tgoop.com/Apostolic_Answers/3425
Create:
Last Update:
Last Update:
አባ እንጦንስ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ተናግሯል:
በአንድ ወቅት ጠላት በዓለሙ ሁሉ ላይ ያጠመዳቸውን ወጥመዶች ተመለከትሁና “ከእነዚህ ማን ሊያመልጥ ይችላል?” በማለት በሃዘን ውስጥ ሆኜ ስጠይቅ: “ትሁት ሰው ያመልጣል” የሚል ድምጽ አደመጥሁ..
——————————————
ትህትና በክርስትና ውስጥ ትልቁን ቦታ ይይዛል ከፍቅር ጋር.. ጌታ ኢየሱስ ራሱ ከእኔ ተማሩ በማለት “እኔ የዋሕ በልቤም ትሑት ነኝ” ብሏል.. አምላክ ሲሆን ሰው በመሆኑም ትልቁን ትህትና አሳይቶናል.. ስለዚህም ጌታ በልቡ ትሑት ከሆነ የክርስቶስ ልብ ያለው እርሱ ትሑት ነው.. ያለ ትሕትና የክርስቶስ ልብ አይኖረንም.. የክርስቶስ ልብ ካለን ግን ወደ ሰማይ ከፍ ብለናል.. ስለዚህ አውግስቲንም : “ትእቢት መላእክትን ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፤ ትሕትና ደግሞ ሰዎችን ከምድር ወደ ሰማይ ያወጣል” ይላል.. በአንደበት ያልሆነ በልብ የሆነ ትሕትናን ጌታ ይስጠን(በነገራችን ላይ ከልብ ትሑት ለመሆን እርዳኝ ተብሎ ይጸለያል)
መልካም ውሎ
@Apostolic_Answers
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3425