tgoop.com/Apostolic_Answers/3315
Last Update:
ትዝ ይለኛል አንድ ጊዜ ወደ 4ኪሎ አካባቢ ነው.. ለቤተ ክርስቲያን በጣም የቀኑ የሚመስሉ ነጠላ እና መሰል ነገር የለበሱ ሰው ሰላም ሲሉ መሬት ድረስ ዝቅ የሚሉ ወጣት ልጆች እያወሩኝ..
“እንዲህ እየተለበሰ (ኮፍያውን እና የጸሐይ መነጽሬን መሰለኝ.. ከዛ ውጪ የለበስኩት እንኳን ያው ንጹሕ ከመሆን የዘለለ ነገር አይኖረውም መቼስ.. ግን ቀጫጫ ስለሆንኩ ፍንዳታ ከመሰልኩ እንጃ ሎል😁😁) እንዲህ እየለበስን እንዴት የሚያዩንን ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን መጋበዝ ይቻላል..??” እያሉ እርስ በእርስ በአግራሞት እየተቀባበሉ ያወሩ ጀመር..
ነጠላውን ተመልከት ራሱን ችሎ ትርጉም አለው.. እንዲህና እንዲያ ነው ትርጉሙም ይሉ ጀመር.. እና የሆነ ሰዓት ላይ ጀጅመንታል ሆነው(በፍርድ ወንበር ተቀምጠው) እያወሩ እንደሆነ ተሰማኝና ብዙ ሰዓት ሰጥቼ ስለ ልብ አወራቸው ጀመር.. አንዳንዴም በኃይል ስለ ነጠላውም እናገራቸው ጀመር..
ሰዎች ነጠላን በማየት ብቻ ወደ እግዚአብሔር ሊመጡ አይችሉም.. ስለዚህ ነጠላ ለብሰን ብንወጣ ኦርቶዶክስ እንደሆንን ይታወቃል እንጂ ሌላ የተመልካቹ ልብ ላይ ሚጨምረው ነገር የለም.. ምናልባት ውብ ሆኖ ከታየው ነጠላ እንዲለብስ ካላነሳሳኸው በስተቀር..
ክርስቲያኖች የተጠራነው ክርስቶስን አሳይተን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሰዎችን እንድንመልስ ነው.. ክርስቶስ የሚታየው ደግሞ በሕይወታችን ውስጥ ነው.. ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ ተባለ እንጂ ነጠላችሁ በሰው ፊት ይብራ አልተባለም.. ስለዚህ ሰዎችን የምንስበው በክርስቶስ ብቻ ነው.. ነጠላው ግን እንደ መላእክቱ ነጭ(ብርሃናዊ) ሆነን በአምልኮ ቅዳሴ ሰዓት እንድንቆርብበት የተሰጠን ነው..
ክርስቶስ ከነጠላም ከሕግም ሁሉ ይቀድማል.. ወንድሞቼና እህቶቼ የአለባበስ ነገር ቀስ እያለ የሚቀረፍ ነው.. ክርስቶስ ብቻ ወደ ልባችን ይግባ.. ቅኖች እንሁን ክፋት በልባችን አይኑር.. ክርስቶስን በልቡ ላይ ያነገሰ ሰው ልቡ የክርስቶስ ዙፋን ሆነለት ማለት ነው.. ሌላው ነገር ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣ ነው..
@Apostolic_Answers
BY ሐዋርያዊ መልሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Apostolic_Answers/3315