tgoop.com/Apostolic_Answers/3420
Create:
Last Update:
Last Update:
አባ ፓመቦ እንጦስን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል.. “ምን ማድረግ ይገባኛል?”
አባ እንጦንስም ሲመልስ:- “በራስህ ጽድቅ አትታመን፣ ባለፈው አትጨነቅ፣ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ”
———————————
ይሄ ለብዙዎቻችን ትምህርት ነው.. በተለይ አንደበትን መግዛት.. በውሎዋችን ምናምን በጣም ከምንቀርባቸው ወዳጆቻችን ጋር ቀላል ስለሚሆንብን በጣም ያልተገባ ነገርን እናወራለን.. ይሄ ደግሞ ቀስ እያለ ልቅነትና ግድ የለሽነትን ያመጣል.. ስለዚህ በተቻለ አቅም ቀስ በቀስ አንደበታችንም ቁጥብ መሆን አለበት..
መዝሙረኛውም “አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ። “[መዝ 141: 3] እንደሚለው ነው..
መታመናችንም ሁሉ በእግዚአብሔር ይሁን ረዳታችን እርሱ ነውና.. ያለ እርሱም ምንም ልናደርግ አንችልምና.. በራሳችን ጽድቅ መታመን የጀመርን ቀን እግዚአብሔር ሊተወን ይችላልና..
መልካም ውሎ
@Apostolic_Answers
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3420