tgoop.com/Apostolic_Answers/3416
Last Update:
ነጻ ፈቃድ ባይኖረንስ ግን..??
"አብ ከሰባው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም።" [ዮሐ 6 44]
ይህንን ቃል ይዘው ፕሮቴስታንቶች[ሉተራኖችና ካልቪኒስቶች] ሰው ሙሉ በሙሉ በውድቀት ውስጥ ስለገባ ነጻ ፈቃዱን እንዳጣውና ስለዚህም በፈቃዱ ወደ ጌታ መምጣት ስለማይችል አብ በፈቃዱ በምርጫው ይስበዋል ይላሉ.. የት ላይ ብለዋል..?? ለምሳሌ በእምነት መግለጫ ደረጃ ብቻ፡ [formula of concord – solid declaration, concerning free will, 26; Belgic confession: article 14; Westminster confession, chap 9:3]
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን ይህንን የመጽሐፍ ክፍል ሲተረጉም እንዲህ ይላል፡
-ማኒኪያኖች(የማኒ ተከታይ ኖስቲኮች - መነናውያን) ከዚህ ቃል(ከዮሐ 6፡ 44) በመነሣት “በራሳችችን ሥልጣን የሚሆን ምንም ነገር የለም” ይላሉ፤ ነገር ግን ገለጻው የሚያሳያው የፈቃዳችን መሪ(አለቃ) ራሳችን እንደሆንን ነው። አንድ ሰው እንዲህ ሊል ይችላል፡ “ሰው ወደ እርሱ መምጣት የሚችል ከሆነ ታድያ መሳቡ ለምን አስፈለገው".. ነገር ግን ቃላቱ የእኛን ነጻ ፈቃድ የሚያስወግዱ አይደሉም፤ ይልቁንም ድጋፍን ወይም እርዳትን እንደምንፈልግ የሚያሳይ ብቻ ነው። [Homilies on John, hom. XLVI]
ከዚህ ምን እንረዳለን..?? ፕሮቴስታንቲዝም በተለይ "ጸጋ ብቻ" በሚለው ትምህርቱ የ16ኛው ክ/ዘመን [ግ]ኖስቲሲዝም እንደሆነ ነው..
@apostolic_Answers
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3416