Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/DIYAKONAE/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
ትምህርተ ኦርቶዶክስ@DIYAKONAE P.3797
DIYAKONAE Telegram 3797
ኒቆዲሞስ፡የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት

በመ/ር ጌታቸው በቀለ

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሠረት ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በዚህ ሰባተኛው ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኒቆዲሞስ ለተባለ የአይሁድ አለቃ ያስተማረው ትምህርት ይነበባል፣ ይተረጎማል፣ ይዜማል /ዮሐ ፫፥፩-፳፩/፡፡

ኒቆዲሞስ ማን ነዉ?

ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል /ዮሐ ፩-፪/፡፡ በአይሁድ አለቆች ፊትም “ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሣ መርምርና እይ” አሉት እንጂ አልተቀበሉትም /ዮሐ ፯፥፵፰-፶፪/። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ /ዮሐ ፲፱፥፴፱/። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን የፈሪሳውያን አለቃ፣ የኦሪት መምህር ብቻ ሳይሆን የኦሪት ምሁርም ነበር፡፡ በእርሱ ደረጃ የነበሩ ታላላቅ የአይሁድ ምሁራን መንፈሳዊ ሥልጣናቸውና ሹመታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ረስተው በሕዝቡ ላይ የሚመጻደቁ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው ዕውቀትን የሚገልጥ እውነተኛ አምላክ፣ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም ሲገለጥ የአይሁድ ምሁራን የጌታን መገለጥ አልወደዱትም፡፡ የእርሱ ትሕትና የእነርሱን ትዕቢት የሚያጋልጥ ነበርና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሄዱትን ሁሉ ይነቅፉ ይከስሱ ነበር፡፡ ጌታችንም የፈሪሳውያን ሐሳባቸው በግብዝነት የተሞላና ከንቱም እንደሆነ ነግሯቸዋል፡፡ ለደቀመዛሙርቱም ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ የሚበልጥ ሥራን እንዲሰሩ አስጠንቅቋቸዋል /ማቴ.፭፥፳፤ማቴ.፲፮፥፮/፡፡

ኒቆዲሞስ ወደ ጌታችን በሌሊት የሄደዉ ለምንድነው? ለምን በቀን አልሄደም?

ኒቆዲሞስ በመጀመሪያ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው በቀን ሳይሆን በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታችን ከሄደባቸው ምክንያቶች አንዱ በቀን መሄድን ስለፈራ ነው። ለዚህም የቤተ ክርሰቲያን አባቶች በዋናነት ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ፡፡ የመጀመሪያው የአይሁድ መምህር ሆኖ ሳለ በቀን በሕዝብ ፊት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መማር ስላፈረ ነው የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አይሁድ “ከእኛ ወገን በክርስቶስ ያመነ ቢኖር ከምኩራብ ይሰደድ” የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ነበርና ያንን ፈርቶ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ፍራቻዎች ኒቆዲሞስን ወደ ክርስቶስ ከመምጣት አላገዱትም፡፡
ኒቆዲሞስ በርቀት በአደባባይ ድንቅ ተአምራትን ሲያደርግ ያየውን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀርቦ መጠየቅ መማር ፈልጓል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው ተአምራት የተረዳው ነገር ቢኖርም ቀርቦ ደግሞ ከእርሱ ከራሱ ስለማንነቱ መስማት ፈልጓል፡፡ ወደ ክርስቶስም ቀርቦ “መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን” አለው /ዮሐ.፫፥፪/፡፡
ኒቆዲሞስ ግን ከእነዚህ ከፈሪሳዊያን መካከል የተገኘ ልዩ ምሁረ ኦሪት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ራሱን ለእውነት ልቡን ለእምነት አዘጋጅቶ ከሁሉ ቀድሞ በሌሊት ክርስቶስን ፍለጋ የመጣ ከእነዚህ ፈሪሳዊያን ወገን ተለይቶ ወደ ጽድቅ መንገድ የተጠራ ነው፡፡ ሹመት እያለው ሁሉ ሳይጎድልበት በዙርያው የነበሩት ከእኛ በላይ ማን አዋቂ አለ የሚሉ ከእውነት ጋር የተጣሉ ጌታችንን የሚያሳድዱ በእርሱም የሚቀኑና ጌታችንንም ለመግደልም ዕለት ዕለት የሚመክሩ ሁነው ሳለ ኒቆዲሞስ ግን እውነትን ለማወቅ እልቅናው ሳይታሰበው፣ ከአካባቢው ጋር መመሳሰልን ሳይመርጥ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሊማር በሌሊት መጣ፡፡ መምህረ ትሕትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የኒቆዲሞስን ትሕትናውን ተቀብሎ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትውልድ ሁሉ የሚማርበትን ረቂቁን ምስጢረ ጥምቀትን አስተማረው፡፡

