tgoop.com/Apostolic_Answers/3281
Last Update:
አንድ ሙስሊም ወንድም "አባ ጊዮርጊስ እኮ ለእግዚአብሔር እጅ እግር ጥፍር እንዳለው ተናግሯል በመጽሐፍ ምስጢር 1፡62" ብሎ ጽፎ አየሁ..
[መጨረሻ ላይ ያስቀመጥናትን ማስረጃ እስክታዩ ድረስ አንብቡ]
መጽሐፉ ላይ አዎ ይህ ብቻ ሳይሆን በርካታ የአካል ክፍሎችን እየዘረዘረ እግዚአብሔር እነዚህ ነገሮች አሉት እያለ አስቀምጧል.. ለምሳሌ ደረትንም ጨምሮ ከላይ ከፍ ስትል ቁጥር 59 ላይ። እግዚአብሔር ዓይኖች እና ሌሎችም እንዳሉት በጽሑፍ ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስ ላይም በጣም በተደጋጋሚ ተቀምጧል እና አባ ጊዮርጊስም ለእያንዳንዱ ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ እያጣቀሰ ነው ያስቀመጠው።
ታድያ ግን ምን ለማለት ነው የሚለውን ግን መረዳት ያለብን ይመስለኛል.. ትናንት በድምጽ እንዳስቀመጥኩላችሁም እግዚአብሔር የተለያዩ ክፍሎች ስብስብ(composite) ሊሆን እንደማይችል ሊቁ አያጣውም ብዬ አስባለሁ.. ስለዚህም እየተናገረ ያለው እኛ ላይ የሚታዩ የአካል ክፍሎች እግዚአብሔር ላይም አሉ ሲል ልክ እንደ እኛ በቅርጽ በቅርጽ ሆነው የተከፋፈሉ ለማለት ሳይሆን ከአካል ክፍሎቹ ተግባራት አንጻር የተነገረ ነው.. ለምሳሌ ዓይን አለው ካለ ያያል ነው.. እርሱ ያያል ግን እንዴት ነው የሚለው አይመረመርም።
እንዴት ስለ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ልትናገር ቻልክ ካላችሁኝ አባ ጊዮርጊስ ራሱ በሌላ ቦታ አንድ አይሁዳዊ "የእግዚአብሔር ፊቱ
ወዴት ነው ንገሩኝ?" እያለ በተከራከረ ጊዜ የመለሱበት መንገድ ነገሩን ግልጽ ስለሚያደርገው ነው.. ምን ብሎ መለሰለት..??
[ለመለኮት ወርድና ቁመት፣ ላይና
ታች፣ ቀኝና ግራ፣ #ያለው_አይደለም፡፡
በአራቱ ማዕዘን ምሉዕ ነው እንጂ፡፡
ለመለኮት በፊቱ #ደረት በኋላውም
ጀርባ #ያለው_አይደለም እንደተጻፈ
መለኮቱ በሁሉ የመላ ነው እንጂ አለ፡፡]
[ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 6፡4]
ለእግዚአብሔር ደረት እንዳለው ተናግሮ ነበር ግን ደግሞ በዚህ መጽሐፍ ላይ እንደምንመለከተው "ደረት ያለው አይደለም" ብሎ በግልጽ አስቀምጧል.. ስለዚህም የአካል ክፍሎች እንዳሉት የሚናገር የሚመስል ነገር ስናይ ከተግባራቸው አንጻር ወስደን ብናልፈው እላለሁ
@Apostolic_Answers
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3281