tgoop.com/Apostolic_Answers/3443
Create:
Last Update:
Last Update:
አንዳንድ ወንድሞች(በመንፈሳዊ ስም
ያሉ) እህቶችን ፎቶ ያስልካሉ አሉ.. ያው ፎቶ ስል ይገባችኋል ሲጀመር እናንተ እዚህ ላይ ንቃተ ሕሊና አላችሁ ሎል.. ያው ከፎቶ በተጨማሪ ደግሞ ገንዘብ ምናምን ማለት ነው..
እና ይህ ነገር ሲነገር አንዳንድ ሰዎች ምን ይላሉ..?? “ሴቷ ማን ላኪ አላት የራሷ ጉዳይ ነው” ይላሉ.. እንዴት እንደሚያናድደኝ እንደዚህ ዓይነት አሳብ.. ያው እህቶችም ራሳቸውን ከነውር መጠበቅ አለባቸው ግልጽ ነው ግን በጣም ነው የሚያሳዝኑት በቃ በየዋሕነት ያው መውደዳቸውን ለመግለጽ ይህንን አድርገው ይሆናል አልያም በጣም lustful ሆነውም ይሆናል.. ግን ምንም ቢሆን ትልቁ ሃላፊነት ያለው አገልጋዩ ጋር ነው..
ወደ ንስሐ ያቀርባታል ተብሎ ሲጠበቅ ጭራሽ ከባሏ ውጪ ሊያየው የማይገባውን ገላዋን ካስላከ ይሄ ጸቡ ከክርስቶስም ጋር ነው.. የጌታ ጠላት ነው.. በተለይ ሥራዬ ብሎ አንድ ሰው ይህንን ነገር በተደጋጋሚ እያደረገ እየኖረ ካለ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል.. ለንስሐ የሚወቅሰውን የጌታን መንፈስም ስለሆነ እየተቃወመ ያለው ለንስሐም መነሳሳት አይችልም..
የእንደዚህ ዓይነት ነገር ሰለባ የሆናችሁ እሕቶች እንግዲህ አይዟችሁ ከአሁን በኋላ ደግሞ ተጠንቀቁ ተማሩበት.. ንስሐ ግቡና ወደ ቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ተመለሱ..
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3443