ዳግመኛ የመወለድ ምስጢር

ኒቆዲሞስ ዳግመኛ የመወለድን ምስጢርን ለማወቅ ልቡናውን ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ ኒቆዲሞስ በመጀመርያ የጥምቀትን ነገር ሲሰማ ለመቀበል ተቸግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ግን የኒቆዲሞስን አመጣጥ በማየት ልቡናውንም ከፍ ከፍ ስላደረገ ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት፡፡ “ቅዱሱን ማወቅ ማስተዋል ነው” ተብሎ በምሳሌ መጽሐፍ እንደተጻፈ /ምሳ 9፥11/ ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ኅብረት ወጥቶ በትሕትና ወንጌልን ለመማር፣ በሃይማኖት ልቡናውን ለእግዚአብሔር ቃል አዘጋጀ፡፡ ለአብርሃም የግዝረትን ጸጋ የሰጠ ጌታ በትሕትና ለቀረበው ኒቆዲሞስ የግዝረት ጸጋ ፍጻሜ የሆነች የልጅነት ጥምቀትን ነገር አስተምሮታል፡፡

ኒቆዲሞስ ወደ መድኃኔዓለም ለመማር የሄደው በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሚታሰብበት የዐቢይ ጾም ሰንበት በጸሎተ ቅዳሴ የሚዜመው የክቡር ዳዊት መዝሙር “በሌሊት ጎበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፣ ፈተንኸኝ፣ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር” ይህን የሚያስረዳ ነው /መዝ.፲፮፥፫/፡፡ ሌሊት በባሕሪው ሕሊናን ለመሰብሰብ በተመስጦ ለመማር የሚመች ነው፡፡ ክርስትናም በተጋድሎ ሕይወት በመትጋት ሥጋን በቀንና ሌሊት ለነፍስ እንዲገዛ በማድረግ የሚኖር ሕይወት ነው፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱን “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያንም በቀንና በሌሊት በኪዳኑ በቅዳሴው በማህሌቱ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡

ዮሐንስ ወንጌላዊ ይህንን የኒቆዲሞስን ምስክርነት “ከእነርሱ አንዱ በሌሊት ቀድሞ ወደ እርሱ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው። እነርሱም መለሱና፡- አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።” በማለት ገልጾታል /ዮሐ.፯፥፶-፶፪/፡፡ ኒቆዲሞስ ያለፍርሐትና ያለ ሀፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል፡፡ ካህናቱን መጽሐፍ ጠቅሶ እውነትን ተናግሮ አሳፍሯቸዋል፡፡ ኒቆዲሞስ እስከ መጨረሻው በመጽናት ለታላቅ ክብር በቃ፡፡

tgoop.com/DIYAKONAE/3797
Create:
Last Update:

BY ትምህርተ ኦርቶዶክስ

Share with your friend now:
tgoop.com/DIYAKONAE/3797

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Select: Settings – Manage Channel – Administrators – Add administrator. From your list of subscribers, select the correct user. A new window will appear on the screen. Check the rights you’re willing to give to your administrator. Telegram is a leading cloud-based instant messages platform. It became popular in recent years for its privacy, speed, voice and video quality, and other unmatched features over its main competitor Whatsapp. As the broader market downturn continues, yelling online has become the crypto trader’s latest coping mechanism after the rise of Goblintown Ethereum NFTs at the end of May and beginning of June, where holders made incoherent groaning sounds and role-played as urine-loving goblin creatures in late-night Twitter Spaces. “[The defendant] could not shift his criminal liability,” Hui said. Private channels are only accessible to subscribers and don’t appear in public searches. To join a private channel, you need to receive a link from the owner (administrator). A private channel is an excellent solution for companies and teams. You can also use this type of channel to write down personal notes, reflections, etc. By the way, you can make your private channel public at any moment.
from us

Telegram ትምህርተ ኦርቶዶክስ
FROM American