tgoop.com/Apostolic_Answers/3415
Create:
Last Update:
Last Update:
ስለ እግዚአብሔር ፍርድ አባ እንጦስ ሲያሰላስል ከቆየ በኋላ አምላኩን እንዲህ በማለት መጠየቅ ይጀምራል፦
"ጌታዬ ሆይ! አንዳንድ ሰዎች ገና ልጅ እንዳሉ የሚሞቱትና ሌሎች ደግሞ ከመጠን በላይ እስኪያረጁ ድረስ የሚቆዩት ለምንድን ነው? አንዱ ደሃ ሌላ ደግሞ ባለ ጠጋ የሚሆነውስ ስለ ምን ነው? ኃጢአተኞች የሚበለጽጉበትና እውነተኞች የሚያጡበት ምክንያትስ ምንድን ነው?"
ከዚህ በኋላ አንድ ድምጽ "እንጦንስ ሆይ! ትኩረትህን ወደ ራስህ አድርግ! እነዚህ ሁሉ ሊሆኑ የቻሉት እንደ እግዚአብሔር የፍርድ አሠራር ነው። ስለ እነርሱ ታውቅ ዘንድ ለአንተ የተሠጠህ ነገር የለም!" በማለት ሲናገረው አደመጠ።
——————————--
አንዳንዴ በሕይወታችን ውስጥ የማንረዳቸው የእግዚአብሔር አሠራሮች ይኖራሉ.. ይህም ከእኛ አቅም አንጻር ነው.. ልክ ለአንድ ሕጻን ልጅ ሁሉም ነገር እንደማይነገረውና ሲያድግ እንደሚደርስበት ሁሉ እግዚአብሔር አባታችንም በብዙ ነገር ሕጻናት ለምንሆን ለእኛ ልጆቹ በትንሳኤ ሰዓት ወይም ወደ እርሱ እስክንሄድ ድረስ ብዙ ነገሮችን ከማወቅ ሊሸፍን ይችላል ነው። ስለዚህም ለድኅነት የተሰጠንና የራሳችን ጉዳይ ላይ እናተኩር በቀረው ግን በእግዚአብሔር እንመን..
መልካም የጌታ ቀን
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3415