#መጋቢት_27
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለአባታችንና ለአምላካችን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
✞ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም - ክ ር ስ ቶ ስ ✞
ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈፀመው የማዳን ስራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት።
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፤ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት።
ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዘበቱበት።
ራሱንም በዘንግ መቱት።
እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ። በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ገረፉት።
ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። ሰባት ታላላቅ ታአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ። ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ።
በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አስራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።
በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍጹም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ።
ለእኛ ለኃጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኀማማቱ፤ አምስቱ ቅንዋቱ፤ ስለ ቅዱስ መስቀሉ፤ ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን።
-------------------------------------------
"በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ። ሕማማችንንም ተሸክሟል። እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ። ስለ በደላችንም ደቀቀ። የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ። በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳ ፶፫፥፬-፭)
<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>
#ስንክሳር_ዘወርሃ_መጋቢት
ይቀላቀሉ ሌሎችንም ይጋብዙ!
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE

Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
ኒቆዲሞስ፡የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት
በመ/ር ጌታቸው በቀለ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሠረት ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በዚህ ሰባተኛው ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኒቆዲሞስ ለተባለ የአይሁድ አለቃ ያስተማረው ትምህርት ይነበባል፣ ይተረጎማል፣ ይዜማል /ዮሐ ፫፥፩-፳፩/፡፡
ኒቆዲሞስ ማን ነዉ?
ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል /ዮሐ ፩-፪/፡፡ በአይሁድ አለቆች ፊትም “ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሣ መርምርና እይ” አሉት እንጂ አልተቀበሉትም /ዮሐ ፯፥፵፰-፶፪/። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ /ዮሐ ፲፱፥፴፱/። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።
ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን የፈሪሳውያን አለቃ፣ የኦሪት መምህር ብቻ ሳይሆን የኦሪት ምሁርም ነበር፡፡ በእርሱ ደረጃ የነበሩ ታላላቅ የአይሁድ ምሁራን መንፈሳዊ ሥልጣናቸውና ሹመታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ረስተው በሕዝቡ ላይ የሚመጻደቁ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው ዕውቀትን የሚገልጥ እውነተኛ አምላክ፣ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም ሲገለጥ የአይሁድ ምሁራን የጌታን መገለጥ አልወደዱትም፡፡ የእርሱ ትሕትና የእነርሱን ትዕቢት የሚያጋልጥ ነበርና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሄዱትን ሁሉ ይነቅፉ ይከስሱ ነበር፡፡ ጌታችንም የፈሪሳውያን ሐሳባቸው በግብዝነት የተሞላና ከንቱም እንደሆነ ነግሯቸዋል፡፡ ለደቀመዛሙርቱም ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ የሚበልጥ ሥራን እንዲሰሩ አስጠንቅቋቸዋል /ማቴ.፭፥፳፤ማቴ.፲፮፥፮/፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ ጌታችን በሌሊት የሄደዉ ለምንድነው? ለምን በቀን አልሄደም?
