Telegram Web
አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች አንድ “የገድል መጽሐፍ” በሲኖዶስ ደረጃ በመወገዙ የተደሰቱ አይመስልም.. ምክንያቱም ገድልን እያነሱ ማጭበርበርን ስለሚያስቀር ማለት ነው..

እንዴት..??

ቤተ ክርስቲያን ከታወቁ ትምህርቶቿ(ዶግማዎቿ) ውስጥ አንዲት ነጥብ እንኳ አትቀንስም አትጨምርም.. ታድያ ግን በተለይ ገድላት ተአምራት ሲሆን እንደ ሁኔታው ታይቶ የሆነ የታሪክ ማሻሻያ አልያም እርማት ልትሰጥ ጫን ሲል ደግሞ ሙሉ መጽሐፉንም ልታወግዝ ትችላለች.. ስለዚህ እነዚህን ከመሰሉ መጽሐፍት ላይ ያለአግባብ የተገኘውን ሁሉ እየጠቀሱ ክርስቲያኖችን ለማስደንገጥ መሞከር ማለት ጅልነት ይሆናልና ነው..

እንግዲህ አሁን የትኛውም ክርስቲያን በእነዚህ መጽሐፍት ላይ ባሉ በምንም ዓይነት ታሪኮች እንደማይወዛገብና ተሳስቶም ከሆነ ይታረማል እያለ ለመቀበል ብዙም ሳይታገል እንደሚያልፈው ግልጽ ያደርገዋል ነው..

@Apostolic_Answers
845👏75👍60🤣36🙏9😱2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧኸ ጋይስ.. እንደምታዩት ስፖርት ጀምረናል..

ውጥር ውጥር የምትል ሁላ አነጥፍሃለው..
🤣1.37K😁15456🙈35🤩11🙏7👏3😱3🤔2
ኃጢአትን እየወደዱ እግዚአብሔርን እፈራለሁ ማለት አይቻልም።

[ሲራክ 15:13]
______________

እግዚአብሔርን መውደድ እና ማፍቀር ብቻ ሳይሆን እርሱን መፍራትም ከኃጢአት እንድንርቅ ያደርገናል.. ሰው ኃጢአትን የሚያደርገው በእግዚአብሔር ፊት ነው.. መዝሙረኛውም እንዲሁ “በፊትህም ክፋትን አደረግሁ” እንዳለው ነው..

ታድያ ክፋት ኃጢአት የሚፈጸመው በእግዚአብሔር ፊት ከሆነ በሌላ አማርኛ ወንጀልን በዳኛው(በፈራጁ) ፊት መፈጸም ማለት ነው.. ዳኛውን ብንፈራ በፊቱ ወንጀልን አንፈጽምም ነው.. ስሊህም እግዚአብሔርን መፍራትም ከኃጢአት ያርቃል..

አንዳንዴ ግን እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በጣም ክፉ ድካም ውስጥ ገብቶ ኃጢአት ውስጥ ሊወድቅም ይችላል.. ከወደቀም ግን የፈጠነ ንስሐ ገብቶ ይቆርባል.. ስለዚህም ከንስሐ እና ቁርባን ሕይወት አንራቅ..

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
1.03K🙏188😢24👍9🔥4🤣3
ሎጥ ለኖረባቸው፥ ራሳቸውንም ላኮሩ ሎጥንም ለተጸየፉት ሀገሮች አልራራላቸውም።
ኃጢአተኞችን ሕዝቦች ይቅር አላላቸውም፤ በኃጢአታቸው ጠፉ እንጂ።

ሲራክ 16: 8-9
____________

በሎጥ ዘመን እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን በኃጢአታቸው ብዛት አጠፋቸው.. ሎጥ ግን በመካከላቸው ሆኖ በኃጢአታቸው ብዛት አይተባበራቸውም ነበር.. ይልቁንም ከእነርሱ ጋር በኃጢአት ባለመቀላቀሉ ይገፉት ነበር.. እግዚአብሔር ግን እርሱን አድኖ ኃጢአተኛውንና ሴሰኛውን ሕዝብ አጠፋው.. ጴጥሮስም ስለ እርሱ እንዲህ ያለው ነው:

“ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ..”
[2ጴጥ 2: 7-8]

ስለዚህ እኛም ሰው ሁሉ በሚተባበርበት ኃጢአት ውስጥ አንቀላቀል.. ጌታም ያድነናል.. መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
727🙏127🥰29👏11👍5
አርሲ ላይ በርካታ ክርስቲያኖች ተገደሉ የሚል ዜና ሰማሁ..

