tgoop.com/Apostolic_Answers/3414
Last Update:
ቅዱስ አባ እንጦስ በገዳም ውስጥ በሚኖርበት ጊዜ ብዛት ባላቸው የኃጢአት አሳቦች ይጠቃ ነበር። ስለሆነም በአንድ ወቅት ጥያቄውን ለእግዚአብሔር እንዲህ በማለት ያቀርባል፦
"ጌታዬ ሆይ! እኔ ልድን እወዳለሁ፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ክፉ አሳቦች ብቻዬን ሊተዉኝ አልቻሉም። በዚህ መከራ ውስጥ ስሆን ምን ባደርግ ይሻለኛል?"
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ተነሥቶ ወደ ውጪ ሊወጣ ሲል አንድ እርሱን የሚመስል ሰው ቁጭ ብሎ ሥጋጃ(እንደ ምንጣፍ ያለ ነገር?) ሲሰራ ይመለከታል። ያ ሰው ጥቂት ከሠራ በኋላ ሥራውን አቋርጦ ይነሣና መጸለይ ይጀምራል። ጸሎቱን እንደጨረሰም ተመልሶ ሰሌን መስፋቱን ይቀጥላል። እንደገና ተነሥቶ ደግሞ ይጸልያል። በዚያን ወቅት ይህንን ሁሉ ያደረገው የእግዚአብሔር መልአክ ሲሆን ይህንንም ያደረገው አባ እንጦንስን ሊያርመውና ሊያስተምረው ፈልጎ ነው።
በመጨረሻም መልአኩ "እንደዚህ ካደረግህ ትድናለህ" ይለዋል። አባ እንጦንስም እነዚህን ቃላት ሲሰማ እጅግ ከመደሰቱ በላይ ድፍረትንም ተጎናጸፈ። ከዚህ በኋላ አድርግ የተባለውን ስላደረገ ዳነ።
———————————-
እንጦንስ በኃጢአት አሳብ አብዝቶ ይፈተን የነበረው ከጸሎት ሰዓቱ በኋላ እንዲሁ ቁጭ ይል ስለነበር ነው። እኛም በኃጢአት አብዝተን እንዳንፈተንና እንዳንወድቅ ሥራ ፈተን አንቀመጥ.. ምንም ቢሆን ቤት ውስጥም ውጪም በሆነ ሥራ ራሳችንን ቢዚ እናድርግ
መልካም ውሎ
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3414