ኒቆዲሞስ በመጀመሪያ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው በቀን ሳይሆን በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሌሊት ወደ ጌታችን ከሄደባቸው ምክንያቶች አንዱ በቀን መሄድን ስለፈራ ነው። ለዚህም የቤተ ክርሰቲያን አባቶች በዋናነት ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ፡፡ የመጀመሪያው የአይሁድ መምህር ሆኖ ሳለ በቀን በሕዝብ ፊት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መማር ስላፈረ ነው የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አይሁድ “ከእኛ ወገን በክርስቶስ ያመነ ቢኖር ከምኩራብ ይሰደድ” የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ነበርና ያንን ፈርቶ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ፍራቻዎች ኒቆዲሞስን ወደ ክርስቶስ ከመምጣት አላገዱትም፡፡
ኒቆዲሞስ በርቀት በአደባባይ ድንቅ ተአምራትን ሲያደርግ ያየውን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀርቦ መጠየቅ መማር ፈልጓል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው ተአምራት የተረዳው ነገር ቢኖርም ቀርቦ ደግሞ ከእርሱ ከራሱ ስለማንነቱ መስማት ፈልጓል፡፡ ወደ ክርስቶስም ቀርቦ “መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን” አለው /ዮሐ.፫፥፪/፡፡
ኒቆዲሞስ ግን ከእነዚህ ከፈሪሳዊያን መካከል የተገኘ ልዩ ምሁረ ኦሪት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ራሱን ለእውነት ልቡን ለእምነት አዘጋጅቶ ከሁሉ ቀድሞ በሌሊት ክርስቶስን ፍለጋ የመጣ ከእነዚህ ፈሪሳዊያን ወገን ተለይቶ ወደ ጽድቅ መንገድ የተጠራ ነው፡፡ ሹመት እያለው ሁሉ ሳይጎድልበት በዙርያው የነበሩት ከእኛ በላይ ማን አዋቂ አለ የሚሉ ከእውነት ጋር የተጣሉ ጌታችንን የሚያሳድዱ በእርሱም የሚቀኑና ጌታችንንም ለመግደልም ዕለት ዕለት የሚመክሩ ሁነው ሳለ ኒቆዲሞስ ግን እውነትን ለማወቅ እልቅናው ሳይታሰበው፣ ከአካባቢው ጋር መመሳሰልን ሳይመርጥ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሊማር በሌሊት መጣ፡፡ መምህረ ትሕትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የኒቆዲሞስን ትሕትናውን ተቀብሎ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትውልድ ሁሉ የሚማርበትን ረቂቁን ምስጢረ ጥምቀትን አስተማረው፡፡
ዳግመኛ የመወለድ ምስጢር
ኒቆዲሞስ ዳግመኛ የመወለድን ምስጢርን ለማወቅ ልቡናውን ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ ኒቆዲሞስ በመጀመርያ የጥምቀትን ነገር ሲሰማ ለመቀበል ተቸግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ግን የኒቆዲሞስን አመጣጥ በማየት ልቡናውንም ከፍ ከፍ ስላደረገ ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት፡፡ “ቅዱሱን ማወቅ ማስተዋል ነው” ተብሎ በምሳሌ መጽሐፍ እንደተጻፈ /ምሳ 9፥11/ ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ኅብረት ወጥቶ በትሕትና ወንጌልን ለመማር፣ በሃይማኖት ልቡናውን ለእግዚአብሔር ቃል አዘጋጀ፡፡ ለአብርሃም የግዝረትን ጸጋ የሰጠ ጌታ በትሕትና ለቀረበው ኒቆዲሞስ የግዝረት ጸጋ ፍጻሜ የሆነች የልጅነት ጥምቀትን ነገር አስተምሮታል፡፡
ኒቆዲሞስ ወደ መድኃኔዓለም ለመማር የሄደው በሌሊት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በሚታሰብበት የዐቢይ ጾም ሰንበት በጸሎተ ቅዳሴ የሚዜመው የክቡር ዳዊት መዝሙር “በሌሊት ጎበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፣ ፈተንኸኝ፣ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር” ይህን የሚያስረዳ ነው /መዝ.፲፮፥፫/፡፡ ሌሊት በባሕሪው ሕሊናን ለመሰብሰብ በተመስጦ ለመማር የሚመች ነው፡፡ ክርስትናም በተጋድሎ ሕይወት በመትጋት ሥጋን በቀንና ሌሊት ለነፍስ እንዲገዛ በማድረግ የሚኖር ሕይወት ነው፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱን “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያንም በቀንና በሌሊት በኪዳኑ በቅዳሴው በማህሌቱ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡
ዮሐንስ ወንጌላዊ ይህንን የኒቆዲሞስን ምስክርነት “ከእነርሱ አንዱ በሌሊት ቀድሞ ወደ እርሱ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው። እነርሱም መለሱና፡- አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምርና እይ አሉት። እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ሄደ።” በማለት ገልጾታል /ዮሐ.፯፥፶-፶፪/፡፡ ኒቆዲሞስ ያለፍርሐትና ያለ ሀፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል፡፡ ካህናቱን መጽሐፍ ጠቅሶ እውነትን ተናግሮ አሳፍሯቸዋል፡፡ ኒቆዲሞስ እስከ መጨረሻው በመጽናት ለታላቅ ክብር በቃ፡፡

ኒቆዲሞስም ከጌታችን በተማረው ትምህርት ጸንቶ ለመኖር የበቃ አባት ነው፡፡ የሃይማኖቱ ጽናትም በተግባር የተፈተነ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የአይሁድን ድንፋታ ሳይፈራ “እሱን ያገኘ ያገኘኛል” ሳይል በድፍረት የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን በንጹሕ የተልባ እግር በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር፣ በጌቴሴማኒ የቀበረ ሰው ነው /ዮሐ.፲፱፥፴፰/፡፡ ኒቆዲሞስ ከሐዲስ ኪዳን ካህናት ቀድሞ የጌታችንን ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው ክቡር ሥጋ ለመገነዝ የበቃ አባት ነው፡፡ የጌታችንን ክቡር ሥጋ ገንዘው ሲቀብሩም በጸናች የተዋሕዶ እምነት ጌታ እንደገለጠላቸው “ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል፣ ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት” የሚለውን ቤተክርስቲያናችን እስከ ዕለተ ምጽአት የክርስቶስን ሥጋና ደም ስትባርክ የምትጠቀምበትን ጸሎት እስከ ፍጻሜው እየጸለዩ ነበር፡፡ በዚህም ኒቆዲሞስ ከሐዲስ ኪዳን ካህናት ቀድሞ ምስጢረ ጥምቀትን ከጌታ እንደተማረ፣ የሐዲስ ኪዳንን የምስጢራት አክሊል ምስጢረ ቁርባንንም እንዲሁ ተማረ፡፡ ይህንንም በሚመለከት ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ አብሮት ይቀድስ የነበረውን ንፍቅ ካህን በባረከበት አንቀጽ “በዚህ ምስጢር እየተራዳኝ ከእኔ ጋር ያለ ይህንን ካህን እርሱንም እኔንም ሥጋህን እንደገነዙት እንደ ዮሴፍና እንደ ኒቆዲሞስ አድርገን” /ቅዳሴ ማርያም፤ ቁ.115/ ብሏል፡፡
እንደ ማጠቃለያ
እኛም እንደ ኒቆዲሞስ በዕውቀታችን፣ በሥልጣናችን፣ በሀብታችን፣ ባለን ማንነት ሳንታበይ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ የእውነተኛ አባቶችን ትምህርት፣ ምክርና ተግሣጽ ልናዳምጥ በተግባርም ልናውለው ይገባናል፡፡ ምድራዊ አመክንዮ ሳያሰናክለን በቀንና በሌሊት ወደ አማናዊት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለምስጋና መሄድ ይኖርብናል፡፡ ክርስትና ምድራዊ ስጦታና ተዓምራት በሚገለጥበት በገሊላ ባሕር አጠገብ ብቻ ሳይሆን መከራና ስቃይ ባለበት በቀራንዮም መገኘትን ይጠይቃል፤ በፈተናና በመከራ ጊዜም ቢሆን በእምነት ልንጸና የበለጠም በመታመን ልናገለግል ይገባል፡፡
ከኒቆዲሞስ ሕይወት ተምረን በሃይማኖት እንድንጸና የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል” /ማር.፲፮፥፮/ በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ ይፍቀድልን፤ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፤ አሜን፡፡
ምንባባት ኒቆዲሞስ
መልዕክታት
✍️ ሮሜ ፯፥፩-፲፱
✍️ 1ኛ ዮሐ.፬፥፲-ፍጻ
ግብረ ሐዋርያት
✍️ ሐዋ.ሥራ ፭፥፴፬—ፍጻ
ምስባክ
✍️ መዝ.፲፮÷፫
ሐውጽከኒ ሌሊት ወፈተንኮ ለልብየ፥
አመከርከኒ ወኢተረክበ አመጻ በላዕሌየ፤
ከመ ኢያንብብ አፍየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው
ትርጉም፦ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፡፡
ወንጌል
✍️ ዮሐ.፫÷፩-፳
የዕለቱ ቅዳሴ
✍️ ቅዳሴ እግዚእ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ሃይማኖተ አበው
✍️ ቅዳሴ ማርያም
✍️ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት

Forwarded from Elohe pictures ♱ (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM

ሆሣዕና በአርያም = እንኳን አደረሳችሁ!
☞ የዐቢይ ጾም ፰ኛ ሳምንት #ሆሣዕና
✔ የዕለቱ መዝሙራት፣ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል
❖ የሆሣዕና ዋዜማ /የቅዳሜ ማታ መዝሙር
«ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ።»
ትርጉም፦
የፋሲካ በዓል ሳምንት ሲቀረው የእውነተኛ አምላክ ደቀ መዛሙርት የእግዚአብሔር ሀገር ወደ ሆነችው ደብረ ዘይት ቁልቁለት ሲደርሱ ወደ እርሱ ለመታዘዝ ቀረቡ፤ ብዙ ሕዝብ፣ ልጆችና ሽማግሌዎችም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ተጭኖ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸው ዘንድ በፍጹም ደስታ ኢየሩሳሌም ገባ።
#መልዕክታት
➊. ዕብራ. ፰:፩-ፍጻሜ /8÷1-ፍጻሜ
ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን። (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➋. ፩ኛ ጴጥ.፩÷፲፫ እስከ ምዕ ፪÷፲፩
ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➌. ግብረ ሐዋርያት
የሐዋ. ፰:፳፮-ፍጻሜ /8÷26-ፍጻሜ
የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን
ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው
መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ፡፡
በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡
እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ፡፡
ትርጉም፦
በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና÷
(መዝ.፹÷፫)
.
✝ ወንጌል
ዮሐ.፲፪÷፩-፲፩
ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
፠ የሌሊት ሆሣዕና
+ ምስባክ
ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር።
ባረክናክሙ እምቤተ እግዚእብሔር፡፡ እግዚእብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ፡፡
ትርጉም፦
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤
ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ፡፡
ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤
(መዝ.፻፩፯÷፳፮)
.
✝ ወንጌል
ሉቃ.፲፱÷፩-፲፩
ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢያራኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር፡፡ እነሆ÷ የቀራጮች አለቃ ስሙ ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤
(ተጨማሪውን ያንብቡ)
✞ ዘነግህ
(በጊዜ ዑደት ውስተ ቤተ መቅደስ)
+ ምስባክ
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር።
ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ ኢየሩሳሌም።
ኢየሩሳሌምሰ ሕንፅት ከመ ሀገር።
ትርጉም፦
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝ ደስ አለኝ፡፡
ኢየሩሳሌም ሆይ÷ እግሮቻችን በአደባባዮችሽ ቆሙ፡፡
ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት፡፡
(መዝ ፻፳፩ ፣ ፩ /121፥1)
+ ወንጌል
ማቴ. ፳፥፳፱-ፍጻሜ
ከኢያሪኮም በወጣ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተከተሉት፡፡ እነሆ÷ ሁለት ዕውራን በመንገድ አጠገብ ተቀምጠው ነበር፤ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር፡፡
ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን :-
እስመ አጽንዐ መናስግተ ኆኃትኪ፡፡
ትርጉም:-
ኢየሩሳሌም ሆይ÷ እግዚአብሔርን አመስግኚ÷
ጽዮንም ሆይ÷ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጸንቶአልና÷
መዝ.፻፵፯÷፩
.
★ ወንጌል
ማርቆስ ፲፥፵፮-ፍጻሜ
ወደ ኢያሪኮም ገባ፤ ከኢያሪኮም በወጣ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ብዙ ሰውም ነበረ፤ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
+ ምስባክ
ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት፣
በኃበ እለ ያስተሐምምዎ፣
አስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ።
ትርጉም፦
ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤
እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በሚያስተነትኑበት በደስታ በዓልን አድርጉ፡፡
(መዝ ፻፲፯፥፳፯)
.
+ ወንጌል
ማቴዎስ ፱፥፳፮ እስከ ምዕ ፲÷፲፰
.
☞መዝሙር => ዘምዕዋድ
አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ እስመ እምጽዮን ይወጽእ ሕገ ወቃለ እግዚአብሔር እምኢየሩሳሌም ንሣለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን
.
☞መዝሙር => <<ሰመያ አብርሃም>>
ሰመያ አብርሃም ወይቤላ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ በዕምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
.
☞መዝሙር => ወትቤ ጽዮን
ወትቤ ጽዮን አርኅው ሊተ አናቅጸ ይባኡ ሕዝብ ብዝዙኃን ወያዕትቱ ዕብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
.
✝ መዝሙር => "ባርኮ ያዕቆብ"
ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽእ እምኔከ ዘየሐጽብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦሙ ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም
.
★+መልዕክታት
➊ ዕብራ ፱÷፲፩-ፍጻሜ
ክርስቶስ ግን ለምትመጣይቱ መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ÷ የሰው እጅ ወደ አልሠራት÷ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➋1ኛጴጥ ፬÷፩-፲፪
ክርስቶስ ስለ እኛ በሥጋው ከተሰለቀ÷ እናንተም ይህቺን ዐሳብ ጋሻ አድርጋችሁ ኑሩ፤ በሥጋዉ መከራ የተቀበለ ከኀጢአት ድኖአልና፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
➌ የሐዋ/ሥራ ፳፰÷፲፩-ፍጻሜ
ከሦስት ወር በኋላም በዚያች ደሴት ወደ ከረመችው ወደ እስክንድርያ መርከብ ወጣን፤ በዚያች መርብ ላይም የዲዮስቆሮስ ምልክት ነበረባት፤ ይኸውም “የመርከበኞች
አምላክ” የሚሉት ነው፡፡ (ተጨማሪውን ያንብቡ)
.
✞ ምስባክ
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ፡፡
በእንተ ጸላዒ፡፡
ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡
ትርጉም፦
ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡
ስለ ጠላት÷
ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡
(መዝ ፰:፪ /8÷2)
.
+ ወንጌል
ዮሐንስ ፭÷፲፩-፴፩ /5÷11-31
እርሱም መልሶ÷ “ያዳነኝ እርሱ፡- አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” አላቸው፡፡ አይሁድም... (ተጨማሪውን ያንብቡ)
✞ ቅዳሴ = ዘጎርጎርዮስ (ነአኵቶ) [በዕዝል ዜማ]
♦-♥ መልካም የሆሣዕና በዓል ♥ -♦

Forwarded from Elohe pictures ♱ (࿈ ᙘᴇꋊɪ ፲፮ ♱¹²)
ውድ የቻናላችን ተከታዮች
ከዚህ በፊት በጠየቃችሁን መሰረት የአብነት ትምህርት
ምርጫችሁን ያደረጋችሁ በመመዝገብ በብፁዕነታቸው አማካኝነት በነፃ አብነት መማር ትችላላችሁ
👉ቅኔ
👉አቋቋም
👉ጾመ ድጓ/ምዕራፍ ወይስ ሌላ...
ምን እከፍላለው ብለው ሳይጨነቁ ፣ ያለ ምንም ክፍያ ልናስተምሮት በonline ዝግጅታችንን ጨርሰናል !!!
ሰፊ ማብራርያ የምትፈልጉ
👇👇👇👇👇👇👇
@Kinfemikael12
ማነጋገር ትችላላችሁ
በተጨማሪ
👉 የፈለጉትን ትምህርት ቀለል ባለ መንገድ እና በአጭር ጊዜ ለማስጨረስ የራሳችን ማስተማሪያ መንገድ አዘጋጅተን እየጠበቅናችሁ ነው
👉 በእያንዳንዱ ጉባኤም ከ50 በላይ ተማሪ ስለማንቀበል ሳይሞላብዎት በፍጥነት ይመዝገቡ🙏
https://www.tgoop.com/Abnetschoolcalifornia

👉 ልዩ ዕለት
የዛሬቱ ዕለት ከሁሉም ዕለታት ልዩ ዕለት ናት የድንቅ ምሥጢር መገለጫ ልዩ ዕለት
ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ እንዲል ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይይዙታል ማለትም በሰባቱ ዕለታት ተፈጥረው የተመለኩ ፍጥረታት የአምላክን አምላክነት ይመሰክራሉ ማለት ነው የመሰከሩባት ልዩ ዕለት
አንድም ሰባቱ ተአምራት ተፈጽመው ጌትነቱን የሚሰብኩባት ልዩ ዕለት
➟ ፀሐይ የጨለመባት ልዩ ዕለት
➟ጨረቃ በደም የታጠበችባት ልዩ ዕለት
➟ከዋክብትም ጽናተቸውን የለቀቁባት ልዩ ዕለት
➟ካምስት መቶ ብቅ ከስድስት መቶ ዝቅ የሚሉ ሙታን ከመስቀሉ እግርጌ እንደ አሸን የፈሉባት ልዩ ዕለት
➟ መቃብራት የተከፈቱባት ሙታን የተነሱባት ልዩ ዕለት
➟ ድንጋዮች የተፈተቱባት ልዩ ዕለት
➟የቤተ መቅደሱ ከሦስት ካራት የተቀደደባት ልዩ ዕለት
➣ መድኀን ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በፈቃዱ የለየባት ልዩ ዕለት
➣ ምእመንንም የሞሸረባት ልዩ ዕለት
➣ እጁን በደም ነክሮ ለኖረ ሽፍታ ወንበዴም ምሕረት የወረደባት
➣ገነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችባት ልዩ ዕለት ወዘተርፈ
በአጠቃላይ ከሰው ልጆች ይልቅ ደግሞ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታት እግዚአብሔርነቱን የመሰከሩባት ልዩ ዕለት ናት
➣ እኛስ የፀሐይን ያህል መስክረን ይሆን ?
የጨረቃን ያህልስ እንባ አልቅሰን ደም ደም አልቅሰን እዝኅ በማለቅስ በእንባ በደም በመራጨት መስክረን ይሆን ?
የከዋክብትን ያህልስ መስክረን ይሆን ?
የሙታንን ያህልስ
የድንጋዮችን ያህልስ ልባችን ተሰንጥቆ ይሆን ?
የመጋረጃውን ያህል ምን ያህል ተብሰክስከን ይሆን ?
➟ ነገሩስ ከእነዚህ ሁሉ እንደምናንስ ምንም እንደማይሰማን ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ገልጾታል
እስኪ እንስማው
"ፀሐይ ሰኢኖ ጽዕለተ እግዚእ ጸዊረ ብርሃኖ ለጽልመት ሜጠ ወንሕነሰ እም ጽልመት አከይነ ወኢ እምልብነ ንፈቱ ንትነሳሕ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ ርእሶ ሰጠጠ ወንሕነሰ በእንተ ኀጢአትነ ኢተነሳሕነ ወኢ በልብነ ንፈቱ አጻብአ ፈረስ ወፀር ተንሢኦሙ አማሰኑ ብሔረነ ከመ ለእግዚአብሔር ፈሪሀነ ውስተ ንስሓ ንግባእ ወበዘሂ ኢተነሳሕነ ወኢደንገፅነ ንትነሳሕ እንከ"
➟ትርጉም
ፀሐይ እንኳ የጌታውን ስድብ መሸከም ተስኖት ብርሃኑን ወደጨለማ ለውጧል እኛ ግን ከጨለማ ከፍተናል ከልባችንም ንስሓ ለመግባት አልወድም የቤተ መቅደሱም መጋረጃ በደል ሳይኖርበት ራሱን ቀዷል እኛ ግን ስለኀጢአታችን ከልባችን ንስሓ ለመግባት አንወድም እግዚአብሔርንም በመፍራት ንስሓ ወደንስሓ እንድንመለስ የጠላትና የፈረስ እጣቶች ተነስተው ሀገራችንን አጥፍተዋል በዚህም ንስሓ አልገባንም ንስሓ ለመግባትም እንግዲህ አልደነገጥንም ።
ወንበዴውን የማረ ጌታ ይማረን
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
የዛሬቱ ዕለት ከሁሉም ዕለታት ልዩ ዕለት ናት የድንቅ ምሥጢር መገለጫ ልዩ ዕለት
ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ እንዲል ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይይዙታል ማለትም በሰባቱ ዕለታት ተፈጥረው የተመለኩ ፍጥረታት የአምላክን አምላክነት ይመሰክራሉ ማለት ነው የመሰከሩባት ልዩ ዕለት
አንድም ሰባቱ ተአምራት ተፈጽመው ጌትነቱን የሚሰብኩባት ልዩ ዕለት
➟ ፀሐይ የጨለመባት ልዩ ዕለት
➟ጨረቃ በደም የታጠበችባት ልዩ ዕለት
➟ከዋክብትም ጽናተቸውን የለቀቁባት ልዩ ዕለት
➟ካምስት መቶ ብቅ ከስድስት መቶ ዝቅ የሚሉ ሙታን ከመስቀሉ እግርጌ እንደ አሸን የፈሉባት ልዩ ዕለት
➟ መቃብራት የተከፈቱባት ሙታን የተነሱባት ልዩ ዕለት
➟ ድንጋዮች የተፈተቱባት ልዩ ዕለት
➟የቤተ መቅደሱ ከሦስት ካራት የተቀደደባት ልዩ ዕለት
➣ መድኀን ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በፈቃዱ የለየባት ልዩ ዕለት
➣ ምእመንንም የሞሸረባት ልዩ ዕለት
➣ እጁን በደም ነክሮ ለኖረ ሽፍታ ወንበዴም ምሕረት የወረደባት
➣ገነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችባት ልዩ ዕለት ወዘተርፈ
በአጠቃላይ ከሰው ልጆች ይልቅ ደግሞ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታት እግዚአብሔርነቱን የመሰከሩባት ልዩ ዕለት ናት
➣ እኛስ የፀሐይን ያህል መስክረን ይሆን ?
የጨረቃን ያህልስ እንባ አልቅሰን ደም ደም አልቅሰን እዝኅ በማለቅስ በእንባ በደም በመራጨት መስክረን ይሆን ?
የከዋክብትን ያህልስ መስክረን ይሆን ?
የሙታንን ያህልስ
የድንጋዮችን ያህልስ ልባችን ተሰንጥቆ ይሆን ?
የመጋረጃውን ያህል ምን ያህል ተብሰክስከን ይሆን ?
➟ ነገሩስ ከእነዚህ ሁሉ እንደምናንስ ምንም እንደማይሰማን ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ገልጾታል
እስኪ እንስማው
"ፀሐይ ሰኢኖ ጽዕለተ እግዚእ ጸዊረ ብርሃኖ ለጽልመት ሜጠ ወንሕነሰ እም ጽልመት አከይነ ወኢ እምልብነ ንፈቱ ንትነሳሕ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ ርእሶ ሰጠጠ ወንሕነሰ በእንተ ኀጢአትነ ኢተነሳሕነ ወኢ በልብነ ንፈቱ አጻብአ ፈረስ ወፀር ተንሢኦሙ አማሰኑ ብሔረነ ከመ ለእግዚአብሔር ፈሪሀነ ውስተ ንስሓ ንግባእ ወበዘሂ ኢተነሳሕነ ወኢደንገፅነ ንትነሳሕ እንከ"
➟ትርጉም
ፀሐይ እንኳ የጌታውን ስድብ መሸከም ተስኖት ብርሃኑን ወደጨለማ ለውጧል እኛ ግን ከጨለማ ከፍተናል ከልባችንም ንስሓ ለመግባት አልወድም የቤተ መቅደሱም መጋረጃ በደል ሳይኖርበት ራሱን ቀዷል እኛ ግን ስለኀጢአታችን ከልባችን ንስሓ ለመግባት አንወድም እግዚአብሔርንም በመፍራት ንስሓ ወደንስሓ እንድንመለስ የጠላትና የፈረስ እጣቶች ተነስተው ሀገራችንን አጥፍተዋል በዚህም ንስሓ አልገባንም ንስሓ ለመግባትም እንግዲህ አልደነገጥንም ።
ወንበዴውን የማረ ጌታ ይማረን
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
ቅዳሜ፡–
ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡
የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ።
ጠዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡
ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡
ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡
ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡
በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል።

ብቻህን ማሰብ ስትጀምር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የብቻችን የሆነ ትምህርት የለም። በማኅበር እንማራለን ፤ በማኅበር እንጸልያለን ፤ አንድ ሆነን የተዘጋጀልንን ማዕድ ቅዱስ ቊርባን እንቀበላለን ፤ በመጨረሻም የተዘጋጀልንን የተስፋ አገር እንቀበላለን።
ክርስቶስ ያስተማረ በጉባኤ ነው ፤ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም ጉባኤአዊት ሆና ትቀጥላለች እንጅ ማንም ምንም ቢሆን የራሱን ትምህርት አምጥቶ ሊያስተምር የሚችልበት ዕድል የለውም።
የብቻው የሆነ ክርስቶስ ስለሌለው የብቻው የሆነ ትምህርትም ሊኖረው አይችልም።
ብቻህን ማሰብ ከጀመርህ ከጉባኤው የተለየ አስተምህሮ ማምጣትህ ስለማይቀር “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” የሚለውን የሃይማኖት መግለጫ አስቀድመን እንድናውቅ መደረጉ ስለዚህ ነው።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚኖር ማንም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ካስተማረችው ትምህርት የወጣ እንደሆነ መዐርጉ ፣ የዕውቀት ደረጃው ፣ የወገኑ የሀብቱ ብዛት ሊያድነው አይችልም። በመጀመሪያ ከቃሉ የሰሙ ሰዎች “የተናገርኸውን ትምህርት አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ብለው ይመክሩታል። ምክራቸውን ሰምቶ በዚህ ካቆመ ይተዉታል፤ ምክራቸውን አልሰማ ብሎ ከቀጠለ ግን ወደ መምህራን ያደርሱታል፤ መምህራንንም አልሰማ ካለ ወደ ጉባኤ {ሲኖዶስ} ይቀርባል። ሲኖዶሱን ካልሰማ ተወግዞ ይለያል።
በሰሞኑ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሰጡትን ትምህርት በቪዲዮ አንዲት ወዳጄ ልካልኝ ተመለከትሁት፤ ምናልባት ከባልንጀሮቻቸው ጋር ተማክረውበት ከበታቾቻቸውም ጋር ተከራክረውበት የነበረ ጉዳይ ከሆነ “አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ሊሏቸው ይገባ ነበር።
አሁን ግን በሹክሹክታ ሳይሆን በሰገነት ላይ የተሰበከ የስሕተት ስብከት ስለሆነ ጉዳዩ ከዚህ ያለፈ ይመስለኛል። ከረፈደም ቢሆን ባየሁት መረጃ መሠረት ብዙ ሊቃውንት ሀሳብ ሰጥተውበታል ፤ ይሄ ለብፁዕነታቸው መልካም ዕድል ነው ብየ አምናለሁ። ሀሳባቸውን የገለጹ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን በሊቅነታቸው የምታምንባቸው ሊቃውንት እንደመሆናቸው መጠን ምክሩን ይቀበሉታል ብየ ስለማምን ነው። ሀሳቡን ሳይንቁ በቶሎ በሰገነት ላይ ያጠፉትን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሰገነት ላይ ወጥተው ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። “አትደንግጡ” ብለውናል እንዳንደነግጥ ያድርጉን።
ይህንን ትምህርት አባቶቻችን አልነገሩንም መጻሕፍቶቻችን ላይ ተጽፎ አላገኘነውም።
ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ መጻሕፍቶቻችንን አባቶቻችንን ተቃውመዋል። ዛሬ መልስ አልጽፍም፤ ምክንያቱም መልሱን ከብፁዕነትዎ ስለምጠብቅ ነው።
ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ

Forwarded from ማኅቶት Wave
✅❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
መልካም ዕድል!!!
https://www.tgoop.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk

🕊
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን
🕊 ልደታ ለማርያም ድንግል 🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
† ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: †
[ ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) ]
የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::
ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::
እመቤታችን ከአዳም ስሕተት ብኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: [ኢሳ.፩፥፱]
ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ፳፻፳፪ [2,022] ዓመታት በፊት ተወልዳለች::
"ሙሽራዬ ሆይ ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" [መኃልይ.፬፥፰]
ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ [አሮን] የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር::
ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::
ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ፵ [40] ቀናትም ሲጸልይ ቆየ:: በ፵ [40] ኛው ቀን ፪ [2] ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::
እርሷ ደግሞ :- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ፯ [7] ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::
በ፯ [7] ኛው ቀን [ማለትም ነሐሴ ፯ (7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::
እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: [ቅዳሴ ማርያም]
"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል [ያለ ጥፋት] ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." [መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ.፩፥፱]
እመቤታችን ነሐሴ ፯ [ 7 ] ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች::
የእመቤታችን የዘር ሐረግ :-
- አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
- በእናቷ :-
ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::
- በአባቷ በኩል :-
-ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::
ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::
የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::
አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ ግቢ ጉባዔ ሥነ ሥዕል ክፍል ገጽ የተወሰደ

🎬 ምን አይነት የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ፊልም እና ጥቅሶች ይፈልጋሉ❓️
🎬 JOIN አዳምና ሔዋን ሙሉ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN አቡነ ተክለሃይማኖት ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN ጠቢቡ ሰለሞን ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የሃያል ሳምሶን ሙሉ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የአባ ጳውሊ መንፈሳዊ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN ቅድስት አርሴማ ሙሉ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN የነብዩ ቅዱስ ሙሴ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 JOIN አባ ኖብ ሙሉ መንፈሳዊ ፊልም 👈 ይንኩ
🎬 Join Elohe picture
✅ እንደ ምርጫው መርጠው ይ🀄️ላ🀄️ሉ ✅

https://www.tgoop.com/addlist/kAVvN-thJG44YzA0

𝚆𝚊𝚟𝚎 👉 @Beni_tes
https://www.tgoop.com/addlist/Ka6_NP6UoaYyOWZk