ሰማእትነት መልካም ነው ግን ደግሞ የማንም ኋላ ቀር ጂኒያም እንደፈለገ ክርስቲያኖችን ሊያርድ አይገባም.. ዝም ከተባለ ከሆነ ጊዜ በኋላ እንደ ሶርያ እና ግብጽ እንዳንሆን ያስፈራል
1.05K😢647👍109🙏17🔥13😱11👏10🤣9🤔7
ነገር ግን ንስሐ የሚገቡበትን መንገድ ሰጣቸው፤ ተስፋ የቆረጡ ሰዎችንም ደስ ያሰኛቸዋል። ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፥ ኃጢአትንም ተዋት በፊቱም ጸልይ፥ ለበደልህም ንስሐ ግባ።

ሲራክ 17: 24-25
______________

መልካም ውሎ
978🙏139🥰40👍18👏11😢11🔥7🤔2🤣2
እነሆ እንግዲህ ከመስጠት መልካም ቃል አይሻልምን?
ሁለቱም ሁሉ በጻድቅ ሰው ዘንድ ይገኛሉ።
ንፉግ ልቡናውን ደስ ሳይለው ይሰጣል። ሰነፍም ይላገዳል አያመሰግንምም።

ሲራክ 18: 16-17
______________

ለተቸገሩ እናካፍል.. በየመንገዱ ተርበው ወድቀው ላሉት እንዘንላቸው.. “እኛ ራሳችን ምን አለን..??” አንበል ከኛ የባሰ አስቸጋሪ ሕይወትን እየገፉ ያሉ ብዙ ናቸው.. ስለዚህም እነዛ የተወደዱ በጌታችን በክርስቶስ በኩል የሚዛመዱን በረሃብ እና ልብስ በማጣት የሚሰቃዩ ቤተሰቦቻችንን እንደ አጠቃላይ ሁሉንም ሰዎች እናስብ.. ችግራቸውን መረዳትና ርህራሄ ልባችን ውስጥ ይኑር

ከፍቅር የተነሳ ደስ እያለን እንደው ለምን ትንሽ አይሆንም እንስጣቸው.. ከዛ ግን መልካም ቃልን እንናገራቸው.. እነርሱ እስኪመርቁን አንጠብቅ ይልቁንም “አይዟችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን” እንበላቸው..

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
883🙏124🔥26👍10🤣3
ክርስቶስ ኢየሱስ ጠበቃችን ነው..??

ያው በመጽሐፍ ቅዱስ ወይም በቤተ ክርስቲያን መረዳት ካየነው.. ክርስቲያን ኃጢአት ከሠራ ከኃጢአት ለመላቀቅ ንስሐ መግባት አለበት እና ንስሐ ሲገባ ከኃጢአቱ የሚነጻው ደግሞ በክርስቶስ ሞት ነው.. ያኔ ከ2000 ዓመት በፊት በሰራው የማዳን ሥራ አሁንም ድረስ ደሙ የኃጢአታችን ማስተሰሪያ ከመሆኑ አንጻር ጠበቃ ተብሎ ሊጠራ ይችላል.. 1ዮሐ 2:1 ጀምሮ እንደተገለጸውም..

