Telegram Web
🤪🤪

ድሮ የተሰራ ድጋሜ የተለቀቀ😁😁
🥰752197🤣120😢22🤩15🙏7👏4
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን

ሐዋ ሥራ 28(ሙሉዋን)

የሐዋርያት ሥራ ተፈጸመ: በኢየሩሳሌም ጀምሮ ሮም ላይ አለቀ

@Apostolic_Answers
285🙏36🥰12😢2🔥1
ኧረ አንዱ ፕሮቴስታንት በክርስቶስ የባህሪ ውሕደት የለም ብሎ ሲከራከር ሰማሁ😁😁 ምናልባት አርፍጄ ደርሼ ሳልረዳው ቀርቼ በሆነ..

የባህሪያትን መዋሐድ እኮ ኬልቄዶንም ይቀበላል.. ያው ሁለቱ ባህሪያት ቢዋሐዱም አንድ ከማለት የመሸሽ ነገር ነው የሚታይበት እንጂ.. በጉባኤው ላይ የቄርሎስን ወደ ንስጥሮስ 2ኛ ምልእክት ጠቅሰው እንዲህ ብለዋል:

“በእውነተኛ ውሕደት የመጡት ባሕርያት የተለያዩ ናቸው፤ ከሁለቱም የሆነ አንድ ክርስቶስና አንድ ልጅ ነው - ታድያ ግን የባህርያቱ ልዩነት በውሕደቱ ጠፍቷል ማለት አይደለም”

[Acts of Chalcedon, vol. III pg 119 (address to marcian)]

ተመሳሳይ ነገር 5ኛው session ላይም ይገኛል..

ነገሩን ብዙም ባልሰማም ግን ደግሞ መከራን የተቀበለው ማን ነው ምናምን የሚል ነገር ሲነሳ ነበር.. አሳባቸውን ግልጽ ካደረጉት ከቄርሎስ እና ከኤፌሶን ጉባኤ እንዲሁም ከነ Mcguckin እና ከሌሎችም contemporary scholars አድርጌ እሄድበታለሁ
427👍47😁16🙏12😱2🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጣም ጸዴ የምስጋና ጊዜ..

በዚ ደረጃ ፕሮግራም ማዘጋጀት በጣም ከባድ ነው የምር.. ይሄ ጸዴ ጅማሮ ነው.. በዚሁ ከቀጠለ አስቡት..
1.89K🙏59🔥44🥰31👍22👏13😱8🤣8😢2
አምላክ እንደ እኛ የተለያየ የአካል ክፍሎች አሉት..?? ለምሳሌ ዓይን እግር እጅ ምናምን..??

በእኛ ሃገርም ያለውን አንስቼዋለሁ ያው ቀለል ባለ መልኩ ከጠቀመ በሚለው.. ግን ደግሞ ከትህትና ጋር ያው አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔርን ባልሆነ መንገድ እንዳይስሉት በማሰብ

@Apostolic_Answers
399🙏34👍11🥰10👏4😱2
ጋይስ ያው በዚህ ጊዜ የሚያዋጣው መማር ነውና ለተለያዩ ቤተ እምነቶች የሃሰት ትምህርት መልስ የሚሰጥበት ሌላ ጥሩ ቻናል ያው ይዤላችሁ መጣሁ.. ተቀላቅላችሁ ትከታተሉ ዘንድ እጠይቃለሁ😁😁

👇👇👇

@ChristianAnswersET
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
333👏33👍28🙏9🔥5🤣1
አንድ ሙስሊም ወንድም "አባ ጊዮርጊስ እኮ ለእግዚአብሔር እጅ እግር ጥፍር እንዳለው ተናግሯል በመጽሐፍ ምስጢር 1፡62" ብሎ ጽፎ አየሁ..

[መጨረሻ ላይ ያስቀመጥናትን ማስረጃ እስክታዩ ድረስ አንብቡ]

መጽሐፉ ላይ አዎ ይህ ብቻ ሳይሆን በርካታ የአካል ክፍሎችን እየዘረዘረ እግዚአብሔር እነዚህ ነገሮች አሉት እያለ አስቀምጧል.. ለምሳሌ ደረትንም ጨምሮ ከላይ ከፍ ስትል ቁጥር 59 ላይ። እግዚአብሔር ዓይኖች እና ሌሎችም እንዳሉት በጽሑፍ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስ ላይም በጣም በተደጋጋሚ ተቀምጧል እና አባ ጊዮርጊስም ለእያንዳንዱ ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ እያጣቀሰ ነው ያስቀመጠው።

ታድያ ግን ምን ለማለት ነው የሚለውን ግን መረዳት ያለብን ይመስለኛል.. ትናንት በድምጽ እንዳስቀመጥኩላችሁም እግዚአብሔር የተለያዩ ክፍሎች ስብስብ(composite) ሊሆን እንደማይችል ሊቁ አያጣውም ብዬ አስባለሁ.. ስለዚህም እየተናገረ ያለው እኛ ላይ የሚታዩ የአካል ክፍሎች እግዚአብሔር ላይም አሉ ሲል ልክ እንደ እኛ በቅርጽ በቅርጽ ሆነው የተከፋፈሉ ለማለት ሳይሆን ከአካል ክፍሎቹ ተግባራት አንጻር የተነገረ ነው.. ለምሳሌ ዓይን አለው ካለ ያያል ነው.. እርሱ ያያል ግን እንዴት ነው የሚለው አይመረመርም።

እንዴት ስለ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ልትናገር ቻልክ ካላችሁኝ አባ ጊዮርጊስ ራሱ በሌላ ቦታ አንድ አይሁዳዊ "የእግዚአብሔር ፊቱ
ወዴት ነው ንገሩኝ?" እያለ በተከራከረ ጊዜ የመለሱበት መንገድ ነገሩን ግልጽ ስለሚያደርገው ነው.. ምን ብሎ መለሰለት..??

[ለመለኮት ወርድና ቁመት፣ ላይና
ታች፣ ቀኝና ግራ፣ #ያለው_አይደለም፡፡
በአራቱ ማዕዘን ምሉዕ ነው እንጂ፡፡
ለመለኮት በፊቱ #ደረት በኋላውም
ጀርባ #ያለው_አይደለም እንደተጻፈ
መለኮቱ በሁሉ የመላ ነው እንጂ አለ፡፡]
[ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 6፡4]

ለእግዚአብሔር ደረት እንዳለው ተናግሮ ነበር ግን ደግሞ በዚህ መጽሐፍ ላይ እንደምንመለከተው "ደረት ያለው አይደለም" ብሎ በግልጽ አስቀምጧል.. ስለዚህም የአካል ክፍሎች እንዳሉት የሚናገር የሚመስል ነገር ስናይ ከተግባራቸው አንጻር ወስደን ብናልፈው እላለሁ

@Apostolic_Answers
740👍94🔥21
“ቅዱስ ቁርባን ለእኛ ከዚህ ዓለም ወደ ዘላለማዊው ሕይወት የምንሻገርበት መሻገሪያችን፣ ድልድያችን፣ በራችን፣ ጀልባችን ነው”

[ጋሽ ማርቲን ሉተር: LW 35: 21]

ሉተር በጣም ነው ሚያሳዝነኝ.. ምናለ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ቢቀላቀል ኖሮ እላለሁ አንዳንዴ..

አለ ደግሞ ያ ዝዊንግሊ የሚሉት ህመምተኛ የምስጢራት ጠላት.. ያቺ መሃል ላይ ልሁን ምትለው ካልቪንስ..??😁😁
430😁184🤣113🤩3👍2
እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች በየአቅጣጫው በዝተዋል እና ጌታ ይመስገን..

ያው መቁረብ ያልጀመራችሁ አትሳነፉ አፍጥኑት ለማለት ያህል ነው
749🔥82🙏39🥰26👍17👏3😢1
እንዲህ የሚሉ አባቶች አሉ.. ያው ከፍራቻ አንጻር ነው ግን ይህ ጥሩ አይመስለኝም.. እንደውም አደገኛ ነው..

እዚህ ጉዳይ ላይ መምህራን ለንስሐ አባቶች ሥልጠና ቢሰጡ ምርጥ ነው
👍54374😢61🔥7😁7👏4🤔3🙏3😱2
ቴሌግራም ስገባ በጠዋቱ የደረሰኝ መልእክት..

እኔ ይሄ የሚዲያ ነገር ጌታን በጣም የማመሰግንበትም ስለሆነልኝ በቃ ልርቅ የምችል አልመሰለኝም ከሚዲያው😁😁

እና ደግሞ እንዲህ ወደ ክርስትና አዳዲስ ስለሚመጡ ነፍሳት ጸልዩ ምናምን

መልካም ውሎ
1.28K👏91🙏44🥰27👍22🔥21🤣14
በቃ ለመጨረሻ ጊዜ 2 ቻናሎችን ላስተዋውቃችሁ..

1. የዲያቆን ናቱ.. ትጠቀሙበታላችሁ በተለይ ከአሁን በኋላ 👉 @Stcyril1

2. መራኁት የሚል ስም ያለው.. አውርተንም አናውቅም ምናምን ግን ቲክቶክ ላይ ሳየው መልካም እና የሚጠቅም መስሎኛል እና ያው ላጋራችሁ 👉 @merahuut

ይሄ የመጨረሻ ነው ጋይስ ቴሌግራማችሁን በቻናሎች ሞላሁባችሁ ይቅርታ ግን ያው ለእናንተው ነው.. ወንድሞችም ደግሞ እንዲበረታቱና አብዝተው እንዲሠሩ ነው
448👍54🙏24👏12
በቃ ዛሬ የመጨረሻ ከሆነማ የወንድሞችን ዩትዩብም ላስቀምጥላችኋ ሎል..

1. የዲን ዘማሪ ብስሬ [በአዳዲሶቹ ዝማሬ አመስግኑበት ፕሊስ] 👉 youtube.com/@deaconbisratteshome/

2. የዮሐዴ 👉 youtube.com/@lenefsatube/

3. የባሮኬ [አዲስ ነው ተቀላቅላችሁ ጠብቁ] 👉 youtube.com/@barock2727/

4. የኢዮባ 2ኛ ቻናል 👉 youtube.com/channel/UClqD-UCHugnLT86Em1gTfUg?si=B9xG7ZO2oKczGH6i

አበረታቷቸው ጋይስ..
296🤣148👍33👏6😱5😢1🤩1
ኧረ አንዱ ስለ ትዳር እየመከረ..

“ቅዱስ ጳውሎስም እኮ ካላገባሁ ወዮውልኝ ነው ያለው” እያለ እየመከረ ነው.. ይሄ ነገር ከየት ነው ሎል
🤣499😁35😱189
ብዙ ሰዎች እንዲህ እየላካችሁ ነው.. እውነቱን ለመናገር ሁሌም እንደ አዲስ ነው ደስ የሚለኝ.. ያው ግን እኔ እዚህ የምለቀው ላልጀመሩት እንዲያነሳሳቸው ነው.. ያው የጀመራችሁ በዚሁ ደግሞ ጽኑ ቶሎ ቶሎ መቁረብ አትርሱ.. ስለዚህ ስትልኩ እዚህ ጋር ካልለቀኩት ያው ደስ ሳይለኝ ቀርቶ ሳይሆን ያው አንድ ይበቃል ብዬ ነው በርቱልኝ

እና ደግሞ እንኳን አደረሳችሁ
1.07K🙏89🥰37👏23👍11🔥10🤣7
እኔ ግን ክርስቲያን ባለ ሃብቶች በጣም ነው ሚያሳዝኑኝ.. ምናለ እነሱንም የሚጠቅም ሆኖ ግን ደግሞ ሥራ ያጡ የተቸገሩ ክርስቲያኖችን የሚያስሰራ ትልልቅ ቢዝነስ ማይኖራቸው..

ኧረ በሞቱባት ቅጽበት አንዲትም ሳንቲም ከእነርሱ ጋር እንደማትሄድ ሊነገራቸው ይገባል.. እዚህ ባላችሁ ገንዘብ በፍቅር ሆናችሁ በሰማይ ለዘላለም የምትኖሩበትን ቤት ሥሩበት..

ዮሐንስ አፈወርቅ ፓርቴ ተቀሰቀሰብኝ መሰለኝ ሎል
1.22K👍204🤣103👏33😁17🤔13😢6😱3
2025/10/08 17:36:11
Back to Top
HTML Embed Code: