ

በመዲናይቱ አዲስ አበባም ሆነ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ባሉ ትልል ከተሞች የሚገነቡ ህንጻዎች በቁጥርም ሆነ በመጠን እጅጉን እየጨመሩ መምጣታቸው ይታያል።

🔰በሀገሪቱ ለመኖሪያም ሆነ ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውሉ የህንጻ ግንባታዎች ከምንግዜውም ይልቅ እየጨመሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ከግንባታ እና ተያያዝ እንeቅስቃሴዎች ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ የደህንነት ችግሮች የበርካታ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ እና የንብረት ውድመት ሲከተልም ይታያል ፤ ይሰማል።

❇️ከሰሞኑ እንኳ አዲስ አበባ ውስጥ ለግንባታ የተከማቸ አፈርና ድንጋይ አንድ ቤት ላይ ተደርምሶ የሁለት ቤተሰብ አባላት የሆኑ የሰባት ሰዎችን ህይወት ነጥቋል።

📌የህንጻ ግንባታ ጥራታቸውን ባለመጠበቅ የሚገጥሙ መደረመስን ጨምሮ ለበርካታ ሰዎች ህልፈት እና የንብረት ውድመት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች በተለያዩ ጊዜያት ተዘግበዋል።

ከህንጻ ግንባታ ጋር ተያይዘው ለሚከሰቱ አደጋዎች በግንባታ ወቅት የሚደርስ አደጋን ለመከላከል የወጡ ህጎች አለመተግበራቸው በምክንያትነት ከሚቀርቡ ጉዳዮች አንዱ ሲሆን ግንባታዎችን በርካሽ ግብአት እና የሰው ኃይል ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶች ደግሞ ደረጃቸውን የጠበቁ ህንጻዎች እንዳይገነቡ ከማድረግ አልፎ ለከፋ የሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራም ሲዳርግ እየታየ ነው።

አሁን አሁን ደግሞ በመንግስትም ይሁን በግል በአጠቃላይ ሀገሪቱ የግንባታ ፍላጎት እጅጉን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በመስኩ ተገቢው ክትትል እና ቁጥጥር ካልተደረገ ችግሩ አሳሳቢ ሆኖ እንደሚቀጥል መገመት አያዳግትም።

ለመሆኑ በየአካባቢያችሁ የሚከናወኑ ግንባታዎች ምን ያህል ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው ? የግንባታ ደህንነት ባለመጠበቁ የገጠማችሁ ችግር ይኖር ይሆን ? ዘላቂ መፍትሄውስ ምን ይሁን ትላላችሁ ፤ ሃሳባችሁን አካፍሉን ፤ ተወያዩበትም።

https://www.tgoop.com/COTMp
#ADVERTISNMENT

🌟Our working activities list

🚧General contractor

🚧general finished work /interior design

🚧furniture works

🚧any construction materials supplier

📞 +251932264369
or 0923763281
👉5ኛ አመታዊ የኪነህንጻ  አውደርዕይ

🔰አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
አርክቴክቸር መርሀግብር ተማሪዎች

🚧በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ AAS (Association of Architecture Students) ማህበር ያዘጋጀው 5ኛው አመታዊ የኪነ ህንፃ አውደ ርዕይ ትላንት ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም "ኪነህንጻ በአመታቶች መካከል" በሚል መሪ ቃል ተጀምሯል።

✳️በተማሪዎች የተሰሩ የኪነህንጻ ፣ የውስጥ ፣የገጸመሬት፣  የቤት እቃዎች እንዲሁም  የምርት ንድፎች፣ ቁስምስሎች፣ የጥበብ ስራዎች፣ ስእሎች፣ ወካይ ምስሎች (renderings), ወዘተ...  በአውደርዕዩ ይቀርባሉ።

❇️አውደርዕዩ እስከ ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓም ድረስ የሚቆይ ሲሆን በተጋበዙ እንግዶች ሴሚናሮችን ጨምሮ የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚኖሩ ሲሆን  በዩኒቨርስቲዎች መካከል የሚደረጉ  የንድፍ ውድድሮች እና ሌሎችም ትምህርታዊ ክንውኖች ተዘጋጅተዋል።

📌ሁላችሁም ተጋብዛችኋል❤️

@etconp
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉የዓለም አቀፉን እግርኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) እና የአፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን (CAF) ደረጃን አሟልቶ እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም

@etconp
ADVERTISMENT

ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ሁሉን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት እና ለሁሉም ቅርብ

🔰ምን ይፈልጋሉ?

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

✂️ላሜራ ማስቆራረጥ ማስበሳት ወይንም ማሳጠፍ ከፈለጉ  እንዳያስቡ ሁሉንም ማሽኖች አስገብተናል

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
                    ቁ.2 መርካቶ
                    ቁ.3 ተክለሀይማኖት

0904040477
0911016833
“... ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም ” - አቶ ንጋቱ ማሞ

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፥ በከተማው በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ዘንድሮ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነተ ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ?

- “ ከተማው ውስጥ ብዙ የግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ። በተለይ አሁን ሕይወታቸውን እያጡ ያሉት በኮንክትራክሽን / በግንባታ ዘርፉ ያሉ የቀን ሠራተኞች ናቸው። ”

- “ የቀን ሠራተኞች በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ብዙ ጊዜ ጉልበታቸውን ነው ይዘው የሚገቡት፤ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ቴክኒካል እውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የላቸውም።  እንዴት የሥራ ላይ አደጋን መከላከል እንደሚችሉ ስለጠና እንኳ አይሰጥም። ”

- “ ' #የቀን_ሠራተኞች_እንፈልጋለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችን የኮንስትራክሽን ሳይቶች ላይ እናያለን። በዚያው ሥራ ያጣ መንገደኛ ይገባል ግን ሥራውን ለመከናውን ምን ሊያጋጥም ይችላል ? ብሎ አስቀድሞ የመገመት እውቀት አይኖርም። ”

- “ ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች ላይ ትልቁ ኃላፊነት ይወድቃል። እነርሱ ደግሞ በሚፈለገው ደረጃ ለዘርፉ ትኩረት እየሰጡ አይደለም። አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም። ”

- “ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግንባታው እስኪጠናቀቅ የደህንነት መርሆዎችን ያለመከተል ሁኔታ አለ። ”

Q. መፍትሄውን ምንድነው ?

- “ መፍትሄውማ ፈቃድ ሰጪው አካልም ፈቃድ ከሰጠ በኋላ በየጊዜው ጠብቅ ቁጥጥር በማድረግ ለአደጋ የተጋለጡ አሰራሮችን እየለዩ በህንጻ አዋጁ መሠረት እርምጃዎችን ቶሎ ቶሎ መውሰድ ያስፈልጋል። ”

ሰሞኑን የ7 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የድንጋይ እና አፈር ናዳ አደጋ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች ላይ ባለመድረሱ ለየት ያለ ቢሆንም ይህንኑ አደጋ ጨምሮ በ2016 ዓ/ም እስካሁን 12 ሰዎች በተለያዩ ጊዜዎችና አደጋዎች ሞተዋል።

የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ጨምሯል።

Via Tikvah Ethiopia

@etconp
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር በመሆን የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀመረ

✳️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በመንግስት እና በግል አጋርነት መርኃ ግብር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀመረ።

🔰ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸውን ያስጀመርናቸው 4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ከ14 እስከ 22 ወለል ያላቸው ዘመናዊ ህንጻዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

✳️ከንቲባዋ የግንባታ ተገቢ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ስራ ለገባው ጊፍት ሪል እስቴት በነዋሪዎቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

🚧የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮችን ከህግና አሰራር ጋር በማጣጣም ተግባራዊ በማድረግ አዲስ አበባን ምቹ የስራና የመኖሪያ ከተማ ለማድረግ መስራታችንን ቀጥለናል ሲሉም አክለዋል።

@etconp
Total permissible settlement for isolated footing on sand_____ mm
Anonymous Quiz
50%
25
26%
40
8%
65
15%
30
Intercon Construction Materials 
    
👉 Specialized in construction chemicals, Authorized agent of MC (Conmix) and Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofing Chemicals and Materials (Cementitious, Acrylic,  Crystalline, Bituminious and Liquid membrane, Liquid Glass, Sealants)
● Concrete Repair, Grout   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● External finishes (Quartz paint, Contextra),
● Specialized paints (Thermal and Insulation Paints, Street and Playground Paints)
● Floor hardener, Epoxy, Self-level              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall
👉አዲስ የተገነባውን የመቄዶንያ ህንፃ ለማጠናቀቅ 1.7 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተነገረ።

"ሚያዚያን ለመቄዶንያ" በተሰኘ መርሃ ግብር በዚህ ወር የኢትዮ ቴሌኮም ማህበራዊ ትስስር ገፆችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ አረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከል ኢትዮ ቴሌኮም ገቢ አንደሚያደርግ አቶ ቢኒያም በለጠ ተናግሯል።

የተገልጋዮችን ቁጥር 17,500 ወደ 20,000 ለማድረስ እና ሆስፒታል እንዲሆን በማሰብ በ3.5 ቢሊዮን ብር በመገንባት ላይ ያለው ባለ 15 ወለል ያለው ሕንፃ በተጀመረ በ3 ዓመት ውስጥ 2 ቤዝመንት፤ ግራውንድ እና 12 ፎቅ ወደ ላይ በመገንባት በሶስት ዓመት ተኩል የሕንፃው ግንባታውን ወደ ማጠናቀቁ ተቃርበናል ተብሏል። በአሁን ወቅት ህንፃውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ አቶ ቢነያም ተናግሯል።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን በተለይም ደግሞ እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ፣ መመገብ እና መፀዳዳት የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑና የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አረጋውያንንና አዕምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት ጎዳና ላይ በማንሳት 7,500 በላይ የሚሆኑ ተረጂዎችን በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፤ ሻሽመኔ፣ አደዋ፤ ባህርዳር፣ ሐረር፤ ጋምቤላ እና ጎሬ፣ መቱ፣ ጂማ፤ ሰንዳፋ በኬ፣ ሐዋሳ፣ አሶሳ፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ አምቦ፣ ኮረም፣ ሰመራ፣ ሰቆጣ፣ አምደወርቅ፣ ላሊበላ፣ አዲስ ዘመን፤ አምቦ እና አርባምንጭን ጨምሮ በአጠቃላይ በ25 ከተሞች ውስጥ እየስራ ይገኛል።

በቀጣይ ወሊሶ፣ በሱልልታ፣ ሰበታ፣ ደብረ ብርሃን፤ ሆሳዕና፣ ዲላ፣ ጂግጂጋ፣ እና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችን ለመስራት ከወዲሁ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በኢትዮ ቴሌኮም የትስስር ገፆች ላይ በሚቀላቀሉ አዳዲስ ተከታዮች ወይም (Follower) ብዛት 30 ብር እና
በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ እርዳታ ስለሚደረግልን ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሊንክዲን፣ ዩትዩብ፣ ቲክቶክ ይፋዊ የትስስር ገፆች ፎሎው እና ሼር በማድረግ መቄዶንያን ያግዙ! ተብሏል።

@etconp
2024/04/28 13:07:50
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243