@Apostolic_Answers
910🙏80👍23👏20🔥8🤣8
የእግዚአብሔር ሕዝብ በአርሲ

https://vm.tiktok.com/ZMAGtYsKo/
———
😢40086😁7😱1
ሰካራም ሰራተኛ አይበለጥግም፥
ጥቂቱን የሚያቃልል ብዙውን ያጠፋል።
መጠጥና ሴት ጠቢባንን ያስቷቸዋል፥
ጋለሞታን የሚከተላት በደለኛ ነው።

ሲራክ 19:1-2
_______________

ሰካራምነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው.. ከመንፈሳዊው ባሻገርም ደግሞ ሰካራምነት ማለት በሌላ አማርኛ ወራዳነት ነው የምር.. በመስከርህ ምክንያት በራስህ ላይ ኃጢአትን ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሌላውን ሰላም ትነሳለህ.. የተናቅህ ትሆናለህ.. እና አትበለጽግምም ደግሞ.. ለሃረቄህ ብቻ እየሰራህ ትኖራለህ.. ወደዚህ ደረጃ እንዳትደርስ ከመጠጥ ራስህን አርቅ ወደ መጠጥ አትመልከት።

ሰካራም ቤት አይሰራም
ቢሰራም ቶሎ አይገባም - እንዳልነው ነው ጩጬ እያለን😁😁

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
677🤣85👏32👍27😁17🔥3
ኧረ በካቶሊኩ ዘንድ Vatican news አዲስ ዜና ይዞ ብቅ በሏል.. ነገርዬው ነገረ ማርያም ላይ ያጠነጥናል..

በፖፑም አፕሩቭ የተደረገው ኖት እንደሚገልጸው ከሆነ:

ቅድስት ድንግል “አብሮ ቤዛ/አዳኝ”(co-redemptrix የሚለው በብዙ ካቶሊኮች የሚታመነው መጠሪያዋ አስቸጋሪና አደናጋሪ መሆኑን ገልጸዋል.. እንዲሁም ደግሞ ማርያም “የጸጋ ሁሉ ወደ ሰዎች መፍሰሻ” (mediatrix of all graces) የሚለውንም እምነታቸውን በማንሳት ጸጋ ወደ ሰዎች የሚፈስሰው በማርያም በኩል ሳይሆን በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ በኩል ነው ብለዋል..

ተመስገን.. ነገረ ማርያምን ከመለጠጥ እንዲህ በአዋጅ መታቀብ ሲጀምሩ በጣም ደስ ይላል.. ጌታ ይርዳቸው..
735👏68👍47🔥11🤣11🙏6😢2🙈1
ልጄ ሆይ፥ የበደልኸው በደል፣ የሳትኸውም ነገር ቢኖር፥ እንዳትደግም ተጠንቀቅ፥ ስለ ቀደመው ኃጢአትህም ንስሐ ግባ።
ከክፉ አውሬ እንደሚሸሽ እንዲሁ ከኃጢአት ሽሽ፥ ከአገኘችህ ግን አትለቅህም፤ ጥርሷ እንደ አንበሳ ጥርስ ነው፤ የሰውንም ነፍስ ታጠፋለች።

ሲራክ 21: 1-2
________________

ከኃጢአት ሽሽ.. ወዴት ልሽሽ..?? ወደ ክርስቶስ ሽሽ እርሱ ከባድ ከሚባሉ ኃጢአቶችም ከጠላት ሁሉም መሸሸጊያ ነው.. ሲልም ድል መንሻ ነው.. ወደ ንስሐ እና ቅዱስ ምስጢር ሽሽ..

እንኳን አደረሳችሁ.. መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
1.01K🙏145🥰33😢20👍17👏11🔥8🤣4😱1
ለሴሰኛ ሰው እህሉ ሁሉ(ዝሙቱ ሁሉ) ይጣፍጠዋል፤ እስኪሞትም ድረስ አያርፍም።
ሚስቱን ትቶ የሚሄድ ሰው፥ በልቡ “ጊዜው ጨለማ ነው፤ የሚያየኝ የለም አጥር ይጋርደኛል፤ ከዚህ በኋላ ምን እፈራለሁ? የሚያውቀኝም የለም፤ ልዑልም ኃጢአቴን ይዘነጋልኛል፤ አያስብብኝም” ይላል።
ነገር ግን እንዳያየው የሰው ዓይንን ይፈራል፤ የእግዚአብሔርም ዓይን ከጸሐይ መቶ ሺህ ጊዜ እንዲበራ፥ የሰውንም ሁሉ ሥራ እንደሚያይ፥ ተሰውሮ የሚሠራ ሥራንም ሁሉ እንደሚያውቅ አያውቅም።

ሲራክ 23: 17-19
________________

ዝሙትንም ሆነ ሌላ ኃጢአትን የሚሠራ ሰው.. ሰው ባያየው እንኳን በእግዚአብሔር ፊት ነው ነገሩን የሚፈጽመው.. ያውም ወደ ዘላለም እሳት ሊጥል በሚለችለው አምላክ ፊት ነው የሚፈጽመው.. ስለዚህም ሰውን እንደምናፍር እግዚአብሔርን እንፈረው እንፍራውም ነው.. አቅም አጥቶ ለሚወድቀውም አቅምን የሚሰጠው ራሱ ነውና ቶሎ ቶሎ በንስሐ ወደ እርሱ እንመለስ..

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
990🙏206😢44👍19🤣11🥰1
ቀጥታ ወደ አማርኛ ሲተረጎም:

ቫቲካን የክርስቶስን ብቸኛ አዳኝነት በማስረገጥ co-redemptrix እና “መካከለኛ” የሚለውን መጠሪያ ለማርያም ልንጠቀመው እንደማይገባ ገልጿል።
______________

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ስትል ዶግማ ላይ ተሳስቼ ኖሬ አሁን አስተካከልኩ እያለች አይደለም.. ይልቁንም በብዙዎች ዘንድ እኚህ መጠሪያዎች ጥቅም ላይ ይውሉ ስለነበር.. እና ደግሞ እነዚህን መጠሪያዎች ዶግማ የማድረግ ጥያቄም ስለነበር ቤተ ክርስቲያኒቱ ጭራሹኑ ባንጠቀማቸው አደናጋሪ ናቸው አለች ነው..

ያው ከዚህ ቀደም ዶግማ ይደረግ የሚል እንኳን ክርክር የነበረበትን ነገር ጭራሹኑ ማስወገዷ ነው ባለፈው ሃሪፍ ነው ያስባለን እንጂ ዶግማዋን አርማ አይደለም.. አንድ ፕሮቴስታንት ባልሆነ መልኩ ለመተቸት ሲሞክር አይቼ ነው..

የ6 ደቂቃ ፖስት
330👍54🤣14👏9🔥5😱1🙈1
ይቅርታ ልጠይቅ መሰለኝ..

በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከጥቂት አመታት በፊት በፕሮቴስታንት ተሐድሶዎች የተፈጠረው ነገር ብዛቱን ትናንት ለጉዳዩ ቅርብ ከነበሩ ሰዎች እየሰማሁ በጣም ነው የገረመኝ.. በብዙዎች ክርስቲያኖች ዘንድ አደገኛ የልብ ቁስለት ነው ያደረሰው.. እና አንዳንድ ሰዎች በቅንነት እኔን የሚቃወሙ ካሉ ያ ነገር ውስጣቸው ስላለ ነው.. ቁስላቸውን ነው የሚሰማቸው..

እና በቅንነት ከክፋት ውጪ ሆናችሁ የምትተቹኝ ወንድም እና እህቶቼ.. በአንድም በሌላም ላስከፋኋችሁ በጌታ ፊት ሆኜ ይቅርታ ጠይቃችኋለሁ.. እወዳችኋለሁ.. እኔም የቤተ ክርስቲያኔ ነገር ስለሚያንገበግበኝ ብቻ ነው ምፈጣጥነው😊😊 እና ይህንን ተረድታችሁ ይቅርታ አድርጉልኝ.. አይዟችሁ ደግሞ..

አክሊል

@Apostolic_Answers
1.2K👏85👍53🥰38🙏36🤣16😢15🔥6🤩5🤔4
“ክርስቶስ እንዲሁ በነጻ አስቀድሞ ከነበርንበት ነጻ ያወጣን ብቻ አይደለም.. ይልቁንም ወደ ፊት ለሚኖርብን መንፈሳዊ ውጊያም ያስታጠቀን ነው እንጂ”

[ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: hom. On Romans]
_________________

ክርስቲያን ከጌታ የተሰጠውን ትጥቅ ታጥቆ በንቃት የሚኖር ከሆነ ሁሌም አጋንንትን እና ኃጢአቶችን ድል እየነሣ ይኖራል.. ይህንን ትጥቅ የፈታ ቀን ግን ቡም ያኔ ቀስ በቀስ መመታት ይጀምራል.. ከዚያም በፍጥነት መውደቅ ይጀምራል..

ግን የምስራች አለን..

በዚህ ወቅትም ኢየሱስ መሸሸጊያ ነው.. የጠላትንና የኃጢአትን ሁሉ ውጊያ የምናሳልፈው በኢየሱስ ተሸሽገን ነው.. እንደ አንድ ሕጻን ልጅ ከአቅሙ በላይ የሆነ ሰው ሲገጥመው ሮጦ በአባቱ ሥር እንደሚሸሸገው.. ከዛም እንደ ገና ደግሞ እንዲሁ በነጻ ያስታጥቀናል.. አቅምን ይሰጠናል.. ስለዚህ ጌታችን በተዋጋን ጊዜ ተዋጊያችን ነው በተሸሸግን ጊዜም መሸሸጊያችን ነው..

ስለዚህም ከመዝሙረኛው ጋር ሆነን እንዲህ እንላለን:

መዝሙረ ዳዊት 32
7፤ አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥
ከጣርም ትጠብቀኛለህ፤
ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።

ጌታ ሕዝቡን ይጠብቅ

@Apostolic_Answers
823🙏116👍14🥰13🔥7🤣5
አሁን አይደል እንዴ የማየው.. በቃ ፕሮቴስታንቶች በትንሹም በትልቁም ከክርስቲያኖች ጋር ሲወያዩ አላቃሾቻቸው ቤታቸው ሄደው ማልቀስ ሥራቸው ሆኖ ቀረ አይደል ሎል😁😁

በቅርቡ ከአንድ ፕሮቴስታንት ጋር እየተወያየን ነበር እና አሳቡን አጠር አድርጌ ላስቀምጥላችሁና ከዛ በኋላ ካገኘሁት ቪዲዮውን እለቅላችኋለሁ እዚሁ ላይ ልታዩት የሚገባ ይመስለኛል..

👇👇👇👇👇

እኔ፦ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" የሚለው የዮሐ 1፡1 ክፍል "ሊሳሳት የማይችል"(infallible) ነው?

ፕሮቴስታንቱ፦ አይ ይሄ ዓ/ነገር ስለሆነ ሊሳሳት የማይችል(infallible) ተብሎ መጠራት አይቻልም..

እኔ፦ መልካም የዮሐንስ ወንጌልስ "ሊሳሳት የማይችል" ይባላል?

ፕሮቴስታንቱ፦ አዎ

እኔ፦ የዮሐንስ ወንጌል "ሊሳሳት የማይችል" እየተባለ ግን ደግሞ ዮሐንስ 1፡1 "ሊሳሳት የማይችል" ተብሎ ሊጠራ አይችልም ብሎ ያስተማረህ ማን ነው ከራስህ ከፕሮቴስታንቶችም ቢሆን?

ፕሮቴስታንቱ፦ ላንተ ማስረጃ መስጠት አይጠበቅብኝም..

እኔ፦ በዚህ ዓይነት ጳውሎስ ለምሳሌ "ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በልብህ ብታምን በአፍህም ብትመሰክር ትድናለህ" ብቻ ብሎ መልእክት ቢልክ ይሄ 1 ዓ/ነገር ስለሆነ ይህንን መልእክቱን "ሊሳሳት የማይችል" ብለህ ላትጠራው ነዋ።
____________

ፕሮቴስታንቱ በእርግጥ ወደ መጨረሻ ላይ አምኖ ነው የወጣው አንድ ቃልም ቢሆን ከጸሐፊው አንጻር "ሊሳሳት የማይችል"(infallible) ተብሎ ይጠራል ብሎ.. ያው አንዳንድ ጓደኞቹ ሲያለቅሱ ስላየሁ ነው😁😁

እስቲ ቪዲዮውን ማግኘት የምትችሉ ከታች ኮመንት ላይ አስቀምጡልን ፕሊስ
303😁73👏15🤔5👍4
ሐዋርያዊ መልሶች Chat
እኛ እንዴት ነው መረዳት ያለብን ትንሽ ብትልበት
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተያያዘ ከላይ ላለው እኛስ እንዴት ነው መረዳት ያለብን ለሚለው..

1. መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መጽሐፍ ቅዱስነቱ ስንቀበለው በጥቅሶችና በመጽሐፉ መካከል ልዩነትን እየፈጠርን አይደለም.. ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ስንል የእግዚአብሔር ቃል እያልን ከሆነ ጥቅሶችንም ሊመለከት የሚችል ነው

2. መጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴ(infallible) ነው..?? ለሚለው ጥያቄ ያው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንጩ ራሱ እግዚአብሔር ነው ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ እስትንፋስ ወይም ቃል እየተባለም ይጠራል.. ስለዚህም እግዚአብሔር አይሳሳቴ ነውና መጽሐፉም ሊሳሳት አይችልም.. እዚህ ላይ inerrancyን እና infallibilityን አብዝቶ በመለያየት ጥቅሶቹ inerrant ናቸው እንጂ infallible አይደሉም ለሚለው ሙግት የቃሉን ትርጉም ማየት በቂ ነው.. infallible ማለት ስህተት የማይሰራ(incapable of making mistake) ብቻ ሳይሆን ስህተት ሊሆን የማይችል(incapable of being wrong) ማለትም ነው.. መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት ሊሆን አይችልምና አይሳሳቴ(infallible) ልንለው እንችላለን ነው።

ይህ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱሳት መጽሐፍት የትምህርት መመዘኛና ዳኛም ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስቀምጣልና(letter 189:3) መዳኘት የሚችሉት እነርሱ አይሳሳቴ ናቸውና ነው።

ስለዚህም ይህንን infallible የሚለውን ቃል ለመጽሐፍ ቅዱስ በሃገር ውስጥም በውጭ ሃገርም ያሉ ኦርቶዶክስ መምህራን የሚጠቀሙበት ለዛ ነው.. ሁለቱን ቃላት በመለያየት አንዱን እንጠቀማለን አንዱን አንጠቀምም የሚል ግን ከሚታወቅ የኦርቶዶክስ መምህር ሰምቼ አላውቅም..

3. መጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴ ነው ስንል መጽሐፍ ቅዱስ ሙስሊሞቹ ለቁርአን እንደሚሉት ቃል በቃል እንደው ብቅ ያለ ሳይሆን በሰዎች አገላለጽ ዘመናትንና ባህልን ባማከለ መልኩ የተጻፈ ነውና በውስጡ ለድኅነታችን ከተሰጠን አስተምህሮ አንጻር ምንም ዓይነት እንከን የማይገኝበት እንከን አልባ ነው እንላለን.. ስለዚህም የቁጥር ልዩነትም ሆነ ሌላ ሌላ እንደ ኦርቶዶክስ ለእኛ አሳሳቢ አይደለም ማለት ነው።

ሌላ ጥያቄ ካላችሁ ከታች ኮመንት ላይ እያየሁ እመልሳለሁ
189🥰19🙏16👍5👏5🔥1
"የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል"
[ዕብራውያን 4፡ 12]

ለመጨመር ያህል እዚህ ላይ ጳውሎስ እንደሚናገረውም መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አንድ የታሪክ መጽሐፍ እንዲሁ የሚነበብ ብቻ ሳይሆን በቅን ልብ ለሚያነበው በውስጡ እግዚአብሔር actively የሚሠራበት መጽሐፍ ነው(በጽሑፍ ያለው ብቻ ሳይሆን በተሰበከውም መሆን እንደሚችል ግን ይያዝ) ለዛም የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራም ነው የሚለው.. ከዚህ አንጻር የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ነውና ሁሌም ይሠራልና አይሳሳቴ ነው ሊባል ይችላል..

@Apostolic_Answers
👍209172🙏25👏18🤣4🥰3
2025/11/19 04:32:38
Back to Top
HTML Embed Code: